Последние посты

4-3-3 Tech
22 сент., 18:10
አሊባባ የኤአይ ውድድሩን አፋፍሟል፤ እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር የሚደርስ ሞዴል እያበለጸገ ነው።የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዕድገቱን ለማፋጠን አዲስ ቺፕ፣ ከፍተኛ አቅም ያለው የኤአይ ሞዴል እና ሰፊ የዳታ ማዕከል መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚረዳ እቅድ ይፋ አድርጓል።ኩባንያው ከአሁኑ ዋና የኤአይ ሞዴሉ እስከ አራት እጥፍ የሚበልጥ አዲስ ሞዴል እያሰለጠነ ነው። የሞዴሉ መጠን ከ5 እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር ሊደርስ እንደሚችል አስታውቋል። ይህም የኤአይ ሞዴሎች የማሰብ፣ የመተንበይ እና ውስብስብ ሥራዎችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ካለው ዓለም አቀፍ ውድድር ጋር የሚገናኝ እርምጃ ነው።አሊባባ የኤአይ መሠረተ ልማቱንም በስፋት ለማሳደግ እየሰራ ነው። የአሊባባ ክላውድ ዓለም አቀፍ የዳታ ማዕከላት አቅም ከ20 ጊጋዋት እንዲሻገር አቅዷል። ይህ ኤአይ ከሞዴል ልማት ባሻገር ቺፕ፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ዳታ ማዕከላትን ያካተተ ሙሉ የቴክኖሎጂ ሰንሰለት ለመገንባት የሚደረግ ኢንቨስትመንት መሆኑን ያሳያል።የኤአይ ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለአሊባባ እንደ ኩባንያ የንግድ ዕድልን ከማስፋት ባሻገር፤ ለክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ለዳታ ማዕከላት፣ ለሴሚኮንዳክተር እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ የገበያ ፍላጎት እየፈጠረ ነው።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
22 сент., 16:01изменён
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰውና ሮቦት መካከል የተደረገ የ ቦክስ ፍልሚያ🙆♂️🙆♂️🥶https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
21 сент., 15:08
ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ የ11 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለንዋይ ሊያፈስ ነዉ።የጃፓኑ ሶፍትባንክ ኩባንያ በኦፕን ኤ.አይ ያለውን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ቦንድ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ኩባንያው 10 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዶላር እንዲሁም 1 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዩሮ ለመሸጥ እየተዘጋጀ ነው። ከቦንድ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ ፈሰስ ለሚያደርገዉ መዋዕለንዋይ የሚዉል መሆኑ ተነግሯል።የቦንድ ሽያጩ በታቀደው መጠን ከተጠናቀቀ 7 ኢለቨን (7-Eleven) የተሰኘዉ ኩባንያ በአዉሮፓዊያኑ 2021 ይዞት የቆየውን የ10.93 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል።የተዘጋጀዉ ቦንድ በተያዘዉ መስከረም የመጨረሻ ቀናት ለሽያጭ ለማቅረብ መታቀዱም ተገልጿል። ሶፍትባንክ እና ኦፕን ኤ.አይ ከዚህ በፊት በጃፓን በኤ.አይ የታገዙ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ብሎም በአሜሪካዉ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት (ስታርጌት ) ላይ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
19 сент., 12:16
ጄሚኒ Ai ሦስት ኩባንያዎች ሀክ አደረገ.....የበይነ መረብ ጥቃቱን የፈጸመው ትዕዛዝ ሳይሰጠው በራሱ ፈቃድ ሲሆን፤ እንዲህ ያለ ክስተት የመጀመሪያው እንደሆነም ተገልጿል።ጉግል ለቢቢሲ እንደገለጸው ጄሚኒ "በበይነ መረብ ላይ ለሕዝብ ይፋ የሆነ መረጃን በመጠቀም የይለፍ ቃሎችን ገምቶ ከደረሰባቸው በኋላ" ወደ ድረ ገጾቹ ገብቷል።ጄምኒ ላይ የበይነ መረብ ደኅንነት ሙከራ እየተደረገበት ሳለ ድርጊቱን እንደፈጸመ ተገልጿል። ድረ ገጾቹ የሙከራው አካል እንደሆኑ አስቦ ሰርጎ መግባቱንም የጉግል ኃላፊ ለቢቢሲ አስረድተዋል።የኤአይ ሞዴሉ ወደ ድረ ገጾቹ ከገባ በኋላ "መቆሙን" ኃላፊው አክለዋል።መረጃውን የበይነ መረብ ጥቃቱ ለደረሰባቸው ኩባንያዎች ማሳወቁን ጉግል ገልጿል።ባለፉት ሳምንታት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ተጠናክረዋል። ኤአይ እየሄደበት ያለው ፍጥነት እንዲገታ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ፖለቲከኞችም እየጠየቁ ይገኛሉ።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
17 сент., 15:12
ማይክሮሶፍት ለሰው ልጅ ደህንነትና ክብር ቅድሚያ የሚሰጥ አዲስ የኤ.አይ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሊያወጣ ነው።ማይክሮሶፍት በቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ምርምር እና ልማት በትክክለኛው አቅጣጫ ለመምራት የሚያስችል አዲስ የሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።በረቂቅ መመሪያው መሠረት የማይክሮሶፍት የኤ.አይ ሥርዓቶች ከሰዎች የሚሰጣቸውን ማስተካከያዎች መቀበል፣ ለሰዎች ሊገባ በሚችል መንገድ መግባባት እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተግባራቸው በሰዎች ቁጥጥር ሥር መሆን የሚችሉበትን አቅጣጫ ማካተት ዋና ትኩረቱ ነው።ኩባንያው ይህንን መመሪያ ለማዘጋጀት የዘርፉ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የብዙ ወራት የጥናት እና የውይይት ጊዜያት እንደወሰደ ገልጿል። የሕዝብ አስተያየትንም የሚያካትተው መመሪያ ኩባንያው በቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የኤ.አይ ሞዴሎች ለማሠልጠን እንደ መሠረታዊ አቅጣጫ ይውላል።የማይክሮሶፍት ኤ.አይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙስጠፋ ሱሌይማን መመሪያው ኩባንያው ለሚያለማቸው የኤ.አይ ሥርዓቶች ሁሉ መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
15 сент., 15:46
ለ90 ዓመታት ሳይፈታ የቆየዉ የሂሳብ እንቆቅልሽ በ88 ሰዓታት ዉስጥ ተፈታ።ኦፕን ኤአይ አዲስ ሞዴል እና 10 ሺህ የሚጠጉ የኤ.አይ ኤጀንቶችን በመጠቀም ለ90 ዓመታት ያህል መፍትሔ ያልተገኘለትን የሂሳብ ስሌት በ88 ሰዓታት ውስጥ እንደፈታ ገልጿል። ኩባንያዉ ናቪዬ-ስቶክስ የተሰኘዉ ሂሳባዊ ስሌት ዉስጥ የሚገኘዉን የዘመናት ጥያቄ ነዉ መፍታት የቻለዉ።ናቪዬ-ስቶክስ ሂሳባዊ ስሌት(equation) እንደ ውኃ፣ አየር እና መሰል ነገሮች እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ለመረዳት የሚያስችል የሂሳብ ክፍል ነዉ። ኦፕን ኤአይ እንደገለጸው የኤ.አይ ኤጀንቶቹ ሂሳባዊ ስሌቱን ለመፍታት ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል።በተጨማሪም 130 ቢሊዮን የኤ.አይ ቶከኖችን ተጠቅመዋል። ኩባንያው እንዳስታወቀዉ ይህ ሥራ የ10 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ነው። ይህ ሂሳባዊ ግኝት በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያዎች ተጣርቶ ከተረጋገጠ ኦፕን ኤ.አይ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አሸናፊ ይሆናል።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
12 сент., 05:45
Tom 😭😭😭😂😂https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
11 сент., 17:32
አይ Ai ማናየው ጉድ የለም ዘንድሮ 😭😭😂😂https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
11 сент., 04:42
ወቸው ጉድ 😂😂😂አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ስራ እንዳይቀማ በማለት ሮቦቶች ተቃውሞ አሰሙሰዎች በቴክኖሎጂ ምክንያት ስራ አጥ እንዳይሆኑ እና የስራ ዋስትናቸው እንዲጠበቅ ለማስጠንቀቅ 30 የሚጠጉ ሮቦቶች በፖላንድ ዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስቴር ቢሮ ፊት ለፊት ተቃውሞ አሰሙ።ሰልፉን ያዘጋጁት አክቲቪስቶች፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ማሽኖች የሰውን ስራ ሊወስዱ የሚችሉበትን አደጋ በመቃወም መንግስት ጥብቅ የቁጥጥር ህጎችን እንዲያወጣ ጥሪ አቅርበዋልhttps://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
11 сент., 04:25
ወድ የ 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ ቤተሰቦች እንኳን ለ 2018 የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት ዕለት በሰላም በጤና አደረሳቹ አደረሰን 🌼ዓመቱን የሰላም የጤና ያቀድናቸው ዕቅዶች በሙሉ ከሀጢያት በስተቀር ግብ የሚመቱበት ያደርግልን ፣ አመታትን በቸርነቱ የሚፈራርቀው ፈጣሪ 2018ትን አስጀመሮ እንዳሰጨረሰን 2019 በሰላም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን መልካም ፍቃዱ ይሁንልን 🙏መልካም አዲስ ዓመት ❤️@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
4-3-3 Tech
10 сент., 05:00
አፕል የመጀመሪያውን ታጣፊ ስልክ ማምረቱን ተከትሎ አስቀድሞውኑ ታጣፊ ስልክ የነበራቸው ሳምሰንግ በገፃቸው የለቀቁት ቪዲዮ 😂😂https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
10 сент., 04:23
🔰 iPhone 18 Pro Maxhttps://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
9 сент., 20:29изменён
አፕል የመጀመሪያውን ታጣፊ ስልክ «iPhone Duo» ይፋ አደረገ፤ የመነሻ ዋጋውም ታወቀ!የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ አፕል (Apple) በብዙዎች ሲጠበቅ የነበረውን የመጀመሪያውን ታጣፊ ስልክ «iPhone Duo» ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።የስልኩ ዋና ዋና ባህሪያት1. ሲታጠፍ የፓስፖርት ያህል መጠን ያለውና 5.4 ኢንች ስክሪን የሚጠቀም ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሲከፈት ደግሞ ወደ 7.6 ኢንች ሰፊ ስክሪን ይቀየራል።2. ተጠቃሚዎች ቪዲዮዎችን ለማየት፣ ለጨዋታዎች እንዲሁም ሁለት አፕሊኬሽኖችን ጎን ለጎን ከፍተው ለመጠቀም የሚያስችል ሰፊ የመመልከቻ እድል ይሰጣል።3. ሁለቱም ስክሪኖች የ ProMotion እና Always On ቴክኖሎጂዎችን የያዙ ሲሆን፣ በፀሐይ ብርሃን ውስጥ የመመልከት አቅማቸውም እስከ 3,000 nits የሚደርስ ከፍተኛ የብርሃን መጠን ያለው ነው።4.ስልኩ በ Star White እና Night Sky ቀለሞች ለገበያ የቀረበ ነው።የመነሻ ዋጋ እና በኢትዮጵያ ብር ምንዛሬየስልኩ የመነሻ ዋጋ በኤምሬትስ ገበያ 8,499 ዲርሃም (Dh 8,499) ሆኖ ተቆርጧል።በዛሬው የባንክ ምንዛሬ (1 AED = 43 ETB በሚለው ስሌት)፦
4-3-3 Tech
9 сент., 10:00
ጉግል የኤአይ የአየር ሁኔታ ትንበያን ወደ ኃይል ዘርፍም አስገባጉግል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአየር ሁኔታን በተሻለ ደረጃ ለመተንበይ የሚያስችለውን WeatherNext 3 የተሰኘ አዲስ ሞዴል ከሰሞኑ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ሞዴሉ የሙቀት መጠንንና እርጥበትን ጨምሮ የንፋስ ፍጥነት፣ የደመና ሽፋን እና የፀሐይ ብርሃን ወደ መሬት የሚደርስበትን መጠን ይተነብያል። በተለይም ከመሬት 100 ሜትር ከፍታ ላይ የሚኖረውን የንፋስ ፍጥነት መተንበይ መቻሉ ለንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ጠቃሚ መረጃ ነው።የአየር ሁኔታ ትንበያው በተለይ የንፋስና የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ለሚያስተዳድሩ ተቋማት ወሳኝ ነው። ምክንያቱም እነዚህ የኃይል ምንጮች በአየር ሁኔታ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው የሚመረተውን ኃይል አስቀድሞ ማወቅ የኃይል አቅርቦትንና ፍላጎትን ለማመጣጠን ያግዛል። ሞዴሉ የሳተላይት ምስሎችንና ከየአየር ሁኔታ መለኪያ ጣቢያዎች የሚገኙ መረጃዎችን በመጠቀም ትንበያውን ያዘጋጃል።ጉግል እንዳስታወቀው ሞዴሉ ከተለያዩ የዝናብ መረጃ ምንጮች ጋር ሲነጻጸር እስከ 60 በመቶ የሚደርስ መሻሻል አሳይቷል። ሞዴሉ የጉግል ፍለጋ፣ ጄሚናይ፣ ጉግል ካርታ እና ጉግል ክላውድን ጨምሮ የተለያዩ የጉግል ስርዓቶች እንዲጠቀም ተደርጓል። በዚህም ጉግል ኤአይን ከአየር ሁኔታ ትንበያ ጋር በማጣመር የኃይል ምርትን፣ ስርጭትንና አጠቃቀምን በተሻለ ሁኔታ ለማቀናጀት የሚያግዝ አዲስ ቴክኖሎጂ ወደ ገበያው አስገብቷል።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
9 сент., 04:57
ቴስላ ያለ መሪ እና ፔዳል የሚሰራውን “ሳይበር ካብ” (Cybercab) የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ...የኤሎን መስክ ኩባንያ የሆነው ቴስላ, በዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውን ሙሉ በሙሉ በራስ ሰር (Driverless) የሚንቀሳቀሰውን “ሳይበር ካብ” (Cybercab) የተሰኘውን የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በአሜሪካ (ቴክሳስ ኦስቲን) በይፋ ሥራ አስጀምሯል።ቁልፍ መረጃዎች ፡-ዲዛይን እና አሰራር፡ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) እና ካሜራዎች ብቻ የሚመራ ሲሆን፣ የመሪ መሽከርከሪያ (Steering Wheel) ወይም የፍሬን/አክሰለሬተር ፔዳሎች የሉትም።ምቾት እና አገልግሎት፡ ለሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ የተነደፈ ሲሆን፣ ውስጡ እንደ ሰፊ መዝናኛ ላውንጅ የተዘጋጀ ግዙፍ የክትትል ስክሪን እና እጅግ ዘመናዊ የድምፅ አቀንቃኝ ተካትቶለታል። ተሳፋሪዎች በልዩ የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ታክሲውን ጠርተው መጠቀም ተጀምረዋል።የወደፊት ዕቅድ፡ ኤሎን መስክ የዚህ ተሽከርካሪ የሽያጭ ዋጋ ወደፊት ከ30,000 ዶላር በታች እንደሚሆን ገልፆዋል።https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
8 сент., 04:25
የቴክኖሎጂው ዓለም ተለወጠ — መሪና ፍሬን የሌለው መኪና በይፋ ሥራ ጀመረ!ቴስላ ሳይበርካብ፡ ራሱን ችሎ የሚነዳው የነገው መኪናበሳይንስ ልቦለድ ፊልሞች ላይ ብቻ የምናየው አስደናቂ ቴክኖሎጂ አሁን የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ሆኗል! ቴስላ ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተዋይነት የሚመራውንና ምንም ዓይነትመሪ፣ ነዳጅ መስጫ ወይም ፍሬን የሌለውን "ሳይበርካብ" የተባለውን ኤሌክትሪክ መኪና በአሜሪካ ኦስቲን ቴክሳስ ለሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስጀምሯል።አሁን በስልክዎ መተግበሪያ ታክሲ ሲጠሩ መኪናው ብቻውን መጥቶ በር ከፍቶ ይጭንዎታል — በሹፌሩ ወንበር ላይ ግን ማንም የለም!መኪናውን ልዩ የሚያደርጉት ዋና ዋና ነገሮች፡-1. ምንም ዓይነት መሪ የለውም 2. የነዳጅ እና ፍሬን መስጫ የለውም 3. አሽከርካሪ ወይም ሹፌር የለውምበአሜሪካ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት መኪናው የሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ የፈረስ ጉልበት ያለው ኤሌክትሪክ ሞተር እና የካርቦን ነፃ ባትሪ የተገጠመለት ሲሆን፣ በአንድ ሙሉ ቻርጅ እስከ አራት መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር መጓዝ ይችላል።
4-3-3 Tech
7 сент., 06:44
ቻይና ዓለም አቀፍ ቀዳሚ የሆነውን አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቀደችየቻይና ብሔራዊ የመድኃኒትና የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO የተሰኘውን የሳንቲም ያህል መጠን ያለው አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ (BCI) ቴክኖሎጂ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ሰጥቷል።በጽንግሁዋ ዩኒቨርሲቲ እና በኒውራክል ቴክኖሎጂ የተገነባው ይህ መሳሪያ፣ ከምርምር ማዕከላት ውጭ የሰዎችን የእንቅስቃሴ አቅም ለመመለስ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ያገኘ በዓለማችን የመጀመሪያው በአእምሮ ውስጥ የሚተከል ቴክኖሎጂ ሆኗል።የኢሎን መስክ ኒውራሊንክ (Neuralink) አሁንም በሰው ልጅ ላይ በሚደረግ የሙከራ ደረጃ ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፣ NEO ግን ደህንነቱን ባስቀደመው ልዩ ዲዛይኑ ምክንያት በፍጥነት የንግድ ፈቃድ ማግኘት ችሏል።መሳሪያው የአእምሮ ክፍሎችን ጥሶ ከመግባት ይልቅ ስምንት ሴንሰሮቹ ከአእምሮ ውጫዊ ሽፋን (dura mater) ላይ በደህና ሁኔታ የሚያርፉ በመሆናቸው የህብረህዋሳት ጉዳትንና ደም መፈሰስን በእጅጉ ይቀንሳል። ይህ ፈቃድ በፅኑ የአንገት አጥንትና የሕብረ-ሰstandard አደጋ ምክንያት ሙሉ በሙሉ የእጅና የእግር ሽባነት ለገጠማቸው ነገር ግን የተወሰነ የእጅ እንቅስቃሴ ላላቸው ከ18 እስከ 60 ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ አዋቂዎች ብቻ የሚያገለግል ነው።በ11 ሆስፒታሎች ውስጥ በተደረጉ የሕክምና ሙከራዎች፣ ስርዓቱ በቤት ውስጥ በአእምሮ እዘዛ ዕቃዎችን የመጨበጥ ድጋፍ በመስጠት 100 በመቶ ስኬት አስመዝግቧል።ይህ ቴክኖሎጂ የሰዎችን የሃሳብ ፍላጎት በመተርጎም ከሮቦቲክ
4-3-3 Tech
4 сент., 15:31
ሮቦት ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቷል 🫣😂😂https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 Tech
4 сент., 04:31
ኤ.አይ የኢኮኖሚና የአኗኗር ሥርዓትን እያዘመነ ነውጉግል የምድር ገጽታ መረጃዎችን በመጠቀም የህዝብ ጤና፣ የምግብ ዋስትና፣ የአካባቢ አደጋ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ለመተንበይ የሚያስችል “ፕላኔታዊ ትንበያ ሞተር” (Planetary Prediction Engine - PPE) የተሰኘ ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል። ቴክኖሎጂው ከተፈጥሯዊ ቋንቋ ትዕዛዝ በመነሳት የጂኦስፓሻል መረጃን ከመፈለግና ከማጽዳት ጀምሮ የመረጃ ባህሪያትን ማዘጋጀት፣ ሞዴሎችን ማሰልጠን፣ ውጤታቸውን መገምገም እና የትንበያ ሪፖርት ማዘጋጀት ድረስ ያሉ ሂደቶችን በራሱ ያከናውናል።በተለይም ቀጠናዊ የምግብ ዋስትና ሁኔታ መተንበይ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን መገመት፣ የበሽታ ወረርሽኞችን መከታተል እና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነትን ለመለየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ይህ ቴክኖሎጂ በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ይሠራል። በመጀመሪያ ተገቢውን የጂኦስፓሻል መረጃ በራሱ ይፈልጋል፤ በመቀጠል የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማጣመር ለትንበያ የሚያገለግል የመረጃ ስብስብ ያዘጋጃል፤ በሶስተኛ ደረጃም የተለያዩ የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን በመፈተሽ ትንበያውን ያዘጋጃል።ሥርዓቱ ከGoogle Earth Engine እና Data Commons ከመሳሰሉ የጂኦስፓሻል መረጃ ማዕከሎች መረጃ ከማግኘቱ በተጨማሪ፤ በእነዚህ ምንጮች የማይገኝ መረጃ ሲያስፈልግ ከድረ ገጽ ላይ በመፈለግ፣ ከመንግሥታዊ ፖርታሎችና ከአካዳሚክ ምንጮች መረጃ ሊሰበስብ ይችላል። ለመረጃ ማጣራትና ሞዴል ለመገንባት ሳምንታት ይፈጅ የነበረውን ሥራ የፕላኔታዊ ትንበያ ሞተር ወደ ጥቂት ደቂቃዎች ሊያሳጥረው
4-3-3 Tech
3 сент., 18:19
Open Ai እጅግ በጣም ኃይለኛ የሆነውን የ Ai ሞዴል 'GPT-6 Astra' ግልጋሎትን መስጠት ጀምሯል።🥶🥶GPT-6 Astra ምንድን ነው? በምሳሌ እንካቹ...የዱሮ Ai 👉 “ኢሜይል ጻፍልኝ” ብለን ስንጠይቅ ኢሜሉን ይፅፋል...አዲሱ GPT-6 Astra ግን ፦👉 “ይህን የደንበኛ ቅሬታ አስተካክልልኝ” ስትሉት እሱም ችግሩን ተረድቶ → ምላሽ አዘጋጅቶ → መረጃዎችን አጣርቶ → አስፈላጊ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ → ለውጦችን አድርጎ → ስራውን ሰርቶ ይጨርሳል።ስለዚህ ትልቁ ለውጥ፦AI ከማስረዳት ወይም ከመመለስ አልፎ “ሙሉ ስራን ለኛ ወደ መሥራት” ተሸጋግሯል።🧠 ቀላል ምሳሌየቀድሞውን Ai ፦ “ለንግድ ድርጅቴ የሚሆን ዌብሳይት ሠራልኝ።” ብለን ስንጠይቅ የቀድሞ AI የተወሰነ የኮድ ጽሁፍ ይልካል።
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →