gram news
Аватар канала ሰሌዳ | Seleda

ሰሌዳ | Seleda

@seledadotio

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Seledanewsbot

ПроектыENНовости

53,686подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ሰሌዳ | Seleda

    14 нояб., 05:44

    የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብር ካባና የምስጋና ሽልማት አበረከተየትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብር ካባና የምስጋና ሽልማት አበርክቷል።ሽልማቱ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ሕዝባዊ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው የተበረከተላቸው።የክብር ካባውንና የምስጋና ሽልማቱን ያበረከቱት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) ናቸው።በዚህ የእውቅና ሥነ ስርዓት ወቅት የሕዝባዊ ውይይቱን አስፈላጊነትና የማኅበረሰቡን ድምፅ በቀጥታ የማዳመጥ ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።@Seledadotio @Seledadotio
    4,16064225433Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    14 нояб., 04:01

    በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት በሽታ ለስትሮክ ህመም የመጋለጥ ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ሚጨምር ተገለፀበእርግዝና ወቅት የሚያጋጥም የደም ግፊት እና ከእርግዝና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ተጓዳኝ የጤና እክሎች ነፍሰ ጡሮችን ለስትሮክ በሽታ እንደሚያጋልጣቸው በአግዘን ኒውሮሎጂ ሴንተር ጠቅላላ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ኤደን እንየው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።በእርግዝና ጊዜም ሆነ ከእርግዝና ውጪ የሚከሰት የደም ግፊት በሽታን መቆጣጠር ካልተቻለ ለስትሮክ የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው ሲሉ አሳስበዋል።እንደ ህክምና ባለሙያዋ ገለጻ ከእርግዝና ጋር ተያይዞ በሰውነት ውስጥ የሚፈጠር የደም መወፈር ከደም ግፊት ጋር ተዳምሮ ነፍሰ ጡር እናቶችን ለስትሮክ ህመም ይዳርጋሉ።በመሆኑም ነፍሰ ጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሚከሰትን የደም ግፊት እና የስኳር መጠን ችላ ሳይሉ በየጊዜው ተገቢውን የሕክምና ክትትል ማድረግ እና የደም ግፊታቸውን መቆጣጠር እንደሚገባቸው ዶክተር ኤደን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ስትሮክ በአንጎል ውስጥ የደም ዝውውር ሲቋረጥ ወይም የደም ቧንቧ ሲፈነዳ የሚከሰት አደገኛ ሕመም ሲሆን፣ ድንገተኛ የፊት መጣመም፣ የንግግር መዛባት እና በአንድ ጎን የእጅና እግር መስነፍ ዋና ዋና የበሽታው ምልክቶች መሆናቸውን ዶክተር ኤደን ለጣቢያችን ጨምረው ገልጸዋል።@Seledadotio @Seledadotio
    4,9601411Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 19:18

    ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ 520 ኢትዮጵያዉን ሞት ተፈርዶባቸዋልየሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪነት የወነጀሏቸዉ 520 ያክል ኢትዮጵያዉያን በሞት እንዲቀጡ መወሰናቸዉን አንድ የትግራይ ክልል ባለሥልጣን አስታወቁ።የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሓይሽ ሰባጋዲስ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የሞት ቅጣታቸዉን በመጠባበቅ ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያዉያን አብዛኞቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች ናቸዉ። ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ካለፈዉ ሰኔ ጀምሮ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል 34 ኢትዮጵያዉያን በስቅላት ተቀጥተዋል።የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በሥቅላት ከተቀጡት አምስቱ ቅጣቱ የፀናባቸዉ ባለፈዉ ሳምንት፣ ሁለቱ ደግሞ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ነዉ።በሥቅላት የተቀጡና የተፈረደባቸዉ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን «በአደንዛዥ ዕፅ ደላሎች የተታለሉ፣ ሌሎቹ በዝዉዉሩ የተሳትፉ የተቀሩት ደግሞ አደንዛዥ ከሚያዘዋዉሩ ሰዎች ጋር የተገኙ ናቸዉ።» ይሁንና ብዙዎቹ የተፈረደባቸዉ ጠበቃና አስተርጓሚ በሌለበት በማያዉቁት ቋንቋ ባስቻሉ ፍርድ ቤቶች ነዉ። የሞት ቅጣቱ እስካሁን ያልተፈፀመባቸዉ ሰዎች ምሕረት እንደረግላቸዉ የኢትዮጵያ መንግሥት መጠየቅ እንደሚገባዉ አቶ ሓይሽ አሳዉቀዋል።እንደ DW ዘገባ ትግራይ ዉስጥ ከ2013 ጀምሮ በሚደረገዉ ጦርነት፣ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የክልሉ ወጣቶች ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ ወደተለያዩ ሐገራት ተሰደዋል ።@Seledadotio @Seledadotio
    5,9804318222Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 19:10изменён

    «በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ባድመ አካባቢ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ልውውጥ መካሄዱና ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ ተገለጸ»​ዛሬ ሕዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ከአዲ ቦክራይ እስከ ቢያራ አዲ አስመሩ ባሉት የድንበር አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የኤርትራ ሠራዊት በከባድ መሣሪያዎች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተመላክቷል።​በኢትዮጵያ በኩል የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እና በኤርትራ በኩል የሚተኮሱ ከባድ መሣሪያዎች ወደ ሰፊ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩ ተገልጿል።​የአካባቢው ነዋሪዎች ሌሊቶችን በከፍተኛ ፍንዳታዎችና ድብደባዎች ማሳለፋቸውን እና ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ሱቆችንና ገበያዎችን ዘግተው አካባቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተነግሯል።​@Seledadotio @Seledadotio
    5,580154421Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 19:06

    የስልሳ አምስት ዓመት አዛውንት የአስራ አንድ አመት ተዳጊ ላይ በፈፀሙት አስገድዶ መድፈር ወንጀል በእስራት ተቀጡ።በጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ በቦሣ ኪቶ ቀበሌ የስልሳ አምስት አመት አዛውንት የአስራ አንድ አመት ተዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በመፈፀማቸው በእስራት መቀጣታቸውን የጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ ፅፈት ቤት የሴቶች ና ሕፃናት ወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል፡፡ወንጀል ምርመራ ክፍል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ማርታ ዋቅጅራ ለብስራ ሬድዮ እንደተናግሩት ተከሣሽ ወንድሙ ብዛየሑ የተባሉ የስልሳ አምስት አመት አዛውንት የአስራ አንድ አመትዋን ልጅ አታለው በፈፀሙት የግብረ ስጋ ድፍረት በእስራት ተቀጥዋል።የስልሳ አምስት አመቱ አዛውንት የአስራ አንድ አመትዋን ልጅ ወላጅ ቤተሠቦችዋ ከቤት አለመኖራቸውን በማረጋገጥ የሸንኮራ አገዳና ብስኩት በመግዛት ዘመድ መስሎ በማታለል የግብረ ስጋ ድፍረቱን መፈፀሙን ተናግረዋል።በአስራ አንድ አመትዋ ልጅ ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ቤተሠቦችዎ ከሔዱበት ሲመለሱ አይተው ለፖሊስ አመልክተው ወዲያው አዛውንቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልፅዋል።ፖሊስም ተጐጂዋን ልጅ በሕክምና በማስመርመር የምርመራ መዝገቡን በማስረጃ በማረጋገጥ ለአቃቢ ሕግ መላኩን ገልፀዋል።አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን መዝገብ ተመልክቶ በሕፃናት ላይ በሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ የመሠረተ መሆኑን ገልፀዋል።በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር3ቀን 2019ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሽ የስልሳ አምስት ዓመት አዛውን በአስራ ሁለት አመት እስራት እንዲቀጡ የወሠነባቸው መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ማርታ ዋቅጅራ ጨምረው ገልፀዋል።@Seledadotio @Seledadotio
    5,5001914821Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 18:37изменён

    በባንክ ጥበቃ በጥይታ የተመታው ወጣት ሕይወት ማለፉ ተሰማ።በዛሬው ዕለት ቀን በቦሌ አካባቢ (በካርን ሳፊል እና አስራት ህንፃዎች አጠገብ) በሚገኝ የባንክ ተቋም ፊት ለፊት በመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ዙሪያ በተፈጠረ አሳዛኝ የተኩስ አደጋ የአንድ ወጣት ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ።እንደ ታዲያስ አዲስ ዘገባ፣ ክስተቱ መነሻውን ያደረገው አረንጓዴ ፒጆ ተሽከርካሪ ይዞ በመጣ ወጣት እና በባንክ ተቋሙ የጥበቃ ሰራተኛ መካከል በተነሳ ውዝግብ ነው። በወቅቱ «እዚህ ማቆም አትችልም» በሚል ቀላል በሚመስል ንትርክ የተነሳው አለመግባባት ወጣቱ ተሽከርካሪውን አቁሞ ወደ ስራው ጉዳይ ከሄደ በኋላ ሲመለስ ወደ ከፋ ግጭት አድጓል።ወጣቱ ተሽከርካሪውን ለማንሳት ሲመለስ የጥበቃ ሰራተኛው በከፍተኛ ቁጣና ንዴት ውስጥ ሆኖ ተከታታይ ተኩስ እንደከፈተበት የዓይን እማኞች ገልጸዋል።በጥይት ተመቶ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ወጣት ወዲያውኑ ወደ አያት ሆስፒታል ቢወሰድም፣ የደረሰበት የከፋ ጉዳት ህይወቱን ለማትረፍ ባለመቻሉ ሕይወቱ አልፏል።በሌላ በኩል፣ ጥቃቱን የፈጸመው የጥበቃ ሰራተኛ ድርጊቱን ፈጽሞ በድንጋጤና በሁከት ውስጥ ሆኖ ፖሊስን ለመጥራት መሞከሩን እንዲሁም መሳሪያውን ጥሎ ለመሸሽ እንደተንቀሳቀሰ ተገልጿል።ቀላል በሚመስል የመኪና ማቆሚያ አለመግባባት የሰውን ሕይወት የቀጠፈው ይህ አሳዛኝ ድርጊት በአካባቢው ማህበረሰብ እና በዓይን እማኞች ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንና ቁጣን ፈጥሯል።@Seledadotio @Seledadotio
    5,770531321Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 17:57изменён

    በሆሳዕና በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ​ዛሬ ከቀኑ 9:50 ላይ ከሆሳዕና ወደ ማዞሪያ ሲጓዝ የነበረ "ኮድ 3-24200 ደ.ህ" አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በቃጫ ቢራ ወረዳ ሚኖ ቀበሌ "ታችኛው ዋዶሌ" አካባቢ በፍሬን ችግር ተገልብጦ የአስከፊ አደጋ ሰለባ ሆኗል።በአደጋው የሰባት ወንዶች ሕይወት ሲያልፍ፣ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።​ አራት ከባድ እና ሁለት ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በአሁን ሰዓት በሺንሽቾ እና በዱራሜ ሆስፒታሎች የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።​የወረዳው ትራፊክ ፖሊስ አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ቴክኒክን ቅድመ ዝግጅት እንዲያረጋግጡ እና አደጋ በሚበዛበት በዚህ ስፍራ ልዩ ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያሽከረክሩ አሳስቧል።@Seledadotio @Seledadotio
    6,460388511Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    13 нояб., 14:21изменён

    በመርካቶ አካባቢ ከሰው ልጅ የመኖር ደረጃ በታች ያሉ ቤቶች በማሻሻል ዘመናዊ መንደሮች እንደሚገነቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገለጹ​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ መርካቶ ቅጠል ተራ አካባቢ የተገነቡ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፤ አቅም በፈቀደ መጠን በአካባቢው የሚገኙ እና ለኑሮ የማይመጥኑ ቤቶችን በማፍረስና በማሻሻል የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።​በመርካቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገነባውን ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ለአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀደውን 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ እውን ለማድረግ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረት፣ የሞርጌጅ ፋይናንስ አሠራርን ማመቻቸት እና በቅንጅት መሥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ መቆየቱን ገልጸዋል።​የልማት እና የብልጽግና ዋነኛ መለኪያ የዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሕይወት መቀየር መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን የተገነቡት ቤቶችም ቀደም ሲል ከነበሩት በተለየ መልኩ ጥራታቸውን የጠበቁና ለረጅም ዓመታት የሚያገለግሉ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።@Seledadotio @Seledadotio
    7,75024209441Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 18:52

    በሕይወት እያለ የራሱን የሐዘን ባነር ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦካ ቀበሌ በሕይወት እያለ የራሱን ፎቶ በመጠቀም "ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" የሚል የሐሰት የሐዘን መግለጫ ባነር ያዘጋጀ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።​የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሽካ እንደገለጹት፡ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥንና አለመረጋጋትን የፈጠረ አሳዛኝ የስነ-ምግባር ግድፈት ነው። ህብረተሰቡ የሐሰት ወሬዎችን ሳያጣራ እንዳያምንና በጥንቃቄ እንዲመለከት አሳስበዋል።በማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ በሚቀልዱ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይቀጥላል። ​በግለሰቡ ላይ የሚደረገው የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ህጋዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ክትትሉ እንደሚቀጥል ጠቅሶ መረጃውን የሰሜን ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አጋርቷል።@Seledadotio @Seledadotio
    2,52038162211Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 18:04изменён

    የጓደኛውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥር በመውሰድ 20ሺህ ብር ያወጣው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።ግለሰቡ ወንጀሉን የፈጸመው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።ጉታ ገመዳ የተባለው ግለሰብ ከግል ተበዳይ ጋር በጓደኝነት አንድ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ የግል ተበዳይ ቤት ውስጥ ያስቀመጠውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥሩን በመውሰድ ከግል ተበዳይ የሂሳብ ደብተር ፊርማ ጋር በማመሳሰል በክ/ከተማው ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ 20ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡ግለሰቡ ገንዘቡን ካወጣ በኋላ የግል ተበዳይ በደረሰው መልዕክት አማካኝነት ባንኩን በመሄድ ይጠይቃል።ገንዘቡ ወጪ መደረጉን ምላሽ የተሰጠው የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለአቅራቢያው ሙገር ፖሊስ መምሪያ አመልክቷል፡፡አቤቱታው የደረሰው ፖሊስም ምርመራውን በማጣራትና ባንኩ ውስጥ የነበረን ካሜራ በመጠቀም ወንጀል ፈጻሚውን በመለየት ከነ ኤግዚቢቱ ማስመለሱን የመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኢ/ር ዮሴፍ ገረመው ተናግረዋል።ወንጀል ፈጻሚው ክስ እንደተመሰረተበትም ኃላፊው ገልፀዋል።ግለሰቦች የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥራቸውን ከራሳቸው ውጪ ለየትኛውም አካል አሳልፈው መስጠት ወይም በግዴለሽነት ለወንጀል ተጋላጭ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እንደሌለባቸው የገለጹት ኃላፊው ደንበኞች ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄዱም የባንክ ባለሙያዎች የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ትክክለኛ ማንነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡@Seledad
    3,8501411521Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 17:44изменён

    የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የቅበላ መስፈርት በተላለፉ ተቋማት ላይ ጥብቅ እገዳና የእርምጃ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ​የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የቅበላ መስፈርት ሳያሟሉ ተማሪዎችን በተቀበሉ ከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።​በመመሪያ ቁጥር 987/2016 መሠረት መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ያደራጁ ተቋማት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበሉ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት እገዳ ይጣልባቸዋል።በተጨማሪም መስፈርቱን ያላሟሉ ተማሪዎች ወዲያውኑ ከትምህርት ገበታቸው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ተቋማቱ የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ አለባቸው።​ሕግ ተላላፊ ሆነው የተገኙ አካላት በ20 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ አድርገው ሪፖርት እንዲያቀርቡ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህንን ለማያከብሩት እስከ ሙሉ በሙሉ መዘጋት የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል።እንዲሁም ማንኛውም የትምህርት ተቋም የፈቃድና የእድሳት ደብዳቤውን ለህዝብ በሚታይ ቦታ የመለጠፍ ግዴታ ተጥሎበታል።@Seledadotio @Seledadotio
    3,870621Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 16:43изменён

    የ2019 አ.ም ኢሬቻ በዓል መስከረም 23 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፣ መስከረም 24 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ እንደሚከበር ተገለፀየኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ በ2019 የኢሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ እንደገለፁት በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መስከረም 23 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፣ መስከረም 24 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ ይከበራል፡፡በዓሉን ከዚህ ቀደሙ በላቀ መልኩ በባህላዊ አልባሳት ደምቆ እና ተውቦ ማክበር ይገባልም ብለዋል።በአሉን ለማክበር የሚመጡ ማህበረሰቡ አባላት እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በአሉን በአንድነት በፍቅር በመከባበር እና በአንድነት እንዲያከብሩም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡በተጨማሪም የዘንድሮው የኢሬቻ በአል ከበፊቶቹ አመታት አከባበር በላቀ እና በደመቀ መልኩ ስለሚከበር ያለ ምንም የሀይማኖት ልዩነት የሁሉም እምነት ተከታይ በአንድነት እንዲያከብረው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡@Seledadotio @Seledadotio
    4,76029203211Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 13:22

    የጨጓራ ህመምን የሚያባብሱ 6 ዘመን አመጣሽ ምግቦች!ዛሬ በዘመናዊ አኗኗራችን ምክንያት በስፋት የምንመገባቸውና የጨጓራ ህመም እና አሲድ መዛባትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያባብሱ 6 ዋና ዋና ምግቦችና መጠጦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦የታሸጉ እና የተቀናበሩ ምግቦች (ቺፕስ እና ብስኩቶች): በውስጣቸው ከፍተኛ የኬሚካል መከላከያ እና ስብ ስላላቸው የጨጓራን ሽፋን በማስቆጣት የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዘገያሉ።የታሸጉ ለስላሳ እና የኃይል ሰጪ መጠጦች: በውስጣቸው ያለው ጋዝ እና አሲድ የጨጓራን በር እንዲላላ በማድረግ አሲድ ወደ ላይ እንዲመለስ (Acid Reflux) ያደርጋሉ።የተጠበሱ ፈጣን ምግቦች (በርገር እና ፍሬንች ፍራይስ): ስብ የበዛባቸው በመሆኑ በጨጓራ ውስጥ ለመፈጨት ረጅም ጊዜ ስለሚወስዱ ጨጓራ ከመጠን በላይ አሲድ እንዲያመነጭ ያደርጋሉ።ቅመም የበዛባቸው ዘመናዊ ምግቦች (እንደ ኮሪያ ኑድልስ): በቃሪያ ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የጨጓራን የውስጥ ሽፋን በቀጥታ በመኮርኮር የማቃጠል ስሜት እና ህመም ያስከትላል።ሰው ሰራሽ ጣፋጮች እና ኬኮች: በጨጓራ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን በማዛባት ለጋዝ፣ ለሆድ መንፋት እና ለጨጓራ መቆጣት ይዳርጋሉ።በባዶ ሆድ የሚወሰዱ የካፌን መጠጦች (ቡና): የጨጓራ አሲድ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጨምሩ የጨጓራ ማቃጠል እና ቁስለት የመከሰት እድልን ያፋጥናሉ።@Seledadotio @Seledadotio
    6,3602863111Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 11:58изменён

    በኢትዮጵያ ያለው የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት እና የድሮን ጥቃቶች አስቦኛል - የተባበሩት መንግስታትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዲሱን የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት መመሥረት፣ የቀጠለውን የጸጥታ ችግር እና የድሮን ጥቃት ዘገባዎችን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ።ትላንት በተካሄደው የተመድ ዕለታዊ የዜና መግለጫ ላይ የተቋሙ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ እንደተናገሩት፣ ተመድ በኢትዮጵያ ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ወቅት በተከሰቱ አዳዲስ ኩነቶች «ጥልቅ ስጋት» እንደገባው አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ «ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን» ብለዋል።አክለውም «ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም፤ ወይም መሠረታዊ ቅሬታዎችን አይመልስም» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ወገኖች ለውይይትና ለንግግር ዳግም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።@Seledadotio @Seledadotio
    6,68027108511Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 10:48изменён

    ናይጄሪያ በሮቦት የተደገፈ የመጀመሪያውን ቀዶ ሕክምና አከናወነችየናይጄሪያ የሕክምና ባለሙያዎች በካንሰር የተጠቃን ኩላሊት በሩቅ ሆኖ በሮቦት እርዳታ በስኬት በማስወጣት አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል። ይህ እመርታ በሀገሪቱ የሕክምና እድገት ላይ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል።የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገለጹት፤ የቦታ ርቀት ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና የማግኘት መብታቸውን ሊከለክላቸው አይገባም። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ህሙማን ጥራት ያለው ሕክምና ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ጉዞ በእጅጉ ይቀንሰዋል።ይህን ስኬት ለማስቀጠልም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 150 የሕክምና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥን አዲስ የሮቦቲክ አካዳሚ እንደሚቋቋም ተነግሯል።@Seledadotio @Seledadotio
    6,7802611111Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 09:00

    በቻይና ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስወገድ እንዲቧጨሩ የሚያደርግ ልዩ የቧጨራ ሳሎን ተከፈተበቻይና የ32 ዓመቱ ዣንግ ሺያኦቻኦ ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስታገስ በሰራተኞች በቀስታ የሚቧጨሩበትን ልዩ የአገልግሎት ሳሎን ከፍቶ በወር ወደ 100,000 ዩዋን ያህል ገቢ እያገኘ መሆኑ ተዘግቧል።ዣንግ ይህን ያልተለመደ የንግድ ሀሳብ ያገኘው በኢንተርኔት ላይ ባየው አጭር ቪዲዮ መሆኑን ገልጿል። በቪዲዮው ላይ አንዲት ሚስት የባለቤቷን ጀርባ በቀስታ ስትቧጭ ተመልክቶ አስተየየት ሰጪ የነበሩ ሰዎችም “እንዲህ ያለ አገልግሎት ቢኖር ገንዘብ እንከፍላለን” የሚሉ መልዕክቶቹን በመመልከቱ ወደዚህ ስራ መግባቱ ተናግሯል።የመጀመሪያው የቧጨራ ሳሎን ከተከፈተ ብዙም ሳይቆይ ሁለተኛ ሳሎን መክፈት ችሏል ሁለቱም ሳሎኖች በአጠቃላይ በወር ወደ 100,000 ዩዋን የሚጠጋ ገቢ እንደሚያገኝ ተነግሯል።ደንበኞች በጀርባቸው ተኝተው ሰራተኞች በልዩ የፕላስቲክ ጥፍሮች በመጠቀም ሰውነታቸውን በቀስታ ይቧጫሉ። ዣንግ ይህን ሥራ ለመጀመር ልዩ የቧጨራ ቴክኒኮችን ራሱ መመርመርና መፍጠር እንደነበረበት ገልጿል።አንድ ሰዓት የቧጨራ አገልግሎት 300 ዩዋን ያስከፍላል።የንግዱ ዋና ዓላማም ሰዎች የከተማ ሕይወት የሚያመጣውን ጭንቀት እንዲያስታግሱና የእንቅልፍ ጥራታቸውን ለማሻሻል ዘና የሚያደርግ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።ዣንግ የከተማ ነዋሪዎች የጭንቀት ደረጃ ከፍ ያለ በመሆኑ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ፍላጎት እንዳለ በመግለጽ አንዳንድ ደንበኞችም አገልግሎቱ ከማሳጅ ይልቅ የበለጠ ዘና እንደሚያደርጋቸው እንደነገሩት ተናግሯል።
    7,02031132221Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 08:38изменён

    በራያ አላማጣ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ​ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም በራያ አላማጣ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተደጋጋሚ ከባድ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ።​የጥቃቱ ሰዓት እና ዒላማዎች፦ ጥቃቱ ከጠዋቱ 4:10 ሰዓት አካባቢ የጀመረ ሲሆን፤ በአላማጣ ከተማ ዋጃ መውጫ ሓውጃኖ ትምህርት ቤት፣ ፋጫ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ንጉሥ ቸኮለ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አላማጣ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል።​የደረሰ ጉዳት፦ በሓውጃኖ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት ብቻ 17 የህወሓት ታጣቂዎች መሞታቸውን ምንጮች ማረጋገጣቸው የተነገረ ሲሆን፤ የቆሰሉ ታጣቂዎችም በአምቡላንስ ወደ መሆኒ እየተወሰዱ እንደሚገኙ ተመላክቷል።​@Seledadotio @Seledadotio
    6,4701054221Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 08:34

    ሱቅዎን በደብተር እየመዘገቡ ነው?በወር መጨረሻ ትርፍዎ ስንት እንደሆነ፣ የትኛው ዕቃ እየሸጠ እንደሆነ፣ ምን ያህል ዕቃ እንደጎደለ ለማወቅ ስንት ሰዓት ይፈጃል?መዝገብ በአንድ ጠቅታ ያሳይዎታል።✅ እያንዳንዱ ሽያጭ በማን፣ በስንት ዋጋ እንደተሸጠ ይመዘገባል ✅ የፈረቃ መዝጊያ — መሳቢያው ከሽያጩ ጋር ይታረቃል ✅ የክምችት ቆጠራ — በመዝገቡና በመደርደሪያው መካከል ያለውን ልዩነት ያሳያል ✅ ኢንተርኔት ሳያስፈልግ ሙሉ ቀን ይሰራልለሱቅዎ እንዲዘጋጅ ያነጋግሩን 👉 @mezgeb_supportመተግበሪያውን ያውርዱ 👉 https://bit.ly/4rnVe0K
    Google PlayMezgeb Stock – Shop Manager - Apps on Google Playoffline-first shop manager built for Ethiopian businesses
    6,220321Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 08:15

    በአዲስ ምዕራብ ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመ ብልሽት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠበአዲስ ምዕራብ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።በዚሁ ብልሽት ሳቢያ• በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው• በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው• አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው• ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው• ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው• ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው• ሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው
    6,28012221Открыть в Telegram
  • ሰሌዳ | Seleda

    22 сент., 07:31изменён

    በሰሜን ሸዋ ዞን ባሶና ወራና ወረዳ የሰባት ልጆቹን እናት በመጥረቢያ የገደለው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ​ጥንዶቹ በሰባት ልጆች የተባረከ አርአያነት ያለው የትዳር ሕይወት ሲመሩ ቢቆዩም፣ ከትዳር ውጭ በተወለደ ልጅ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ቅራኔ ውስጥ ገብተው ነበር።ይህ ውዝግብ እየተባባሰ በመሄዱ፣ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባል አቶ አሠበ በላይነሕ ባለቤታቸውን ወ/ሮ ሒሩት ጌታቸውን በዱላ መተው መሬት ላይ ከጣሉ በኋላ በመጥረቢያ ደጋግመው በመምታት ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።​ተከሳሹ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ እጁን ለፖሊስ የሰጠ ሲሆን፣ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለፍትሕ መምሪያ በመላኩ የከባድ ሰው መግደል ክስ ተመስርቶበታል።የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ድርጊቱ ጨካኝና ከባድ ቢሆንም፣ ሁለት የክስ ማቅለያዎችን በመመልከት ተከሳሹን በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።@Seledadotio @Seledadotio
    6,57026115531Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота