gram news
Аватар канала ስለ ቀልባችን

ስለ ቀልባችን

@sle_qelbachn1

«በሰውነት ውስጥ አንዲት ቁራጭ ስጋ አለች፤ እሷ ከተስተካከለች መላው ሰውነት ይስተካከላል፤ እሷ ከተበላሸች መላው ሰውነት ይበላሻል።እሷም ቀልብ (ልብ) ነች።» 📚[ቡኻሪና ሙስሊም]

ПроектыENРелигия

41,800подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ስለ ቀልባችን

    23 сент., 07:45

    የዱሃ ሶላት...ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል።ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360 መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች።የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን! -- t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    7,610337386Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    22 сент., 18:06

    ✔️አንድ ምርጥ ቦታ ልጠቁማችሁ! የኡስታዝ ዐብዱ ረዛቅ አል ባጂ የሆነው ❝ኢኽላስ መርከዝ❞ ለ2 ዓመት የሚቆይ የቁርኣን ሂፍዝና የኪታብ (አቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ) ትምህርቶች ምዝገባ ጀምሯል፤ አጋጣሚውን ተጠቀሙበት! ✅️ በአዳሪ (ለወንዶች ብቻ)፦ ከ10 እስከ 20 ዓመት በተመላላሽ (ለወንድም ለሴትም) ከ5 ዓመት ጀምሮ 🚨ቦታው ውስን ስለሆነ ልጆቻችሁን ቀድማችሁ አስመዝግቡ። የምዝገባ ቀኑም
  • ስለ ቀልባችን

    22 сент., 13:27

    መፍትሄ ከመስጠት በላይ፣ 'አለሁልህ' የሚል የቅርብ ሰው ማግኘት ብቻውን ለሰዎች ትልቅ ትርጉም አለው።
    9,58026718557Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    22 сент., 07:26

    እውነቴን ነው የምላችሁ አላህ የወደደልንን፣ የመረጠልንን እና የጻፈልንን ነገር በሙሉ ልብ መውደድና መቀበል ስንችል፦ • ይህች አላፊ ዱንያ በፈተናዋ አታሸንፈንም፣ • የሕይወት ማዕበል ሁሉ ከመንገዳችን ፈጽሞ አያናውጠንም፣ • የሚገጥመን መከራ ወኔያችንን አይረታውም፣ • የችግርና የፈተና ብዛት አይበታትነንም፣ • የቱንም ያህል የከበደ ሐዘን ቢያንዣብብ በቁማችን ጥሎ አያስቀረንም።ምክንያቱም እያንዳንዱ ፈተና ከጀርባው ታላቅ ጥበብ እንዳለው፣ እያንዳንዱ ህመምም ከአላህ ዘንድ ምንዳ እንደሚያስገኝ ያመነ ቀልብ ፈጽሞ አይሸነፍም። በአላህ ውሳኔ የረካ ልብ በማንኛውም ውጣ ውረድ ውስጥ ሰላምና ስክነትን ያገኛል። t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
    10,8004071711Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    21 сент., 18:43

    ነብዩላህ ዩሱፍን ወደ ዝሙት ጠራቻቸውአቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
    10,700видео1413Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    21 сент., 11:22

    ➔ ዛሬ ላይ እጅግ በርካታ ሴቶች እንደ ቀላል ነገር የሚመለከቱት፣ ነገር ግን በአላህና በመልእክተኛው ዘንድ እጅግ የከበደና አስከፊ ከሆኑ ወንጀሎች ተርታ የተመደበ አንድ አጥፊ ድርጊት አለ፤ እርሱም አንዲት ሴት ሽቶ ተቀብታ አጅነቢይ (ባዕድ) ወንዶች ባሉበት መውጣቷ ነው።ይህንን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦ ❝ማንኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ፤ ሽታዋን ያሸቱ ዘንድ በሰዎች (በአጅነቢይ ወንዶች) አጠገብ ካለፈች፤ እርሷ ዝሙተኛ ናት!❞ [አቡ ዳዉድ፣ ቲርሚዚይ እና ነሳኢይ]የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶ ተቀብታ የወጣችን ሴት «ዝሙተኛ ናት» በማለት የጠሯት ዝም ብለው አይደለም። ሽቶ የአንድን ወንድ የስሜት ህዋሳት የሚቀሰቅስ፣ ልቡን የሚያሸፍት እና አይኑን ወደ እርሷ እንዲያነጣጥር የሚያደርግ ገዳይ መርዝ ነው። እርሷ በወጣችበት መንገድ ሁሉ የወንዶችን ስሜት በማነሳሳት የዓይን ዝሙት፣ የልብ ዝሙትና የሀሳብ ዝሙት እንዲፈጽሙ በር ከፋች ትሆናለች፤ በዚህም ሳቢያ በፈጸሙት ወንጀል ሁሉ ሙሉ ተካፋይ ትሆናለች።አደጋው በዚህ ብቻ አያበቃም! ይልቁንም ወደ አላህ ቤት መስጂድ ለመስገድ ስትሄድ እንኳ ሽቶ ከተቀባች ሶላቷ ተቀባይነት እንደሌለው በሌላ ሐድስ ተነግሯል።ልብ በይ! ወደ አላህ ቤት፣ ለዒባዳ እና ለሶላት ለመሄድ ሽቶ መቀባት እንዲህ የሚያስጠይቅና ሶላትን ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ፤ ለገበያ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለቢሮ፣ ለመንገድ እና ለሰርግ ድግሶች ሽቶ ተቀብቶ በአጅነቢይ ወንዶች ፊት መዘዋወር ቅጣቱ ምን ያህል የከፋ ይሆን?! t.me/Sle_qelbachn1 t.me
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    12,9002816811Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    20 сент., 15:20изменён

    ⚠️ማሳሰቢያ!💙በቻናላችን ላይ የሚታዩት ማስታወቂያዎች በቴሌግራም በራሱ የሚገቡ (Telegram Ads) እንጂ እኛ የለቀቅናቸው አይደሉም። አብዛኛዎቹ አስተማማኝ ስላልሆኑ እንድትጠነቀቁ አደራ እላለሁ።📱ይህን ችግር ለማስቆም የቻናላችንን 'ሌቭል' ከፍ ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣ ፕሪሚየም አካውንት ያላችሁ በተከታዩ ሊንክ 'ቡስት' (Boost) በማድረግ እንድታግዙን እጠይቃለሁ። የሚፈለገው መጠን ለመድረስ ጥቂት ነው የቀረን!🔗ይህን ሊንክ በመጫን Boost ያድርጉን!👇 https://t.me/boost/Sle_qelbachn1https://t.me/boost/Sle_qelbachn1
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    11,40011813Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    20 сент., 14:41

    ሐቂቃ የኢማንን ጥፍጥና ቀምሶ፣ የለሊት ሶላትን ለዛ አጣጥሞ፣ በሰኞና ሀሙስ ፆም ነፍሱ ረክታ የነበረች ቀልብ... ዛሬ ግን ልቡ ደርቆ የለይል ሶላት የከበደውን ሰው ያህል የተቀጣ ማንም የለም!ከመቅረብ በኋላ መራቅ፣ እንዴት ያለ ስውር ስቃይ ነው?! አላህ ሆይ፤ ትልቁ ቅጣት ዱንያን ማጣት ሳይሆን አንተን ማጣት ነውና... የደረቀ ልባችንን በራህመትህ አርጥበው፤ ያጣነውን ጣዕም መልስልን፣ ወደ አንተ መልሰን!
    11,3003411459Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    20 сент., 10:57

    የአጎቱን ልጅ ወደ ዝሙት ጠራት!🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
    11,000видео13443Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    20 сент., 05:48изменён

    👉መስከረም 25 መዝገባ ይዘጋል!!📢አስደሳች ዜና ለጠቅላላው የሙስሊም ማህበረሰብ!📖​ኢኽላስ የቁርኣን እና የተርቢያ ማዕከል የ10 ወር የቆይታ ጊዜ ያለው የበጋ ልዩ ኮርስ ማዘጋጀቱን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!🪶የፕሮግራሙ ልዩነት፦ በዚህ 10 ወር ውስጥ ማንኛውም እውቀት ፈላጊ ጧሊበል ዒልም ሊቀራቸው የሚገቡ መሠረታዊ የሸሪዐ የትምህርት ፈኖችን ልዩ የእውቀት ማዕድ ተዘጋጅቶልዎታል!​ልጆቻችሁን እና እራሳችሁን በቁርኣን፣ በስነ-ምግባር እና በእስልምና እውቀቶች ለማነፅ እና ለማበልፀግ የቀረበ ወርቃማ አጋጣሚ!​ የትምህርቱ ​በወንድም አብዱረዛቅ አል-ባጂ አስተምህሮ የሚሰጥ ይሆናል።​📚 የሚቀሩት ፈኖች ​ ●​ ዓቂዳህ ●​ ፊቅህ አሻፊኢይ ●​ ኡሱሉል ፊቅህ ●​ ቀዋዒዱል ፊቅሂ ● ​አዳብ እና ሱሉክ
    11,100видео7094Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    19 сент., 16:25

    🤍ቀልብ እረፍት የምታገኘው፣ ወጣትነትም ከፈተና የሚጠበቀው በሐላል ጎጆ (በትዳር) ጥላ ስር ነው።በአላህ ፈቃድ በዚሁ «ስለ ቀልባችን» ቻናላችን ላይ፤ ✔️ ወደ ትዳር ለመግባት ላሰቡ፣ ✔️ ትዳር ለዘገየባቸው፣ ✔️ በትዳር ውስጥ ላሉና ቤታቸውን በሰኪና መምራት ለሚፈልጉ ሁሉ...🌸ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት አመራር ድረስ የሚያመላክት አንዲት ድንቅና አጭር ኪታብ በቅርቡ እንጀምራለን፣ ኢንሻ አላህ!🎯የቻናላችን ዋነኛ ዓላማ ቀልብን ማስተካከል እስከሆነ ድረስ፣ ወጣቱን ከዝሙት ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ ማመላከት የትምህርቱ ትልቁ አካል ነው ብለን እናምናለን።በዚህ ሐሳብ ላይ ምን ትላላችሁ? 👍 📱➔ t.me/Sle_qelbachn1
    11,9009093411Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    19 сент., 12:16изменён

    ተጫጭተናል ማለት ተጋብተናል ማለት አይደለም! ~ በነገራችን ላይ...እጮኝነት ማለት ኒካህ አይደለም! እጮኝነት ማለት «ወደፊት ልንጋባ አስበናል» የሚል የተስፋ ቃል ብቻ ነው።ኒካህ እስከሌለ ድረስ እሷ ላንተ አጅነቢይ ናት፤ አንተም ለእሷ ባዕድ ወንድ ነህ። ብዙዎች አያስተውሉትም እንጂ፣ በርካታ ትዳሮች ገና በጠዋቱ የሚፈርሱት፣ የተሳኩ እንዳይሆኑ የሚቀሰፉት ከተጫጩ በኋላ በሚሰሩት ስህተት ምክንያት ነው።ሸይጧን ወደ ዝሙት የሚያስገባው በአንድ ጀምበር አይደለም፤ ደረጃ በደረጃ ነው። ➔ መጀመሪያ «እሱኮ የወደፊት ባልሽ ነው ማውራት ትችላላችሁ» ይላችኋል። ➔ ቀጥሎ ከእኩለ ሌሊት የስልክ ወሬዎች ጋር ድንበር የለሽ የፍቅር ቃላት ይጀመራሉ። ➔ ከዚያም በአይንም፣ በልብም፣ በምላስም ዝሙት ውስጥ ትወድቃላችሁ። ➔ በመጨረሻም ገደቡ ተሰብሮ አካላዊ ዝሙት ላይ ይደረሳል።ታድያ በአላህ ቁጣና በሀራም የተበከለ ግንኙነት በምን ሂሳብ ሰላማዊ ትዳርን ሊወልድ ይችላል?!ፍቅር ልክ እንደ ንፁህ ፍሬ ነው። ሰዓቱን ሳይጠብቁ ጥሬውን በሀራም የለቀሙት እንደሆነ፣ ሰርጉ ቀን ሲደርስ የሚበላ ጣፋጭ ፍሬ አይገኝም። ለትዳር የተጠበቀው ናፍቆት፣ ክብርና ሀያዕ በእጮኝነት ዘመን ይሟጠጣል። ሰርግ ተብሎ ወደ አንድ ቤት ሲገቡ ፍቅሩ አልቋል፤ ወንጀሉ ልብን አድርቆታል፤ በረካውም ርቋል። መጨረሻው ወይ በፀፀት ማልቀስ፣ ወይ በትንሽ ነገር መጣላትና ወደ ፍቺ መሮጥ ይሆናል።እሳትን እቅፍ ውስጥ አስገብቶ «አይፈጅም» አይባልም። ወጣትነት፣ ስሜት እና የሸይጧን ጉትጎታ ተደምረው እንዳያጠፏችሁ ብልሆች ሁኑ! ◇ ከተዋደዳችሁና ቤተሰብ
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    14,8004284422Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    18 сент., 19:42изменён

    ➔ በሃላል መተያየት፣ ➔ ከዚያም እጮኝነት፣ ➔ ከዚያም ኒካህ፣ ➔ ከዚያም ሰርግ።ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፤ የእውነት የሚወድሽ ከሆነ መንገዱ ይሄው ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    13,6005374530Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    18 сент., 16:29

    ልጆቻችሁን በተርቢያ ለማነፅ ከፈለጋችሁ.🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
    14,700видео12494Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    18 сент., 13:55

    ክፍል ❺ 📜የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂ ✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
    14,2001538Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    18 сент., 11:46изменён

    ✔️አንድ ምርጥ ቦታ ልጠቁማችሁ!የኡስታዝ ዐብዱ ረዛቅ አል ባጂ የሆነው ❝ኢኽላስ መርከዝ❞ ለ2 ዓመት የሚቆይ የቁርኣን ሂፍዝና የኪታብ (አቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ) ትምህርቶች ምዝገባ ጀምሯል፤ አጋጣሚውን ተጠቀሙበት!✅️ በአዳሪ (ለወንዶች ብቻ)፦ ከ10 እስከ 20 ዓመት በተመላላሽ (ለወንድም ለሴትም) ከ5 ዓመት ጀምሮ🚨ቦታው ውስን ስለሆነ ልጆቻችሁን ቀድማችሁ አስመዝግቡ። የምዝገባ ቀኑም-እስከ መስከረም 25-2019 ድረስ ብቻ ነው የሚቆየው!📞ስልክ፦ 0919829850 0911119260 💬 ቴሌግራም፦ @bajjiz
    15,800видео906Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    18 сент., 04:39

    ከአቡ ሁረይራ (ረድየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-❝ ትጥበት አድርጎ ወደ ጁምዓ የመጣ፣ ከዚያም የተገራለትን ያህል(ሱና ሶላት) የሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ ኹጥባውን እስኪጨርስ ዝም ብሎ ያዳመጠ፣ በመቀጠልም አብሮት የሰገደ ሰው፤ በዚያች ጁምዓ እና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል ያለው እንዲሁም ተጨማሪ የሶስት ቀናት (ወንጀሉ) ይማርለታል።❞◇ሰሒሕ ሙስሊም 857 t.me/Sle_qelbachn1
    Иллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችንИллюстрация к посту канала ስለ ቀልባችን
    15,20024519Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    17 сент., 18:59

    ወንጀል መስራት፣ማጥፋት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ስናጠፋ «ይቅር በለን» የምንለው እሱን ብቻ ነው፡፡ መጠጊያም ሆነ መሸሻችን እሱ ነው፡፡ እሱኑ እንፈራለን፤ ወደሱ እንሸሻለን፡፡ የሚገርም ነው! ከሱ ወደሱ እንሸሻለን!፡፡ ከሱ ሌላ መሄጃ የለንም፡፡ ሌላ አምላክ የለንም፡፡ ሌላ ጌታ የለንም፡፡ የት እንሄዳለን?፡፡ የትም!!
    15,40048311316Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    17 сент., 13:09изменён

    ስትጨነቅ ምንድን ነው የምታደርገው?🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል-ባጂስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
    17,500видео20954Открыть в Telegram
  • ስለ ቀልባችን

    16 сент., 04:27изменён

    ❝ድንግል ስላልሆንኩ ትዳርን እፈራለሁ ላለች እህት የተላከ መልእክት!❞ ~ ውድ እህቴ ሆይ!ሰው ነሽና ተሳስተሻል፤ አማኝ ነሽና ተፀፅተሽ ወደ ጌታሽ ሮጠሻል። አላህ ደግሞ ተውበት አድራጊዎችንና ወደ እርሱ የሚመለሱትን እጅግ ይወዳል። ታዲያ ይቅር ባዩ ጌታሽ በራሕመቱ የሸፈነልሽን ስህተት ይዘሽ፣ ዛሬም ድረስ ራስሽን የምትወቅሺውና የሐላሉን የትዳር በር በራስሽ ላይ የምትቆልፊው እስከ መቼ ነው?እውነተኛው ንፅህና የተውበት እንባ ያጠበው የልብ ንፅህና ነው። ረሱል (ﷺ) «ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው ልክ ምንም ወንጀል እንዳልነበረው ነው» ብለውናል።ሸይጣን ሁለት ጊዜ ያጠቃሻል፦1. በመጀመሪያው ወቅት ወደ ወንጀል እንድትገቢ አታሎሻል፤ 2. ዛሬ ደግሞ «አንቺ ድንግል አይደለሽም፣ ስለዚህ ለትዳር ብቁ አይደለሽም፣ ነገ ትዋረጃለሽ» እያለ በተስፋ መቁረጥ እና በብቸኝነት ወጥመድ ውስጥ እንድትኖሪ ይፈልጋል።● ጥያቄ 1፡ «ቢክራ ሳልሆን እንዴት አገባለሁ? ለማግባት ብቁ ነኝ?»- ምላሽ፡- አዎን፣ ሙሉ በሙሉ ብቁ ነሽ! ትዳር በኢስላም ለድንግሎች ብቻ የተፈቀደ ሸቀጥ አይደለም። የነቢያችን ﷺ ሚስቶች ከእናት አዒሻህ በስተቀር ሁላቸውም ቀደም ሲል ያገቡ (ቢክራ ያልነበሩ) ናቸው።በሸሪዓው ሚዛን የሴት ልጅ ትልቁ ክብር የሚለካው በዲኗ፣ በስነ-ምግባሯና አላህን በመፍራቷ እንጂ በአንድ የአካል ሽፋን ብቻ አይደለም።
    19,80071010137Открыть в Telegram