gram news
Аватар канала TIKVAH-SPORT

TIKVAH-SPORT

@tikvahethsport

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469

ПроектыENСпорт

291,000подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 20:02изменён

    “ በሀንሲ ፍሊክ ሥራ ተደስቻለሁ ” ዣቪስፔናዊው የኔዘርላንድ አሰልጣኝ ዣቪ አሰልጣኝ ሀርናንዴዝ ሀንሲ ፍሊክ በባርሴሎና እየሰሩ የሚገኙትን ነገር አድንቋል።“ ሀንሲ ፍሊክ በጣም ጥሩ ሥራ እየሰራ ነው ይሄን ማየቴ በጣም አስደስቶኛል “ ሲል ዣቪ ተናግሯል።ባርሴሎናን ሁልጊዜ እንደሚከታተል የገለፀው ዣቪ የአሁኑ ትውልድ ትልቅ ነገር ሊያሳካ እንደሚችል ገልጿል።ስለ ላሚን ያማል ያነሳው ዣቪ “ ላሚን ያማል የተለየ ተጨዋች ነው ገና 19ዓመቱ ነው "ብሏል።“ ያለ ጥርጥር አንድ ቀን ባሎን ዶር ያሸንፋል ነገርግን አሁን ለማሸነፍ ለእሱ ጥሩ አመት ሊሆን ይችላል " ሲል ጨምሮ ተናግሯል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    7,80078841Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 17:48

    “ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው ” አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን“ ያልተማረ እና ግብዝ ከሆነ አሰልጣኝ ጋር ልንጫወት ነው ” እስራኤልበ አውሮፓ ኔሽንስ ሊግ እስራኤል ከአየርላንድ ጋር ከቀናት በኋላ እንዲጫወቱ መርሐ ግብር ወጥቶላቸዋል።ይሁን እንጂ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።የአየርላንድ አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን “ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው “ ሲሉ ተናግረው ነበር።አክለውም “ አሁንም ድረስ ሩሲያ ታግዳ እስራኤል ለምን እንዳልታገደች ማብራሪያ አላገኘሁም " ብለዋል።የእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ በሰጠው ምላሽ “ የአየርላንድ አሰልጣኝ ላሳየው አለማወቅ እና ግብዝነት መድኃኒት አላገኘንም “ ብሏል።ፌዴሬሽኑ አክሎም “ አለመማርን ፤ ድድብና ኤና ግብዝነትን ከሚወክል አሰልጣኝ ጋር እንጫወታለን "ሲል ፅፏል።ዛሬ በአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ሆቴል የተገኙ ደጋፊዎች ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን እንዳያደርግ ጠይቀዋል።በተጨማሪም 160 ያህል የአየርላንድ ስፖርተኞች ጨዋታው እንዳይደረግ ፊርማ አሰባስበው አስገብተዋል።ጨዋታው እሁድ ምሽት 3:45 በሀንጋሪ እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለታል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    29,80026352292062Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 15:29изменён

    “ ይሄ የመጨረሻ አመቴ መሆኑን አላውቅም “ ሮናልዶፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሔራዊ ቡድኑ እስከመቼ እንደሚቆይ " አላውቅም " ሲል ተናገረ።“ የዛሬን ነው የምኖረው ለረጅም ጊዜ አላስብም ” ያለው ሮናልዶ “ የመጨረሻ አመቴ ነወይ ? ለሚለው ምናልባት ፤ ግን እናያለን " ብሏል።“ በአካላዊ ሁኔታዬ እና ፅናቴ ላይ የተመሰረተ ነው ፤ እውነቱን ለመናገር አላውቅም ይሄን የምለው ከልቤ ነው “ ሲል ሮናልዶ የተናገረው።አክሎም “ አሰልጣኙ እኔ ካላስፈለኩት መሄድ እችላለሁ ጊዜው ሲደርስ እኔ ራሴ አነጋግረዋለሁ ” ብሏል።“ ለቡድኑ አስተዋጽኦ እያደረግኩ እንዳልሆነ ከተሰማኝ ሻንጣዬን አንስቼ እሄዳለሁ " ሲል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተናግሯል።ሮናልዶ በቀጣይ አላማው 1,000 ግቦች ላይ መድረስ እና ኔሽን ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ መሆኑን ገልጿል።አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነገው የዌልስ ጨዋታ በቋሚነት እንደሚሰለፍ አረጋግጠዋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    41,3004181472387Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 15:26изменён

    የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?የስፔን ላሊጋ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።በዚህም መሰረት :-⏩ ኪሊያን ምባፔ⏩ ራፊና⏩ ዴቪድ⏩ ሰርጂዮ ካሜሎ እና⏩ ፌር ኒኖ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 15:24

    переслано из @wanawsportwear

    ውድድር ካለ ዋናው አለ!🔗ማህበራዊ ገጾቻችን🔗 Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube ⭐️| #WanawSportwear
    36,200видео13Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 14:20изменён

    ኤሪክሰን ከክለቡ ጋር ተለያይቷል !ዴንማርካዊው አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከዎልፍስበርግ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየቱ ተገልጿል።ኤሪክሰን ከሶስት ወራት በፊት በወዳጅነት ጨዋታ ላይ ራሱን ስቶ መውደቁ አይዘነጋም።አሁን ላይ ዎልፍስበርግ በስምምነት ተጨዋቹ እስከ 2027 ያለውን ውል ማቋረጡ ተገልጿል።ክርስቲያን ኤሪክሰን ሰኔ ወር ላይ ከገጠመው ድንገተኛ አደጋ በኋላ ሜዳ ላይ አልታየም።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    37,3001285182Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 14:15

    የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ❓በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።በዚህም መሰረት :-⏩ ማቲውስ ኩንያ⏩ ዩሪ ቴሌማንስ እና⏩ ኮቢ ማይኖ የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ❓@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    37,000218714Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    23 сент., 13:44

    ቶተንሀም ወሳኝ ተጫዋቹን በጉዳት አጣ !ስፔናዊው የቶተንሀም የመስመር ተጨዋች ፔድሮ ፖሮ የ ሀምስትሪንግ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።በዚህም ምክንያት ፔድሮ ፖሮ ለአንድ ወር ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።የ 27ዓመቱ ተጨዋች ፔድሮ ፖሮ በጉዳቱ ምክንያት ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ይታወቃል።ፔድሮ ፖሮ ቶተንሀም በሊጉ ከማንችስተር ዩናይትድ በሚያደርገው ጨዋታ የማይገኝ ይሆናል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    38,3001064544321Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 18:08изменён

    የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማን ይሆናል ?የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ሪቻርድ ሂውዝ ጋር መለያየቱ ይታወቃል።አሁን ላይ ሊቨርፑል በቀጣይ ማንን በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሊሾም እንደሚችል ታውቋል።የ " FSG " የቴክኒክ ዳይሬክተር የሆኑት ጁሊያን ዋርድ ቀጣዩ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን ሊሾሙ መሆኑ ተገልጿል።ሀላፊው ከዚህ በፊት በ 2022/23 የውድድር ዘመን በተመሳሳይ ሀላፊነት አገልግለው ነበር።ጁሊያን ዋርድ በ 2012 ከማንችስተር ሲቲ ለቀው ነበር ሊቨርፑልን የተቀላቀሉት።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    20,60010513543Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 16:43изменён

    የኢትዮጵያ እና ሴኔጋልን ጨዋታ ማን ይመራል ?ኢትዮጵያ ከሴኔጋል ጋር የምታደርገውን የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።በባሕር ዳር ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ካሜሮናዊው ዳኛ ዊሊ ሴቴፋን ንጋህ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።ዋና ዳኛው ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ቡድን ከሞሮኮ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መርተው ነበር።ጨዋታው ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ቀን 10:00 ሰዓት በባሕር ዳር ስታዲየም ይደረጋል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከሱዳን የምታደርገውን ጨዋታ ላይቤሪያዊው ዳኛ ዋሽንግተን ን ዶሎ እንዲመሩ ተመርጠዋል።ጨዋታው አርብ ምሽት 1:00 ሰዓት በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም ይደረጋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    31,500991671Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 15:57изменён

    “ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም ዳኛው አንዳች ስህተት አልሰራም “ ዣቪየር ቴባስ“ ቴባስ ተቋሙን ተጠቅሞ ክለባችንን እያጠቃ ነው ” ሪያል ማድሪድሪያል ማድሪድ የላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ስለ ክለቡ ለሰጡት አስተያየት ምላሽ ሰጥቷል።ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ከደርቢው በኋላ ዳኞችን ተጠያቂ ማድረጉን ተችተው ነበር።“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም “ ያሉት ቴባስ ዳኞች ላይ ጫና ማሳደር ነው አላማቸው ብለዋል።“ ሮሜሮ በቀይ መውጣት እንዳልነበረበት አምናለሁ ሁይሰን በቀይ መውጣቱ ትክክል ነው “ ሲሉ ነው የተናገሩት።ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ “ ቴባስ ማድሪድን ለማጥቃት ተቋሙን መጠቀሙ ተቀባይነት የለውም "ብሏል።አክሎም “ ቴባስ የሊጉን ገፅታ ማበላሸቱን ቀጥሎበታል ፣ የላሊጋ ፕሬዝዳንት የውድድሩ ባለቤት አይደለም "ሲል ገልጿል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    34,70018041275Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 14:48

    የሲቲ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።በዚህም መሰረት :-- ኤርሊንግ ሀላንድ- ማርክ ጉሂ እና- ኤሊዮት አንደርሰን በእጩነት መቅረብ ችለዋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    35,3001091073Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 14:47

    переслано из @wanawsportwear

    3ኛው_ዙር_ዋናው_የዶክተር_ብሩክ አማረ መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር በአርባምንጭ ከተማ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።ከሶስት ዓመት በፊት መስከረም 10 ቀን በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ዶክተር ብሩክ አማረን ለማስታውስና መልካም ስራዎቹን ለመዘከር ቤተሰቡ ከዋናው ስፖርት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "ዋናው የዶ/ር ብሩክ አማረ ሦስተኛ ዓመት መታሰቢያ የእግርኳስ ውድድር" ከመስከረም 8 እስከ 10 በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።✍️ ለአሸናፊዎች አጓጊ ሽልማቶች የሚበረከቱ ሲሆን፤ በየአንዳንዱ ጨዋታም የላቀ ብቃት ላሳዩ ተጫዋቾች የ Man of the Match ስጦታ ተዘጋጅቷል! 📍ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ። ⭐️ዋናው ወደፊት🔣🔣🔣
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 13:28изменён

    የቶተንሀም ስፖንሰር ውሉን አቋረጠ !ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ስፖንሰሩን አጥቷል።የቶተንሀም ይፋዊ የፈርኒቸር ስፖንሰር ሲዲዝ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡ ተገልጿል።ተቋሙ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ስምምነት የውል ማቋረጫ አንቀጽ ተጠቅሞ እንደሚያቋርጥ ተነግሯል።ተቋሙ ውሉን የሚያቋርጠው ቶተንሀም ደካማ የውድድር ዘመን ጅማሮ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ቶተንሀም በሊጉ በሁለት ነጥብ ሃያኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    38,9002666922744Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 13:16изменён

    “ የጆታ ህልፈት ለእግርኳስ ያለንን ፍቅር አሳጥቶን ነበር ” አንዲ ሮበርትሰንየቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች አንዲ ሮበርትሰን የዲያጎ ጆታ ህልፈት ቡድኑ ላይ የስነ ልቦና ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።“ ጆታ ለእኛ እግርኳስ ተጨዋች ብቻ አልነበረም ” ያለው ሮበርትሰን “ እሱ ጓደኛችን ፤ መልበሻ ቤት ውስጥ የቅርባችን ሰው ነበር "ብሏል።“ እጅግ በጣም የሚያም እና ልብ የሚሰብር ጊዜ ነበር ያሳለፍነው “ ሲል ሮበርትሰን ተናግሯል።አክሎም “ በወቅቱ የእግርኳስ ፍቅራችንን አጥተናል ፣ ቤተሰቡ እና ልጆቹ እንደዛ ሲጎዱ ስናይ ስለጨዋታ ማሰብ አልቻልንም "ብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    38,9002668612531Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 11:56

    አርቴታ ውላቸውን ለማራዘም ተስማሙ !የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ከስምምነት እንደደረሱ ቢቢሲ ዘግቧል።ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ያላቸው ኮንትራት በውድድር አመቱ መጨረሻ ያበቃ ነበር።አዲሱ ውል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ከአስር አመት በላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል ተብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    42,60039591312164Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 10:35изменён

    ቫልቬርዴ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፌዴ ቫልቬርዴ በማድሪድ ደርቢ የቁርጭምጭሚት ጉዳት አጋጥሞታል።ተጨዋቹ " ግሬድ ሶስት " የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ ይፋ አድርጓል።በዚህም ምክንያት ቫልቬርዴ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።ሪያል ማድሪድ ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ ከቪያሪያል ጋር የሊግ ጨዋታውን ያደርጋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    45,4001005710611Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    22 сент., 08:43изменён

    “ ባሎን ዶር ካሸነፍኩ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ አበረክታለሁ ” ኪሊያን ምባፔፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ባሎን ዶር ካሸነፈ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደሚያደርግ ገልጿል።የካሜሮን የዘረ ሀረግ ያለው ምባፔ " ፈረንሳይ ብወለድም አስተዳደጌ በአፍሪካ ባህል የተቃኘ ነው "ሲል ገልጿል።“ ወደ አፍሪካ ስሄድ ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ያደርግልኛል ከህዝቡ ፍቅር ይሰማኛል “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።ለአፍሪካ የባሎን ዶር ድምፅ ሰጪዎች መልዕክት ያስተላለፈው ምባፔ “ በመጀመሪያ እስካሁን ለሰጡኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ "ብሏል።አክሎም " አፍሪካን ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ እግሬ እዛ በሄደ ቁጥር የመወደድ ስሜት ይሰማኛል " ብሏል።ከአፍሪካ የተገኘ እንደመሆኑ ሰዎች ከባሎን ዶር ጋር ስሙን ሲጠሩ እንደሚደሰት ኪሊያን ምባፔ ተናግሯል።“ የባሎን ዶር ሽልማቱን አሸንፌ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደማደርግ ተስፋ አደርጋለሁ ” ኪሊያን ምባፔ@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    50,8006134103633105Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    21 сент., 21:29изменён

    ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ጥሪ ቀርቦለታል ! አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አርጀንቲና ለተጨዋቾች ጥሪ ስታቀርብ ሊዮኔል ሜሲን በስብስቧ አካታለች። ሊዮኔል ሜሲ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ጨዋታውን እንዲያደርግ እንደተዘጋጀለት ተገልጿል። አርጀንቲና ከሳምንታት በኋላ ከቤኒን በምታደርገው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በይፋ ይሸኛል ተብሎ
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    57,2008545630301211Открыть в Telegram
  • TIKVAH-SPORT

    21 сент., 19:47изменён

    ዎት ዌግሆርስት ለምን መነጋገሪያ ሆነ ?ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ዎት ዌግሆርስት ከጨዋታ በፊት እጆቹን ተጠቅሞ ያልተለመደ ነገር ሲያደርግ ነበር።ዌግሆርስት በሰዓቱ ባደረገው ድርጊት ደጋፊዎች የቀለዱበት ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያውም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።ይሁን እንጂ ዎት ዌግሆርስት ያደረገው አእምሮውን ይበልጥ ዝግጁ ለማድረግ የነርቭ ልምምድ ነበር።ተጨዋቹ ከጨዋታው በፊት አእምሮውን ለማንቃት የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንደተጠቀመ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።በኔዘርላንድ እውቅና ያላቸው የነርቭ ሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር ኤሪክ ሼርደር ስለ ሁነቱ ሲያስረዱ “ እጅን ለማንቀሳቀስ የአንጎላችንን ብዙውን ክፍል ይፈልጋል “ ይላሉ።“ እጅ ሲንቀሳቀስ አብዛኛው የአንጎላችን ክፍል በቅንጅት ይሰራል “ ያሉት ባለሙያው “ ስለዚህ ያንን ሲያደርግ ብዙውን ክፍል ያነቃቃል " ብለዋል።“ በመሰረቱ ያንን ማድረግ ስርዓቱን እንደማዘጋጀት ነው አእምሮን እንደመክፈት ነው "በማለት ተናግረዋል።ዎት ዌግሆርስት ወደ ጨዋታው ከገባ በኋላ ወሳኝ የአቻነት ግብ በማስቆጠር ቡድኑ ቲዌንቴ ፒኤስቪን እንዲያሸንፍ ረድቷል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
    Иллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORTИллюстрация к посту канала TIKVAH-SPORT
    56,600349362412Открыть в Telegram