gram news
Аватар канала Theo-Sophia

Theo-Sophia

@theo_sophia_apology

ትምህርተ ነቢያትን ፣ ትምህርተ ሐዋርያትን ፣ ትምህርተ ሊቃውንትን ተገን ያደረገ ፤ ኦርቶዶክሳዊ ርዕዮተ ዓለምን ከፍልስፍናዊ ዳሰሳ ጋር የሚያቀርብ ቻናል እነሆ🏛

ПроектыENРелигия

6,510подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Theo-Sophia

    22 сент., 17:01

    ይህች ፍጥረት ኃያል ናት፤ ወደ ክፋት ካዘነበለች ታላቅ ጥፋትን ታደርጋለች፤ በጎ ምግባርን ከያዘች ግን ዓላማዋን ላለመተው ሕይወቷን እንኳን አሳልፋ ትሰጣለች። ይህች ማናት?
  • Theo-Sophia

    21 сент., 18:33

    ሰላም ለአጻብኢከየመንግስተ ሰማይ ምስጢሯን በምድር ላይ ትገልጥ ዘንድ መጻህፍትን ለማገላበጥ ለተፈጠሩ የእጅ ጣቶችህ ሰላምታ ይገባል።እንደ ዕዝራ መጻህፍትን የምታውቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሆይእግዚአብሔር የወደዳት የቅድስና ጥበብህ መወለጃዋ ወዴት ነው?ሀገሯስ ወዴት ነው።
    Иллюстрация к посту канала Theo-SophiaИллюстрация к посту канала Theo-Sophia
    9097327Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    21 сент., 10:26

    переслано из @mstaketsehay

    ◈ወንድማችን እፎይን አይዞህ አለማለት ንፉግነት ነው። ◈ "በጕዞው ርዱት።"፩.ቆሮ.፲፮፥፲፩◈እኔ ደክሞ ያዘጋጀው መጽሐፉን ከእጀ ገብቶ እስካነበው እስካነበው ጓጉቻለሁ፤አንተሽ? አንቺስ?◈ከራሴ ጀምሮ ባለካባ እና ባለ ዳባ ተጠራቅሞ አንድ መስመር መራመድ ያልቻለነውን ራሱን ሰጥቶ እንዴት መሥራት እንደሚቻል ያመላከተ ጥቡዕ ወንድም ነው።◈በባዶው ተወልዶ እህል ጨርሶ ከመሞት እንዲህ በወጣትነት እድሜው አስተምሮ አብርቶ ማለፍ ዘለዓለማዊ ሕያውነት ነው።◈አቅሙ ያላችሁ እፎይን በሁሉም አይነት ማንገድ ማገዝ ያስፈልጋል።◈የወጣበት የወረደበት ትምህርቱ ከሁሉ እንዲደርስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የድርሻውን ይወጣ።◈ከፍርሀት፣ከትእቢት፣ከስንፍና እንዲጠብቀው፣የሰማእያን ጆሮ እንዲከፈትለት ሁሉም፦ገዳማት፣ጉባኤ ቤቶች፣ምእመናን በጸሎት ሊያስቡት ይገባል።◈አብረውት የሚወጡ የሚወርዱ ወንድሞችንና እኅቶችን ሁሉ እግዚአብሔር የበለጠ ጸጋውን፣ትጋቱን፣ጽንዓቱን፣አንድነቱን፣ፍቅሩን እንዲሰጣቸው በሁሉ ክርስቲያኖች ዘንድ ሊታሰቡ ይገባል።◈"ሰዓሊ ለነ ቅድስት" የምትሉ ሁሉ የአቡነ ዘበሰማያት ሰባራ የለውምና አስቧቸው።"እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት እርሱን የሚመስሉትንም አክብሯቸው።"ፊል.፪፥፳፱
    Иллюстрация к посту канала Theo-SophiaИллюстрация к посту канала Theo-SophiaИллюстрация к посту канала Theo-Sophia
    1,01090432Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia pinned a file

    21 сент., 05:28

  • Theo-Sophia

    20 сент., 21:13изменён

    በባለፈው ጊዜ ከቴዎፍሎስ ጋር በተያያዘ በጻፍናት ጠንከር ያለች ትንሽ post ላይ ተጨማሪ ነገር እንዲዘጋጅ ለጠየቃችሁ ልጆች እንዲሆን የተሰናዳ ጽሁፍ እነሆ። ቴዎፍሎስ ዮሐንስ አፈወርቅ ላይ ካደረሰው ግፍ በተጨማሪ እንደ ሰው ያለውን ጠባይ በደንብ ትመለከቱበታላችሁ። በጥንቃቄ አንብቧት። ምክንያታዊ የሆነና በማስረጃ የተደገፈ ትችት፣ አስተያየት እንቀበላለን።
    1,220файл2853Открыть в Telegram
  • Live stream finished (1 hour)

    20 сент., 20:03

  • Theo-Sophia

    20 сент., 18:33

    ገባ ገባ በሉ ሰዎችhttps://t.me/Theo_Sophia_apology?livestream
    TelegramTheo-Sophiaትምህርተ ነቢያትን ፣ ትምህርተ ሐዋርያትን ፣ ትምህርተ ሊቃውንትን ተገን ያደረገ ፤ ኦርቶዶክሳዊ ርዕዮተ ዓለምን ከፍልስፍናዊ ዳሰሳ ጋር የሚያቀርብ ቻናል እነሆ🏛
  • Live stream started

    20 сент., 18:31

  • Theo-Sophia

    20 сент., 17:18

    переслано из @kale_amin

    በዘመናት ውስጥ ማስተዋልን ከጥበብ ጠባይን ከትህትና የያዙ አርአያነታቸውን ልንከተል የሚገባን ብዙ ሴቶች ይገኛሉ። መፅሐፍ ቅዱስ ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች ሰነፍ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች ይላል። ጠቢባን ሴቶች ከትዳራቸውም ባለፈ የብዙ ነፍሳትን ህይወት ሲያተርፉ እንዲሁም ጦርነቶችን ሲያስቆሙ እንመለከታለን።በእስራኤል ምድር ሳኦል በነገሰበት ዘመን ጠባዩ ክፉ የሆነ እንዲሁም በስንፍናው የሚታወቅ ናባል የሚባል ሰው ነበር። ይህ ሰው መልከመልካም እና ጥበብን ከትህትና ጋር አስተባብራ የያዘች አቢጊያ የምትባል ታላቅ አዕምሮ ያላት ሚስት ነበረችው። ዳዊት በምድረ በዳ ሳለ የናባል እረኞችና በጎች በጠላት እንዳይደፈሩ ጥበቃ ሲያደርግላቸው ነበር።ነገር ግን ናባል በጎቹን በሚሸልትበት ቀን ለዳዊት የሚገባውን ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም እንዲያውም የስድብ ቃላትን ሲናገር እንመለከታለን። በዚህ ጊዜ ዳዊት አብረውት የነበሩትን ሰይፍ በማስታጠቅ ናባልን እንዲሁም ከርሱ ወገን የሆነውን ወንድ ሁሉ ለማጥፋት እየማለ ወደ ናባል ቤት ተነሳ። ከናባል እረኞች አንዱ ዳዊት እና ከእርሱጋር ያሉ ሰዎች በበረሃ ስላደረጉላቸው መልካምነት የናባል አፀፋ ግን ተቃራኒ መሆኑን ለአቢጊያ በነገራት ጊዜ አደጋው የከፋ መሆኑን በመረዳት በፍጥነት ተነሳች። ለዳዊትና ለሰዎቹም የሚገባቸውን በማሰናዳት በመንገድ አገኘቻቸው። ባየቻቸውም ጊዜ በግንቧራ በመደፋት ይህንን እንዳያደርግ ስትማፀነው እና በእጁ ደም በማፍሰስ ለራሱ ፀፀት ውስጥ እንዳይገባ ብሎም ወደፊት በእስራኤል እንደሚነግስ በመንገር ጥበብ የተሞላበትን ልመና ታቀርባለች። በዚህም ዳዊት
    Иллюстрация к посту канала Theo-SophiaИллюстрация к посту канала Theo-Sophia
    1,0902533Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    20 сент., 12:45

    ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ ዛሬም ከ3 ሰአት ተኩል ጀምሮ የኦሪት ዘጸአት ትምህርታችንን እንቀጥላለን። መጽሀፍ ቅዱስ መማር የሚፈልጉ ጓደኞቻችሁን ይዛችሁ በሰአታችን እንገናኝ።
  • Theo-Sophia

    19 сент., 18:13

    ለምእመናን የሚነገረው ትምህርት እውነት የሆነው ብቻ አይደለም። ለመንፈሳዊ ሕይወታቸውና ለቤተ ክርስቲያናዊ ህልውናቸው አስፈላጊ የሆነውንም የጠበቀ መሆን አለበት። የመምህሩም ድርሻ ምእመናን በሃይማኖት ጽኑዓን፣ በምግባር ደግሞ መንፈሳውያን እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ብዙ ጊዜ ግን እነዚህን ሁለት ጠባያት በአንድ ላይ አናገኛቸውም። አንዳንዶች ስለ እውነቱ ብቻ በመጨነቅ ጨካኞች ይሆናሉ ሌሎች ደግሞ ለምዕመናን በማሰብ ሰነፎች እና ቸልተኞች ይሆናሉ። ከዚህ ይልቅ እንደ ቀደሙ አባቶቻችን በተለይም እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዳቦ ከማር ጋር ፣እንጀራም ከወጥ ጋር እንደሚቀርብ እውነትንም ከፍቅር ጋር አዋሕደን ልንሰጥ ይገባናል። መምህራን ለትምህርቱ ቅንነት ብቻ ተጨንቀው ለምእመናን ልቡና ደንታ የሌላቸው ጨካኞች ሊሆኑ አይገባም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከልክ በላይ በመራራት ሰበብ ተግሣጽንና እውነትን ከመናገር የሚቆጠቡ፣ ቁርጠኝነት የጎደላቸው ሰነፎች ሊሆኑ አይገባም። ሐዋርያው እንዳስተማረ እውነትን በፍቅር መያዝ ይገናባል። የመናፍቃንን መዝሙር መስማት ወይም መጀመሪያ ኦርቶዶክሳውያን ሆነው በኋላ ግን ተሃድሶ የሆኑ ሰዎችን የቀድሞ መዝሙራቸውን መስማት ይገባል? በአሁኑ ወቅት ቀድሞ በቤተ ክርስቲያን የነበሩ፣ ዛሬ ግን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ኅብረት የሌላቸው አገልጋዮች (ዘማርያንና ሰባኪያን) በኦርቶዶክሳዊ እምነት ሳሉ ያዘጋጇቸውን ዝማሬዎችና ስብከቶች “ብንሰማ ችግር አለው?” ተብሎ ሲጠየቅ በተደጋጋሚ እንሰማለን። ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አንድ መርህ ከአባቶች እንውሰድ ቅዱስ ቪንሴንት ዘሌሪንስ (St. Vincent of
    1,3405091Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    19 сент., 06:52

    переслано из @kale_amin

    Heaven is beautiful. Heaven is precious. I wish we would all struggle to enjoy Heaven.Tamav Iriniመንግሥተ ሰማያት ውብ ናት። መንግሥተ ሰማያት እጅጉን የከበረች ናት። ሁላችንም እርሷን ለመውረስ ብንጋደል እመኛለሁ።ቅድስት ኄራኒ
  • Theo-Sophia

    18 сент., 07:45изменён

    አባ አፉም እንዲህ አለ "ከእኔ ጋር እንደምትስማማና ከእንግዲህ እንደማትቃወመኝ አምናለሁ።"ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ "አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ወይም ለምጻም፣ ወይም ሽባ ወይም ዕውር የእግዚአብሔር አምሳል ነው ብለህ እንዴት ትናገራለህ?"አይ ቴዎፍሎስ 😁
    1,5402375432Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    17 сент., 19:31

    አዲስ የእህቶች ጉባኤ ነው።እዚሁ አኛው ጋር ያሉ ሴቶች እህቶች ሚሳተፉበት ቻናል ነው ተቀላቀሉ እና አበረታቷቸው።
  • Theo-Sophia

    17 сент., 19:30

    переслано из @kale_amin

    ክርስቲያኖች ስለ ሴቶች በተለየ ሁኔታ ማውራት ለምን ይጠበቅባቸዋል? ክርስትና ለሁሉም አይደለምን? በእርግጥ የክርስትና እምነትና አስተምህሮ ለ አለም ድህነት ሁሉ የሚሰበክ ነው። ወንዶችም ሴቶችም በ እግዚአብሔር አርአያ እና አምሳል እኩል የተፈጠሩ ናቸው እግዚአብሔር ሁለቱንም እኩል ለቅድስና፣ እኩል ክርስቶስን ለመሻትና ለማግኘት ጠርቷቸዋል።ሆኖም ግን እኩል ናቸው ማለት ፈጽሞ አንድ አይነት ናቸው፣የሚገጥሟቸው ፈተናዎችና ድክመቶች ሁልጊዜም አንድ አይነት ናቸው ማለት አይደለም።በቤተክርስቲያናችን ጾታ ምእመናን የሚባል አስተምህሮ አለ። እያንዳንዱ ጾታ ምእመን የሚያጋጥመው የራሱ የሆነ ፈተና እና ጾር አለ።ለምሳሌ ካህናት በ ትእቢት፣ መነኮሳትና አረጋውያን በሥሥት፣ ወጣት ወንዶች በ ዝሙት፣ ወጣት ሴቶች ምንዝር ጌጥ አብዝተው በመውደድ ይፈተናሉ። ሴቶች የተለያዩ ጥያቄዎችና ጫናዎች ይገጥሟቸዋል ከውበት፣ ከተቃራኒ ጾታ ግንኙነት፣ ከጋብቻ፣ ከእናትነት፣ከተለያዩ የማንነት ጥያቄዎች፣ ከስራ፣ ከቤተሰብ፣ ከብቸኝነት፣ እና ከራስ ክብር ጋር የተያያዙ ብዙ ውሳጣዊ ጥያቄዎችን ያስተናግዳሉ።እዚህም ጥያቄዎች በጥንቃቄ ተወስደው ሊታዩና ሊጠኑ ይገባቸዋል።እነዚህኑ ጥያቄዎች በመያዝ አሁን ወዳለንበት ዘመን ስንመለከት ደግሞ ዘመናችን የተለያዩ መልሶችን በአንድም በሌላም መልኩ ለ ሴቶች ሲያቀርብ እንመለከታለን። እነዚህ መልሶች ደግሞ ቤተክርስቲያናዊ የሆኑም ቤተክርስቲያናዊ ያልሆኑም ሊሆኑ ።እለት እለት በየ ማህበራዊ ሚዲያው ሴቶች ቁንጅና ምን እንደሆነ፣ ስኬት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር(የተቃራኒ ጾታ ጋር የሚኖር ግኙነት) ምን መምሰል
  • Theo-Sophia

    17 сент., 08:46изменён

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም መስከረም 7 በዚህች ቀን ምእመናንን ከክፉ የመርቅያን እርሾ የጠበቀ፣ ስለአባቶቹ ሃይማኖት የጥርስ መርገፍን፣ የጽሕም መነጨትን፣ ከመንበር መሳደድን እና ሌሎች ብዙ መከራዎችን የታገሰ የተዋህዶ አርበኛ የተዋህዶ ጠበቃ 25ተኛው የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ በግዞት ሳለ አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከኛ ጋር ትኑር አሜን።ዳግመኛም በዚህች ቀን በወንጌላዊው አንደበት የተመሰገነች እና የከበረች የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የጻድቁ ካህን ዘካርያስ ደግሞ ሚስት የምትሆን እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ አረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከኛ ጋር ይሁን።ዳግመኛም በዚህቺ ቀን የጌታችን አያት ትሆን ዘንድ በእግዚአብሔር የተመረጠች፣ ቅዱስ ከሆነ ትዷሯ እመቤታችንን ያስገኘች ቅድስት ሐና ተወለደች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሐና በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ይድረሰን አሜን።ዳግመኛም በዚህች ቀን የቡሩክ ኤጲስቆጶስ የሳዊርያኖስ፣ እግዚአብሔር ሰማእትነትን ከእናታቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ የመረጣቸው የነ ቅዱስ አጋቶን፣ ጴጥሮስ፣ አሞንና፣ ዮሐንስ የእናታቸውም ራፊቃ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከኛ ጋር ትኑር አሜን።እግዚአብሔር አምላካችን በቅዱሳን ጻድቃን በሰማእታትም ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከኛ ጋር ትኑር አሜን።እንኳን ለቅዱስ ዲዮስቆሮስ የእረፍት በአል አደረሳችሁ ።
    Иллюстрация к посту канала Theo-SophiaИллюстрация к посту канала Theo-Sophia
    1,67075422Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    16 сент., 19:23

    የቤተ ክርስቲያን አባቶች በማኅበረሰብ ተጽዕኖ ሊያድርባቸው ይችላል? ወይም ደግሞ በወቅቱ በነበረው የሳይንስ ዕውቀት፣ ወይም በወቅቱ በሚታወቀው ታሪክና በሌሎች ውጫዊ ነገሮች እምነታቸው ሊቀረጽ ይችላል? ፌሚኒስቶች ብዙዉን ጊዜ ስለ አባቶች ሲነሳ ያላቸው አማራጭ እነርሱን ወደ ጎን ማድረግ ወይም ደግሞ መቃወም ስለሆነ በቅዱሳን አባቶች ላይ የሚያነሡት የመጀመሪያው ተቃውሞ ይኸው ነው።ለዚህ የምንሰጠው ምላሽ የሚከተለው ነው ።መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን አባቶች ላይ እንዲህ ዓይነቱ ውጫዊ ተጽዕኖ(external influence) እንዲያድርባቸው ሊፈቅድ ይችላል!። ይህንን ማለትም ሆነ መቀበል ችግር የለውም። የማንቀበለው ግን ያ ተጽዕኖ በዘፈቀደ፣ ዕውርና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ የተፈጠረ ነው የሚለውን አባባል ነው(blind, irrational and arbitrary influence )።በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ከሆነ፣ ምናልባትም ይህ ከመንፈስ ቅዱስ የአሠራር መንገዶች አንዱ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እንደ ተራ ግለሰብ አባቶች በአንድነት ያላቸው እምነት ምክንያት የለሽ ስሜታዊ እና መንፈቅዱስ የለሽ ነው የሚሉ ካሉ ኦርቶዶክሳውያን ሊሆኑ አይችሉም።ይሄ ኑፋቄ ነው!!።በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ግን ማለትም መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የማህበረሰቡን ነባር እምነቶች ወደ ቤተክርስቲያን ሊያስገባ ይችላል።በታሪክ ውስጥ አባቶች ከዘመኑ ማኅበራዊ ሐሳቦች ጋር የተስማሙባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ።ሌላው ደግሞ ማኅበረሰቡ ከፍ አድርጎ የሚመለከታቸውን ነገሮች ፈጽሞ ትኩረት ያልሰጡባቸው ጊዜዎች አሉ። ለምሳሌ፣ ዲሞክራሲ ለግሪካውያን
  • Theo-Sophia

    16 сент., 06:57

    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባል ሁልጊዜ ለሚስቱ ያለውን ፍቅር በቃላት መናዘዝ አለበት ይላል።እውነቱን ለመናገር ይህ ነገር እንዲሁ ለባል እና ለሚስት ብቻ አይደለም በመድኃኒታችን በክርስቶስ ላሉ ለእህቶቻችንም ጭምር እንጂ።ምንም እንኳ እንደምንወዳቸውና እንደምናከብራቸው ቢያውቁም፣ ሁል ጊዜ እንድናስታውሳቸው ይወዳሉ። ስለዚህ በክርስቶስ ያሉትን እህቶቻችንን ሁሉ ያለ ምንም ልዩነት ቤተክርስቲያንን እንደምንወድ ልንወዳቸውና ፍቅራችንን ልንገልጽላቸው ይገባል።
    1,83086964Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    15 сент., 01:25

    በዲዮቅልጢያኖስ ጊዜ ከክርስቲያኖች ወገን ፔላግያ ዘአንጾኪያ የምታባል ሰማዕት ነበረች ።የመታሰቢያ ቀኗ የተለያየ ቢሆንም(እንደየ ትውፊቱ) በሁሉም ዘንድ የተከበረች ቅድስት ናት። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው እድሜዋ ወደ 15 አካባቢ ነበር ወታደሮች ወደቤቷ ሊወስዷት ሲመጡ በቤት ውስጥ ለብቻዋ ነበረች።የወታደሮቹኑም የዝሙት አዝማሚያ ባየች ጊዜ ፣አንድ ጊዜ ልብሴን ልቀይር ብላ ወደ ውስጠኛው ቤት ገባች።ነገር ግን ልብሷን ቀይራ አልተመለሰችም፣ ከቤቱ ጣራ ላይ ወጥታ ወደታች ራሷን ጣለች በዚህም ምክንያት ስለ ደንግልናዋ አረፈች።ልብ የምንለው ነገር ቢኖር ፔላግያ አንደኛ ለተራ ነገር ራሷን አልገደለችም ።ይህች ሴት አይደለም ክርስቶስን ልትክድ ይቅርና ንጽህናዋን እንኳን ልትተው አልወደደችም። ሁለተኛ ደግሞ ምናልባት ከቤቱ ጣራ የዘለለችው ለማምለጥ አስባ እንጂ ሆን ብላ ራሷን ለመግደል ላይሆን ይችላል። ከምንም በላይ ግን ይህች ሴት የ15 ዓመት ልጅ፣ ድንግል እና ሰማዕት ነበረች። ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ አምብሮስ ስለ ክብሯ እና ስለ ንጽህናዋ ስለ ቆራጥነቷ ጽፈዋል።በቀድሞ ክርስቲያኖች ዘንድ(አሁንም ባሉት) በተለይ ደግሞ በአንጾኪያ እጅግ የምትወደድ ቅድስት ነበረች።በረከቷ በእውነት ይደርብን!እንኳን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ አምብሮስ ኖሩ እንጂ እዚህ ቢሆን ፍትሐት ይደረግላት ወይስ አይደረግላት ነበር ጭቅጭቁ።
    2,0906613541Открыть в Telegram
  • Theo-Sophia

    14 сент., 18:57

    “ከሀብታም ወይም ከተከበረ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙ ሴቶችን ማግባት እየቻልኩ ሳለ ያንን ሁሉ አልፈለግሁም። ይልቁንም አንቺን፣ ያማረ ጠባይሽን፣ ቅንነትሽን፣ የዋህነትሽንና የረጋ መንፈስሽን ወደድሁ እንጂ።………………..ከምንም ነገር በላይ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ይበልጥብኛል፤ ከአንቺ ጋር ከመጣላት ወይም ከመቃረን የበለጠ የሚያመኝ ምንም ነገር የለም።…..ሁሉ ነገሬን ባጣ፣ ፈጽሞ ምስኪንና ለማኝ እንኳ ብሆን፣ ታላቅ አደጋና ማንኛውም ዓይነት መከራ ቢደርስብኝ፤ የአንቺ ልብ ለእኔ ታማኝ እስከሆነ ድረስ ያ ሁሉ ለእኔ ምንም አይደለም፤ በደስታ እችለዋለሁ።” በላት ወገን ይህን የተናገረው ሮምዮ አይደለም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በኤፌሶን ትርጓሜው ነው።