gram news
Аватар канала ሳይኮሎጂ | Psychology

ሳይኮሎጂ | Psychology

@psychologycentral

በየቀኑ ስለ Psychology የሚለቀቅበት ቻናል ነው! For any question : @BirukXL

ПроектыENПсихология

59,801подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    22 сент., 19:18

    📚ጨርቃቸውን ጥለው ያበዱ መጽሐፎች የሚለቀቁበት ቻናል! ከፍቅር መጽሐፎች እስከ አስፈሪ የማፊያ መጽሐፎች ድረስ ሁሉም በሽ በሽ ነው ።📖መፅሀፍቶችን ለማግኘት 👉@AmbaBooks✅ 👉@AmbaBooks✅
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    22 сент., 17:39

    ስለ አንድ ነገር ጥቂት እውቀት ያላቸው ሰዎች እራሳቸውን እንደ ትልቅ አዋቂ አድርገው የማሰብ እና ከመጠን በላይ በራስ የመተማመን አላቸው። በተቃራኒው ግን፣ ስለ ጉዳዩ በጥልቀት የሚያውቁ እና ባለሙያ የሆኑ ሰዎች ነገሩ ሰፊ መሆኑን ስለሚረዱ፣ በራሳቸው ላይ ያላቸው መተማመን ዝቅተኛ ባይሆን እንኳን "ብዙ የምቀረው ነገር አለ" የማለት እድላቸው ሰፊ ነው።@PsychologyCentral✅
    1,97043131053Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    22 сент., 15:30

    Leal Market — ። ለ scammer ቦታ የለንም ​በግሩፑ ላይ በብዛት የሚያቀርቧቸው ልዩ ልዩ ምርቶች (ለምሳሌ፦ channel፣ Group፣ Social media account እዚ group ላይ መገበያየት ሚችሉበት group ማንኛውንም ነገር መሸጥም ሆነ መግዛት ተችላላቹ group ይቀላቀሉ ✅https://t.me/lealfrvmarket ቻናላችን ✅ https://t.me/lealfrvmarketOwner - @Lealfrv ማንኛውንም channel ውይም group መሸጥም መገዛትም ከፈለጋችሁ ያናግሩን
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    21 сент., 04:15

    "የሕይወትህ ደስታ የተመሠረተው በአስተሳሰብህ ጥራት ላይ ነው።"@PsychologyCentral✅
    5,4701143024152Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    20 сент., 04:43

    "መልካም ቃላት አጭር እና ለመናገር ቀላል ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የእነሱ ማሚቶዎች በእውነት ማለቂያ የለሽ ናቸው።"— Mother Teresa —@PsychologyCentral✅
    6,680998741Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    19 сент., 04:42

    ወጣትነት ማለት...."ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም!ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም!ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም!ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም!ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም!ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ
    7,870126902113128Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    18 сент., 18:04изменён

    "ሰው ትልቁን ትምህርት የሚያስተምር... ከተማረው ሳይሆን ከኖረው ካስተማረህ ነው!@PsychologyCentral✅
    6,590912818116Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    18 сент., 03:41

    ጭንቅላት እንደሆድ አይደለም ሲጎድል አያስታውቅም!- Arabic Proverbs@PsychologyCentral✅
    7,66016042191584Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    17 сент., 17:09

    ልብ ወለድ ማንበብ ርህራሄን ይጨምራል. ይህም የሚሆነው በምናነበው ልብ ወለድ ውስጥ ያሉ ታሪኮች አእምሮአችንን የሌሎችን ስሜቶች እንዲረዳ ስለሚያስተምረው ነውምንጭ : ሳይኮሎጂ@PsychologyCentral✅
    8,6801124910662Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    17 сент., 04:13

    📔 The Magic of Thinking Bigትልቅ ሕልም ለማሳካት ትልቅ ዕድል ብቻ አያስፈልግም… ትልቅ ማሰብ ያስፈልጋል። ይህ መጽሐፍ ስለ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ራስህን በምን ያህል መጠን እንደምታይ ያሳየናል።@PsychologyCentral ✅
    9,170файл5652221Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    16 сент., 16:45

    📔 The Magic of Thinking Big | በትልቁ ማሰብአንድ ቀን ሁለት ወጣቶች አንድ አይነት እድል አገኙ ሁለቱም ተመሳሳይ ቦታ ነበሩ፣ ተመሳሳይ ጊዜ ነበራቸው፣ ሁለቱም ህልም ነበራቸው።የመጀመሪያው ግን እድሉን አይቶ፦ “እኔ እችላለሁ?” ብሎ ጠየቀ ሁለተኛው ደግሞ፦ “እንዴት አድርጌ እችላለሁ?” ብሎ ጠየቀ።ከዚያ በኋላ ሁለቱ በአንድ መንገድ አልተጓዙም ምክንያቱም የሚለያያቸው እድሉ አልነበረም፤ ስለ ራሳቸው የነበራቸው እምነት ነበር።ይህ በትክክል የDavid J. Schwartz The Magic of Thinking Big የሚያነሳው ትልቁ ጥያቄ ነው፦“ሕይወትህ የሚገደበው በእውነተኛ አቅምህ ነው? ወይስ በራስህ ላይ ባስቀመጥከው ገደብ?”መጽሐፉ “ትልቅ አስብ” ሲል በህልም ውስጥ ብቻ እንድትኖር አይነግርህም። የሚነግርህ ነገር የምታስበው መጠን በውሳኔህ፣ በተግባርህ እና በራስህ ላይ በምትገነባው እምነት ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ነው።ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ይገድባሉ። “እኔ እንደዚያ ሰው ልሆን አልችልም።” “ይህ ለእኔ አይደለም።” “እኔ የምችለው ይህን ያህል ብቻ ነው።”
    9,640433612433Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    15 сент., 15:48изменён

    Jason Padgett ይባላል ፣ መጠጣት እና ከሴቶች ጋር መጨፈር ይወዳል። በተለይ ትምህርት የሚባል ነገር ያቅለሸልሸዋል ። ታዲያ አንድ ቀን እንደዚሁ ለመጠጣት አንድ ባር ውስጥ ከገባ በኋላ ከሰዎች ጋር ይጣላል። ታዲያ በዚያ መሃል ነበር የተበሳጩት ሰዎች ከባሩ አውጥተው ክፉኛ የደበደቡት ፣ በተለይ ጭንቅላቱን በጣም መተውት ነበር።በነጋታው ሲነሳ የሚያውቀው ዓለም ተቀይሮ አገኘው። ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ ነገር ሲመለከት በጂኦሜትሪ ቅርጾች (Fractals) እና በሂሳብ ቀመሮች የተሰሩ ይመስሉታል ፣ የውሃ ጠብታ ሲፈስ፣ የብርሃን ነጸብራቅ ሲያርፍ... ሁሉም ለአይኑ Calculus ስሌት ሆነው መታየት ጀመሩ።ጀለስ ተደብድቦ ሲነሳ የMaths ሊቅ ሆኖ ራሱን አገኘው። ታዲያ ሳይንቲስቶች Jason ላይ "Acquired Savant Syndrome" የተባለ በጣም ብርቅዬ የአንጎል ሁኔታ እንዳጋጠመው ተናግረዋል። ይህ ሁኔታ በአንጎል ላይ በሚደርስ ጉዳት ሳቢያ ቀደም ሲል ተደብቀው የነበሩ የሂሳብ ወይም የኪነጥበብ ክህሎቶች በድንገት ሲቀሰቀሱ የሚከሰት ህመም ነው። ሊቅ የመሆን ህመም 🙌ከዚህ ህመም ይሰውረን 😁 ወይስ ..... ?@PsychologyCentral ✅
    8,5601594919876Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    15 сент., 03:55

    Perfection / ፍጹምነትፍጹምነት ላይ ሰው መድረስ ባይችልም ወደ ፍጹምነት ማደግ ግን ይችላል።ብዙ ጊዜ ፍጹም ለመሆን ስንሞክር ራሳችንን perfect አድርገን ለሰዎች ለማሳየት ስንጥር ጊዜ እናባክናለን ራሳችንንም እናስጨንቃለን"ፍጹም! ፣ የማይሳሳት ሰው በዚህ ምድር ላይ የለም።"Perfect ለመሆን የምናደርገውን ጥረት ትተን እለት እለት ስህተታችንን እያረምን ራችንን ማሳደግ ላይ ብናተኩር የተሻለ ነው።@PsychologyCentral✅
    9,3301261715943Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    14 сент., 17:21

    💖 ከ5 አመታት በፊት ክፍል ውስጥ ጓደኞቼ ተሰብስበው ስለ አንድ መፅሐፍ እየተወያዩ ነበር! ምን መፅሐፍ እንደነበር ትዝ አይለኝም ፣ ነገር ግን አንድ ትዝ የሚለኝ ነገር ቢኖር እንዴት እንደገረጣሁ ነበር!ጠጋ ብዬ ከአንድ ወንበር ተቀመጥኩና ምን እያወሩ እንደሆነ ለመረዳት ብሞክር ምንም ሊገባኝ አልቻለም! አንዱን ጓደኛዬን ጠጋ ብዬ ስለምን መፅሐፍ እያወሩ እንደሆነ ብጠይቀውም ክርክሩ ውስጥ በጣም ተመስጦ ስለነበር ዞር ብሎ ሊያየኝ አልቻለም።ታዲያ ዝም ብዬ ከምቀመጥ በማለት ዝም ብዬ "እሱ መፅሐፍ እኮ ብዙ ሰዎች ይጠሉታል" አልኩኝ። ትልቅ ስህተት!በኔ ቤት አሪፍ መናገሬ ነበር። ግን ዳኒ የተባለው ያ ቅልብልብ ልጅ "ቆይ መፅሐፉን አንብበከዋል?" አለኝ። እኔኮ ጥያቄውን ስጠይቅ መፅሐፉ እንዴት አሪፍ እንደሆነ ይነግሩኛል ብዬ ነበር። ዳኒ ግን .... ድሮም ሲፈጥረው ምላሱን አስቀድሞ የፈጠረው ..... አሁን በማይሆን ሰአት እንደዚህ አይነት ጥያቄ ይጠይቀኝ!እሱ ብቻ ጠይቆ ነገሩ ያለፈ ቢሆን አሪፍ ነበር ፣ ግን ሙሉው የግሩፑ ትኩረት እኔጋ ሆነና ፣ ሁሉም መፅሐፉን እንዳነበብኩት ለማወቅ ዞር ብለው መመልከት ጀመሩ።በቃ እንዳልጠጣ በማለት "አልጨረስኩትም ፣ አሁን እያነበብኩት ነው" አልኳቸው።አቤት ቅሌት ፣ ይሄ ዳኒ የሚባለው ልጅ ምናለ መሬት ተከፍታ ብትውጠው። መልሶ "ስንተኛው ምእራፍ ላይ ነህ" ብሎ አልጠየቀኝም! ድሮስ ምን ጠብቄ፣ ዳኒ እያለ ማውራት አልነበረብኝም! ማስተዋል ነበረብኝ! እሱ ልጅ ግን ሲያድግ ጠበቃ የሚያዋጣው ይመስለኛል!ብ
    9,4605232221Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    14 сент., 14:09

    🇪🇹 ከባርነት እስከ ሥልጣን… እንዴት?ከሳይኮሎጅ ወጣ እንበልና ታሪክን እንይ እስኪ አንድ ኢትዮጵያዊ በባርነት ተወስዶ በሕንድ እንዴት ኃያል መሪ ሆነ? ማሊክ አምባር ማን ነበር? እንዴትስ ከቀንበር ወደ ወንበር ደረሰ?👉 ይህን አስገራሚ ታሪክ ሙሉውን ያንብቡ!@PsychologyCentral✅
    8,590файл3633322Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    14 сент., 08:49

    ከባርነት እስከ ሕንድ ኃያል መሪ… ማሊክ አምባር ! አንድ ኢትዮጵያዊ በባርነት ከአገሩ ተወስዶ በሕንድ የፖለቲካና የጦር ታሪክ ውስጥ እንዴት ኃያል መሪ ሊሆን ቻለ? ማሊክ አምባር በሐረርጌ የተወለደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ በወጣትነቱ በባርነት ተወስዶ ከአፍሪካ እስከ ባግዳድ፣ ከዚያም እስከ ሕንድ ደረሰ። ነገር ግን የተጀመረው በባርነት የነበረው ሕይወት በዚያ አላበቃም። በጦር ሜዳ ብቃቱን አሳይቶ፣ ወታደሮችን
    8,600160136542Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    14 сент., 05:05

    ከባርነት እስከ ሕንድ ኃያል መሪ… ማሊክ አምባር !አንድ ኢትዮጵያዊ በባርነት ከአገሩ ተወስዶ በሕንድ የፖለቲካና የጦር ታሪክ ውስጥ እንዴት ኃያል መሪ ሊሆን ቻለ?ማሊክ አምባር በሐረርጌ የተወለደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ በወጣትነቱ በባርነት ተወስዶ ከአፍሪካ እስከ ባግዳድ፣ ከዚያም እስከ ሕንድ ደረሰ። ነገር ግን የተጀመረው በባርነት የነበረው ሕይወት በዚያ አላበቃም።በጦር ሜዳ ብቃቱን አሳይቶ፣ ወታደሮችን አሰባስቦ፣ በመጨረሻም ኃያል የፖለቲካ መሪ ሆነ። ከሙግሃል መንግሥት ጋር ተዋግቶ ድል አድርጓል፤ በሕንድም የማይረሳ አሻራ ጥሏል።ሙሉ ታሪኩን ይጠብቁ@PsychologyCentral✅
    9,64062116542Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    13 сент., 17:46

    💬 የመወያያ እርስሰው ለምን የሚጎዳውን ነገር ደጋግሞ ያደርጋል?
    9,13080149443Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    13 сент., 06:00изменён

    ዲሲፕሊን ራስህን መቅጣት አይደለም፤ ራስህን ከራስህ ድክመት ማዳን ነው።የምትፈልገውን ነገር ሁልጊዜ ማድረግ ነፃነት አይደለም። አንዳንዴ ነፃነት ማለት የምትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ የሚጠቅመውን መምረጥ ነው።✅ ትኩረትህን የሚሰርቁትን ነገሮች ተው፤ ራስህን ፈልግ።✅ደስታን ፈልግ፤ ግን ለጊዜያዊ ደስታ የወደፊትህን አትሽጥ።✅ አእምሮህ አካልህን ይመራው፤ ፍላጎትህ አእምሮህን እንዲገዛ አትፍቀድ።✅ ስጋዊ ፍላጎትን መቆጣጠር ማለት ራስህን መከልከል ሳይሆን፣ ራስህ የፍላጎትህ ባሪያ እንዳትሆን ማድረግ ነው።ምክንያቱም ራስህን መግዛት ከቻልክ፣ ሌላ ሰው ሊገዛህ የሚችለው ቦታ ይቀንሳል።ራስን ከመግዛት የበለጠ የሚያስደስት ነፃነት የለም። ራስን ከመግዛት የበለጠ የሚያሳምም ባርነትም የለም።ዲሲፕሊን ማለት ዛሬ ራስህን በትንሹ መገደብ ነው፤ ነገ ግን በራስህ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖርህ ማድረግ ነው።📕 Discipline Is Destiny ✍️ Ryan Holiday
    11,200109238622Открыть в Telegram
  • ሳይኮሎጂ | Psychology

    12 сент., 15:35

    📔 ወንጀልና ቅጣትአንዳንድ ቅጣቶች ከፍርድ ቤት አይመጡም… ከህሊና ይጀምራሉ ይህ መጽሐፍ ወንጀልን ብቻ ሳይሆን የሰውን አእምሮ፣ ህሊና እና ውስጣዊ ትግል ያሳየናል።@PsychologyCentral ✅
    10,500файл3374311Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота