gram news
Аватар канала Ministry of Health, Ethiopia

Ministry of Health, Ethiopia

@mohethiopia

The official Telegram Channel of the Ministry of Health of the FDRE. Our vision is to see healthy, productive & prosperous Citizens of Ethiopia. HEALTHIER CITIZENS FOR PROSPEROUS NATION! 📞 +251-11-551-8031 🔗 www.moh.gov.et 📧 moh@ethionet.et

ПроектыENЗдоровье

15,800подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Ministry of Health, Ethiopia

    9 июн. 2024 г., 18:15

    የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሠር ማእከል የጨረር ህክምናን ጨምሮ አምስት አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን አስመርቆ ለአገልግሎት አቀረበ።ዩኒቨርሲቲው የካንሠር የጨረር ህክምና፣ የስነ አእምሮ ተኝቶ ህክምና፣ የፎሮንሲክ እና የስነ መመረዝ ህክምና እንዲሁም የማህበረሰብ ሞዴል መድሀኒት ቤት አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ የጨቅላ ህጻናት የጽኑ ህክምና የልህቀት ማእከል፣ የአጥንትና መገጣጠሚያ ህክምና በአዲስ መልክ አደራጅቶ ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን የሴንትራል ኦፕሬሽን ክፍል የማስፋፋያ ስራዎች እየሰራም ይገኛል።በማስመሪቂያ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ለብዙ ጊዜ ሲጠበቅ የቆየው የካንሰር ማእከል የጨረር ህክምና ለአገልግሎት በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እየተሰሩ ያሉ የጤና ፕሮጀክቶች በቅርቡ ይፋ የሆነውን አራተኛው የጤና ፓሊሲ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮች ጋር በእጅጉ የተሳሰሩ መሆናቸው ገልጸዋል። እነዚህ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስገባቱ የጤና ፖሊሲውን ለመተግበር ብሎም ዜጎች በጤናው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ፍላጎት ማርካት እንደሚያስችል ተናግረዋል።የአዋሳ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የተገነባው የጨረር ህክምና በአገራችን አራተኛው የጨረር ህክምና መሆኑን የገለጹት ዶክተር ደረጀ የህክምና ዘርፉን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚወስድ በመሆኑ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት እንደሆነም ነው የተናገሩት።በከፍተኛ ወጪ
    49,10028415526221413Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    9 июн. 2024 г., 18:15

    የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሠር ማእከል የጨረር ህክምናን ጨምሮ አምስት አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን አስመርቆ ለአገልግሎት አቀረበ።📱 www.moh.gov.et📱 @MoHEthiopia📱 Ministry of Health,Ethiopia📱 twitter.com/FMoHealth📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    42,30031174Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    6 июн. 2024 г., 08:19

    ጤናችን በምርታችን! የሃገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚቢሽን ከሰኔ 15-20፣ 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይምጡ፣ ይጎብኙ፣ ይካፈሉ!📱 www.moh.gov.et📱 @MoHEthiopia📱 Ministry of Health,Ethiopia📱 twitter.com/FMoHealth📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    34,000171021Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    3 июн. 2024 г., 16:31

    ቆልማማ እግር በፈጣሪ ቁጣ ወይም በዘር የሚከሰት አይደለም!#clubfootawareness📱 www.moh.gov.et📱 @MoHEthiopia📱 Ministry of Health,Ethiopia📱 twitter.com/FMoHealth📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
  • Ministry of Health, Ethiopia

    3 июн. 2024 г., 16:28

    በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ በማጽደቅ ተጠናቋል።በጄኔቫ ስውዘርላንድ የአባል አገራትን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ሲካሄድ የነበረው 77 ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ በ2005 ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) ላይ የተደረገዉን ማሻሻያ እና ሌሎች የመፍትሄ ሀሳቦችን ( Resolutions) በማጽደቅ ተጠናቋል።ሃገራችን የአፍሪካ ቡድንን በማስተባበር የጋራ አቋም እንዲያዝና በቀረቡት ማሻሻያዎች ውስጥ ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሳደግ ለታዳጊ ሃገራት ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ማሻሻያዎች እንዲጸድቁ ከፍተኛ አስተዋጾዖ ያበረከተች ሲሆን የሃገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፉና በተለይም በአፍሪካ ሃገራት ላይ የንግድና ትራንስፓርትና ኢኮኖሚ ረገድ አስገዳጅ ግዴታዎች የሚጥሉ ሃሳቦች እንዳይካተቱ ማድረግ ተችሏል፡፡ከ300 በላይ ፕሮፓዛል በአባል አገራት ቀርቦ ማሻሻያ ተደርጎ የፀደቀዉ ዓለምአቀፍ የጤና ደንብ (International Health Regulations 2005 ) በዋናነት በህብረተሰብ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ወቅት የሀገራት ዝግጁነትና ምላሽ አሰጣጥ አቅምን ለማሻሻል እንዲሁም አለም አቀፍ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነዉ። በዚህ መሰረት ተሻሽሎ የጸደቀው የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋና ወረርሽኝ ሲከሰት ፍትኃዊ የሆነ የህክምና ግብዓት ተደራሽነት
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    38,50019181Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    2 июн. 2024 г., 10:08изменён

    በህፃናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር በወቅቱ ከታከመ መዳን እንደሚችል ያውቃሉ? #clubfootawareness📱 www.moh.gov.et📱 @MoHEthiopia📱 Ministry of Health,Ethiopia📱 twitter.com/FMoHealth📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    42,3001431Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    2 июн. 2024 г., 10:05

    ጤና ሚኒስቴር የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ።በወባ ፕሮገራም ላይ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ያካሄዱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ አገራዊ የወባ ህሙማን ጫና 76 በመቶ ሲሆን 222 ወረዳዎች ደግሞ የወባ በሽታ ስርጭት የሚሸፍንባቸው አከባቢዎች ናቸው ብለዋል፡፡በቀጣይ ስድስት ወራት በ222 ወረዳዎች በትኩረትና በቅንጅት በመስራት በ50 በመቶ ለመቀነስ እንደሚቻል የገልፁት ሚኒስትር ዴኤታው በወባ ፕሮግራም ላይ የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡አጋር ድርጅቶች በየደረጃው ካሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የወባ ስርጭትን በዘለቂ ለመግታት የጋራ ዕቅድ በመንደፍ መስራት እንደሚገባቸው አሳውቀዋል፡፡ጤና ሚኒስቴር የተጀመረውን የወባ ስርጭት የመቀነስ እንቅስቃሴ አጋር ድርጅቶች አድንቀው በሁሉም ዘርፍ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ጠቁመዋል፡፡@MoHEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
  • Ministry of Health, Ethiopia

    9 мая 2024 г., 02:07

    “የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ ናቸው፤ ይህም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላካች ነው፡፡” አቶ መሃሙድ መሃመድ የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊብሄራዊ የወባና ሌሎች ትንኝ ወለድ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሃሙድ መሃመድ ግምገማዊ መድረኩን በይፋ ሲከፍቱ እንደተናገሩት ጤና ሚኒስቴር የዘንድሮውን የወባ እና የሌሎች ትንኝ ወለድ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን፣ በወባ ላይ የተሰሩ የጥናትና ምርምሮች ሲምፖዚየምን እና የዓለም ወባ ቀን በዓል አከባበርን በሶማሌ ክልል እንዲካሄድ ዕድል በመስጠቱ በክልሉና በጤና ቢሮው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡አቶ ማሃሙድ አክለውም የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በመሆናቸው የታማሚዎች ቁጥር የመጨመር አዝማሚ እያሳየ መሆኑን አስታውቀው ይህም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላካች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በጤና ሚኒስቴር የወባና ሌሎች ትንኝ ወለድ በሽታዎች መከላከልና መቆጠጠር ዴስክ ኃላፊ አቶ ጉዲሳ አሰፋ የብሄራዊ የወባና ሌሎች ትንኝ ወለድ በሽታዎች ፕሮግራምን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደገለጹት በባለፈው አንድ ዓመት 19.7 ሚሊዮን የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር መሰራጨቱንና የ2.3 ሚሊዮን አጎበሮች ግዥ በሂደት ላይ መሆኑን
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    18,7003792Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    7 мая 2024 г., 06:51

    እናት ባትኖር …የዛሬ 24 አመት ገደማ ሃብታሙ ተካልኝ የ11 አመት ልጅ ነበር፡፡ አንድ ምሽት የሃብታሙ አባት አቶ ተካልኝ በጭንቀት ቤት ውስጥ ይንጎራደዳሉ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ህጻን ሃብታሙ የወላጅ እናቱን ጭንቀት የተሞላበት የስቃይ ድምጽ ሰማ፡፡ “እማዬ ምን ሆነች?” ሲልም አቶ ተካልኝን ጠየቀ፡፡ አባትም “እናትህ ምጥ ይዟታል፤ ልጅ ልትወልድ ነው፤ እህት ወይም ወንድም ልታገኝ ነው” በማለት ለልጃቸው አስረዱ፡፡ይሁን እንጂ እንዳሰቡት እናት በቀላሉ መገላገል አልቻሉም፡፡ ጎረቤታቸው የነበሩት ነርስ፣ ሲ/ር ስርጉት ተጠሩ፡፡ ሲ/ርም ጉዳዩን በጽኑ ካስተዋሉ በኋላ የህጻን ሃብታሙ እናት ወደ ሆስፒታል ባስቸኳይ መወሰድ እንዳለባቸው ተናገሩ፡፡ መኪና ተጠራና ጉዞ ወደ ሆስፒታል ሆነ፡፡ ህጻን ሃብታሙም እናት እና አባቱን በመከተል ወደዚያው አመራ፡፡በሆስፒታሉ ማዋለጃ ክፍል ደጃፍ አባት ለሰአታት ይንጎራደዳሉ፡፡ ህጻን ሃብታሙም በጭንቀት የክፍሉ ደጃፍ ኩርምት ብሎ ተቀምጧል፡፡ ከሰአታት ጭንቀት በኋላ የሆስፒታሉ ሚድዋይፍ ከማዋለጃ ክፍሉ ብቅ አሉ፡፡ በወቅቱ ህጻን ሃብታሙ ሊረዳው ባልቻለ አገላለጽ ሚድዋይፏ ስለሆነው ለአቶ ተካልኝ ማስረዳት ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ሚድዋይፏ የህጻን ሃብታሙ እናት ወንድ ልጅ መገላገላቸውን ገለጸች፡፡ ወደ ህጻን ሃብታሙም ጠጋ ብላ ወንድም እንደተወለደለት አበሰረች፡፡ ከዛም ወደ ልጁ ጠጋ ብላ የነገረችው እውነታ እስከ ዛሬም ከልቡ አልጠፋም፡፡ “ማሙሽ እናትህን በጊዜ ወደ ሆስፒታል ባታመጧት ኖሮ ሟች ነበረች” ስትል ሚድዋይፏ ለህጻን ሃብታሙ ሹክ አለች፡፡ህጻን ሃብታሙም “እማዬ ባትኖር
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    14,8003228311Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    4 мая 2024 г., 12:52

    እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም ፋሲካ!#HappyEaster2024@MoHEthiopia
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    13,700832Открыть в Telegram
  • Ministry of Health, Ethiopia

    4 мая 2024 г., 12:51

    የአለም የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ ቀን ከታካሚዎች እና ወላጆች ጋር ተከብሯል።የሆፕ ኤስ ቢ እና ኤች የተራድኦ ድርጅት የአለም የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ ቀን ከታካሚዎች እና ወላጆች ጋር ያከበረ ሲሆን፤ በተቋሙ የህክምና ክትትል የሚያገኙ ታካሚዎች ወላጆች ለፋሲካ በአል የማእድ ማጋራት መርሃ ግብርም ተካሂዷል፡፡በጤና ሚኒስቴር የመሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ እና የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ ታካሚዎች የክብር አምባሳደር አቶ እስክንድር ላቀው በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ተቋሙ ለታካሚዎች እያደረገ ለሚገኘው እንክብካቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡HOPE-SBH ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ ህጻናት ላይ የሚከሰት የጤና ጉዳትን ለመቅረፍ፣ ለመከላከል እና ሁሉን አቀፍ አቀራረብን በመከተል የህክምና ክትትል ለማቅረብ በርካታ አስፈላጊ ተግባራትን እያካሄደ እንደሚገኝና ከ3700 በላይ ታካሚዎች አገልግሎት መስጠቱን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት፣ እንዲሁም በሆስፒታሎች የጤና ትምህርት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ቤዛ በሻ ተናግረዋል።በስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ የጤና ጉዳት የተከሰተባቸው ህጻናት በመድረኩ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ከተቋሙ ለተደረገላቸው አገልግሎት እንዲሁም ማእድ ማጋራት በዝግጅቱ የተገኙ ወላጆች ምስጋና አቅርበዋል፡፡የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሲፋለስ የሚከሰተው እናቶች በተገቢዉን የቅድመወልድ የጤና ክትትል ባለማድረግ እና የፎሊክ አሲድ እጥረት ሲያጋጥም
    Иллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, EthiopiaИллюстрация к посту канала Ministry of Health, Ethiopia
    12,9007552Открыть в Telegram