gram news
Аватар канала ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

@wahidcom

ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

ПроектыELРелигия

62,400подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    23 сент., 04:49изменён

    አሥ ሠላም ዐለይኩም ያ ጀምዓህ! በነገራችን ላይ ድብቅ ቃለ ጉባኤ"Agenda" ተሰቷቸው በሙሥሊም ማሊያ ለኦርቶዶክስ እና ለፕሮቴስታንት የሚጫወቱ ሁለት በሠለምቴ ስም ሠርጎ ገቦች አሉ፥ እነዚያን ሰዎች ስም ሳንጠቅስ በድርጊታቸው ሥራቸው አደባባይ ላይ እየተገለጠ ነው። በቅርቡ ኢንሻ አሏህ ጭንብላቸው ይገለጣል። ንግግር እና እግር ሲለያይ ጠርጥሩ! ንግግሩ ሙሥሊም እግሩ ካፊር ቤት የሚሄድን ጠርጥሩ! መሬት ላይ መሥጂድ ላይ ያላችሁ ሰዎች መሥጂዳችሁን ጠብቁ! እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን በዓይነ ቁራኛ ተከታትላችሁ ማኅበረሰባችሁን አንቁ።
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    13 сент., 13:23изменён

    ተቀባዩ ፍጡርበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَአንዱ አምላክ ሕይወትን፣ እስትንፋስን እና ሁሉንም ነገር ለሁሉ "ይሰጣልና፦ የሐዋርያት ሥራ 17፥25 እርሱም ሕይወትን፣ እስትንፋስን እና ሁሉንም ለሁሉ "ይሰጣልና። οὐδὲ ὑπὸ χειρῶν ἀνθρωπίνων θεραπεύεται προσδεόμενός τινος, αὐτὸς διδοὺς πᾶσι ζωὴν καὶ πνοὴν καὶ τὰ πάντα·አንዱ አምላክ ለኢየሱስ ሕይወትን ሰጥቶታል፦ ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ እንዲኖር ሕይወት ሰጥቶታልና። ὥσπερ γὰρ ὁ Πατὴρ ἔχει ζωὴν ἐν ἑαυτῷ, οὕτως καὶ τῷ Υἱῷ ἔδωκεν ζωὴν ἔχειν ἐν ἑαυτῷ."ሕይወትን ሰጥቶታልና" የሚለው ይሰመርበት! "ኤዶኬን ዞኤን" ἔδωκεν ζωὴν ማለት "ሕይወት ሰጠው" ማለት ነው። ወልድ በራሱ የራሱ ማንነት እንዲኖረው አብ ለወልድ የሰጠው ሕይወት ነው፥ "አብ ሕይወት አለው" ማለት "አብ ህልውና አለው" ማለት ከሆነ "ወልድ ሕይወት እንዲኖረው" ማለት "ወልድ ህልውና እንዲኖረው" ማለት ነው። እዚህ ዐውድ ላይ "ሕይወት" የተባለው የራስ ሃልዎት"Self existence" ነው፥ እያንዳንዱ ማንኛውም ማንነት የራሱ ሃልዎት አለው። ኢየሱስ በባዶነት የተቀደመ፣ ሕይወት አልባ የነበረ፣
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    4 сент., 08:16изменён

    መለኮታዊ ክፍልፍልነትበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡112፥1 በል «እርሱ አሏህ አንድ ነው»። قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ"ሙረከብ" مُرَكَّب ማለት "ውቅር" "መነጣጠል" "ክፍልፍ"Complex" ማለት ሲሆን "ተርኪብ" تَرْكِيب ማለት "ክፍልፍልነት"Complexity" ማለት ነው፥ በኢሥላም ሥነ መለኮት "ተርኪብ ኢላሂይ" تَرْكِيب إِلٰهِيّ ማለት "መለኮታዊ ክፍልፍልነት"Divine Complexity" ማለት ነው። ተርኪብ ኢላሂይ በኢሥላም ኢንካር የተደረገ እሳቤ ነው፥ "ኢንካር" إِنْكَار ማለት "ውግዝ"Anathema" ማለት ሲሆን አሏህን የአካል ውቅር፣ ክፍልፍል እና ድምር አርጎ መውሰድ "ተርኪብ ኢላሂይ" ነው።በክርስትና ሥነ መለኮት "መለኮታዊ ነጠላነት" የሚባል እሳቤ ቢኖረውም "መለኮታዊ ነጠላ" የሚባለው አብ ነው፥ አምላክን በአካል ሦስት ማድረግ በራሱ መለኮታዊ ክፍልፍልነት ሲሆን ይህ መከፋፈል በቀጰዶቅያ ሥነ መለኮት"Cappadocian Theology" ጎልቶ ታይቷል። ለምሳሌ፦ አንደኛው የቀጰዶቅያ አበው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ የአካላት መከፋፈል እንዳለ ነግሮናል፦ "ሦስቱ በትክክል ሲከፈሉ ክፍፍሉ የአካላት እንጂ የአምላክነት አይደለም"። Orations (Gregory Nazianzen) Oration 37 Number XXII(22)የአካል መከፋፈል ካለ ይህ አስተምህሮት ነጠላነት ሳይሆን ክፍልፍልነት ነው። "ሚያ ኡሲያ ትሬይስ ሒፓስታቴይስ" μία οὐσία, τρεῖς ὑποστάσεις ማለት "አንድ ባሕርይ ሦስት አካላት" ማለት ነው፥
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    31 авг., 09:32изменён

    አሏህ አምሳያ የለውምበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَአምላካችን አሏህ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነው፥ ለእርሱ ሞክሼ የለውም፦ 19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና አምልከው! እርሱን በአምልኮቱ ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا"ሠሚይ" سَمِيّ ማለት "ሞክሼ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ከፍጥረት የሚመስለው ምንም ነገር የለም፦ 42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُእዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስሊ" مِثْلِ የሚለው የግሥ መደብ ነው፥ "ሚስል" مِثْل ወይም "ሚሳል" مِثَال የስም መደብ ሲሆን "አምሳያ" "ምሳሌ" ማለት ነው። ለአሏህ ምንም ዓይነት አምሳል የለውም፥ ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም፦ 114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ"ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ቢጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    28 авг., 10:45изменён

    ቡጢበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።22፥11 ከሰዎች በጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን የሚያመልክ ሰው አለ። وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ"ቡጢ"Boxing" ማለት "አምስት ጣቶችን በማጠፍ እና በመኮርመት ፊት ላይ ድብደባ ማሳረፍ" ማለት ነው፥ ቡጢ ከሥነ ጥበብ"Art" ቢሆንም ሥረ መሠረቱ ግን ዐረማዊ ልማድ"Pagan Custom" ነው። የሮማዊ የትግል፣ የድብድብ፣ ጦርነት አምላክ "ማርስ"Mārs" ሲባል የእርሱ ሥነ ጥበብ "የማርስ ሥነ ጥበብ"Martial art" ተብሎ ይታወቃል፥ ይህ የዐረማዊ ልማድ ከዛ ጀምሮ ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሕይወት ውስጥ እንደ ጤናማ ስፓርት መታየቱ ማፈር እና መክሰር ነው። ውጪው የትጉኅ እና የታታሪ ሰው መገለጫ ቢመስልም ውስጡ ግን መብረድ እና መንደድ ያለበት ስሜታዊ ጉዳይ ነው፥ በዲኑል ኢሥላም ሰውን በቡጢ ፊቱን መምታት እና መደብደብ ሐራም ነው፦ ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 49 ሐዲስ 41 ቁጥር 2559 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ አንዱ በሚጋደልበት ጊዜ ፊትን ከመምታት ይቆጠብ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِذَا قَاتَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَجْتَنِبِ الْوَجْهَ ‏"‌‏.‏ይህ በሆነበት አግባብ ቡጢን ከዲን ጋር አያይዞ ጮቤ መርገጥ ምን ያህል ወጥ የረገረ ነገር መሆኑ ከወዲሁ የታወቀ ነው፥ ፊትን መቶ እና ደብድቦ በሚያስሸልም
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    27 авг., 11:12изменён

    16ኛው ክፍለ ዘመን በፕሮቴስንታንት አውራ አስረገጥ ተሓድሶ"Magisterial Reformation" የተጀመረው ተቃውሞ አምስት ብቻዎች"Five solae" አዋቅሯል፥ እነዚህ አምስት ብቻዎች የሚባሉት፦ 1ኛ. መጽሐፍ ብቻ"Sola Scriptura" 2ኛ. እምነት ብቻ"Sola Fide" 3ኛ. ጸጋ ብቻ"Sola Gratia" 4ኛ. ክርስቶስ ብቻ"Solus Christus" 5ኛ. ክብር ለአምላክ ብቻ"Soli Deo Gloria" ናቸው።"ክብር ለአምላክ ብቻ"Soli Deo Gloria" በሚል ማዕቀፍ ውስጥ ከአምላክ ውጪ ለሌላ ነገር ስግደት ሆነ ክብር ክልክል መሆን ይካተታል፥ ነገር ግን የቲክ ቶክ ፕሮቴስታንት የሙሥሊም ሙግት ሲያንቆራጥጧቸው ለማምለጥ "ለዳዊት የአክብሮት ስግደት ተሰግዶለታል" ብለው አረፉት። ቆይ "የአክብሮት ስግደት" የሚለው ትምህርታችሁ በአንቀጸ እምነታችሁ ከሌለ ከሙግት ለማምለጥ ለምን መዋሸት አስፈለገ?✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    26 авг., 13:09

    የበላይነት ስሜት"superiority complex" እና የበታችነት ስሜት"inferiority complex" ሁለቱም በሽታዎች ናቸውና የሥነ ልቡና ህክምና ያስፈልጋቸዋል። ላዕላይ በራስ መተማመን"over confidence" ለንቀት፣ ለትዕቢት እና ለውድቀት ይዳርጋል፥ ታኅታይ በራስ መተማመን"under confidence" ለባዶነት፣ ለብቸኝነት እና ለጥፋተኝነት ስሜት ይዳርጋል። አምላካችን አሏህ እርሱ ባስቀመጠልን አኽላቅ እና አደብ የምንሰተር ያርገን!✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    24 авг., 17:07изменён

    ይህ የቀደምት ሠለፎች ዐቂዳህ ሆኖ ሳለ የራሳቸው ሥነ መለኮት የማያውቁ የክርስትና ዘለሰኛ ሚሽነሪዎች አምላክ "ፊት" እንዳለው እና አማንያን በፍርድ ቀን ፊቱን እንደሚያዩ በቅጡ አልተረዱም፦ ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ “ሰው አይቶኝ አይድንምና "ፊቴን" ማየት አይቻልህም፡” አለ። וַיֹּאמֶר, לֹא תוּכַל לִרְאֹת אֶת-פָּנָי: כִּי לֹא-יִרְאַנִי הָאָדָם, וָחָי.እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓኒም" פָנִים ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት ደግሞ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ነው፦ ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ “ሰው አይቶኝ አይድንምና "ፊቴን" ማየት አይቻልህም፡” አለ። καὶ εἶπεν· οὐ δυνήσῃ ἰδεῖν τὸ πρόσωπόν μου· οὐ γὰρ μὴ ἴδῃ ἄνθρωπος τὸ πρόσωπόν μου καὶ ζήσεται.አምላክ "ፊቴ" እያለ "ፊት የለህም" ብሎ ከእርሱ ጋር ሙግት መግጠም ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? የአምላክ ፊት ማንም በዚህ ዓለም ማየት አይችልም። አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ሰለሚኖር እርሱን መቼም ቢሆን ከቶ አንድ ስንኳ ያየ የለም፦ 1ኛ ዮሐንስ 4፥12 አምላክን ማንም ከቶ አላየውም። Θεὸν οὐδεὶς πώποτε τεθέαται· ዮሐንስ 1፥18 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው አንድ ስንኳ የለም። Θεὸν οὐδεὶς ἑώρακεν πώποτε· 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    24 авг., 17:07изменён

    የአምላክ ፊትበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ"ሲፋህ" صِفَة ማለት "ባሕሪ"Attribute" ማለት ነው፥ የአሏህ ሲፋህ "ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة እና "ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ተብሎ ለሁለት ይመደባል። "ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة ማለት "የምንነት ባሕሪ"Passive Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ሕያውነት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ጥበብ፣ ኃይል፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር፣ ፊት ወዘተ "ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة ነው። "ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ማለት "የድርጊት ባሕሪ"Active Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ፈጣሪነት፣ ፍርድ፣ ይቅርባይነት፣ ከዐርሽ በላይ የበላይነት ወዘተ "ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ነው።"ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة እራሱ "ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة እና "ሲፋህ ኸበሪያህ" صِفَة خَبَرِيَّة ተብሎ ለሁለት ይመደባል። "ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة ማለት "ትርጉማዊ ባሕሪ"Semantic Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ሕያውነት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ጥበብ፣ ኃይል ወዘተ በዐቅል የምንረዳቸው "ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة ወይም "ሲፋህ ዐቅሊያህ" صِفَة عَقْلِيَّة ነው። "ሲፋህ ኸበሪያህ" صِفَة خَبَرِيَّة ማለት "አዋጃዊ ባሕሪ"Informative
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    20 авг., 08:44изменён

    የእንጨት አምልኮበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አሏህን እንጂ ሌላን አታምልኩ! እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ»። أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌበኦርቶዶክስ እና በካቶሊክ ክርስትና "ዕፀ መስቀል" የሚባል ስግደት እና አምልኮ የሚቀበል ግዑዝ ነገር አለ፥ "ዕፅ" ማለት "እንጨት" ማለት ሲሆን "ዕፀ መስቀል" ማለት "የእንጨት መስቀል" ማለት ነው። በግሪክ ኮይኔ "ስታውሮስ ክይሎን" σταυρός ξύλον ሲባል ይህ የእንጨት መስቀል የማይሰማ እና የማይለማ እንዲሁ የማይናገር እና የማይጋገር ግዑዝ ነገር ሆኖ ሳለ በኦርቶዶክስ ይሰገድለታል፦ የዘወትር ፀሎት ቁጥር 8 "ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”-ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው"ለእንጨት መስቀል መስገድ አግባብ ነውን? ዘርዓ ያዕቆብ ከደረሳቸው መጻሕፍት አንዱ "መስተብቁዕ ዘመስቀል" ነው፥ "መስተብቁዕ" ማለት "ልመና" "ጸሎት" ማለት ሲሆን "መስተብቁዕ ዘመስቀል" ማለት "የመስቀል ልመና" ማለት ነው። መስተብቁዕ ዘመስቀል ላይ መስቀል እና ማርያም ከፈጣሪ ጋር ተካክለው ምስጋና እንደሚቀርብላቸው ይናገራል፦ መስተብቁዕ ዘመስቀል ቁጥር 8 "ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተዐረዩ በክብሮሙ""ለእነዚህ ሁለት ፍጥረታት የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል፥ በክብር ተካክለዋልና""ሁለቱ" የተባሉት "መስቀል እና ማርያም" ሲሆኑ እነዚህ ሁለት ፍጡራን ከፈጣሪ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    16 авг., 12:36изменён

    ፍዝዝ፣ ድንግዝ እና ድንዝዝ ብላችሁ መውቀሱን እና መክሰሱን ትታችሁ በእናንተ መጽሐፍ ያለውን ይህንን ነጥብ ተመልከቱ! አምላክ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል፦ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥4 እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ "ይፈልጋል"። ὃς πάντας ἀνθρώπους θέλει σωθῆναι καὶ εἰς ἐπίγνωσιν ἀληθείας ἐλθεῖν.በአዲሱ መደበኛ ትርጉም "ይፈልጋል" ለሚለው የገባው ቃል "ቴሌይ" θέλει ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ቴሎ" θέλω ነው፥ "ቴሌማ" θέλημά ማለት "ፈቃድ"will" ማለት ሲሆን ቴሌማ እራሱ "ቴሌማ አፖዶሲስ" θέλημά ἀπόδοσις እና "ቴሌማ ፕሮታሲስ" θέλημά πρότᾰσῐς ተብሎ ለሁለት ይከፈላል። "ቴሌማ አፖዶሲስ" θέλημά ἀπόδοσις ማለት "ቀዳማይ ፈቃድ" ማለት ሲሆን ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የአምላክ ቀዳማይ ፈቃድ ነው፥ "ቴሌማ ፕሮታሲስ" θέλημά πρότᾰσῐς ማለት "ደኃራይ ፈቃድ" ማለት ሲሆን ሰዎች ካመፁ ለገሃነም መሆናቸው የአምላክ ደኃራይ ፈቃድ ነው። ዮሐንስ ዘደማስቆ"John of Damascus" ይህንን ነጥብ አፋፍቶ እና አዳብሮ አስቀምጦታል፦ "እንዲሁም የአምላክ የመጀመሪያ ፍላጎት ሁሉም ሰው እንዲድን እና ወደ መንግሥቱ እንዲመጣ መሆኑን ማስታወስ አለብን! 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥4 እርሱ ቸር አምላክ ስለሆነ ከቸርነቱ እንድንካፈል እንጂ ለቅጣት አላዘጋጀንም፥ ነገር ግን እርሱ ፍትሓዊ አምላክ ስለሆነ ኃጢአተኞች ቅጣት እንዲደርስባቸው ፈቃዱ ነው።
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    16 авг., 12:34изменён

    የአሏህ ፈቃድበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።81፥29 የዓለማቱ ጌታ አሏህ ካልፈቀደ አትፈቅዱም፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ"መሺኣህ" مَشِئَة የሚለው ቃል "ሻአ" شَاءَ ማለትም "ፈቀደ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ፈቃድ"Will" ማለት ነው፥ የአሏህ ፈቃድ "መሺኣህ ሙቀደማህ" مَشِئَة مُقَدِّمَة እና "መሺኣህ ነቲጃህ" مَشِئَة نَتِيجَة ተብሎ ለሁለት ይከፈላል። ፨ "ሙቀደማህ" مُقَدِّمَة ማለት "ቀዳማይ"Antecedent" ማለት ሲሆን "መሺኣህ ሙቀደማህ" مَشِئَة مُقَدِّمَة ማለት "ቀደማይ ፈቃድ"Antecedent Will" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም፡፡ ለባሪያዎቹ ከህደትን አይወድም፦ 3፥108 አሏህ ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም፡፡ وَمَا اللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِّلْعَالَمِينَ 23፥31 አሏህ ለባሮቹ በደልን የሚሻ አይደለም፡፡ وَمَا اللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِّلْعِبَادِሰዎች ቢክዱ አሏህ ከከሓዲዎች የተብቃቃ ነው፥ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም። ብናምን ግን እርሱን ይወድልናል፦ 39፥7 ብትክዱ አሏህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፥ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም። ብታመሰግኑ እርሱን ይወድላችኋል፡፡ إِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمْ ۖ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ ۖ وَإِن
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    15 авг., 10:16изменён

    ኢየሱስ መንገድ ነው!በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُኢየሱስ ወደ ጌታ አምላክ የሚያደርስ መንገድ ስለሆነ ለፊልጶስ፦ "የእውነት እና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ" አለው፦ ዮሐንስ 14፥6 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ "የእውነት እና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፥ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም"።(የ 2000 ዕትም 80 አሓዱ)ግዕዙም በተመሳሳይ፦ "አነ ውእቱ ፍኖተ ጽድቅ ወሕይወት" እንደሚለው ተመልከት! "መንገድ" ማለት በመነሻ እና በመዳረሻ መካከል ያለ "መካከለኛ"Mediator" ነው፥ ካለ መካከለኛ መልእክተኛ በኩል ወደ ጌታ አምላክ መድረስ አይቻልም፦ 1 ጢሞቴዎስ 1፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው "መካከለኛው" ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,ይህ ጥቅስ በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ "መካከለኛ" የተባለው ከአንዱ አምላክ ውጪ "ሰው" እንደሆነ ይናገራል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "መካከለኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ሜሲተስ" μεσίτης ነው። ሙሴ ከኢየሱስ መላክ በፊት በብሉይ ኪዳን በአምላክ እና በሕዝቡ መካከል ሆኖ መልእክት ሲያስተላልፍ የነበረ መካከለኛ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    12 авг., 11:08изменён

    የአምልኮ መገዛትበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ"የባሕርይ መገዛዛት"Ontological subordination" ማለት በባሕርይ የማይመሳሰሉ ሆነው ነገር ግን በባሕርይ አንዱ ከሌላው ስለሚበልጥ በመካከላቸው ገዥ እና ተገዥ አለ። ለምሳሌ፦ ሰው እና እንስሳ በምንነት የተለያዩ "ባሕርይ"Essence" ስላላቸው ሰው ገዥ እንስሳ ተገዥ ነው፦ መዝሙር 8፥6 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት። πάντα ὑπέταξας ὑποκάτω τῶν ποδῶν αὐτοῦ,እዚህ አንቀጽ ላይ ለመገዛት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ሲሆን ገዥው ሰው ተገዥው በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ ነው፦ ዘፍጥረት 1፥28 የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ "ግዙአቸው"። መዝሙር 8፥8 በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።እንስሳ ሰውን የሚገዛው የባሕርይ ቢሆንም የአክብሮት መገዛት እንጂ የአምልኮ መገዛት አይደለም። ነገር ግን ኢየሱስ ፍጡር ስለሆነ ለአምላክ የሚገዛበትን ለማሳየት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ነው፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    10 авг., 14:16

    በባይብል የገደለ ብቻ ሳይሆን አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደላል፦ ዘሌዋውያን 27፥17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል። ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።ኢየሱስ ሲመጣ ደግሞ ሕጉ ጠብቆ እና አጥብቆ የሞት ፍርድ የሚገባው የገደለ ብቻ ሳይሆን በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ የሞት ፍርድ እንደሚገባው አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦ ማቴዎስ 5፥21-22 ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።"የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት በዘሌዋውያን 27፥17 "ፈጽሞ ይገደል" የሚለው ከሆነ "በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት "ፈጽሞ ይገደላል" ማለት ነው። እንደውም ኢየሱስ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ፦ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" ብሏል፦ ራእይ 13፥10 "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"።በተጨማሪ ሬካብ እና ወንድሙ በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ገብተው ኢያቡስቴን ገድለዉት እራሱን ቆረጡት፥ ዳዊትም ሬካብን እና ወንድሙ በዓናን አስገድሎ እጃቸውን እና እግራቸውን እንዲቆረጥ አድርጓል፦ 2 ሳሙኤል 4፥7 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት። ሳሙኤል 4፥12 ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፤ እጃቸውን እና እግራቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው።ኢዮአብ እና ሠራዊቱ በአሞን ከከተማ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    10 авг., 14:16

    የነቢያችን"ﷺ" ቅጣትበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا"ቂሷስ" قِصَاص የሚለው ቃል "ቋሶ" قَاصَّ ማለትም "አመሳሰለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማመሳሰል" ማለት ነው፦ 2፥179 ባለ አእምሮዎች ሆይ! ለእናንተም በማመሳሰል ሕግ ውስጥ ሕይወት አለላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ፡፡ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَእዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ ልብ አድርግ! ሰው ጤናማ ሕይወት ይኖር ዘንድ አምላካችን አሏህ ቂሷስን ደንግጓል፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦ 5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም "ማመሳሰል" አለባቸው» ማለትን ጻፍን፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌአሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    8 авг., 09:59изменён

    ገድልበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።2፥193 ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ "ተጋደሉዋቸው"። وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ"ገድል" የሚለው የግዕዝ ቃል "ተጋደለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ውጊያ" "ትግል" "ፍልሚያ" "መዋጋት" "መጋደል" "ጦርነት" ማለት ነው፦ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥18 በእርሱ መልካም "ጦርነት" ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ።እዚህ አንቀጽ ላይ "ጦርነት"War" ለሚለው በግዕዙ የገባው ቃል "ገድል" ሲሆን የግዕዙ መጽሐፍ "በከመ ተነብዮ ዘላዕሌከ ከመ ትጽናዕ በኵሉ "ገድል" ሠናይ" ይለዋል። ለቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ከጥንት ጀምሮ የተሰጠ ሃይማኖት አንድ ሃይማኖት ሲሆን ለቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ስለ ተሰጠ ሃይማኖት መጋደል ይገባል፦ ይሁዳ 1፥3 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት "እንድትጋደሉ" እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።ከጥንት የነበሩት ነቢያት በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ፦ ዕብራውያን 11፥34 በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።"ኢትዮጽያዊ ቄርሎስ" በሚል ማዕረግ የሚጠራው የሥነ መለኮት ምሁር አቦ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሃይማኖትን በካዱት ሰዎች ላይ ያለው ብይን በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የሞት ፍርድ እንደሆነ ተናግሯል፦ መጽሐፈ ምሥጢር 2፥28 "እነሆ ሃይማኖትን በካዱት ላይ በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የሞት ትእዛዝ
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    5 авг., 20:12

    ምሥጢረ ትዳርይህ ወንድ ልጅ አንድ ሚስት አለው፥ ያቺ ሚስቱ በአካል አራት ናቸው። አራቱ ሴቶች በአካል፣ በስም እና በግብር አራት ሲሆኑ በሚስትነት ግን አንድ ናቸው፥ አራቱም ሴቶች ሚስት የሚለውን ቃል ይጋራሉ። ኸዲጃ ሚስት ናት፣ ዘይነብ ሚስት ናት፣ ሰሚራህ ሚስት ናት፣ አሚራህ ሚስት ናት። ነገር ግን አራቱ አካላት አንድን ሚስትነት ስለሚጋሩ ለወንድ አንድ ሚስት ናቸው። ስለዚህ አንድ ወንድ አራት ሴቶች ሲያገባ ሚስቱ ግን አንዲት ናት።ይህ "ምሥጢረ ትዳር" ካልተገለጸልህ አይገባህም።
    Иллюстрация к посту канала ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"Иллюстрация к посту канала ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    28 июл., 11:48изменён

    ኢሳይያስ 7፥14 ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት"LXX" ላይ "ወጣት ሴት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓርቴኖስ" παρθένος ሲሆን በትርጉም ደረጃ "ድንግል" ብቻ ሳይሆን "ወጣት ሴት" ማለትም ነው፦ ዘፍጥረት 24፥43 "እነሆ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም "ቆንጆ"፦ "ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ" ስላት። ἰδοὺ ἐγὼ ἐφέστηκα ἐπὶ τῆς πηγῆς τοῦ ὕδατος, καὶ αἱ θυγατέρες τῶν ἀνθρώπων τῆς πόλεως ἐκπορεύονται ἀντλῆσαι ὕδωρ, καὶ ἔσται ἡ παρθένος, ᾗ ἂν ἐγὼ εἴπω, πότισόν με ἐκ τῆς ὑδρίας σου μικρὸν ὕδωρ, ዘፍጥረት 34፥3 ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፥ "ብላቴናይቱንም" ወደዳት፥ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት። καὶ προσέσχε τῇ ψυχῇ Δείνας τῆς θυγατρὸς ᾿Ιακὼβ καὶ ἠγάπησε τὴν παρθένον καὶ ἐλάλησε κατὰ τὴν διάνοιαν τῆς παρθένου αὐτῇ.እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቆንጆ" "ብላቴናይት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓርቴኖስ" παρθένος ሲሆን ሰባው ሊቃናት "ወጣት ሴት" የሚለውን አስበው እንጂ "ድንግል" የሚለው አስበው ስላልሆነ አኪላስ፣ ቴዎቶዶስ እና ሲማቲከስ የተባሉ ጥንታዊ የግሪክ መተርጉማን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ የኢሳይያስ 7፥14 ላይ ያለውን አንቀጽ ሲተረጉሙ "ኔአኒደስ" νεάνιδες ማለትም "ኮረዳ" ብለው ግልጽ እና የማያሻማ ቃል አስቀምጠውታል። ግሪክ ሰፕቱአጀንት የትርጉም
  • ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

    28 июл., 11:44изменён

    ድንግል ማርያምበአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌበዕብራይስጥ "በቱላህ" בְּתוּלָה ማለት "ድንግል" ማለት ነው፥ በታናኽ "በቱላህ" בְּתוּלָה በነጠላ 32 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ወንድ የማያውቃት ድንግል ሴት ናት፦ ዘፍጥረት 24፥16 ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት "ድንግል" ነበረች። וְהַנַּעֲרָ֗ טֹבַ֤ת מַרְאֶה֙ מְאֹ֔ד בְּתוּלָ֕ה וְאִ֖ישׁ לֹ֣א יְדָעָ֑הּእዚህ አንቀጽ ላይ "ድንግል" ለሚለው የገባው ቃል "በቱላህ" בְּתוּלָה ነው፥ ይህቺ ሴት ርብቃ ስትሆን እርሷ ድንግል ብቻ ሳትሆን ቆንጆ ወጣት ሴት ነበረች፦ ዘፍጥረት 24፥43 ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም "ቆንጆ" ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ። וְהָיָ֤ה הָֽעַלְמָה֙ הַיֹּצֵ֣את לִשְׁאֹ֔ב וְאָמַרְתִּ֣י אֵלֶ֔יהָ הַשְׁקִֽינִי־נָ֥א מְעַט־מַ֖יִם מִכַּדֵּֽךְ׃እዚህ አንቀጽ ላይ "ቆንጆ" ለሚለው የገባው ቃል "አልማህ" עַלְמָה ሲሆን "ኮረዳ" "ወጣት ሴት" "ብላቴናይት" ማለት ነው፦ ዘጸአት 2፥8 "ብላቴናይቱ" ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። הָֽעַלְמָ֔ה וַתִּקְרָ֖א אֶת־אֵ֥ם הַיָּֽלֶד׃ ምሳሌ 30፥19 የሰው መንገድ ከ-"ቆንጆ" ጋር ነው። וְדֶרֶךְ גֶּבֶר