Последние посты

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 15:44
በመዲናዋ የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓት በይፋ ሥራ ላይ ዋለቴክኖሎጂው በከተማዋ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተፈራ ሞላ ተናግረዋል።የቴክኖሎጂው ቁልፍ ግልጋሎቶች፦✔️የተቀናጀ የተሽከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር ሥርዓትን በአንድ ማዕከል ይመራል፣✔️በከተማዋ የሚታየውን የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይፈታል፣✔️ኅብረተሰቡ የተሻለና የሰለጠነ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል፣✔️የሰው ንክኪን በማስቀረት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ያግዛል።➕ ይህ አዲስ አሠራር የተሽከርካሪ ምደባ፣ የተቆጣጣሪ ምደባ፣ የሠራተኞች ክትትል፣ የተገልጋይ ጥቆማ፣ የሴክተር ሪፖርት እንዲሁም የአውቶቡስ ዕለታዊ ክስተት ሪፖርቶችን በአንድነት አካትቶ የያዘ መሆኑም ተገልጿል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 15:37
ፈረንሳውያን የፖሊስ ራስን የመከላከል ረቂቅ ሕግ ለመቃወም በፓሪስ ሰልፍ አካሄዱ🇫🇷 ሰልፈኞች በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ዋና ከተማ ጎዳናዎች በመውጣት፤ ለሕግ አስከባሪ አካላት ራስን የመከላከል ወይም ሕጋዊ የጦር መሣሪያን አጠቃቀም መብት የሚሰጠውን ረቂቅ ሕግ ኀዳር 1ዐ በሴኔት ከመታየቱ በፊት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።አዘጋጆቹ የፖሊስ ጭካኔን፣ መዋቅራዊ ዘረኝነትን እንዲሁም በማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች እና በወጣቶች ላይ የሚደርሰውን አፈና አውግዘዋል።"ዛሬ እዚህ የተገኘሁት ስለ ሀገራችን ወጣቶች እና ዴሞክራሲ ሁኔታ ስላሳሰበኝ ነው። ብዙ ወጣቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ታስረዋል። ተደጋጋሚ ተቋማዊ ጥቃቶች የሚፈጽም፤ ጭካኔው እየጨመረ የመጣ መንግሥት ነው ያለን፤ ይህ ደግሞ በጣም አሳሳቢ ነው። የሀገሪቱ ሁኔታ ያስጨንቀኛል፣ ስለ ቤተሰቤ እጨነቃለሁ፣ በመጪዎቹ ወራትም ጭካኔው እንደሚቀንስ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ አንድ ተቃዋሚ በስፍራው ለሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 15:21
❗️ ፑቲን፣ ሺ ጂንፒንግ እና ትራምፕ በሼንዘን፣ ቻይና ኅዳር 10 የሦስትዮሽ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ክሬምሊን አረጋገጠበስብሰባው ዙሪያ ስምምነት ላይ መደረሱን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አስታውቀዋል።የሦስትዮሽ ግንኙነቱ ኅዳር 9 እና 10 ከሚካሄደው የእስያ ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ጎን ለጎን ይካሄዳል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 15:10изменён
ዚምቧቤ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ 'የመንገድ እልቂትን' ለመግታት ጥረቷን አጠናከረች"የትራፊክ አደጋዎች የእንቅስቃሴ አይቀሬ ውጤት ተደርገው መቆጠራቸውን መቀበል አንችልም" ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ኬምቦ ሞሃዲ በሃራሬ በተካሄደው ከፍተኛ የመንገድ ደኅንነት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።👉 እስከ መስከረም 20 ድረስ በተመዘገቡ 48 ሺህ 150 አደጋዎች 1 ሺህ 979 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ እንዲሁም 8 ሺህ 061 ሰዎች ለተለያየ ጉዳት መዳረጋቸው አጽንኦት ሰጥተው፤ አደጋዎቹ "መከላከል የሚቻሉ" እንደነበሩ አክለው ገልጸዋል።የመንገድ አደጋዎችን ለመከላከል በምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃዲ የተዘረዘሩ እርምጃዎች፡-✔️ጠንካራ የፖሊስ ቁጥጥር እና በሕግ አጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ✔️የትራፊክ ደኅንነት ምክር ቤቱን ወደ ጠንካራ የመንገድ ደኅንነት ኤጀንሲ መለወጥ፣ ✔️ለተጎጂዎች ድጋፍ የሚውለውን የመንገድ አደጋ ፈንድ ረቂቅ አዋጅ ማፋጠን፣ ✔️በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚለቀቁ የቤት እንስሳትን ጉዳይ መፍታት እና ሕገ-ወጥ አጥሮችን ማስወገድ፣ ✔️የተተዉ ተሽከርካሪዎችን የሚመለከቱ ሕጎችን መከለስ፣ ✔️በተለይ በወጣቶች ዘንድ አልኮል እና ሌሎች አደንዛዥ ንጥረ ነገሮችን ወስዶ ማሽከርከር ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ።📉 የትራንስፖርትና መሠረተ ልማት ልማት ሚኒስትር ፌሊክስ ምሆና ዚምቧቤ እ.ኤ.አ በ2030 በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን ሞትና የአካል ጉዳት ቢያንስ በ50% ለመቀነስ ቁርጠኛ እንደሆነች በድጋሚ አረጋግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 14:44
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከሩሲያ ብሔራዊ ታሪካዊ ሙዚየም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ🇪🇹🇷🇺 ስምምነቱ የተፈረመው ዓድዋ ድል መታሰቢያ የተሳተፈበት እና ኅዳር 3 እና 4 ቀን "መጪውን መፍጠር" በሚል በሩሲያ ሞስኮ በተካሄደው 3ኛው ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ መሆኑን ተቋሙ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።ይህ አጋርነት የኢትዮጵያን የቅርስ ተቋማት ከዓለም አቀፍ ሙዚየሞች ጋር በማስተሳሰር፤ ለባለሙያዎች ልውውጥ፣ ለጋራ ምርምር፣ ለኤግዚቢሽን እና ለዘመናዊ የሙዚየም አስተዳደር ልምድ ቅብብል ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።🗣 የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ፤ በሁነቱ ላይ የተቋሙን ራዕይ እንዲሁም የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሙዚየሞች የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 14:14
#viral | የሩሲያ ሶዩዝ-2.1ቢ ሮኬት ሁለት የግል ሳተላይቶችን ወደ ህዋ አመጠቀ🚀 መንኮራኩሮቹ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የምድር ገጽ ምሥሎችን እንደሚያነሱ የሩሲያ የመንግሥት ኮርፖሬሽን ሮስኮስሞስ አስታውቋል።👉 የሚሰበሰበው መረጃ የመሬት አጠቃቀምን ለመቆጣጠር፣ ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን ለመለየት፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከታተል እና ለአካባቢያዊ ተግዳሮቶች መፍትሄ ለመስጠት ይውላል ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 13:58
49ኛው የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በማኒላ ተጀመረቢያንስ 19 የዓለም መሪዎች እና የተቋማት ኃላፊዎች ከእሁድ እስከ ማክሰኞ በፊሊፒንስ ዋና ከተማ በሚካሄደው የ "አሴአን" ጉባኤ ይሳተፋሉ።👉 በጉባኤው ከ100 በላይ ሰነዶች ይፈረማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የ "አሴአን" የዲጂታል ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ስምምነት ርክክብ፣ በምያንማር ጉዳይ ዙሪያ የተደረሰውን የአምስት ነጥብ ስምምነት ወደ ተግባር የሚያሸጋግሩ እርምጃዎች እና በዲጂታል እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ምህዳሮች የህጻናትን መብት የሚያስጠብቅ መግለጫ በዋናነት ይጠቀሳሉ።የባሕር ትብብር ሰነድ የጉባኤው እጅግ ወሳኝ ውጤት መሆኑን የፊሊፒንስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴሬሳ ላዛሮለስፑትኒክ ገልጸዋል፡፡ ይህም የፊሊፒንስ የ "አሴአን" ሊቀመንበርነት ዘመን ዋነኛ ትኩረት መሆኑንና የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የባሕር ማዕከል በሀገሪቱ ሊቋቋም እንደሚችልም አፅንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 нояб., 13:38
የገላን ሁለገብ ወደብ የመልቲሞዳል ሎጂስቲክስ ማዕከል መዳረሻ ሆነይህ ፈቃድ የተሰጠው በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋራ ውሳኔ መሆኑን የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።ቁልፍ ዝርዝሮች፦🔶 የካርጎ ድርጅቶች ለመርከብ ጭነቶቻቸው የገላን ሁለገብ ወደብን እንደ መጨረሻ መዳረሻ መጠቀም ይችላሉ፣🔶 ጭነቶች በአንድ ወጥ ሰነድ ከጅቡቲ በቀጥታ በባቡር ወደ ገላን ተጓጉዘው በዚያው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ይፈፀምላቸዋል፣🔶 አስመጪዎችና ላኪዎች አጭር የማጓጓዣ ጊዜ፣ ዝቅተኛ የሎጂስቲክስ ወጪና ቀላል የጉምሩክ አገልግሎት ያገኛሉ፣🔶 በየብስ ትራንስፖርት መስመሩ ላይ የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ ይቀንሳል፣🔶 ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመሮች ወደ ኢትዮጵያ የገበያ እምብርት ይበልጥ ይቀርባሉ።👉 40 ሄክታር መሬት ላይ የተዘረጋው የገላን ሁለገብ ወደብ የጅምላ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘኖች፣ ኮንቴነር ማቆያ ስፍራ እና 10.7 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ተሟልቶለታል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 18:25
#Viral | ታዳጊው የግራና ቀኝ ትከሻውን በፊት ለፊት ሲያገናኝ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ትኩረትን ስቧል📹 ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስልየዚህን ታዳጊ ልጅ ይህን ልዩ ክህሎት እንዴት አገኙት? አስተያየትዎን ያጋሩን 👇✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 18:05
የበለጸጉ ሀገራት አፍሪካ እና የሰው ልጅ ወደፊት እንዲራመዱ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መቀበል አለባቸው - የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንትዓለም በዕውነት ወደፊት መራመድ ካለባት የበለጸጉ ሀገራት አፍሪካውያን በታሪክ አጋጣሚ ጉዳት እንደደረሰባቸው አምነው በመቀበል፣ አኅጉሪቱ እኩል ደረጃ ላይ መድረስ እንድትችል የካሳ ክፍያ ሊከፍሉ ይገባል ሲሉ ጆን ኩፉኦር በአክራ ከተካሄደው 'የ2026 የምዕራብ አፍሪካ የስርጭት ባለሙያዎች ኮንቬንሽን' ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።🗣 ጋና የትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ እጅግ ከባድ ወንጀል ተደርጎ እውቅና እንዲሰጠው በተባበሩት መንግሥታት ያስጸደቀችውን ተነሳሽነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ የገለጹት የቀድሞው ፕሬዝዳንት፤ ይህም ከታሪክ ጥበብ የሚቀዳ አስፈላጊ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 17:50
ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የማንጎ ማቀናበሪያ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ሊገነባ ነውየሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲው አል ናስር ክለብ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በደቡብ ምዕራብ ሴኔጋል ሴዲሂዩ ክልል የሚተገበር "ኤስኤም10 አግሮ" የተሰኘ የግብርና ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አፍሪካዊያን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ፕሮጀክቱ በየዓመቱ የሚባክነውን የማንጎ ምርት በመቀነስ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው።የፕሮጀክቱ ዐበይት ነጥቦች፦🟠 የኢንቨስትመንት መጠን፦ 20.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር🟠 የመሬት ስፋት፦ በ500 ሄክታር መሬት ላይ 78,000 ገደማ የማንጎ ችግኞች ይተከላሉ፡፡🟠 የኢንዱስትሪ ማቀናበሪያ፦ የማንጎ ቅቤን ጨምሮ ልዩ ልዩ የማንጎ ተዋጽኦዎችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡🟠 የሥራ ዕድል፦ ለአካባቢው ነዋሪዎች 1,000 ቀጥተኛ እንዲሁም በርካታ የትራንስፖርትና ተዛማጅ ሕዋሳት ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡🟠 ሥልጠናና ምርምር፦ ለአካባቢው ወጣቶችና አምራቾች የሚሆን የግብርና ሥልጠና እና የምርምር ማዕከልን ያካትታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 17:35
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለሕዝቦቻቸው የተሻለ መጪ ጊዜ በጋራ ለመሥራት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ - የሩሲያ የባሕል ማዕከል ዳይሬክተር 🇷🇺🤝🇪🇹ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ግንኙነት እንዳላቸው ዳይሬክተሩ ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ፤ የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን የፎቶግራፍ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 17:15
🇪🇹 ከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርበመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዋና ዋና ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የገቡና በማጠናቀቂያ ላይ የሚገኙ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 224 ሺህ 805 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳላቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።የፕሮጀክቶቹ የማልማት አቅምና የተጠቃሚዎች ቁጥር፦◻️ የተንዳሆ መስኖ ፕሮጀክት፦ 60,000 ሄክታር የሚያልማ - 120,000◻️ የከሰም መስኖ ፕሮጀክት፦ 20,000 ሄክታር - 40,000◻️ ጊዳቦ (ሎት 2)፦ 13,420 ሄክታር - 26,840◻️ ወልመል (ሎት 1 እና 2)፦ 12,040 ሄክታር - 24,080◻️ ጎዴ መስኖ፦ 10,000 ሄክታር- 20,000◻️ የቄጦ መስኖ፦ 5,000 ሄክታር - 10,000◻️ ጨልጨል (ሎት 2)፦ 4,145 ሄክታር - 8,290
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 17:02
ሩሲያ የሌሎችን ባህል ለማወቅ እና በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መድረክ ፈጥራለች - የዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ተሳታፊ በሩስያ የተካሄደው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ዓለም በአንድነት፣ በጋራ እና በትብብር መሥራት እንዲችል መሠረት የሚጥል መሆኑን ኢትዮጵያዊው የመድረኩ ተሳታፊ ኤርሚያስ ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። 🔙 የ2026 የዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ191 ሀገራት የተውጣጡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 16:45
❗️❗️❗️ የማሊው ፕሬዝዳንት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ማዕከል ምረቃ ላይ ህዝቡን 'የሽግግሩ ባለቤቶች' ሲሉ አወደሱ 🇲🇱 አሲሚ ጎይታ ሰኞ ዕለት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ማዕከል ሲመረቅ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት መግለጫ፤ በማሊ ህዝብ ዘንድ ለታየው የፅናት እና የፈታኝ ጊዜያት ግንዛቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ "በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት የትግስቱ እና የድጋፉ ባለቤት የሆነውን
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 16:26изменён
የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት መታሰቢያ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ ☦️ የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ኪሪል 80ኛ ዓመት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅ ጥናት፣ ምርምር እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ተከፍቷል። 🇷🇺🇪🇹 በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 16:01
የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከበረየሀዲያ ሕዝብ የማህበረሰባዊ ትስስር፣ የፍቅርና የርህራሄ እሴቶች የሚንጸባረቁበት "ያሆዴ" ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና እንግዶች በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከብሯል።ከአጎራባች ዞኖች እና ክልሎች የተወከሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የባሕል ጭፈራዎች የበዓሉ ተጨማሪ ድምቀቶች እንደነበሩም ተዘግቧል፡፡የ"ያሆዴ" በዓል ማብሰሪያ የሆነው "ሳቴ" (ደመራ) የመለኮስ ሥነ-ስርዓቱ በበዓሉ ተሳታፊዎች በተለይም በወጣቶች በተለያዩ የ"ያሆዴ" ሀገረሰባዊ ሙዚቃዎች ታጅቦ ተከናውኗል።ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 15:35
#Viral | በጓሮ ሲያንቀላፈ ነግቶበት የተገኘው ጅብየበቆሎ ማሳ ውስጥ ምሽቱን መሽጎ ያነጋው ጅብ ከስንፍና ይሆን በጤና እክል ባይታወቅም ተኝቶ ተገኝቷል፡፡📹 ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስልእርስዎስ በአካባቢዎ ላይ እንዲህ አይነት ሁኔታ ቢያጋጥምዎ ምን ያደርጋሉ? ሐሳብዎን ያጋሩን 👇✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 15:20
የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የእጅ-አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያዎች ናቸው - ማሊያዊው ጋዜጠኛ🔊 አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ገለልተኛ አይደሉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችን ፍላጎት እና የውጭ ፖሊሲ ለማገልገል በፕሮፓጋንዳ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው ሲሉ ማሊያዊው ጋዜጠኛ ሙላዬ ሀሰን ሀይዳራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።🌍 እንደ ተናጋሪው ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡፡◾️የመረጃ የበላይነቱን በእጃቸው ማድረግ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በአኅጉሪቱ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ማስቆም አለባቸው።◾️ የአፍሪካ ሀገራት በግፍ ኢላማ እንደተደረጉ ስለሚሰማቸው ራሳቸውን መከላከል ይኖርባቸዋል ያሉት ጋዜጠኛው፤ አንዳንድ ሀገራት በርካታ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃንን መዝጋት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።🇷🇺 በአንፃሩ ሩሲያ (የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጩባቸው ሀገራት ጭምር) በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም ሲሉ ሀይዳራ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 сент., 15:05
ሕገ-ወጥ አደን በሊቢያ በሚገኙ ፍልሰተኛ ወፎች ላይ አደጋ ደቅኗል - ባለሙያዎችሕገ-ወጥ አደን በሊቢያ የሚገኙ የፍልሰተኛ ወፎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ባለሙያዎች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።◻️ አሳሳቢ መጠን፦ የሊቢያ ማኅበር ለወፎች ፕሬዝዳንት ኻሊድ አል-ጣይብ እንደገለጹት፤ በየዓመቱ ወደ 500,000 ገደማ ወፎች ታድነው የሚገደሉ ሲሆን፤ ይህም የተሻሻሉ ሕጎች እና ጥብቅ የቁጥጥር መጠኖች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጉ ያሳያል።◻️ ዘመናዊ ስጋቶች፦ በሊቢያ ከተመዘገቡት 361 የፍልሰተኛ ወፍ ዝርያዎች መካከል እጅግ በርካቶቹ በመረብ እና በነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ኢላማ እንደሚደረጉና ይህም በዘመናዊ የአደን ቴክኖሎጂ እና በሕገ-ወጥ ዝውውር የበለጠ እንደባሰ የ"አልሀያ" የዱር አራዊት እና የባህር ሕይወት ያላቸው ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተር ሳሊህ አል-ሻላዊ አፅንኦት ሰጥተውበታል።◻️ የመጠፋፋት አደጋ፦ የንግድ አደን ዝርያዎችን ለመጠፋፋት አደጋ የሚያጋልጣቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ በሊቢያ ከታዩ ሦስት ዓመታት እንደሆናቸው የሊቢያው ምሁር ናሲር ዳዉድ ጠቁመዋል።ℹ️ ከኅዳር እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ወፎች የተሻለ የምግብ አማራጭ ለማግኘት እና አኅጉሪቱ በሚኖራት የእርጥበት ወቅት በዚያ ለማሳለፍ ከአውሮፓ እና ከእስያ ወደ አፍሪካ ይሰደዳሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲
Ссылки
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →