gram news
Аватар канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

@orthodoxbiblestudy2017

“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።” — ማቴዎስ 22፥29 ዓላማችን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብ ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ መፍጠር ነው ! "ጨለማን ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት!"

ПроектыENРелигия

6,980подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    20 сент., 13:48

    + የመዝሙረ ዳዊት ጥናት + (Book Of Psalms)እንቀጥላለን
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    20 сент., 13:44

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    20 сент., 13:44

    መጽሐፈ ኢዮብ 42 ምእራፎች ያሉት መጽሐፍ ነው።በይዘት በዚ መልኩ ከፋፍሎ ማጥናት ይቻላል :-
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    19 сент., 20:10изменён

    + የመጽሐፈ ኢዮብ ጥናት + (Book of Job) (ክፍል 2)ይህ መጽሐፍ ስለ ሰብአዊ መከራ የሚያትተውን የዋናውን ነገር ርእስ ተያያዥነት ባለው ሁኔታ በመግለጽ ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ለማስረዳት ባለው ጥንካሬና ግልጽነት፣ ስለክፉ መንፈስና የሰይጣን ፈተና አስከፊነት፤ እንዲሁም ፈተናን ሁሉ በእግዚአብሔር ታምኖ ድል ማድረግ የሚቻል ስለመሆኑ በስፋት የሚያስገነዝብ ነው፡፡የኢዮብ መጽሐፍ ሥነ ጽሑፋዊ ባሕርይ በግጥምና በስድ ንባብ የተቀረጸ ሆኖ ሥነጽሑፋዊ ዋጋው ከፍተኛ ነው፡፡የኢዮብ መጽሐፍ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶችን በሚያስደንቅ ሁኔታ አዋሕዶ የያዘ ነው።የመጽሐፉ አወቃቀር ከአጻጻፍ ስልቱ ወይም በአስተዋጽኦ መልክ ከሚቀርበው የእያንዳንዱ የጽሑፍ አካል የሚታይ ሲሆን ሥነ ጽሑፋዊ ባሕርይ በግጥምና በስድ ንባብ የተቀረጸ ነው።መጽሐፉ ሦስት የኢዮብ ወዳጆቹ የሆኑ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡና ከደረሰበት መከራና ሥቃይ ሊያጽናኑት ውይይት መጀመራቸውን ይገልጻል። እነዚህ ወዳጆቹ ሥቃዩ የደረሰበት በኃጢአቱ ምክንያት መሆኑን ገልጸው ንስሓ በመግባት ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም እንዲመሠርት ይመክሩታል፡፡ ነገር ግን ኢዮብ ንጹሕ መሆኑን ስለሚያውቅ ምክሩን በመቀበል ፈንታ የእግዚአብሔርን የአያያዝ ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡ከዚህ በኋላ “ኤሊሁ" የሚባል ሌላ አዲስ ሰው ይመጣና ለችግሩ መፍትሔ ይሆናሉ ብሎ ያሰባቸውን ነገር ግን ለውጥ የማያመጡ አራት ንግግሮች ያቀርባል፡፡ ወደ ኋላ እግዚአብሔር ራሱ ኢዮብን ያነጋግረዋል ።የእግዚአብሔርም ንግግሮች የኢዮብን ስሜት ይለውጡታል፤
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:37изменён

    + የመጽሐፈ ኢዮብ ጥናት + (Book of Job) (ክፍል 1)መጽሐፈ ኢዮብ ባለ ጸጋና በእግዚአብሔር ላይ ባለው ጽኑዕ እምነት የታወቀ ኢዮብ የተባለ ደግ ሰው ስም የተሰየመ መጽሐፍ ነው፡፡ከመጽሐፉ ይዘት አንጻር ጸሐፊው በአንድ አምላክ የሚያምን እስራኤላዊ መሆኑ የተረዳ ነው፡፡ ኢዮብ የኖረበትና ታሪኩ የተፈጸመበት ጊዜ "በዘመነ አበው" ነው።መጽሐፉ የተጻፈበት ዘመን 750 ቅ.ል.ክ. ገደማ ሲሆን ይህም እስራኤላውያን በአሦራውያን ከመማረካቸው ቀደም ብሎ ነው።መጽሐፉ "የጥበብ መጻሕፍት" እየተባሉ ከሚጠሩ ቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል የሚመደብ ሲሆን በሕዝበ እስራኤል እምነትና ትውፊት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በጥንታዊነቱ በይዘቱ በቅርጹና በአጻጻፍ ስልቱ ከመስጰጦምያ፥ ከግብፅና ከሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች ሥነ ጽሑፎች ጋር የሚመሳሰልባቸው ነጥቦች እንዳሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ኢዮብ ከእስራኤል በስተምሥራቅ የኤዶም ሰሜናዊ ክፍል በሆነችው ዖፅ /አውስጠድ/ ተብላ በምትጠራው (አንዳንድ ሰዎች ኦፅ ትባላለች ይላሉ) አገር ነዋሪ የነበረ ሰው ነው፡፡በስተምሥራቅ ይኖሩ ከነበሩት ሀብታሞች ሁሉ የተከበረና ባዕለ ጸጋ (እጅግ ብዙ ሀብት ያለው ሰው) እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገረለት ሰው ነው፡፡ሚስት አግብቶ ዐሥር ልጆችን ወልዷል።ከእነዚህም ሰባቱ ወንዶች ሦስቱ ደግም ሴቶች ናቸው።ሀብቱም በመጽሐፈ ኢዮብ እንደተገለጠው ሰባት ሺሕ በጎች፤ ሦስት ሺሕ ግመሎች አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች (ወይፈኖቹ ጊደሮቹ ላሞቹ ሳይቆጠሩ) እንዲሁም አምስት መቶ አህዮች ነበሩት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:24изменён

    + የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት ጥናት +1.መጽሐፈ ኢዮብ 2.መዝሙረ ዳዊት 3.መጽሐፈ ምሳሌ 4.መጽሐፈ ተግሣጽ 5.መጽሐፈ ጥበብ 6.መጽሐፈ መክብብ 7.መጽሐፈ መኀልየ መኀልይ 8.መጽሐፈ ሲራክሁሉንም ለየብቻ እናያቸዋለን ።
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:23

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:22

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:21

    መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮንን በ8 ዓበይት ክፍሎች ከፍሎ በዚ መልኩ ማጥናት ይቻላል :-
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:13изменён

    +የመጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ጥናት+ዮሴፍ የስሙ ትርጉም “ይጨምር” ማለት ነው።በዚህ ስም ከተጠሩ ሰዎች የያዕቆብ ዐሥራ አንደኛ ወንድ ልጅ የራሔል የበኩር ልጅ (ዘፍ 30:22)፤ በአናጢነት ሥራ ሲተዳደር የነበረውና የሥጋ ዝምድና ያለው ከዳዊት ዘር የተወለደው (ሉቃ 2:4)የማርያም እጮኛ ተብሎ ለፋሲካ በዓል ከማርያም ጋር ኢየሱስን ወደ ኢየሩሳሌም የወሰደው (ማቴ 1:18-25) እንዲሁም ቅንና ጻድቅ የነበረው የሸንጐ አማካሪ በመሆኑ አይሁድን ስለፈራ ክርስቶስን በስውር ይከተል የነበረ፤ በራሱ መቃብር ለመቅበር የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ከጲላጦስ የለመነና የቀበረው (ማቴ 27:57-60) የአርማትያሱ ዮሴፍ የተባሉት ተጠቃሾች ናቸው።ይህኛው ዮሴፍ ግን ከላይ ከተጠቀሱት ልዩ ታሪክ ያለው ከ38-100 ዓ.ም. የነበረ የታሪክ አዋቂና ጸሐፊ በዓለሙም ዕውቀት የታወቀ ሰው ነው፡፡ዮሴፍ የኮርዮን ልጅ በመሆኑ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን (Josephus Flavius) ተብሎ ይጠራል።ተወልዶ ያደገው በኢየሩሳሌም ሲሆን ወቅቱም አይሁድ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ከፍተኛ ጥረት በሚያደርጉበት ዘመን ነበር።በወቅቱም ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን የጦርነቱ ዋና ተሳታፊ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት መሆኑ ከታሪክ ምሁርነትና ጸሐፊነት ቀጥሎ የሚነገርለት ሰው እንዲሆን አስችሎታል፡፡በዮሴፍ ወልደ ኮርዮን የተዘጋጀው መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ81 ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡መጽሐፉ የአይሁድን አጠቃላይ ጉዞ እስከ 70 ዓመተ ምሕረት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መቃጠል ድረስ ያለውን ታሪክ በዝርዝር
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:12

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:11

    መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 10 ምእራፎች ያሉት መጽሐፍ ነው።በይዘት በዚ መልኩ ከፋፍሎ ማጥናት ይቻላል :-
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:05изменён

    + የመጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ጥናት +መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ስለጽድቅና ኩነኔ ስለ ትንሣኤ ሙታን ስለ ሓላፍያትና መጻዕያት(ስላለፉት እና ስለሚመጡት) አጠቃላይ ሁኔታ የሚያትት ነው።መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ሦስተኛውን የመቃቢስ ትውልድ ማለትም "መቃቢስ ዘአልዓዛር" የተባለውን ክፍል የያዘና አይሁድ እንዴት እንደዳኑ ይተርካል።ይኸውም የሰውን ልጅ ሕይወት በዘመናት እይታ የብሉያትና የሐዲሳት ንጽጽር የቀረበበት ነው፡፡ሰብአው ሊቃናት እና የግእዙ ጥንታውያኑ የመጽሐፍ ቅጂዎች ሁለቱን መጻሕፍት አንድ መጽሐፍ አድርገው እንደሚቆጥሩ የታወቀ ነው፡፡መቃብያን ሣልስ መቃቢስ ዘአልዓዛር የተባለውን የመቃቢስ ትውልድ መሠረተ ታሪክ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው።በዘመነ ክርስቶስ የነበሩት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ሲጠይቁት የነበረውን የኃጢአት የጽድቅና የኩነኔ ሁኔታዎች የትንሣኤ ዘለክብርና ዘለሀሣር በአጠቃላይ ስለ ትንሣኤ ሙታን ስለመጻዕያትና ኀላፍያት የጠየቋቸው አስቀድሞ መልስ የተሰጠበት መጽሐፍ ነው። ዘመኑም 1221-204 ከቅ.ል.ክ በፊት በነገሠው በግብፅ ንጉሥ በበጥሊሞስ ዘመነ መንግሥት አይሁድ ከጥፋት ስላዳኑበት ሁኔታ በስፋት የሚተርክ መጽሐፍ እንደሆነ ይነገራል (መ. መዝ ቃላት 1992: ገጽ 36)ተፈጸመ
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:03

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:02

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:01

    መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ 21 ምእራፎችን የያዘ መጽሐፍ ነው።በይዘት በዚ መልኩ ከፋፍሎ ማጥናት ይቻላል :-
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 16:00

    + የመጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ጥናት +መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ መቃቢስ የተባለው የሞዓብ ንጉሥ እስራኤላውያንን ከተዋጋ በኋላ ተጸጽቶ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዳስተማራቸው የሚዘክር መጽሐፍ ነው።ይኽ መጽሐፍ በአብዛኛው የመቃቢስ ዘሞዓብን ታሪክ የሚናገር ነው።ተፈጸመ
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 15:58

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 15:57

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  • ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    18 сент., 15:57

    Иллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትИллюстрация к посту канала ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት