Последние посты

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 11:13
переслано из @orthodoxtewahdoc
📌#የፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ታሪክ ❣️❶❹🥀◉አረጋዊ ማለት ያረጀ፣የሸመገለ ፣ አዋቂ ትልቅ ሰው ማለት ነው:: አባታችን ይህ ስም የተሰጣቸው ገና ልጅ እያሉ ነበር አባታችን አቡነ አረጋዊ ከተሰሐቱ ቅዱሳን (ከሮምና ኤሽያ ከመጡት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበር፡፡ እናታቸው ንገሰተ እደና ትባላለች፡፡📌የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ይባል ነበር፡፡ የሚካኤል ማለት ነው ፡ ጥበብ መንፈሳዊ ሲማሩ አድገው ወደ እሰክድርያ ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ አባምኔቱ፡ አባ ጳኩሚስ፡በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓርገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡ የንጉስ ልጅ መባልን የንጉስ አልጋ ወራሽነትን ሸሽተው የሞቀ ቤተ ሰቦቻቸውን ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባምኔቱም ወደዚህች የሕይወት መንገድ ስለመራህን ብፁህ አረጋዊ መባል ይገባሃል ፡ ብለው የበሰለ አስተሳሰባቸውን መሠረት አድርገው ገና አንድ ፍሬ ህፃን እያሉ አረጋዊ ተብለው ተጠሩ፡፡🥀❤️ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ መዐረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል። በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ሲያስተምሩ የሀገራችንን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በክነፉ ተሸክሞ አክሱ አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሶ ሄደው ስለ ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱ ሁሉ ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ራሳቸውን ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡ለቅዱሳኑ መምጣት ዋነኛው ምክንያት ንጉስ አልሜዳ ያነሳውን የምንታዌ(የሁለት በህሪ)ትምህርት በመቃወማቸው የደረሰባቸውን የነገስታት ጫና ለመከላከል ሲሉ ነው፡፡ የአባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀመዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸው እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሱ፡፡ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፡11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡ ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው መስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡📌በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ቅዱሳን መላእክት ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው📌ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል፡፡በረከታቸው፣ ቃልኪዳናቸው አማላጅነታቸው አይለየን አሜን 🙏ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን🙏✝️💒ጆይን https://t.me/OrthodoxtewahdocTelegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 11:13
переслано из @orthodoxtewahdoc
🌹#ሙሽራው_ገብረ_ክርስቶስ_ማነው⁉🌹♨•••ወር በገባ በ14 የሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ወርኀዊ በዓሉ ነው።- ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ወላጅ አባቱ የቍስጥንጥንያው ንጉሥ #ቴዎዶስዮስና እናቱ ንግሥት #መርኬዛ በስለት ያገኙት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆነ ሃይማኖትን እያስተማሩት በምግባር በእጅጉ ተንከባክበው አሳድገውታል።የአባቱን ንግሥና በመውረስ ቍስጥንጥንያን እንዲገዛላቸው በመፈለግ ወላጆቹ ለአካለ መጠን ሲደርስ የሮሙን ንጉሥ ሴት ልጅ አጋቡት፡፡ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና የሠርጉ ዕለት ሌሊት የእርሱንም ሆነ የሙሽይቱን ድንግልና እንደጠበቀ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ሩቅ ሀገር በመሄድ በቤተክርስቲያን ተቀምጦ ከነዳያን ጋር ተደባልቆ በመለመን ለምኖ ያገኘውንም ለሌሎች እየመጸወተ በጾም በጸሎት ተጠምዶ 15 ዓመት ኖረ፡፡✞ እመቤታችን ተገልጻ ለአንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋይ የገብረ ክርስቶስን ጽድቅ ብትነግረው ምሥጢሩን ለሀገሩ ሁሉ አዳረሰበት፡፡ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስም ‹‹ግብሬ ታወቀ፣ ከዚህ ውዳሴ ከንቱ ልሽሽ›› በማለት ወደሌላ ሀገር በመርከብ ሲጓዝ ፈቃደ እግዚአብሔር መርከቢቱን ያለ አቅጣጫዋ ወስዶ አባቱ ደጅ አደረሰው፡፡ ማንነቱን እንደደበቀና ዓለምን ምን ያህል እንደናቃት ይረዳ ዘንድ በአባቱና በንጉሡ ደጅ የኔ ቢጤ ለማኝ ሆኖ ለአባቱ ውሾች የሚሰጠውን ፍርፋሪ እየተመገበ አሁንም 15 ዓመት ሙሉ በትዕግስት ተቀመጠ፡፡የአባቱ አሽከሮች እንኳን እጣቢና ቆሻሻውን ሁሉ እየደፉበት ሲያሠቃዩት የአባቱ ውሾች ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር፡፡ በአጠቃላይ ገብረ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የታላቅ ንጉሥ ልጅ ሲሆን ነገር ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ ስለ ጽድቅ ተሰዶ እየለመነ ያገኘውን እየመጸወተ በጾም በጸሎት እየተጋደለ 30 ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፡፡በመጨረሻም ጌታችን እመቤታችንን፣ ቅዱሳን መላእክትን ሁሉ፣ ከገብረ ክርስቶስ በፊት የነበሩ ነቢያትን ሁሉ፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ቃልኪዳን ከገባለት በኋላ ከጌታችን ጋር አብረውት የመጡት ሁሉ በታላቅ ክብርና ምስጋና እያመሰገኑት ጌታችን ክብርት ነፍሱን በእቅፉ ተቀብሎ አሳርጓታል፡፡የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በቅዳሴ ላይ ሳሉ ከንጉሡ ቤት ሄደው የገብረ ክርስቶስን ሥጋ እንዲያመጡ የእግዚአብሔር ድምፅ ከሰማይ በትእዛዝ መጣላቸውና ሄደው ቢያዩ የገብረ ክርስቶስን ሥጋ በንጉሥTelegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 11:13
переслано из @orthodoxtewahdoc
💙#አባ መቃርስ ማን ናቸው⁉🌹☞📕•••ወር በገባ በ14 የአባታችን የአባ መቃርስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው በልጅነቱ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እየተማረ አደገ፡፡ የዓለምን ከንቱነት ተመልክቶ ዳግመኛም የኃጢአንንና የጻድቃን ዎጋቸው አይቶ ወደ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ከመነኮሰም በኃላ የ10ቀን መንገድ ተጉዞ ኩዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ላይ ደረሰ፡፡☞በዚያም ኩዕንትን ወደ መልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል በዚህም ተራራ ላይ ብቸኛ ነኝና ሰብስቦ የሚያገባልኝ የለም፡፡ ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራህን ሥጋ በሐሜት የምንበላው አይደለምን?ሌላ ምግብ እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃልብሎ ከዚያች ዕለት ወዲህ ለምግቡ ቆቅ የሚያጠምድ ሆኖ በእግዚአብሔር ፈቃድ በየቀኑ አንድ አንድ ቆቅ የሚያዙለት ሆነ፡፡ ☞በየቀኑም አንድ አንድ ቆቅ እየተመገበ ውኃ እየጠጣ ፈጣሪውን እያመሰገነ በታላቅ ተጋድሎ ሆኖ የሰውን ፊት ሳያይና ከማንም ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ ☞ከቁስጥንጥንያ ከተማ የወጣ አንድ መነኩሴ ዋሻ ሲፈልግ አባ መቃርስ ደግሞ ቆቅ ሲያጠምድ አየውና ለሐሜት ቸኩሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ሄደ ለሊቀ ጳጳሳቱ"ቆቅ እያጠመደ ሥጋ የሚበላ መነኩሴ አገኘሁ፤ እርሱም በሕዝብ ዘንድ ሊስነቅፈን ነው ብሎ ነገረው፡፡ ☞ሊቀ ጳጳሳቱም ከአንድ ሌላ መነኩሴ ጋር ድጋሚ እንዲያረጋግጥላቸው ላካአቸው፡፡ እነርሱም ገና ከበዓቱ ሳይደርሱ አባ መቃርስ ቆቅ ሊያጠምድ ሄደና ያለወትሮው በአንዲት ወጥመድ ሦስት ቆቆችን ተያዙለት፡፡ ☞ሌላ ጊዜ በቀን አንድ ብቻ ነበር የሚያዝለት ዛሬ ግን እግዚአብሔር ለሚመጡት እንግዶችም ጭምር ሲያዘጋችላቸው ነው ያለወትሮም ዛሬ ሦስት ሆነው የተያዙለት፡፡ ]አባ መቃርስም ሁለቱን መነኮሳት ሲያያቸው ሁለት ተጨማሪ ሆነው የተያዙለት ቆቆች የእንግዶቹ መሆናቸውን ዐውቆ ጌታችንን አመስገነው፡፡ ☞እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ እስካቀረበላቸው ድረስ በመቃርስ ላይ ይጠቋቆሙበት ነበር፡፡ ☞አባ መቃርስም ምግብ አዘጋጅቶ ሲጨርስ የራሱን ድርሻ አንዷን ቆቅ አስቀርቶ ሁለቱን ለእንግዶች አቀረበላቸው፡፡ ☞እርሰሱም በልቶ ጨርሶ ቀና ሲል እንግዶቹን መነኮሳት እንዳልበሉ ተመልከተና አባቶቼ ለምን አልበላችሁም?አላቸው፡፡ ☞እነርሱም እኛ መነኮሳት ስለሆንን ሥጋ አንበላም አሉት፡፡ አባ መቃርስም እሺ ተውት አላቸውና እነዚያን አብስሎ በገበታ ላይ ለምግብነት ያቀረበላቸውን ሁለት ቆቆች ሦስት ጊዜ በእስትንፋሱ እፍ ቢልበባቸው ሕይወት ዘርተው በረሩና ወደ ጫካ ሄዱ፡፡ ☞እነዚያ መነኮሳትም እጅግ ደንግጠው ማረን ይቅር በለን ቅዱሱን የእግዚአብሔር ሰው በከንቱ አምተንሀል ብለው እግሩ ሥር ሲወዱቁ እግዚአብሔር የሁላችንን በደል ይቅር ይበለን አላቸው፡፡ ☞ሁለቱ መነኮሳት ወደ ቁሰጥንጥንያ ተመልሰው ለሊቀ ጳጳሳቱ ለሕዝቡ ያዩትን ነገር መሰከሩ፡፡Telegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 11:12
переслано из @orthodoxtewahdoc
††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ አጋቶን ወአቡነ ያሳይ ዘመንዳባ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††††† አባ አጋቶን ዘዓምድ †††††† ታላቁ ጻድቅ በትውልድ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩበት ዘመንም ከ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው:: በእርግጥ 'አጋቶን ' በሚባል ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ቅድሚያውን 2ቱ ይወስዳሉ:: አንደኛው አባ አጋቶን ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሰው የኖሩት አባት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: እኒህኛው 'ዘዓምድ ' ይባላሉ:: ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው::አባ አጋቶን ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር:: በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ: በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ 'ይገባሃል' ብለው ቅስናን ሾሟቸው::የማታ ማታ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ተምኔተ ልባቸውን ፈጽሞላቸው ወደ በርሃ ሔዱ:: ወቅቱ የግብጽ ገዳማት በቅዱሳን ሕይወት የበሩበት ነውና እዚህም እዚያም አበውና እናቶች ይገኙ ነበር::አባ አጋቶንም የከዋክብቱ አበው አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም ደቀ መዝሙር ሆነው ገቡ:: አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከእነዚህ አባቶች ተቀበሉ:: በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ::ጻድቁ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ቅዱሳንን ተጋድሎ ጠዋት ማታእያነበቡ መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑ ነበር:: በተለይ የታላቁን ስምዖን ዘዓምድን ገድል ሲያነቡ ሕሊናቸውን ደስ ይለው: ይህንኑ ገድል ይመኙ ነበር:: እድሜአቸው 50 ዓመት በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ:: ይህን ለገዳሙ አባቶች ቢያማክሯቸው አበው:- "ይበል! ሸጋ ምክር ነው:: እግዚአብሔር ያስፈጽምህ!" ብለው መርቀው አሰናበቷቸው:: አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ:: በጣምም ወደ ዓለም ሳይገቡ: ከዓለም (ከከተማም) በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ::ከዚህች ዕለት ጀምረው ጻድቁ ለ50 ዓመታት ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው: ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም:: ማዕከለ ገዳም ወዓለም ናቸውና ለምዕመናንም ሆነ ለመነኮሳት አጽናኝ አባት ሆኑ:: ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ:: የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል:: የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል:: ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል:: ለራሳቸው ግን ከጸሎት: ከጾምና ከትሕርምት በቀር ምንም አልነበራቸውም:: በተለይ እነዚህ ስራዎቻቸው ይዘከሩላቸዋል:: 1.አጥማቂ ነን እያሉ ሕዝቡን ያስቱ የነበሩ ሰዎችን እየጠሩ እንዲህ የሚያስደርጋቸውን ጋኔን ከእነሱ አስወጥተዋል:: 2.እርሳቸውን ያልሰሙት ግን መጨረሻቸው ጥፋት ሆኗል:: 3.ፍጹም ወንጌልን በሕይወትና በአንደበት መስክረዋል:: 4.ሕዝቡን በንስሃ አስጊጠዋል:: 5.ተግሳጽ የሚገባውን ገስጸዋል::ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላበተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በክብርና በዝማሬ ተቀብረዋል::††† አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ †††††† እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ በጣና ገዳማትውስጥ ያበሩ ኮከብ ናቸው:: ከ7ቱ ከዋክብት (አባ ዮሐንስ፣ አባ ታዴዎስ፣ አባ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻና አባ ሳሙኤል ዘጣሬጣ ) እርሳቸው አንዱ ናቸው:: እነዚህ አበው ከገዳማዊ ሕይወታቸው ባሻገር በምስጉን የወንጌል አገልግሎታቸው የሚታወቁ ናቸው::ገድላቸው እንደሚለው አቡነ ያሳይ የዐፄ ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ ልጅ ሲሆኑ የተወለዱትም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሽዋ: ተጉለት ውስጥ ነው:: ገና በልጅነታቸው ወደ አባታቸው ቤተ መንግስት የሚመጡ መነኮሳትን እግር እያጠቡ ሥርዓተ ምንኩስናን በድብቅ ያጠኑ ነበር::ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ጠፍተው ወደ ትግራይ ተጓዙ:: በዚህም ምክንያት 'መናኔ መንግስት' ይባላሉ:: በዚያም ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ውስጥ ገብተው የታላቁ አባት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ሆኑ::ቀደም ሲል የጠቀስናቸው 7ቱ አበው በዚያ ነበሩና 7ቱም በአንድ ቀን ሲመነኩሱ ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ ነበር:: አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመን ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስ አለ ይባላል::አቡነ ያሳይ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው: ከ2ቱ ባልንጀሮቻቸው (አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ) ጋር ወደ ጣና ሐይቅ መጡ:: በዚያም አካባቢ ተአምራትን እየሠሩ ሕዝቡንም እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ጌታ ወደየፈቀደላቸው ቦታ ተለያዩ::አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ: አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ: ከዚያ ወደ ጉጉቤ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ:: ጻድቁ ወደ አርባ ምንጭ ሒደው ታቦተ መድኃኔ ዓለምን ይዘው ሲመጡ ጣናን የሚሻገሩበት አጡ:: ጌታን ቢማጸኑት:- "ምነው እሷን ድንጋይ ባርከህ አትቀመጥባትም?" አላቸው:: እሳቸውም በእምነት: ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ጣናን ተሻገሩት:: ይህንን ከርቀት ያዩ የዘመኑ ሰዎች "ብዙ ተአምር አይተናል: ነገር ግን ማን እንደ አባ! ጣናን በድንጋይ የተሻገረ" ሲሉ አድንቀዋቸዋል::
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 08:33
переслано из @zikirekdusn
""🌼 በዓለ ጼዴንያ ማርያም ""°ቅዱሳት ሥዕላት (አምላካውያት)🌼°ምክር - ለአገልጋዮች🌼(መስከረም 10 - 2019)
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 06:07
ኩራ! BE PROUD!በምንም ውስጥ እለፍ ማለፍህን በጉልህ ተመልከት፣ ምንም ይድረስብህ ከደረሰብህ ነገር የተማርከውን በሚገባ አስታውስ፣ የፈለከውን ነገር ተቀማ ነገር ግን በመቀማትህ ስለተሰበርከው ሳይሆን ዳግም እርሱን ለማግኘት የጣርከውን ጥረት አድንቅ። ህመምህን መጠቀም ከቻልክ እርሱ ወሳኙ የለውጥህ ግበዓት ነው፤ ፍላጎትህን መጠቀም ከቻልክ እርሱ ወሳኙ የእድገትህ መንገድ ጠቋሚ ነው። በመጣህባቸው እያንዳንዱ መንገዶች ኩራ፣ እራስህ ላይ ባወጣሃቸው እያንዳንዶቹ ወጪዎች ደስ ይበልህ፣ ባለፍካቸው የተለያዩ መሰናክሎች፣ በተወጣሃቸው እያንዳንዱ ህመሞች ደስ ይበልህ፣ በተማርካቸው እያንዳንዱ የህይወት ትምህርቶች ኩራት ይሰማህ። መጓዝ የነበረብህን ርቀት ተጉዘሃል፣ መሔድ የነበረብህ ስፍራ ሔደሃል፣ ለእራስህም ለቤተሰብህም መክፈል የሚገባህን ዋጋ ከፍለሃል። ያለማቋረጥ እየጣርክ ከሆነ በፍፁም ባዶነት አይሰማህ፣ በጭራሽ ምንም እያደረክ እንዳሆነ አይሰማህ። ብሩህ ተስፋህን በጥልቀት ተመልከት።አዎ! ጀግናዬ...! ኩራ! BE PROUD! እራስህን በመሆንህ ኩራ፣ በውስጣዊ ማንነትህ፣ በውጫዊ ገፅታህ፣ በባህሪህና በአንተነትህ ሙላት ይሰማህ። የጎደለህን እያሳደድክ በእራስህ ልትኮራ አትችልም፣ ያጣሀው ላይ እያተኮርክ በእራስህ ደስተኛ ልትሆን አትችልም። ከባዱን እያደረክ ህይወትህን ቀላል አድርገው፣ እራስህን እየፈተንክ ጥንካሬህን አምጣው፣ መገፋትህን የጉዞህ ግበዓት አድርገው። መጠላት፣ መተቸት፣ መገፋት በምንም መንገድ ለእራስህ የሰጠሀውን ዋጋ እንዲያሳንስ አታድርግ። ኩራትህን ከሚገዳደር የትኛውም ተግባር እራስህን ጠብቅ፣ ዋጋህን ከሚያሳንስ ማንኛውም አካሔድ እራስህን ጠብቅ። ከችግሮችህ ለማምለጥ መሮጥ የሚያኮራህ ተግባር አይደለም፣ የእራስህን ህፀፅ ደጋግመህ መመልከት እንዴትም አይገነባህም።አዎ! አሁን ያለህበት ስፍራ ዛሬ ባያኮራህ ነገ እንደሚያኮራህ፣ ዛሬ ያለህበት ሁኔታ ዛሬ ባያስደስትህ ወደፊት እንደሚያስደስትህ እርግጠኛ ሁን። ስሜት ለማይሰጥህ ነገር የመታገል ግዴታ የለብህም፣ ዋጋህን ከማጨምሩ ሰዎች ጋር ህብረት የመፍጠር ሃላፊነት የለብህም፣ በማትወደው መንገድ ጥረትህን የማሳነስ አጣብቂኝ ውስጥ መግባት አይኖርብህም። ኩራት እራስህን ከመቀበል ይጀምራል፣ ኩራት መገለጫው በእራስመተማመመን ነው፣ ኩራት ማሳያው እለት እለት እራስን ለማሻሻል ሳያቋርጡ መትጋት ነው። መንገድህ እንቅፋቶች ቢበዙበት፣ መሰናክል ቢኖረው እንቅፋቶችህን ሳትሸሽ፣ መሰናክልህን ሳትፈራ ለመጋፈጥ ወደፊት በመጓዝህ ብቻ በእራስህ ክራት ይሰማህ። ከጥረትህ በላይ ጥረትህ ውስጥ ትርጉምን ፈልግ፣ ከድካምህ በላይ ዋጋህን ስለመጨመሩ እርግጠኛ ሁን። ላመንክበት ተግባር ቅንጣት እፍረት አይሰማህ፣ ውስጥህን አጠንክር፣ በኩራትም አከናውነው።
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
23 сент., 02:26
አሁን በዚህ ዘመን መነኮሳት እንደሚያመነዝሩ ትሰማላችሁ፤ ድሮ ግን መነኩሴ አመንዝሮ የማያውቅ ይመስላችኋልን ?ድሮ በቪዲዮ ስለማይለቀቅበት ነው እንጂ በኃጢአት የማይወድቅ መነኩሴ ስላልነበረ አይደለም።➡️ሰው ድሮም ይወድቃል፣ ድሮም ንስሐ ይገባል፤ ድሮም ኃጢአት ነበር፣ ድሮም ጽድቅ ነበር።➡️ድሮም ቅዱሳን ባሕታውያን ነበሩ፣ ድሮም ውድቀት የነበረባቸው ነበሩ።➡️ነገር ግን ይህንን ሲያይ ምንኩስናን እየጠላው የሚመነኩስ ይጠፋል ብዬ አስባለሁ።😥ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤✅አንደኛ፡ የመነኮሳትን ኃጢአት ስትሰሙ፣ ሰውዬው የዚያን ዕለት ቢወድቅ ሌላ ቀን ተመልሶ ሊረባ ይችላል።✅ሁለተኛ ደግሞ፡ ሁሉም መነኩሴ እንደዚያ ነው ብላችሁ አትደምድሙ፤እንኳን ሁሉም መነኩሴ፣ ያ መነኩሴ ራሱ ሁልጊዜ እንደዚያ አይደለም—አልቅሶ ንስሐ ይገባል።ገዳማችንን እንጠብቅ!አባ ገብረ ኪዳን🙏


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 20:55
переслано из @orthodoxtewahdoc
☦መልክዓ ቅዱስ ሩፋኤል📗"ቅዱስ ሩፋኤል በእለተ ቀኑ ልጅ አተው በየፀበሉ የሚንከራተቱትን ልጅ ያስታቅፍልን በልጅ ይባርክልን አሜን።🙏https://t.me/Orthodoxtewahdoc
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 18:07
የቀን : እረኛ : የሌሊት : ጠባቂ : ቅዱስ : ሚካኤልቅድስት አፎሚያን ከዲያብሎስ መንጋጋ ያስጣለው: የባሕራንን የሞቱን ጦማር ቀዶ ወደ ሠርግ የቀየረው መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በተአምራቱ በቃል ኪዳኑ የሚታመኑትን ሁሉ ከምሕረት አልባው ከዲያብሎስ ደባ ከአጋንንት ድብደባ ከዚህ ዓለም ፈተና ይጠብቀን። አሜን 🤲❤


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 16:06
✨ ድንግል ሴት ፈተና የሌለባት አይደለችም ✨ 💐 ድንግል ሴት ግን ምንድን ናት?.....👉እኔ ደካማ እና መንፈስቅዱስን ና ፋ ቂ እህታችሁ አሁን የምጽፈው ነገር የበቃ እና የማይታረም ፅሑፍ አይደለም ...ድንግል ሴት ፈተና የማይደርስባት አይደለችም። ወንድም ሴትም በቅድስት ሥላሴ አምሳል ሲፈጠሩ እሷም በአዳም ስጋ እና አጥንት የተገኘች ስለሆነች ፈተናዋ ሁሉ ከወንድ እኩል ጋር ነው። በዝሙት ሃሳብ በስጋ ፍትወት ትፈተናለች።በብዙም ትደክማለች። ይሄንንም ፈተናዋን አልፋ ከስሜቷ አምላኳን አክብራ በንስሃ በእንባዋ ሃሳቧን አጥባ ድንግላናዋን ጠብቃ ለትዳር(ለሚስትነት) አልያም ለምንኩስና ህይወት ትበቃለች። ይሄም የመንፈሳዊ ህይወቷን ብርታት ጽናት ያሳያል።ድንግል ሴት ምድራዊ ህይወት አላት። ድንግላናዋን አስጠብቃ መዋብ ራሷን መጠበቅ ከሰዎች ጋር መቀላቀል ራሷን ሳትስት ከወዳጆቿ ጋር መደሰት መማር ሰርቶ መግባት ነግዶ ማትረፍ የህይወት ገጽ ነው። ራሷን ካለጊዜው ከስጋ ደስታ ከቆጠበች ከዝሙት ከለለች እንጂ ኑሮዋ ሁሉ በአለም እንዳሉት ወጥቶ በመግባት ሂደት ውስጥ ናት። የዚህ ክብር ዋጋ ገብቶሽም ሳታውቂውም ጠብቀሽዋል እና አሁንም በጽናት ቁሚ። የዚህ ዋጋ እጅግ የከበረ ነውና። ለበቁት ሰማያዊ ክንፍን ያሰጠ ህይወት ነው። በድንግልና የተጀመረ ህይወት በክብር የተጀመረ ነውና የትዳርሽ ፍሬ ሁሉ የክርስቶስ የእምነትሽ ስጦታዎች ናቸው። የአንቺ በንጽህና መቆየት ዋጋሽን ከፍ ያደርጋል እና እስከ ቅዱሰ ጋብቻ ዕለት በዝሙት እንዳትወድቂ ተጠበቂ
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 14:02
እኔ አላማ አለኝ!ከራስ ጋር ንግግር፦ "ደክሞኛል ነገር ግን አላማ አለኝ፣ ሰልችቶኛል ነገር ግን ራዕይ አለኝ፣ ደብሮኛል፣ ተነሳሽነቴ ጠፍቷል፣ ተነገሮች ተወሳስበውብኛል፣ ሁኔታዎች አልመቻች ብለውኛል፣ ከምቾቴ መውጣት አስጠልቶኛል፣ አዲስ ነገር መሞከር አስፈርቶኛል ነገር ግን ከነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ የሚበልጥ እለት እለት ልኖረው የሚባ፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ልፋለምለት የሚገባ፣ ስሜቶቼን የምገዛለት ትልቅ ህልም አለኝ። ህልሜ ስለደከመኝ የማቆመው አይደለም፣ ህልሜ ስለሰለቸኝ፣ ስለደበረኝ፣ ውስጤን ጥሩ ስሜት ስላልተሰማኝ ችላ የምለው አይደለም። ህልምን መኖር ማለት እራስ ላይ መሰልጠን እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁ። ባለትልቅ ህልም ባለቤት የሆነ ሰው የሚመራው ሁኔታ፣ ሰው ውይም ስሜቶቹ አይደሉም። የሚመራው ህልሙና ህልሙ ብቻ ነው። ማንም በዓመቱ መጨረሻ መምታት ያለበትን ግብ ለመምታት የሚፈልግ ሰው ለድካምና ድብርቱ እጅ የሚሰጥ ሰው አይደለም። ከማንም በላይ ከጊዜያዊ ሁኔታዎች በላይ እስከጥግ የመጓዝ ብርታቱና ንቃቱ አለው። ገዢ ሃሳቡ ከህልሙ ጋር የሚገኘው ሃሳቡ ነው፣ ቅድሚያ የሚሰጠው ያስቀመጠውን ግብ ለመምታ የሚያግዘውን ተግባር ነው።አዎ! ደክሞኛል ግን አላማ አለኝ! አላማዬን ድካሜን እያስታመምኩ ላሳካው አልችልም። ቢደክመኝም ስራዬን የመስራት ግዴታ አለብኝ፣ ቢሰለቸኝም እስከመጨረሻው የመጓዝ ግዴታ አለብኝ። ዓለም ለህልመኞች ብቻ የምትሆን አይደለችም። ይልቅ ህልመኞች ሆነው ከጊዜያዊው የድካምና የስንፍና ስሜቶች በላይ ለሆኑት ብርቱ ሰዎች የምትሆን ነች። ሃሳባቸው ትልቅ ነውና ተግባራቸውም ትልቅ ነው።
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc
📕#ተአምር_ዘአቡነ_ዘርዓ_ብሩክ🌹📘☞•••ወር በገባ በ13 ታስበው የሚውሉ አባታችን ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታአምር ይህ ነው ስሟ ፋሲካዊት በምትባል ሴትዮ ቤት እግዚአብሔር ዳግመኛ ታላላቅ ተአምራት አደረገ፡፡ ያቺም መልካም ሴት ሁል ጊዜ የዘርዐ ብሩክ መታሰቢያውን ታደረግ ነበር አሱንም ከመውደዷ የተነሳ ተገዛችለት ለቃሉም ታዙችለት፡፡☞በአንድ ወር ለመታሰቢያው የሚሆን የማኀበሯ ተራ በደረሰ ጊዜ ትደክም ጀመር ብዙ ቀን ሰትጥር ስትግር ሰይጣን ቀንቶባት የመታሰቢያውን የወይን ጠጅ አጠፋባት፡፡☞ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ሰለ ኃጢአቴና ሰለ በደሌ ነው ብላ ብዙ ምሾ እያወጣቸ ፈጽማ አለቀሰች፡፡ ☞እግዚአብሔርም የለቅሶዋን ጽናትና ኅዘኗን አይቶ በሰይጣን ቅናት የጠፋባትን ያን ወይን ጠጅ የቃናን ውሃ ለውጦ የጣመ እንዳደረገው ያን ቦዶ እንስራ ወደ ወይን ለወጠው ፈጽሞም ጣፈጠ፡፡ ☞በዚያ በጻድቁ አባቷ ዘርዐ ብሩክ ጸሎት ያ የወይን ጠጅ ተለውጦ እንዳ ጣፈጠ ያቺ ሴት አይታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ እናቱ ድንግል ማርያምንም አመሰገነች በጸሎቱና በአማላጅነቱ ተአምራትን መንክራትን ያየረገላት ቅዱስና ብፁዕ የሚሆን አባታችን ዘርዐ ቡሩክ እጅግ ወደደችው፡፡☞የጣፈጠው ያ የወይን ጠጅም በክቡር የሚካኤል በዓል ቀን ዳግመኛ አለቀባት የነበሩ ብዙ ማኀበርተኞችም እጅግ አዘኑ የወይን ጠጅ ትበደራቸው ዘንድ በየሀገሩ ዞረች የምትሰጣቸው የወይን ጠጅ ባጣች ጊዜ ከዚያ ከሚጣፍጠው የወይን ጠጅ የቀረ(የተረፈ)አንድ ማድጋ ቅራሪ አመጣችላቸው በቀዱት ጊዜ አተላ ሆነ፡፡☞ያዚ ሴትም እጅግ አዘነች ማኀበርተኞችም ሁሉ እንደ አርሷ አዘኑTelegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc



"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc
ልቤ ለመዳን ይሻልና ለዘለአለሚዊነትህ ከከንቱ ሞት ኀጢአት ያድነኝ ዘንድ እማፀንህ አለውለመንግሥትህ ፍፃሜ የሌለው ቃልህና አካልህ በመልክዕና በቁመት እጅግ የከበረ የምትደነቅ የብርሃናት መገኛ እግዚአብሔር አብ ሆይ ከአቅም በላይ በኾነና ለመይወሰን አካለ አቅም ህና ዳግመኛም ግርማ ራእዩ ለሚያስደንቅ መልክዕህ ሰላምታ ይገባል አንተ እውነተኛ አምላክ ሥትሆን ኹሉን በፈቃድህ የፈፀምህ የኹሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አብ ሆይ ኹሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉን ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና በእውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግን አስተምረኝ። እግዚአብሔር አብ ሆይ በለሊትና ቀኑን ሙሉ ምስጋና ይገባሀል።እግዚአብሔር ዓብ ሆይ በክረምት እና በበጋ አውራኀ ልክ ምስጋና ይገባል ። እግዚአብሔር አብ ሆይ በማይታየውም ኹሉ ዘንድ ምስጋና ይገባል አለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የነበረና የአለ የሚኖርም ምስጋናህን እነሆ ሰማይ ይናገራል አቤቱ እግዚአብሔር አብ ሆይ ከሥጋና ነፍስ መከራ እኔ _ን ጠብቀኝ ብርሀንህንም አብራልኝ ለዘላለሙ አሜን ።አባታችን ሆይ https://t.me/OrthodoxtewahdocTelegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc
🌹ወር በገባ በ13 እግዚአብሔር አብ ነው እንኳን አደረሰን🎋♨#መልክዐ እግዚአብሔር አብ 🌹📗•••ፀጋን የምታድል የመከራና የችግር ጊዜያትንም የምታሶግድ ፍፁም አለማዊ አምላክ እግዚአብሔር አብ ሆይ ልመናውን የማታቋርጥ ነፍሴ አስቀድሞ ነብያትህ ኄኖክንና ዕዝራን ማስተዋልን እንደመላኋቸው ንጉስን ከወታደሮች ጋራ የሚያጸና ይቅርታህ ይርዳኝ ትልሀለች ።ወዳጅህ እስራኤልን አፍህን ክፈት እኔም አመላዋለሁ ያልኽው እግዚአብሄር አብ ሆይ አንተ ርኽረኽ እና ፍፁም አምላክ ነህ ምስጋናህን አቀርብ ዘንድ አንደበቴን አዘጋጃለሁ። በደሴተ ፍጥሞለ ለነበረ ቅዱስ ዮሐንስ ራዕይን የገለፅህ እግዚአብሔር አብሆይ ጉድለት ችልታ በሌለበት አዲስ አንደበት የመፀሐፍት ሚሥጥራትን አንብቢና ተርጉሜ ህግህን ለማስተማር የጀመርሁትን አዲስ ግብር እፈፅም ዘንድ አቤቱ ፀጋህን አድለኝ ። ከዘመናት አስቀድሞ የነበርኽ የዘመናት ባለቤት ዘመናትንም አሳልፍኽ የምትኖር በባሕርይህ ጉድለት የሌለብህ በፈጡራን ሁሉ አንደበት የምትመሰገን እግዚአብሔር አብ ሆይ ዘመናትን በፀጥታ የምታፈራርቅ አንተ ነኽና ፈጽሞ ለተመሰገነ ዝክረ ስምህ ሰላምታ ይገባል ከእግዚአብሔር ወልድ እና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስጋርራ ዕሩይ የሆንኽ የብርሃኑ ክበብ ለሚያስደንቅ የራስ ፀጉርህና ምሳሌ የሌለው ምስጋና የሚገባህ እግዚአብሔር አብ ሆይ የሦስትነት የአንድነተመቸሀለ ፀሐይ ለአለም ሁሉ ጌጥ ኾኖ ከምዕራብ። እስከ ምሥራቅ ከምድር እስከ ሰማይ ያበርራል የኹላችን መለያ ክብርህ ሰማያትን የመላ ጌትነትህም ፈጽሞ የተመሰገነ እግዚአብሔር አብ ሆይ ከኹለቱ እግዚአብሔር ወልድና
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc



"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc
#አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ማለት⁉♨☞ወር በገባ በ13 የአቡነ ዮሐንስ (ዘደብረ ቢዘን)ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል ነው እኚህ ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጥቅምት 14 ቀን ተወለዱ ሀገራቸው ትግራይ አድዋ አውራጃ አህሳአ ልዩ ቀበሌ እንዳ መንደር ይባላል።☞አቡነ ዮሐንስ የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ደቀመዝሙር ሲሆኑ፣አቡነ ፊልጶስ ሲያርፉ በሳቸው ተተክው ደብረ ቢዘን ገዳምን በአበምኔትነት አስተዳድረዋል። ☞እንደ ነቢየ እግዚአብሔር ደመናን ዝናም እንዳይሰጥ የለጎሙ የከለከሉ ስለሆኑ "ለጓሜ ደመና" በመባል ይታወቃሉ። ነቢዩ ኤልሳዕ በመንፈስ ቅዱስ ሁሉን እንደሚያውቅ ሁሉ አቡነ ዮሐንስም ሰው በልቡ የሚያስበውን ያውቁ ነበር። ☞አቡነ ዮሐንስ በተወለዱበት ሀገር ትግራይ በአህሳአ በስማቸው የተገደመ ''እንዳ አቡነ ዮሐንስ ገዳም" ፣ዛሬ ደብር ነው። አቡነ ዮሐንስ በመነኮሱበትና ባገለገሉበት በደብረ ቢዘን ገዳም በኅዳር 13 ቀን አርፈው ተቀብረዋል። ☞""አቡነ ዮሐንስ ዘአስገዶም"" በመባልም ይጠራሉ። ☞በስማቸው የተሰሩ 5 አብያ ተክርስቲያናት አሉ አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ጻድቁ ስለ አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ብሎ ከዘመኑ መቅሰፍትና ጥፋት ይሠውረን፡፡ ☞(ገድለ አበው ቅዱሳን ዘደብረ ቢዘን)Telegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc



"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc
🌹📗ሩፋኤል ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው ⁉✳ትርጉሙ እንዲህ ነው ፣ በልሳነ ዕብራይስጥ ሩፋ ማለት ጤና ፣ ፈውስ ፣ መድሃኒት ሲሆን ኤል ማለት ደሞ አምላክ ፣ እግዚአብሔር ማለትነው። ♨አምጻኤ ዓለማት እግዚአ መላዕክት እግዚአብሔር በነገደ መላዕክት አለቆች ይኾኑ ሰብዓቱን ሹሟል ። ቅዱስ ሩፋኤልን ከሊቃነ ነገደ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በመቀጠል በማዕርግ ሶስተኛ ኾኖ የተሾመው ሊቀመላዕክት ነው ፣ ዮሃንስ ወንጌላዊ ቀደም ብሎ ተናግረዋል እንዲህ ይላል ርኢኩ ሰብዓተ መላዕክተ እለ ይቀውሙ ቅድመ እግዚአብሔር ራእ 8:21 ቅዱስ ሩፋኤል የሴቶችን ማህጸን ይፈታ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። መላኩ ሩፋኤል በ 23 ነገደ መላዕክት መናብርት ተብለው የሚጠሩት የተሾመው ብርሃናዊ መላክ ነው ። የነገድ ስማቸውን እንዲህ ነው ፣ አጋእዝት ፣ ሓይላት ፣ ሥልጣናት ፣ ሊቃናትና መናብርት ፣ መኳንንትና አርባብና ፣ ኪሩቤልና ሱራፌል አዕላፍም ፣ ድርገታትም ተብለው ይታወቃሉ ። አለቆቻቸውም ዓስር ናቸው ። እሊኽም ፣ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ፣ ቅዱስ ፋኑኤል ፣ ቅዱስ ራጉኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ፣ ቅዱስ ሱርያል ፣ ቅዱስ ሰዳክያል ፣ ቅዱስ ሰላትያል ፣ ቅዱስ አናንኤል ናቸው ። እሊኽ ነገደ መላዕክትም ለዘለዓለም በሰማያት ሕያዋን ኹነው ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር ወሰናቸው ። ነገር ግን እግዚአብሔር ግን በጠራቸው ግዜ ፈቃዱን ለመፈጸም እሊኽ መላዕክት እስከ ጽርሃ አርያም ይወጣሉ ። በላካችውም ግዜ የፍጥረተ ሁሉ ወሰን እስከኾነችው ጨላማይቱ የባርባሮስ ሥፍራ ድረስ ይወርዳሉ ። ተመልሰውምTelegram"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜንለምት @fentanesh21_23 🗯ፈንታነሽ / የእመ ብርሃን ልጅ🤗
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ
22 сент., 12:47
переслано из @orthodoxtewahdoc


