Последние посты

ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
22 сент., 18:54
◈ያላዋቂ ሴራ መቋጠሪያ እንጂ መፍቻ የለውም። ◈ቤተክርስቲያታችን መፍትሄ ያጣችው መቆጠር እንጂ መፍታት በማይችሉ አላዋቂዎች ምክንያት ነው።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
22 сент., 18:24
◈ዘመኑ የጭፍን ደጋፊዎች እና የአስመሳዮች ነው። ◈ነገ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊሆን የሚችለውን ማየት ስትጀምር ጭፍን ተከታዩና አስመሳይ፣አታላይ ስብስቡ መአት አውሪ ነው እያለ ያሸማቅቅሀል። ◈በተከታዮች፣በአስመሳዮችና በአታላዮች ዘንድ ቀድሞ ሁኔታን መረዳ ከኑፋቄ ይቆጠራል። ◈ለምሳሌ፦በውድቅት ሌሊት ዕንቅልፍ አጥሮህ ድንገድ ብትነቃ ሁሉ የተኛ ስለሆነ ያንተን መንቃት ማን ያውቅልሀል? በአንጻሩ ቀድሞ መረዳትም እንደዚህ ነው።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
22 сент., 17:00
◈የኦርቶዶክሳዊነት አረዳድ የገባውን ሰው ያገኘው ሁሉ አይጭነውም። ◈እንደ ኅዳር አኽያ ሁሉ የሚጭነው ሰው ግን የነቃው በሆዱ እንጂ በአእምሮው አይደለም። ◈ህሊናውን አስተኝቶ በሆድ ብቻ መንቃት የቡኮ ዕቃ መሆን ነው። ◈ነቅቻለሁ ካልህ ወዳጎረሱህ ብቻ አትዙር። ◈የክርስትና ትልቁ ጥቅም ከጥቅም በላይ መሆኑ ነው።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
22 сент., 13:23
ፈለገ አበው ጉባኤ ቤት ለአዳዲስ ደቀ መዛሙርት የወጣ ማስታወቂያ



ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
21 сент., 15:32изменён
ማስታወቂያ የምዕ/ጎጃም ሀገረ ስብከት በውስጡ በሚያስተዳድረው ምሥራቀ ፀሐይ የብፁዕ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የ፬ቱ ጉባኤያት ቤተ ጉባኤ፡- ሀ/ በሐዲስ ኪዳን፡-ብዛት 4 ለ/ በሊቅ፡-ብዛት 5 በድምሩ 9 ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። መመዘኛ መስፈርቶች 1ኛ፡ ቅኔ ከነ ሙሉ ሙያው ያወቀ፤በመምህርነት የተመረቀ፤ 2ኛ፡ ያላገባ፤ ሥልጣነ ክህነት ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ 3ኛ፡ በወንጀል ያልተከሰሰና በሥነ ምግባር የተመሰገነ፤ 4ኛ፡ ዕድሜው ከ20–30 የሆነ ወይም ከ30 ያልበለጠ፤ 5ኛ፡ ከሰበካ ጉባኤ፤ከወረዳ ቤ/ክ እና ከመምህሩ የመሸኛ ደብዳቤ የሚያቀርብ፤ 6ኛ፡ በሊቅ ለሚማሩ በሐዲስ ኪዳን የተመረቀ፤ ስለሆነም እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟላ በአካል ቀርቦ መመዝገብ ይችላል። የምዝገባ ቀን ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ይሆናል። የፈተና፤ ቀን ወደፊት ከምዝገባ በኋላ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል። ጽ/ቤቱ ለበለጠ መረጃ እና በአካል መገኘት ለማትችሉ በዚህ ይደውሉ፡ 09 18 09 05 90 / 09 86 86 89 95


ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
21 сент., 14:46

1,680Открыть в Telegram
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
21 сент., 14:46
የደቀ መዛሙርት ቅበላ ማስታወቂያአንቲ ውእቱ ምሥራቅ ዘወጽአ እምኔኪ ኮከብ ብሩህ የብሩህ ኮከብ መገኛ ምሥራቅ አንቺ ነሽየብፁ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ ምሥራቀ ፀሐይ የአራቱ ጉባኤያት አዳሪ ትምህርት ቤት አራቱ ጉባኤያት የሚነገሩበት ጉባኤ ቤት ነው። ጉባኤ ቤቱ መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ደቀመዛሙርትን ለመቀበል ዝግጅቱን ጨርሷል ከታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ከዛሬ ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ መመዝገብ ይቻላል። የውድድር ቀን በማስታወቂያ የሚገለጥ ይሆናል።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
21 сент., 09:59изменён
◈ዘመነ-ፍሬ፦◈ዘመነ-ፍሬ ከመስከረም ፱_፲፮ የሚታሰበው የሰውን ልቡና በተስፋ ልምላሜ የሚአጥለቀልቀው ዘመን ነው ይሄ ዘመን (ሳምንት)ዘመነ ፍሬ በመባል ይጠራል ።👍ምክንያቱም?፩.)አዝርዕቱ ፪.)አትክልቱ ፫.) እፅዋቱ ◈ከተዘሩበት ከተተከሉበትና በተፈጥሮ ከተገኙበት ጀምሮ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ሰጥቶ በዚህ ምክንያት በቅለውና አድገው አብበውም ለፍሬ የሚበቁበት ዘመን(ወቅት) ስለሆነ ነው።◈የአዝርዕት አይነቶች? ፩.) በሥራቸው የሚአፈሩ ፪.) በጎናቸው የሚአፈሩ ፫ .)በውስጣቸው የሚአፈሩ ፬ .)በራሳቸው የሚአፈሩ ። ናቸው ◈ሁሉም በሚባል ደረጃ ከነዚህ አይጡም።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
21 сент., 06:23
◈መንቃት በልብስ እና በምላስ የሚመስለው ሰው በህላናው ያንቀላፋ ነው። ◈መንቃት በህሊና ፍጥነት በአእምሮ ስክነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
20 сент., 12:27

ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
20 сент., 11:41
ተቀጸል ጽጌና ታሪካዊ አመጣጡ|| መልአከ ጥበብ ስሜነህ አበበ ንጉሡ የአበባ ጉብጉን ሲቀበሉ ደርሼ ነበር። ተቀጸል ጽጌ መከበር የጀመረው ከመች ጀምሮ ነው? አሁናዊ የተቀጸል ጽጌ አከባበርና ሌሎችም ታሪካዊ ሁኔታዎችhttps://youtu.be/Ic7Ry_aseLMYouTubeንጉሡ የአበባ ጉንጉን ሲቀበሉ በእድሜ ደርሼ ነበር || መልአከ ጥበብ ስሜነህ አበበ። ተቀጸል ጽጌና ታሪካዊ አመጣጡተቀጸል ጽጌ መከበር የጀመረው ከመች ጀምሮ ነው? አሁናዊ የተቀጸል ጽጌ አከባበርና ሌሎችም ታሪካዊ ሁኔታዎች #ምሥራቀ_ፀሐይ_ጉባኤ_ቤት #ገብረ_መድኅን_እንየው #ብንያም_ዘውዴ #ሰሎሞን_ላመስግን #aba_gebre_kidan #ethiopia #fewus_menfesawi #ቅዳሴ #Liturgy #ኦርቶዶክስ #ቅዳሴ ማርያም #ፍልሰታ #podcast #ethiopia…
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
20 сент., 11:00





ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
20 сент., 10:59
◈ጉባኤውን ያስፋልን ገዳሙን ይጠብቅልን!! ✝️◈በሰሜን ሸዋ ሀ/ስ/የጉባኤ ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያት ት/ቤት መምህር(የኔታ ነቢየ ልዑል) እና ደቀ መዛሙርት እንኳን ለምረቃ በዓል አደረሳችሁ!! ◈ወንጌላዊ ዓላማን ፀንሰው የሚወልዱ መምህራን ድካማቸው ብዙ ነው። ◈የተቀበሏቸውን ደቀ መዛሙርት ለዓመታት በህሊና ፀንሰው፦ ◈1.)ለምግባቸው፣ ◈2.)ለትምህርታቸው፣ ◈3.)ለአስተሳስባቸው፣ ◈4.)ለልብሳቸው፣ ◈5.)ለጤናቸው፣ ◈6.)ለአገልግሎታቸው፣..እየተጨነቁ አስተምረው ራሳቸውን አስመስለው መውለድ ድካሙ ብዙ ነው። ◈በዚህ ድካም ውስጥ በደከሙ በኔታ ነቢየ ልዑል በኩል ፅንሰታችሁን ጨርሳችሁ ዕትብቱ በማይቆረጥ በመምህርነት ሰንሰለት ሐዋርያዊ ልደትን ያገኛችሁ ወንድሞቻችን ተመራቂ መምህራን እናንተም እንዲሁ ታደርጉ ዘንድ ሐዋርያዊ ቅብብሎሹ ያስገድዳችኋል። ◈በተለይም ባለንበት ዘመን ድኅረ ምረቃችን ጊዜውን መዋጀትና ተናቦ ወንጌልን በአንድ ልብ ማስተማር፣ምእመናንን ከተለያዩ ሥሁት እሳቤዎች መጠበቅ ውዴታ ሳይሆን ግዴታችን ነው። ◈ለግል ፈቃድ ሳይሰስቱ፣ከወንጌል ዓላማ ሳይሳሳቱ ኦርቶዶክሳውያንን እና ኦርቶዶክሳዊነትን ነቅቶ ተግቶ መጠበቅ ካልተቻለ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ጸሐፊዎች ወረቀት ላይ ብቻ ልትቀር እንደምትችል ልንገነዘብ ይገባል። ✝️◈ወንጌል ማለት፦ ◈1.)ሕገ ወንጌል ሕገ ነፍስ ናት፤ ◈2.)ሕገ ወንጌል ሕገ ትሩፋት ናት፤ ◈3.)ወንጌል ሕገ ንሥሓ ናት፤ ◈4.)ወንጌል ሕገ ምናኔ ናት፤ ◈5.)ወንጌል ሕገ ምሕረት ወሂሩት ናት፤ ◈6.)ወንጌል ሕገ ልቡና ሕገ ፍጽምና ናት፤
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
20 сент., 08:35
◈ወንድማችን እፎይን አይዞህ አለማለት ንፉግነት ነው። ◈ "በጕዞው ርዱት።"፩.ቆሮ.፲፮፥፲፩◈እኔ ደክሞ ያዘጋጀው መጽሐፉን ከእጀ ገብቶ እስካነበው እስካነበው ጓጉቻለሁ፤አንተሽ? አንቺስ?◈ከራሴ ጀምሮ ባለካባ እና ባለ ዳባ ተጠራቅሞ አንድ መስመር መራመድ ያልቻለነውን ራሱን ሰጥቶ እንዴት መሥራት እንደሚቻል ያመላከተ ጥቡዕ ወንድም ነው።◈በባዶው ተወልዶ እህል ጨርሶ ከመሞት እንዲህ በወጣትነት እድሜው አስተምሮ አብርቶ ማለፍ ዘለዓለማዊ ሕያውነት ነው።◈አቅሙ ያላችሁ እፎይን በሁሉም አይነት ማንገድ ማገዝ ያስፈልጋል።◈የወጣበት የወረደበት ትምህርቱ ከሁሉ እንዲደርስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የድርሻውን ይወጣ።◈ከፍርሀት፣ከትእቢት፣ከስንፍና እንዲጠብቀው፣የሰማእያን ጆሮ እንዲከፈትለት ሁሉም፦ገዳማት፣ጉባኤ ቤቶች፣ምእመናን በጸሎት ሊያስቡት ይገባል።◈አብረውት የሚወጡ የሚወርዱ ወንድሞችንና እኅቶችን ሁሉ እግዚአብሔር የበለጠ ጸጋውን፣ትጋቱን፣ጽንዓቱን፣አንድነቱን፣ፍቅሩን እንዲሰጣቸው በሁሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ሊታሰቡ ይገባል።◈"ሰዓሊ ለነ ቅድስት" የምትሉ ሁሉ የአቡነ ዘበሰማያት ሰባራ የለውምና አስቧቸው።"እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት እርሱን የሚመስሉትንም አክብሯቸው።"ፊል.፪፥፳፱



ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
19 сент., 13:13
ባይበርደንም ያነደዱትን እየሞቅነው ነው። እሳት ሲበዛ ልብ ያሰላል ደም ያደርቃል። ነገር ግን መቅለጡ ያልተሰማቸው ስላሉ ቁጭ ብለን እየሞቅነው ነው።


ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
19 сент., 10:04изменён
"የምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት"ቴሌግራም ገጽን እናሳድገው። ◈ጉባኤ ቤት በቤትዎ ማለት ይህ አይደል? ◈ገጹ ላልደረሳቸው እናዳርስ!! https://t.me/mstaketsehayTelegramምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤትይህ ቻናል የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ማስተማሪያና ማወያያ ገጽ ነው።
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
19 сент., 08:27



ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
19 сент., 08:21
◈እደግመዋለሁ!! ◈ትልቁ በሽታችን ተከታይነት ነው!! ◈የማፍያ ባሕታዊ ተከታይ፤ ◈የማፍያ አጥማቂ ተከታይ፤ ◈የግለሰብ ዝነኛ ሰባኪ ተከታይ፤ ◈የሆነ ድርጅት ተከታይ፤ ◈የእንተና አባት ተከታይ፤ ◈የማፍያ ነቢያት ተከታይ፤ ◈የሰፈር የመንደር ተከታይ፤ ◈የሥሁት ሥርዓት ተከታይ፤ ◈የቋንቋ ተከታይ፤ ...ተከታይ ብቻ፣ ◈መቸ፣ማን?ለምን? ማለት የማይችል ተከታይ ብቻ፤ ◈ዘመናዊ ፊት ኋላ ቀር ልብ የሆነ ተከታይ ትውልድ፤ ◈ቤተ ክርስቲያን ስትነካ የማይጨንቀው ቲፎዞው ሲነካ እንደ ባለዛር የሚርገፈገፍ ተከታይ፤ ◈የምእመናንን፣የገዳማትን፣የአድባራት፣የአብነት ደቀ መዛሙርትን፣የሀገር..ዕረፍት አልባ መከራ ጉዳዩ ያልሆነ ተከታይ፤ ◈መሠረተ ሃይማኖት፤ ◈መሠረተ ትውፊት፤ ◈መሠረተ ታሪክ፤ ◈መሠረተ ቀኖና፤ ◈መሠረተ ባህል፤..የሌለው ተከታይ፤
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
18 сент., 16:48



ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
18 сент., 13:32изменён
◈አራቱ የተናዱ በሮች፦ 1.)ሀገር በቀል ዕውቀት፤ 2.)ፍትህ ርትዕ ያለው ሥርዓት፤ 3.)ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን፤ 4.)ሀገራዊነትና የሀገር አንድነት፤ኃጥእ ጻድቅ አማኒ መናፍቅ ሳትል ሁሉን ሸክፋ ታስተምር የነበረችው ኦርቶዶክስ ያለ በደሏ በሴራ ትርክት ስትሰደድ የእውነት በሮች ሁሉ ተናዱ።የተናዱ በሮች ደግሞ ማንንም ምንም መጠበቅ አይችሉም።"ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።"ተግ.ሰሎ.፩፥፳፰
