Последние посты

Ministry of innovation and technology (MinT)
17 сент., 06:50
የግራንት አስተዳደር ማዕቀፉ ለጀማሪ ስታርታፖች የሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ ፍትሃዊና ተጠያቂነት ባለው አሰራር ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚያስችል ሲሆን፣ የሬጉላቶሪ ሳንድቦክስ ማዕቀፉ ደግሞ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ከህጋዊ አሰራር ጋር ሳይጋጩ በቁጥጥር ስር ሆነው በገበያ ላይ የሚፈተኑበትን ዕድል ያመቻቻል።በመጨረሻም የመንግስት፤ የልማት አጋሮች እና የስታርታፕ ምህዳር ተዋንያንን በውይይቱ ወቅት የሚያቀርቧቸው ገንቢ አስተያየቶችና ልምዶች ረቂቅ ሰነዶቹን በማበልፀግ፣ አዋጁን ከፖሊሲ ደረጃ ወደ ተግባራዊ ድጋፍ ለማሸጋገር የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክሩት ተገልጿል።




Ministry of innovation and technology (MinT)
17 сент., 06:49
በስታርታፕ አዋጁ የግራንት እና የቁጥጥር ማዕቀፍ (Sandbox) ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡ ================== የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር የስታርታፕና የኢኖቬሽን ሥነ-ምህዳርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገሩ የግራንት አስተዳደር እና የሬጉላቶሪ ሳንድቦክስ ማዕቀፎች የምክክር መድረክ ተካሂዷል።በመድረኩ የተገኙት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ፣ አዲሱን የስታርታፕ አዋጅ በውጤታማነት ወደ ተግባር ለመለወጥ በአዋጁ የተደነገጉ የፋይናንስና የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀትና በፍጥነት ወደተጋባር ማሸጋጋር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።መሪ ሥራ አስፈፃሚው አክለውም፣ የተዘጋጁት አስቻይ ማዕቀፎች ስታርታፖች ተገቢውን የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትንና የህግ ማዕቀፉ ከቴክኖሎጂው ፈጣን እድገት ጋር የሚጣጣምበትን ምቹ ስነምህዳርን እንደሚፈጥሩ አብራርተዋል።የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የኢትዮጵያ ምክትል ዋና ተወካይ ወ/ሮ ቻሩ ቢስት በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ለሥራ ፈጠራና ኢኖቬሽን እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።ምክትል ዋና ተወካይዋ አክለውም፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በ"ትምቡክቱ" (timbuktoo) ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን በመደገፍ የአፍሪካን የኢኖቬሽን ምህዳር እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።




Ministry of innovation and technology (MinT)
16 сент., 09:41
ለአህጉራዊ ውድድርና ምረቃ ወደ ኮትዲቯር (አቢጃን) ለሚያመሩት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የማበረታቻ ሽኝት ተደረገ፡፡ ================= በያንጎ ግሩፕ (Yango Group) አዘጋጅነት በተከናወነው አህጉራዊ የ"Yango Fellowship" ፕሮግራም ከ600 በላይ ከሆኑ አመልካቾች መካከል ተወዳድረው ያለፉ 4 ጎበዝ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ከጉዟቸው በፊት ተገናኝተዋል።ይህ የፓን-አፍሪካ መርሃ ግብር ተስፋ ሰጪ ወጣቶችን በተግባራዊ ክህሎት፣ በአማካሪነት (Mentorship) እና በሥራ ፈጠራ እድገት ላይ ለማብቃት ያለመ ነው።የተመረጡት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም (September 17, 2026) በኮትዲቯር አቢጃን በሚካሄደው አህጉራዊ የውድድርና የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመሳተፍ ሀገራቸውን ይወክላሉ።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጣቶቹ ሀገራቸውን በታላቅ ኩራት በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲወክሉ ለማበረታታት ከጎናቸው መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ከተጀመረ አንድ ዓመት ቢሞላውም ኢትዮጵያውያን ሲወከሉ ግን የመጀመሪያው መሆኑ ተጠቅሷል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቀጣይ ዓመታት ለሚደረጉ ተከታታይ ዝግጅቶች ከያንጎ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በትብብር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት የገለጸ ሲሆን፣ ያንጎ ግሩፕ ላደረገው የፌሎውሽፕ ዝግጅትና ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያሳዩት ላለው አበረታች ውጤት ያለውን አድናቆት የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ለወጣቶቹ በአህጉራዊው መድረክ ላይ ስኬትን ተመኝቷል።




Ministry of innovation and technology (MinT)
11 сент., 18:35
አክለውም በየዓመቱ ወደ ማዕከሉ በመምጣት አረጋውያንን ማዕድ ማጋራታችን ብቻ በቂ ስላልሆነ፣ በየጊዜው በመምጣት ከጎናቸው በመሆን የወገኖቻችንን የመኖር ተስፋ ልናለመልም ይገባል ብለዋል።በመጨረሻም የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ሁልጊዜም ከጎናችን በመሆን የሚያደርጉልን ድጋፍ አለኝታነታቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።ማዕከሉ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ቅርንጫፎቹን እያስፋፋ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በእነዚህ መጠለያዎች የሚጦሩ በርካታ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ወገኖችን በዘላቂነት ለመንከባከብ የሁሉም ወገን ድጋፍ በተቻለ መጠን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።




Ministry of innovation and technology (MinT)
11 сент., 18:35
የ2019 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት በመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል በመገኘት የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አካሄዱ። ================ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን አዲሱን የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ዕንቁጣጣሽ በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ በመቄዶንያ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መረዳጃ ማዕከል ለሚጦሩ 200 አረጋውያን የማዕድ ማጋራት እና የተለያዩ ድጋፎችን አካሂደዋል።በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተክለማርያም ተሰማ በሀገራችን በየቦታው አቅም አጥተው የወደቁ ወገኖችን በማንሳት መጠለያ፣ ምግብና እንክብካቤ እየሰጠ የሚገኘው የመቄዶንያ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መረዳጃ ማዕከል የኢትዮጵያን ትልቅ ኃላፊነት የተሸከመና የሁላችንንም ድጋፍ የሚሻ ተቋም መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።አክለውም፣ በማዕከሉ የሚጦሩ ወገኖችን መደገፋችን ያለንን ወገናዊ አለኝታነት የሚያጠናክር በመሆኑ፣ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ትኩረት ተሰጥቷቸው የተጀመሩ የበጎ አገልግሎት ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ በበኩላቸው ማዕከሉ ለሰው ልጅ ክብር በመስጠት እያከናወነ ያለው በጎ ተግባር ለሀገራችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።


1,360Открыть в Telegram
Ministry of innovation and technology (MinT)
10 сент., 20:37изменён
ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ። አዲሱ አመት የሰላም የጤና እና የእድገት እንዲሆንልን እመኛለው።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ


Ministry of innovation and technology (MinT)
10 сент., 17:18
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ አዲሱን የ2019 ዓመት በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት፥
Ministry of innovation and technology (MinT)
10 сент., 09:24
ሚኒስትሩ አክለውም፣ ቴክኖሎጂ ትርጉም የሚያገኘው በከተሞች ብቻ ሳይሆን በሩቅ ገጠር የምትገኝን እናትና ማሳ ላይ ያለውን አርሶ አደር ህይወት በሚጨበጥ መልኩ መቀየር ሲችል በመሆኑ «የመጨረሻው ማይል» ፍትሐዊነት ቅድሚያ እንደሚሰጠው ገልጸዋል።ተቋማችን የአስፈጻሚነት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ ዘርፎች አስተባባሪ ማዕከል በመሆን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና አዳዲስ ፈጠራዎችን በጠንካራ የፖሊሲ፣ የሕግና የሥነ-ምግባር ማዕቀፍ ይመራል ብለዋል።ከዚህ ቀደም ከተከናወኑት የዲጂታል ጉዞዎች በተቀሰሙ ትምህርቶች ላይ በመመስረት፣ የዜጎችን መረጃ ደኅንነትና የሳይበር ምህዳሩን መተማመን፣ ማረጋገጥ የቴክኖሎጂው ዋና መሠረተ ልማት ተደርጎ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።በመጨረሻም፣ ይኸው መድረክ የቀደሙ አባቶች የዘመን መቁጠሪያ ስጦታ በሆነችው ጳጉሜ 5 ላይ መካሄዱ ለነገዋ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ለመነሳት የታለመ በመሆኑ ተሳታፊዎች በሐቀኝነትና በተግባራዊ ሀሳቦች ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ ቀርቧል።


1,210Открыть в Telegram
Ministry of innovation and technology (MinT)
10 сент., 09:23
"የነገ ቀን" ተብሎ በተሰየመውና «ነገን ዛሬ መገንባት» በሚል መሪ ቃል የሚታሰበው ጻጉሜን 5፤ በተለያዩ ፕሮግራሞች በአዲስ አበባ በሳይንስ ሙዚየም በደማቁ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ================== “ነገን ዛሬ መገንባት: የዲጂታል ሽግግር፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ምግብ ሉዓላዊነትና ሀገራዊ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ማንሰራራት“ አጀንዳዎች ዙሪያ ሀገራዊ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡በሀገራዊ የፓናል ውይይት ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የዲጂታልና የኢኮኖሚ ስኬቶች መድረሻ ሳይሆኑ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ እድገት መነሻ መሆናቸውን ገልጸዋል።አፈ ጉባኤው አክለውም፣ በቅርቡ የተጠናቀቀው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ እና የተካሄደው ሀገራዊ የምክክር ሂደት የሕዝባችንን የመነጋገርና በጋራ የመሥራት ጥንካሬ ያሳዩ ታሪካዊ ምዕራፎች መሆናቸውን ገልጸው፣ የአዲሱ መንግሥት የአምስት ዓመት አደራ ከ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂ ትግበራ ጋር መገጣጠሙ ለሀገራችን የተቀናጀ እድገት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል።ወጣቶች የዚሁ ታላቅ የሽግግር ጉዞ ዋና ባለቤቶችና ግንባር ቀደም ተዋናዮች መሆናቸውን ያመለከቱት አፈ ጉባኤው፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችንና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን ለአምራችነት በመጠቀም የሀገራችንን ችግሮች በሀገር በቀል እውቀትና ፈጠራ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የዲጂታል ሽግግር በስብሰባ አጀንዳነት የሚነሳበት ዘመን አብቅቶ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የግብርናና የአደጋ ስጋት አስተዳደር የጋራ ህያው ደም ሥር ወደ መሆን መሸጋገሩን አብራርተዋል።




Ministry of innovation and technology (MinT)
10 сент., 05:25
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት የነገው ቀን ============= ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን




Ministry of innovation and technology (MinT)
9 сент., 17:03изменён
በሳይንስ ሙዚየም ጳጉሜን 5 ቀን 2018 የሚከበረውን «የነገ ቀን» በዓል አስመልክቶ የስተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፥
