gram news
Аватар канала Wazema Media / Radio

Wazema Media / Radio

@wazema_radio

Wazema is Radio other contents are available either in our website/social media or FM radio stations in Ethiopia. www.wazemaradio.com

ПроектыENРазное

49,734подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Wazema Media / Radio

    13 нояб., 18:03изменён

    ለቸኮለ፤ ዓርብ፣ ኅዳር 4፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ዓዲ ቦኽራይ እና ዓዲ አስመሩ በተባሉ አከባቢዎች በኢትዮጵያና ኤርትራ ሠራዊቶች መካከል ዛሬ ውጊያ መካሄዱን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በአካባቢው በደኅንነት ሥጋት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሠዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መሄዱንም ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡በሌላ በኩል፤ ትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራባዊ ዞን ሽራሮ፣ ሠየምቲ እና አድያቦ በተባሉ አካባቢዎች በመንግሥትና በሕወሃት ኃይሎች መካከል ላለፉት ሁለት ቀናት ውጊያ መካሄዱን ነዋሪዎች ነግረውናል። የኤርትራና የሕወሃት ኃይሎች በጋራ ሲንቀሳቀሱባት ነበር የተባለችው ሽራሮ ከተማ ከአንድ ሳምንት በፊት በመንግሥትና በትግራይ ሠላም ኃይሎች ሥር እንደምትገኝም ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአድያቦ ወረዳ ልዩ ስሙ "ዓዲ ካሕሱ" በሚባል አካባቢም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በመንግሥትና በሕወሃት ኃይሎች መካከል ውጊያ መቀጠሉንና የከባድ መሳሪያዎች ድምጽና የጦር ጄቶች እንቅስቃሴ እንደሚስተዋል ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡ በበሽሬ ከተማም ከዛሬ ጀምሮ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኋላ ተሸከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች እንዳይንቀሳቀሱ የሰዓት ገደብ ተጥሏል።2፤ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ በጓሳ፣ ወለላ ባሕር እና ሾለክት በተባሉ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከሠኞ ጀምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ እየተካሄደ መኾኑን ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ከሠሰባሠበችው መረጃ አረጋግጣለች፡፡ በውጊያው ከክምር ድንጋይ ከተማ እስከ ንፋስ መውጫ ከተማ ያለው መንገድ ለተሽከርካሪዎች ዝግ መሆኑን ነዋሪዎች ነግረውናል። ኾኖም ውጊያ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች የመንግሥትም ኾነ የፋኖ ኃይሎች ለረጅም ጊዜ ይዘዋቸው እንደማይቆዩና ሁኔታው ቶሎ ቶሎ እንደሚቀያየር ነዋሪዎች ገልጸዋል።3፤ ፖሊዮ ቫይረስ በኦሮሚያ ክልል ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን በአምቦ አካባቢ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በደራሼና ጎፋ ዞኖች ተከሠተ። ቫይረሱ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ፣ በኑዌር ዞን እና ኢታንግ ልዩ ወረዳ መከሠቱንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጧል።ቫይረሱ በተከሠተባቸውና ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አምስት ክልሎች ከ11 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የሚያካትት የክትባት ዘመቻ ከኅዳር አጋማሽ ጀምሮ እንደሚካሄድ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። በዘመቻው በ120 የአዲስ አበባ ወረዳዎች 884 ሺሕ 323፣ በ81 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ በ276 የኦሮሚያ ወረዳዎች 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን፣ በ91 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ በ61 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 661 ሺሕ 539 በድምሩ ከ11 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል።4፤ ከ100 ሺሕ በላይ ቤቶችን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በቱሉ ዲምቱ 33 ብሎኮችን እና በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንጻዎችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ዛሬ በጎበኙበት ወቅት ተናገሩ። በአገር ዓቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ መያዙን የጠቀሱት ዐቢይ፤ ዕቅዱን ለማሳካት በሦስት ዋና ዋና ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። በመዲናዋ ብቻ ከ100 ሺሕ በላይ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ግንባታው ሲጠናቀቅ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ዐቢይ ተናግረዋል።በቀጣዮቹ ጊዜያት በመርካቶ አካባቢ "ከሠው ልጅ የመኖሪያ ደረጃ በታች" ሲሉ በገለጧቸው አካባቢዎች መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ እቅድ መኖሩንም ዐቢይ ጠቁመዋል፡፡ ዐቢይ፤ ገንዘብ ሲገኝ በመርካቶ ግራና በቀኝ የሚገኙ በርካታ ቤቶችን በማፍረስና በማሻሻል የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።5፤ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አራት ወራት፤ ለውጭ ገበያ ካቀረበችው ቡና 1 ነጥብ 16 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጠ። ገቢው የተገኘው፤ ወደ ውጭ ከተላከው 167 ነጥብ 8 ሺሕ ቶን ቡና መኾኑን ባለሥልጣኑ ጠቅሷል። የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ24 ነጥብ 6 ሺሕ ቶን እንዲሁም በገቢ የ157 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል። ሦስቱ የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻዎች፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጀርመን እና ቻይና መሆናቸውን ባለሥልጣኑ በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል።6፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለአገር ውስጥና ለውጭ አገራት ከቀረበ የኃይል ሽያጭና ከተጓዳኝ አገልግሎቶች 31 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል አለ። ‎በሩብ ዓመቱ ከኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ 27 ነጥብ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ተቋሙ ገልጧል። የሩብ ዓመቱ ገቢ፤ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል። ከአገር ውስጥ ከተገኘው ገቢ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች 26 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ ሲይዙ፤ የውጭ አገራት 21 ነጥብ 02 በመቶ ድርሻ መያዛቸው ተጠቅሷል።7፤ በሱዳን ድንበር አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ "አርሚ 13" እና "አርሚ 70" የተሠኙ የሕወኃት አባላት ናቸው የተባሉ 27 ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። ታጣቂዎቹ ከሱዳ ግዛት በመውጣት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መመለሳቸውን የገለጠው ሠራዊቱ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩሙሩክ ላይ እጃቸውን መስጠታቸውን ገልጿል። ታጣቂዎቹ መነሻቸው አሶሳን የመቆጣጠር ግዳጅ ተሠጥቷቸው እንደነበር የጠቀሠው ሠራዊቱ፤ ከተልዕኮው መጠናቀቅ በኋላ በዶላር ክፍያ እንደሚፈጸምላቸው ተነግሯቸው ነበር በማለት አክሏል።8፤ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሠን አስመላሽ ኮሚቴ፣ ሰሞኑን በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በራያ ስድስቱ ወረዳዎች የተቋቋመውን የትግራይ ባለአደራ አሥተዳደር አስመልክቶ የተሠራጨው መረጃ ከኮሚቴው አቋምና ከአውድ ውጭ የተተረጎመ ነው አለ። ኮሚቴው በራያ ወረዳዎች የተቋቋመው የትግራይ ባለአደራ አሥተዳደር በሕጋዊ ምርጫ ያልተመረጠ፣ የአካባቢውን ሕዝብ ነጻና እኩል ተሳትፎ ያላረጋገጠ፣ ራሱን የትግራይ ሠላም ኃይል ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ተጽዕኖ ሥር የወደቀና ሕዝባዊ ቅቡልነት የሌለው ነው በማለት ኮኗል። ኮሚቴው፤ ለጥያቄያችን ሕጋዊ ምላሽ ስላልተሠጠ ብቻ ራያ ላይ የተዋቀረውን ባለአደራ አስተዳደር እንደተቀበልን ተደርጎ መወሠድ የለበትም ብሏል።9፤ የኬንያዋ መርሳቢት ግዛት ገዥ መሃመድ ዓሊ፤ በኢትዮጵያ ሞያሌ በሚካሄደው ግጭት ሳቢያ 10 ሺሕ ኬንያዊያን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል አሉ። ገዥው፤ ከሞያሌ በተተኮሱ ተባራሪ ጥይቶች ኬንያ ውስጥ 22 ሰዎች እንደቆሠሉና የሌሎች ሁለት ኬንያዊያን ሕይወት እንዳለፈ ዛሬ በሠጡት መግለጫ ተናግረዋል። ግዛቲቱ የገጠማት ቀውስ ከአቅሟ በላይ ነው ያሉት ገዥው፣ የኬንያ መንግሥት፣፣ ተመድ እና ለጋሾች ለስደተኞች የሚሠጡትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተማጽነዋል። ገዥው፤ ስደተኞቹን ከድንበር ግጭቱ ራቅ ባሉ አካባቢዎች ጊዜያዊ መጠለያዎችን በመገንባት ማዛወር ያስፈልጋል ብለዋል።ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን
    5,90059651Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    12 нояб., 18:10

    ለቸኮለ፤ ሐሙስ፣ ኅዳር 3፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች እድገት በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት 20 ነጥብ 5 ሆኖ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ያወጣው አዲስ የማክሮ ኢኮኖሚ ትንበያ ሪፖርት አመለከተ። አገሪቱ ወደ ውጭ የምትልከው ምርት እድገት ባንጻሩ በቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት በ2 ነጥብ 96 እንዲሁም በ2028 በ2 ነጥብ 93 እንደሚቀንስ ሪፖርቱ ጠቅሷል። በሌላ በኩል፤ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የሚቻለው በገበያ ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን ሲገደብ መሆኑን ያወሳው ሪፖርቱ፤ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ ከአምስት ዓመት በኋላ ወደ 14 ነጥብ 9 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ተንብዩዋል።ሪፖርቱ፤ የትጥቅ ግጭቶችን ማቆምና በፖለቲካዊ ንግግር መፍታት፣ የብርን የመግዛት አቅም በማዳከም ላይ ብቻ የተመሠረተውን አካሄድ ማቆም አስፈላጊ መኾኑን በምክረ ሀሳብ ደረጃ አቅርቧል።2፤ በቀድሞ አጠራሩ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ በአዲሱ አደረጃጀት ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ሱሉልታ ወረዳ፣ ከጎርፎ ከተማ ወጣ ባለ ሥፍራ የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ዛሬ ሐሙስ ማለዳ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ከተሽከርካሪ ላይ ከ50 በላይ ሰዎችን አግተው መውሠዳቸውን ዋዜማ ሠምታለች። ሰዎቹ የታገቱት፣ መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ ወደ ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ በተለምዶ ''ኤፍ ኤስ አር ቅጥቅጥ'' ተብሎ በሚጠራ ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ምንጮች ነግረውናል። ከእገታው ለማምለጥ የሞከሩ ሁለት ሰዎች ታጣቂዎቹ በተኮሱት ጥይት ተመትተው በአካባቢው ወደሚገኝ የሕክምና ተቋም መወሠዳቸውን ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመለክታል።3፤ የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በተሠማሩ ግለሰቦች ላይ የጸጥታና አስተዳደር አካላት ርምጃ እንዲወስዱ አዘዘ፡፡አስተዳደሩ፤ ሕገ-ወጥ የወርቅና ሌሎች ማዕድናት ቁፋሮ፣ አደገኛ ኬሚካሎችን የመጠቀም ልማድ እና ማዕድናትን ከክልሉ ውጭ በሕገ-ወጥ መንገድ የማዘዋወር ድርጊት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጧል። መመሪያውን በማስፈጸም ሂደት ኃላፊነታቸውን የማይወጡ ወይም ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር የሚተባበሩ አካላት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስተዳደሩ አስጠንቅቋል።4፤ ባለፉት ሳምንታት በመንግሥትና በሕወሃት ኃይሎች መካከል ውጊያ ሲያካሄድበት በቆየው የተምቤን ዓብይ ዓዲ ከተማ ከሠኞ ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደተጣለ ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በሰዓት እላፊ ገደቡ መሠረት፤ ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ እንዲሁም እግረኞች ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ እንደተጣለ የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል። ኾኖም የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር፤ በከተማዋ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደተጣለ በይፋ አልገለጠም። አካባቢው በአሁኑ ወቅት በመንግሥት እና በትግራይ ሠላም ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል።5፤ ከሳምንታት በፊት እጃቸውን ለመንግሥት የሠጡት የትግራይ ኃይሎች የደቡብ ግንባር አዛዥ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ወይም በቅጽል ስማቸው መዲድ፤ የሕወሓት የፖለቲካና ወታደራዊ አመራር "በተሳሳተ ስሌት" እና ሙሉ መግባባት ባልተደረሠበት ሁኔታ ጦርነቱን ወደ ኤርትራ ለማሻገር ወስኖ ነበር በማለት ተናገሩ። ጀነራሉ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን በተላለፈ ዘጋቢ ፊልም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርበው በሠጡት ቃል፤ የትግራይ ኃይል የመከላከያ ሠራዊትን የጸረ-ማጥቃት ርምጃ ሊቋቋም የሚችል አቅም እንዳልነበረው ገልጸዋል። ጀነራሉ፤ በዕዝና ቁጥጥር መበታተን ሳቢያ በግንባር ለነበሩ አዛዦች "አፈግፍጉ" የሚል ግልጽ ወታደራዊ እንዳል በወቅቱ እንዳልተሠጠም ብለዋል።6፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሕልፈት በኋላ የዐይን ብሌን መለገስ በሸሪዓ ሕግ የተፈቀድ ተግባር መሆኑን ገለጠ። ምክር ቤቱ ከሕልፈት በኋላ የዐይንን ብሌን በመለገስ ረገድ ዙሪያ ጥያቄ በጤና ሚንስቴር እና በኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት በኩል ጥያቄ እንደቀረበለትና ቁርዓን እና የሸሪዓ መርሆችን መሠረት በማድረግ የዓይን ብሌን መለገስ ከኃይማኖቱ ጋር አይጻረርም የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጧል፡፡ የዐይን ብሌን ልገሳ የሚፈቀደው፤ የለጋሹ ሕልፈት በትክክል ከተረጋገጠ፣ ለጋሹ በሕይወት እያለ በግልጽ ከተናዘዘ እና ከሞት በኋላ የሟች ወራሾችና ቤተሰቦች ለልገሳው ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ መሆኑን ምክር ቤቱ አብራርቷል፡፡7፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የኃይማኖት ነጻነትን በማበረታታት፣ በእምነቶች መካከል መስተጋብሮችን በማጠናከር እና አማኞች በሰላም ማምለክ በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር ዛሬ መወያየታቸውን ገለጡ። አምባሳደሩ፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን በውይይቱ ወቅት መግለጣቸውን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል። በቅርቡ በአርሲ በርካታ የቤተክርስቲያኗ ተከታዮች መገደላቸው እንዲሁም ከቀዬአቸውና ከንብረታቸው መፈናቀላቸው አሜሪካን እንዳሳዘነ አምባሳደሩ መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ፓትርያርኩ በበኩላቸው፤ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም ዘላቂ መፍትሔ ግን ሊገኝ አልተቻለም በማለት ለአምባሳደሩ ነግረዋቸዋል ተብሏል።እንዲሁም፤1፤ በአንድ የመጽሐፍ ጥራዝ ዘጠና ታሪኮችን ያካተተው የደራሲ ሕይወት እምሻው "ቀብር እና ማስካራ" የተሠኘ አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ ኅዳር 5 ቀን ለንባብ ይበቃል። ይህ የደራሲዋ ሰባተኛ መጽሐፍ ሲሆን፣ የመጽሐፉ የሽያጭ መጀመሪያና የፊርማ ሥነ ሥርዓት የፊታችን ቅዳሜ ለገሐር በሚገኘው ጃፋር መጽሐፍት መደብር ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል።2፤ አርታዊ ጋለሪ “ከቶኪዮ እስከ አዲስ አበባ፤ በቀለም ያሸበረቀች ከተማ” የተሠኘ የጃፓናዊው አርቲስት ዮሺሃሩ ኡሩሺዛኮ የግል ሥዕል ዐውደ ርዕይ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ። የዐውደ ርዕዩ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ሕዳር 5 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኘው አርታዊ ጋለሪ የሚከናወን ሲሆን፣ እስከ ሕዳር 12 ቀን ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል። [ዋዜማ]
    9,02062731Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    11 нояб., 22:23

    ለቸኮለ፤ ረቡዕ፣ ኅዳር 2፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ የቡድን 7 አገራት፤ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል እያሽቆለቆለ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ዛሬ ባወጡት መግለጫ ገለጡ። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ድንበር ተሻጋሪ ውጥረት ቀጠናዊ መልክ ሊይዝ እንደሚችል ያስጠነቀቁት የቡድኑ አባል አገራት፤ ሁኔታው ከተባባሰ በቀጠናዊ መረጋጋት፣ በሰብዓዊ ቀውስ፣ በጸጥታ እና የቀይ ባሕር መስመርን ጨምሮ በዓለማቀፍ ንግድ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዱፈልጉና ሲቪሎችን ከጥቃት እንዲጠብቁ አገራቱ ጠይቀዋል። አገራቱ፤ የአገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበር እንደሚያስፈልግም አጽንዖት ሠጥተዋል።2፤ ሦስት የአሜሪካ የሕግ መወሠኛ ምክር ቤት አባላት፤ በኢትዮጵያ "የርስበርስ ጦርነት" እንዳይከሠት አሜሪካ በቂ ዲፕሎማሲያዊ ሚና እየተጫወተች አይደለም በማለት ለውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ በጻፉት ደብዳቤ ወቀሱ። አሰብ ወደብን በወታደራዊ ኃይል የመያዝ ጉዳይ መነሳት የለበትም ያለት ሴናተሮቹ፤ አሜሪካ በማናቸውም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድርድር ውስጥ የወደብ መያዝን የዲፕሎማሲ መሳሪያ እንዳታደርገው ጠይቀዋል። ሴናተሮቹ፤ ኢትዮጵያ አሰብ ወደብን በኃይል ለመያዝ ብትሞክር፣ አሜሪካ ድርጊቱን እንደማትደግፍ ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ አለባት ብለዋል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር መሳሪያ እንዳትሸጥም ሴናተሮቹ ጠይቀዋል።3፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የበለጸጉ አገራት የካርበን ልቀታቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ቱርክ እያስተናገደችው ባለችው የዘንድሮው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ጠየቁ። ዐቢይ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ብዙ ወጪ ባወጣን ቁጥር በትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት ላይ የምናፈሠው ሙዓለ ንዋይ ይቀንሳል በማለት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ከውጭ እንዳይገቡ ማገዷን የጠቀሱት ዐቢይ፤ የቀጣዩ ጉባኤ አስተናጋጅ የሆነችው ኢትዮጵያ ማኅበረሰቦችን የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትለው ጉዳት ለመከላከል በቶሎ ርምጃ ለመውሠድ ቅድሚያ እንደምትሠጥ ተናግረዋል።4፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አማካሪ ጌታቸው ረዳ፤ የኤርትራ እና ሱዳን መንግሥታት በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን ጨምሮ አማጺ ቡድኖችን የማስታጠቅና የማስተባበር ሥራ ይሠራሉ በማለት ከሰሱ። ጌታቸው ይህን ያሉት፣ ከተመድ ዋና ጸሃፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጉዋንግ ኮንግ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። ጌታቸው፤ የኤርትራ መንግሥት በቀጠናው ያደርገዋል ባሉት አፍራሽ ሚና ዙሪያ ለልዩ መልዕክተኛው ሠፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል። በቀጠናው የባሠ ውጥረት እንዳይከሠት የሚያስችል ንግግር ለማድረግ ኤርትራ እና ሱዳን በመጀመሪያ የኢትዮጵያ አማጺ ቡድኖችን ከማስታጠቅና ከመደገፍ መቆጠብ አለባቸው የሚለውን የኢትዮጵያ አቋም ለልዩ መልዕክተኛው እንዳስረዱም ጌታቸው ጠቅሠዋል።5፤ ዓለማቀፍ የአዳዲስ መድሃኒቶችና የሕክምና መሳሪያዎች አምራች ኩባንያዎች አዳዲስ መድሃኒቶችንና የሕክምና ቁሳቁሶችን ተደራሽ ለማድረግ በእቅዳቸው ከሚይዟቸው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ አንድ ሪፖርት አመለከተ። አክሰስ ቱ ሜዲሲን ፋውንዴሽን የተባለው ተቋም ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት፤ ኩባንያዎች አዳዲስ መድሃኒቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከያዟቸውና በሪፖርቱ ከተካተቱት 245 እቅዶች ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፑብሊክ እያንዳንዳቸው የተካተቱት በ10ሩ እቅዶች ብቻ መሆኑን ጠቅሷል። የሦስቱ አገራት በበቂ ሁኔታ አለመካተት፤ መድሃኒት አምራቾች የሕዝብ ብዛትንና የበሽታዎችን ሥርጭት ዋነኛ መስፈርት እንደማያደርጉ የሚጠቁም ተደርጎ ተወስዷል።6፤ የፌደራል መንግሥቱ የሚንስትር ደዔታነት ሹመት የሠጣቸው የስምረት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት ኬርያ ኢብራሂም፣ አዲሱ የመቀለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረና ሌሎች ዘጠኝ አመራሮችና አባላት ራሳቸውን ከፓርቲው አገለሉ። አባላቱ፤ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ጥቂት አባላት የፓርቲውን ሕገ-ደንብ በመጣስ ፓርቲው የመፍረስ አደጋ እንዲደቀንበት አድርገዋል በማለት ከሠዋል። የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በበኩሉ፤ ከፓርቲው ራሳቸውን ያገለሉ አመራሮች የሕዝብ ተቃውሞ ሲበዛባቸው ትኩረት ለማስቀየር የፈለጉና ፓርቲውን ከውስጥ ለማፍረስ በሚስጢር ሲሠሩ የቆዩ ናቸው በማለት ከሷል።በሌላ በኩል፤ ምርጫ ቦርድ የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን ሰብሳቢ የሆኑት ገብረሕይወት ገብረስላሴ የፓርቲውን "ሕገ-ደንብ ጥሠዋል" በሚል ከሳምንታት በፊት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገበት አካሄድ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ነበር ሲል ውሳኔውን ውድቅ አድርጓል።7፤ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ50 ሺሕ ብር በላይ የሆኑ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች 15 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ የሚደነግገው አዲስ ደንብ ሥራ ላይ ዋለ። ዓመታዊ ገቢያቸው ከተጠቀሠው መጠን የማያልፍ የይዘት ፈጣሪዎች ደሞ ቀድሞ የከፈሉት ግብር ለወደፊት ከሚከፍሉት ጋር እንዲካካስላቸው ወይም ተመላሽ እንዲደረግላቸው ደንቡ ደንግጓል። በአዋጁ መሠረት፤ በዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ባለቤት የሆኑ ግብር ከፋዮች ገቢያቸውን አሳውቀው እያንዳንዱ ሩብ ዓመት በተጠናቀቀ በ30 ቀናት ውስጥ ግብሩን መክፈል ይጠበቅባቸዋል። የኢትዮጵያ ነዋሪ የኾነ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የባንክ ሂሳቡ የተከፈተው ከአገር ውጪ መኾኑ ወይም ክፍያው ከአገር ውጪ መፈጸሙ ብቻ ግብር ከመክፈል እንደማያድነው በደንቡ ላይ ሠፍሯል፡፡እንዲሁም፤1፤ "ጉሽን" የተሠኘው አዲስ ተውኔት በሳምንት ሁለት ቀናት መታየት ሊጀምር ነው። በሳምንት አንድ ቀን ዘወትር ረቡዕ ሲቀረብ የቆየው ተውኔቱ፤ ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ዘወትር እሁድ በ12 ሰዓት በዓለም ሲኒማ መታየት እንደሚጀምር አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።2፤ "በር የሌለው ቤት" የተሠኘውና በቡርሃን አል-አሚን ተደርሶ የተዘጋጀ አዲስ ተውኔት ዘወትር ሐሙስ ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዕይታ ላይ ይገኛል።3፤ "የመጨረሻው መጀመሪያ" መጽሐፍ ተርጓሚ አፈወርቅ በቀለ ሐሙስ ኅዳር 3 ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ከመጽሐፉ አንባቢዎቹ ጋር የሚገናኝበት የመጽሐፍ ፊርማ መርሃ-ግብር ለገሐር በሚገኘው ጃፋር መጽሐፍት መደብር ይካሄዳል።[ዋዜማ]
    10,3007482Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    10 нояб., 18:19

    ለቸኮለ፤ ማክሰኞ፣ ኅዳር 1፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ በባድመ ከተማ የኤርትራ ጦር ጭምር የተሳተፈበት ውጊያ በመንግሥት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል መካሄዱን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በትግራይ በድጋሚ ጦርነት ከተቀሠቀሠ ወዲህ ከቀናት በፊት ባድመ ላይ ውጊያ እስኪቀሰቀስ ድረስ የኤርትራ ሠራዊት ከባድመ አካባቢ ወጥቶ እንደነበር ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ ባድመ በሕወሃትም ሆነ በኤርትራ ጦር ሥር እንዳልኾነች ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ከትላንት ጀምሮ የኤርትራ ሠራዊት ሠምበል፣ ገማህሎ እና ዓዲ ጸጸር በተባሉ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሠምተናል።በሌላ በኩል፤ የኤርትራ አዋሳኝ በኾኑት ራማ እና ገማህሎ በተባሉ አካባቢዎች የመንግሥት ሠራዊት ከሕወሃትን፣ የፋኖ ታጣቂዎችንና የአፋር አማጺዎችን ካቀፈው ኃይል ጋር ውጊያ ማካሄዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ የሕወሃት፣ የፋኖ፣ የአፋር እና የኤርትራ ኃይሎች በአካባቢው በጋራ ሲንቀሳቀሱ እንደሚታዩ የገለጹት ነዋሪዎች፤ በተለይ ትላንት ሠኞ ከባድ የተባለ ውጊያ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡2፤ ፌደራል መንግሥቱ ለትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ የሚውል ገንዘብ ከ1 ሳምንት በፊት ወደ መቀለ መላኩን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ጌታቸው፤ ባለአደራ አስተዳደሩ የሠራተኞችን ውዝፍ ደመወዝ ከነገ ጀምሮ እንደሚከፍል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ በክልሉ 140 ሺሕ ገደማ የመንግሥት ሠራተኞች እንዳሉ የጠቀሱት ጌታቸው፤ ኾኖም ምን ያህሉ ወደ ሥራ እንደተመለሱ ወይም ምን ያህሉ ከሕወሃት ጋር ጫካ እንደገቡ ማጣራት እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ አስተዳደሩ፤ በአካል ተገኝቶ ሪፖርት ላደረገ የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ መክፈል እንደሚጀምር ገልጧል።3፤ የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ምዕራብ ትግራይ ተብሎ ለሚጠራው ትግራይ እና አማራ ክልሎች ለሚወዛገቡበት አካባቢ አስተባባሪ ሾመ፡፡ የባለአደራ አስተዳደሩ ሥራ አስፈጻሚ ካውንሥል ሰብሳቢ አሠፋ አብርሃ በጻፉት ደብዳቤ፤ ዳንኤል ነጋሽ ለአወዛጋቢው ዞን ዋና አስተባባሪ ሆነው እንደተሾሙ አስታውቀዋል። ሆኖም፤ ዋና አስተዳዳሪ በሚል ማዕረግ ፋንታ ዋና አስተባባሪውም በሚለው ማዕረግ የተሿሚው ዋና ዋና ኃላፊነቶች ምን እንደሆኑ ደብዳቤው አላብራራም፡፡ ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገችው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡4፤ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከውጭ የሚልኩት ገንዘብ ከቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትና ከለጋሾች ገንዘብ በመብለጥ የአገሪቱ ትልቁ የውጭ ገንዘብ ምንጭ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ገለጠ። ሆኖም ወደ አገሪቱ የሚላከው ገንዘብ ባብዛኛው ቤት፣ ጤና እና ትምህርት በመሳሰሉ ፍጆታዎች ላይ እንጂ በኢንቨስትመንት ላይ እንደማይውል ሪፖርቱ ጠቅሷል። ሪፖርቱ፤ የአስተማማኝ ፖለቲካዊ ሁኔታ አለመኖር፣ የፖሊሲዎች መቀያየርና በንብረት ባለቤትነት መብት ላይ ርግጠኛነት ማጣት የገንዘብ ላኪዎችን አመኔታ እንደሚሸረሽር ሪፖርቱ አውስቷል። ሪፖርቱ፤ የገንዘብ ፍሠቱን ለመጨመር የውጭ ምንዛሬን አስተማማኝነት መጠበቅ፣ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወጪዎችን መቀነስና የገንዘብ ቁጠባ ሥርዓቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብሏል።5፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ፣ ''የዴንጊ ትኩሳት'' ቫይረስ ወረርሽኝ በክልሉ ተከስቷል አለ። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው በተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ናሙና ላይ ምርመራ አድርጎ፤ አምስቱም በቫይረሱ መያዛቸውን እንዳረጋገጠ ቢሮው ገልጧል። ቢሮው፤ በክልሉ ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ አስፈላጊ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲሠሩ አሳስቧል። የደንጊ ትኩሳት በወባ ትንኝ የሚተላለፍ፣ ፍቱን መድሃኒት የሌለው፣ ከባድ ራስ ምታትን፣ ማቅለሽለሽን፣ የድድ መድማትንና ማስታወክን የሚያስከትልና ገዳይ ሊሆን የሚችል በሽታ ነው።6፤ በስካንድናቪያን ባለሀብቶች የተያዘውና በጋምቤላ ክልል በወርቅ ልማት የተሠማራው አኮቦ ሚኒራልስ የወርቅ አውጪ ኩባንያ፤ በጥቅምት ወር 12 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን አስታወቀ። ኩባንያው በነሃሴ ወር 16 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን ገልጦ ነበር። ኩባንያው ከሁለት ዓመት በፊት ወርቅ ማምርት ከጀመረ ወዲህ በጠቅላላው ያመረተው ወርቅ 181 ኪሎ ግራም መድረሱን አዲስ ባወጣው መረጃ ጠቅሷል። የካናዳው አላይድ ወርቅ አውጪ ኩባንያ በበኩሉ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ኩርሙክ ከሚገኘው ጣቢያው ወርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የማጣራት ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።7፤ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የ140 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የተጫራቾች ፍላጎት ከ16 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አስመዘገበ። በጨረታው አንድ የአሜሪካ ዶላር የተሸጠው ከሁለት ሳምንት በፊት ከተካሄደው ጨረታ ጋር ተመሳሳይ በኾነ 159 ብር ከ70 ሳንቲም በሆነ አማካይ ዋጋ ነው። በዛሬው ጨረታ ከተሳተፉት 31 ባንኮች መካከል 26ቱ የውጭ ምንዛሬ አግኝተዋል። ተጫራች ባንኮች በጨረታው ላንድ ዶላር ያቀረቡት ከፍተኛ ዋጋ 160 ብር ከ99 ሳንቲም ሲኾን፣ ዝቅተኛው ዋጋ 159 ብር ከ18 ሳንቲም ነበር።እንዲሁም፣1፤ የሠዓሊ አብርሃም ወልደገብርኤል የሥዕል ሥራዎች የቀረቡበት "የሕይወት መጠበቅ" የተሠኘ የሥዕል ዐውደ-ርዕይ ለዕይታ በቅቷል። ይህ ዐውደ ርዕይ፣ እስከ ህዳር 21 ቀን ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ ጎብኝዎች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ መጎብኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።2፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባሕል ማዕከል የተዘጋጀውና የፊልም አዘጋጁ ሰውመሆን ይስማው የክብር እንግዳ በመሆን የተጋበዘበት ሳምንታዊ ዝግጅት ነገ ረቡዕ ኅዳር 2 ቀን ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ስድስት ኪሎ ካምፓስ በሚገኘው የባሕል ማዕከል ይካሄዳል። መግቢያው በነፃ ነው። [ዋዜማ]
    10,700677211Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    9 нояб., 18:17

    ለቸኮለ! ሰኞ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ የትግራይ የባለአደራ አስተዳደር የውክልናና ሹመት አሠጣጥ ሂደት ጋር በተያያዘ፤ በትግራይ የሠላም ኃይል አመራሮች መካከል ክፍፍል መፈጠሩን ዋዜማ ሠምታለች። የክፍፍሉ ዋነኛ መንስኤ፤ ሹመት አሠጣጡ የትውልድ አካባቢንና የግለሠቦችን ሠንሰለት ማዕከል ያደረገና ለትግሉ አስተዋጽኦ ያላደረጉ ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው የሚል መኾኑን ምንጮች ነግረውናል፡፡በሌላ በኩል፤ በአሁኑ በቡድኑ ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ገብረእግዚያብሔር በየነ መሪነት በመቀለ እና አዲግራት ከተሞች አዲስ የታጣቂ ቡድን አደረጃጀት እየተመሠረተ ነው የሚል ቅሬታ መኖሩንም ተረድተናል። ክፍፍሉን ተከትሎ፤ መመሪያ አንቀበልም ያሉ የታጣቂ ቡድኑ አባላት አሉ ተብሏል። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው አንድ የቡድኑ ወታደራዊ አመራር በበኩላቸው፤ "የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት የሚያሠሙት ሀሰተኛ ውንጀላ ነው" የሚል ምላሽ ሠጥተዋል፡፡2፤ በሞያሌ በቀጠለው ግጭት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሠዎች መገደላቸውን ዋዜማ ሠምታለች። በከተማዋ ጫሙቅ፣ መላብ ፣ 01 እና 02 በተባሉ አካባቢዎች ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ነግረውናል። ከዓርብ፣ ጥቅምት 27 ቀን ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት የተኩስ ድምጽ እንደሚሠማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የፌደራል መንግሥት ኃይሎች ግጭቱን ለማርገብ ወደ አካባቢው አለመግባታቸውን ተረድተናል።በተያያዘ፤ በሞያሌው ግጭት ወደ ኬንያ የተሠደዱ ስደተኞች የምግብ፣ የውሃ እና የመጠለያ ችግር እንደገጠማቸው ተገልጧል። የተመድ የፍልሠት ድርጅት፤ ከስደተኞቹ 80 በመቶዎቹ ዋና ችግራቸው የምግብ እጥረት መሆኑን በዳሰሳ ጥናት እንዳረጋገጠ ገልጧል። ከ10 ስደተኞች ዘጠኙ የመንደራቸው ሁሉም ነዋሪዎች እንደተሠደዱ ገልጸዋል ተብሏል።3፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፤ "ከአቅም በላይ" ተብለው በተጠቀሱ ምክንያቶች የታክስ ዕዳ ጫና ላለባቸው ግብር ከፋዮች ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና ወጥ የምኅረት አሠጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጀ፡፡ ዋዜማ የተመለከተችው ረቂቅ መመሪያ፤ ከአቅም በላይ በኾኑ ምክንያቶች ሕጋዊ የታክስ ግዴታቸውን መወጣት ባለመቻላቸው የዕዳ ምኅረት ጥያቄ ባቀረቡ አካላት ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይገልጻል። ጎርፍ፣ መሬት መንሸራተት ወይም እሳት ቃጠሎ ሲከሠት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የድጋፍ ደብዳቤዎች፤ የንግድ ድርጅት ኪሳራ ወይም አቅም ማነስ ሲያጋጥም በኦዲተር የተረጋገጠ የኦዲት ሪፖርትና የፋይናንስ ኪሳራ መግለጫ እንዲሁም ከባድ ሕመም ወይም የአካል ጉዳት ሲያጋጥም፤ ከሕክምና ተቋም ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ መኾኑ በመመሪያው ላይ ሠፍሯል፡፡ ይሁን እንጂ፤ መመሪያው ሕገ-ወጥ የታክስ ስወራ በፈጸሙ አካላት ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ተብሏል።4፤ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ዛሬ ሰኞ ማለዳ ላይ በፈጸሙት ጥቃት የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ቤጊ አዱኛን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንደገደሏቸው ዋዜማ ሠምታለች። ግድያው የተፈጸመው፤ በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ወረዳዋ መቀመጫ ፊታል ቀድመው በመግባት ቦታ ቦታ ከያዙ በኋላ መሆኑን ምንጮች ነግረውናል። ጥቃቱን ተከትሎ፤ ታጣቂዎቹ በከተማዋ የሚገኙ በርካታ የንግድ መደብሮችን፣ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆችን፣ እንዲሁም የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶች መዝረፋቸውን ምንጮች ገልጸዋል።5፤ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በክልሉ በተፈጠረው ዳግም ጦርነት ምክንያት ለጊዜው በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ። ዩኒቨርሲቲው፤ በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀድሞ የትምህርት ተቋማቸው ለመመለስ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ የምዝገባ ቀኑን ማራዘሙን ጠቁሟል። ነገና ከነገ ወዲያም በተያዘው የትምህርት ዘመን በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የቆዩ ተማሪዎች ወደ ግቢው እንደሚገቡ ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ዩኒቨርስቲው፤ ስንት ተማሪዎቹ በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመድበው እንደቆዩ አልጠቀሠም።6፤ ግብጽ እና ሱዳን፤ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ በምትወስዳቸው የተናጥል ርምጃዎች ይደርሱብናል ያሏቸውን "ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጉዳቶች" የሚያጠናና የካሳ ጥያቄ የሚያቀርብ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማሙ። ኮሚቴው የሚያጠናው "ጉዳት" ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን የማኅበራዊና አካባቢያዊ ጉዳቶችን ጭምር እንደሚያካትት የአገራቱ ባለሥልጣናት መግለጣቸውን የግብጽ ጋዜጦች ዘግበዋል። በኮሚቴ ጥናት ላይ በመመስረት፣ ኢትዮጵያ ለሁለቱ አገራት ካሳ እንድትከፍል ጥያቄ እንደሚቀርብ ባለሥልጣናኑ ተናግረዋል ተብሏል።ኢትዮጵያ፣ በግብጽ ጫና እና ሴራ ለዓመታት የተስተጓጎሉባትን የውሃ ፕሮጀክቶችና በዚህም ሳቢያ የደረሠባትን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ የሚገመግምና የካሳ ጥያቄ የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ "የዓባይ የካሳ ብሄራዊ ኮሚቴ" በቅርቡ ማቋቋሟ ይታወሳል።እንዲሁም፤1፤ በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ1999 ዓ፤ም የተከፈተውና ዘንድሮ 20ኛ ዓመቱን የሚያከብረው የተፈሪ መኮንን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የሥነጥበብ ትምህርት ክፍል የሥዕል ዐውደ ርዕይ አዘጋጅቷል። በዐውደ ርዕይው ላይ ተመራቂ ተማሪዎች ያዘጋጇቸው የሥዕል ሥራዎች ይቀርባሉ። ዐውድ ርዕይው ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በኮሌጁ የሥዕል ማሳያ ይከፈታል።2፤ "ጃዝ ቲዩስዴይ" የተሠኘ የጃዝ (ብሉዝ እና ፈንክ) ሙዚቃዎች የሚቀርቡበት ዝግጅት በየሳምንቱ ማክሰኞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ባዝራ ኮፊ (BazraCoffee) ይካሄዳል። የዝግጅቱ መግቢያ ዋጋ 200 የኢትዮጵያ ብር ነው። [ዋዜማ]
    10,7006310221Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    7 нояб., 17:36

    ዛሬ ቅዳሜ፣ ጥቅምት 28፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ቡልዲግሉ ወረዳ ታጣቂዎች ሐሙስ'ለት በፈጸሙት ጥቃት 52 ሰዎች እንደተገደሉ ተሠማ። ዳለቲ በተባለች ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት መካከል፤ 21ዱ ሲቪሎች፣ 18ቱ የክልሉ የፖሊስ አባላት እና 13ቱ የአካባቢው የሚሊሻ አባላት መኾናቸውን ዋዜማ ሰምታች። ወረዳዋ ከኦሮሚያ ክልል ጋር የምትዋሠን ስትኾን፤ ጥቃቱን የፈጸሙት የአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።2፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እግድ የጣለበት የቀድሞው የኤፈርት ባለአደራ ቦርድ የአዳዲስ የቦርድ አባላትን ሹመት "ሕገወጥ" ሲል ውድቅ አደረገ፡፡ የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ አባል አብርሃም ተከስተ ይመሩት የነበረው ቦርድ፤ አዲሱ ሹመት ተቋማዊ አሠራርን የጣሠ፣ ሕጋዊ ተቀባይነት የሌለው እና የተቋሙን ሀብትና ንብረት በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር ያለመ ነው በማለት ተቃውሞውን ገልጧል፡፡ ለኩባንያው ጊዜያዊ ቦርድ የመሠየም ሕጋዊ ሥልጣን የድርጅቱ ምክር ቤቱ ነው ያለው የቀድሞው ቦርድ፤ የተቋሙ ሠራተኞች፣ የፍትሕ አካላት እና የክልሉ ሕዝብ ውሳኔውን ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።3፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ)፤ በሞያሌው ግጭት ሳቢያ ወደ ኬንያ ለተሠደዱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 3 ሚሊዮን ዶላር መደበ። ተመድ፤ የገንዘብ ድጋፉ ለነፍስ አድን የሚውል የምግብ፣ የውሃ፣ የመጠለያና የጤና ድጋፍ ለሚያደርጉ የረድኤት ድርጅቶች እንደሚሠጥ ገልጧል። ተመድ፤ እስካሁን ወደ ኬንያዋ መርሳቢት ግዛት የተሠደዱት ኢትዮጵያዊያን ብዛት 50 ሺሕ ይሆናሉ ብሏል። ድርጅቱ የእርዳታ አሠጣጡን የሚያስተባብር ቡድን ወደ ሞያሌ ማሠማራቱን አስታውቋል።4፤ ኢትዮጵያ ​በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ለውጭ ገበያ ከላከችው ቡና 878 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች። በተጠቀሠው ጊዜ ውስጥ ከቡና 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፤ የእቅዱ 85 በመቶ እንደተሳካ የቡናና ሻይ ልማት ባለሥልጣን ገልጧል። ይህ ገቢ የተገኘው፤ 144 ሺሕ 433 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በመላክ እንደሆነ የገለጠው ባለሥልጣኑ፤ ለውጭ ገበያ መላክ የተቻለው ግን 131 ሺሕ ቶን ገደማ እንደነበር ጠቅሷል። ውጤቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ​በቡና መጠን የ17 ሺሕ 527 ቶን እንዲኹም ​በገቢ የ115 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተገልጧል። በቡና መዳረሻ፤ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጀርመን እና ቻይና በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል ተብሏል።እንዲሁም፤1፤ በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት የተዘጋጀው የመጽሐፍት ባዛር ተከፍቷል። በዚህ ባዛር ላይ፤ አዳዲስና የአካዳሚክ የጥናት መጽሐፍት ስብስቦች ለሽያጭ መቅረባቸውን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ባዛሩ በቤተ መጽሐፍቱ ዋናው መግቢያ ላይ እስከ ሕዳር 7 ቀን እየተካሄደ ይቆያል።2፤ በገጣሚ ረድዔት ተረፈ የተዘጋጀውና ግጥም ሙዚቃና ጨዋታ የሚቀርቡበት "መገናኛ" ጥበባዊ ዝግጅት ነገ፤ ጥቅምት 29 ቀን በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ይካሄዳል። መግቢያ ዋጋ 600 የኢትዮጵያ ብር ነው። [ዋዜማ]
    10,300491222Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    6 нояб., 19:19

    ለቸኮለ! ዓርብ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያወጣው የመንግስት ሠራተኞችን ምዘና የሚመለከተው አዲሱ ረቂቅ መመሪያ፤ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ የቴክኒክ፣ የባሕሪ እና የተግባር ምዘና እንዲወስድ የሚያስገድድ መሆኑን ዋዜማ ሠምታለች። መመሪያው፤ ሠራተኞች በሥራ መደባቸው ለመቀጠል እንዲሁም ዕድገትና ዝውውር ለማግኘት በሦስቱም የምዘና መስኮች 70 በመቶና ከዚህ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው መደንገጉን ምንጮች ጠቁመዋል። 70 በመቶ ማስመዝገብ ያልቻሉ ሠራተኞች፤ ከሥልጠና በኋላ ዳግም ምዘና የሚያደርጉበት አሠራር እንደሚኖር ምንጮች ገልጸዋል። በምዘናው በቂ ውጤት ማምጣት ያልቻሉ ሠራተኞች፤ ጥቅማቸው ተጠብቆላቸው በገዛ ፍቃዳቸው ከሥራ መልቀቅ የሚችሉበት አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል።2፤ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ታጣቂዎች በድጋሚ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ላይ ጥቃት ፈጸሙ። ታጣቂዎች ትናንት ጥቃቱን የፈጸሙት፣ በሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ መኾኑን የቤተክርስቲያኗ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። በጥቃቱ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችና ክርስቲያኖች እንደተገደሉ ከወረዳው ቤተ ክሕነት መረዳቱን ጣቢያው ጠቅሷል። የአርሲና የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፤ ራቅ ባሉ በተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር በሚያጋጥምባቸው በርካታ ቀበሌዎች የመንግሥት አካላት ጥበቃና ከለላ እንዲሠጡ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ዘገባው አመልክቷል።3፤ በማእከላዊ ትግራይ ዞን ዓዴት፣ ዛና እና ብዘት በተባሉ ገጠራማ አካባቢዎች ዛሬ በመንግሥትና በሕወሃት ኃይሎች መካከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በተለይ "ብዘት" በተባለው አካባቢ በውጊያው በበርካታ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሠ የአካባቢዎው ነዋሪዎች ገልጸውልናል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ሠላም ኃይል የሚድያ ዘርፍ ኃላፊ መንግሥተዓብ ተስፋይ በበኩላቸው፤ አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች ከሚካሄዱ መጠነኛ የተኩስ ልውውጦች በስተቀር "ውጊያ ቆሟል" ብለዋል፡፡በተያያዘ፤ መከላከያ ሠራዊት፤ ከሕወሓት ማረኳቸው ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች አዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ዛሬ አሳይቷል። ለእይታ ከቀረቡት መካከል፤ ከባድ መሳሪያዎች እንዲሁም አነስተኛ ድሮኖችና ወታደራዊ አጥቂ ድሮኖች ይገኙበታል። መሳሪያዎች ለእይታ የቀረቡት፤ መልካ ቃሊቲ በመባል በሚታወቀው የመከላከያ ሎጀስቲክ መመሪያ ውስጥ ነው።4፤ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የመረከብና በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም ትግበራ በመቐለ ከተማ የመለስ ካምፓስ ማዕከል ጀመረ። ኮሚሽኑ፤ አዲስ በተመረጡ አምስት ጊዜያዊ ማዕከላት የቅድመ-መልሶ ማቋቋም መስፈርቶችን ያሟሉ ከ5 ሺሕ 500 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች የምዝገባ ሂደት መጀመራቸውን ገልጧል። በጉዳዩ ዙሪያ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ሠላም ኃይል የሚድያ ዘርፍ ኃላፊ መንግሥተዓብ ተስፋይ፤ ከመቀለ በተጨማሪ በአክሱም፣ ሽሬ፣ አድዋ፣ ማይጨው እና ውቅሮ አዳዲስ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ነግረውናል። ኾኖም በሂደቱ ላይ ታጣቂዎቹ ከቀድሞው በተለየ ዩኒፎርሞችን ባለመልበሳቸው የቀድሞ ተዋጊ መኾን አለመኾናቸውን ለመለየት ትንሽ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደፈጠረ ኃላፊው ተናግረዋል።5፤ በመቀለ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ በተሸከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጧቱ 12 ሰዓት የሚዘልቅ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ፡፡ ሕወሃት ከተማዋን ለቅቆ ሲወጣ ከማረሚያ ቤት የወጡ ሰባት ሺሕ የሚጠጉ ታራሚዎችና የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች በሚፈጽሟቸው የሥርቆትና ሕገ-ወጥ ተግባራት በነዋሪዎች ደኅንነት ላይ ሥጋቶች እንደተደቀኑ የሰዓት እላፊውን የጣለው መከላከያ ሠራዊት ገልጧል፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ በቤታቸውም ሆነ በሥራ ቦታቸው ያስቀመጡ ነዋሪዎች በሦስት ቀናት ውስጥ ያለምንም ቅድመ ምርመራ ለፖሊስ እንዲያስረክቡም ታዘዋል። የጸጥታ አካላት ሕጋዊ የፍተሻ ደብዳቤ በመያዝ ከጧቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት የመኖሪያ ቤቶች ፍተሻ እንደሚያካሂዱም ተገልጧል።ኾኖም፤ የቤት ለቤት ፍተሻውና ፍቃድ ያላቸውም ኾነ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ሥራ ከቀናት በፊት እንደተጀመረ ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት ተረድታለች።6፤ በጋምቤላ ክልል የጋምቤላ ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር፤ በወረዳው ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ሲል አዲስ የሰዓት እላፊ) አወጀ። ከዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ኅብረተሰቡ ከመኖሪያ ቤቱ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይችል አስተዳደሩ ገልጧል። ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የጸጥታ አካላት ውጭ የጦር መሣሪያ በማናቸውም ሰዓት ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ክልክል መሆኑንም አስተዳደሩ አስታውቋል። የሰዓት ገደብና የጸጥታ ቁጥጥር ሥርዓቱ፤ በወረዳዋ የጸጥታ ማስከበር ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና አካባቢውን በፍጥነት ወደ መደበኛ ሰላም ለመመለስ ታስቦ ነው ተብሏል።7፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የትምህርት ዘመኑ ሳይጠናቀቅ የቀጣይ ዓመት ቅድመ ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይ እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ እገዳ የሚጥል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጀ። ዋዜማ የተመለከተችው የአዲስ ረቂቅ መመሪያ፣ መመሪያውን የሚጥሱ ትምህርት ቤቶች መጀመሪያ ምክርና ከዚያም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደሚሠጣቸውና ጥፋታቸውን ማረም ካልቻሉ ግን ለአንድ ዓመት የእውቅና ፈቃዳቸው እንደሚታገድ ደንግጓል። በተማሪዎች ቅበላም ኾነ በትምህርት አሠጣጥ ሂደት በጾታ፣ ኃይማኖት፣ ብሔር፣ ማኅበራዊ መሠረትና የፖለቲካ አመለካከት ላይ የተመሠረተ ልዩነት ወይም አድልዎ ማድረግንም መመሪያው ይከለክላል።እንዲሁም፤1፤ ድምጻዊት አበባ ደሣለኝ ከአሥራ ሦስት ዓመታት በኋላ "መርቂኝ" የተሠኘ አራተኛ የሙዚቃ አልበሟን ኅዳር 4 ለአድማጮች እንደምታቀርብ አስታውቃለች።2፤ የድምጻዊ እሱባለው ይታየው (የሺ) አዲስ የሙዚቃ አልበም ሕዳር 11 ለአድማጮች እንደሚቀርብ ተሠምቷል። ከሙሉ አልበሙ አስቀድሞ የሙዚቃ ቪዲዮ የተሠራለትና አልበሙ ውስጥ የተካተተው "ለየቱ ጊዜ ነው?" የተሠኘው ሙዚቃ ይለቀቃል።3፤ ድምፃዊት ሄለን በርሄ "የበረታ" የተሠኘ ሦስተኛውን የሙዚቃ አልበሟን ትላንት ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን ለአድማጮች ይፋ አድርጋለች። [ዋዜማ]
    10,3009353221Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    5 нояб., 18:11

    ለቸኮለ! ሐሙስ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ የሱዳን መንግሥት በምሥራቃዊ ሱዳን ገዳሪፍ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ የተመደቡ ዲፕሎማቶች በሙሉ በ48 ሰዓት ውስጥ እንዲወጡ አዘዘ፡፡ የአገሪቱ መንግሥት ዲፕሎማቶችን ያባረረው፤ ኢትዮጵያ በአሶሳ የሚገኘውን የሱዳን ቆንስላ በመዝጋት ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ባዘዘ ማግስት ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሱዳን ቆንስላ ዲፕሎማቶችን ሊያባርር ስለመኾኑ ባለፈው እሁድ የሱዳን አምባሳደርን ጠርቶ ማሳወቁን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው የሌላኛቸውን ቆንስላዎች የዘጉት፣ ተቃዋሚ ኃይሎችን በመርዳት ዙሪያ ሲካሰሱ ከቆዩ በኋላ ነው።ኾኖም፤ በገዳሪፍ ቆንጽላ የተመደቡ ዲፕሎማቶች ቀደም ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሠው፣ ሥራቸውን ሑመራ እና አሶሳ ተቀምጠው እየሠሩ እንደቆዩ ምንጮች ነግረውናል። ዲፕሎማቶቹ ሑመራ ውስጥ ጊዜያዊ ጽሕፈት ጭምር ከፍተው እንደነበርም አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ገልጸውልናል።2፤ ጀርመን በአፍሪካ ቀንድ የውጥረቶች መባባስ መቆም አለበት አለች። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆሃን ዋዴፉል፣ የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለቀጠናው እጅግ አስፈላጊ መኾኗን ትናንት ከኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ላይ አጽንዖት መስጠታቸውን መስሪያ ቤታቸው ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። በሰሜን ኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲሠፍን ለሚደረጉ ጥረቶችም ጀርመን ድጋፍ እያደረገች እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋዴፉል አረጋግጠዋል ተብሏል።3፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ምደባ ያላገኙ ሠራተኞች ሲኖሩ ከሁለት ደረጃ ባልበለጠ የሥራ መደብ ዝቅ አድርጎ መመደብ የሚያስችል አዲስ መመሪያ ወጣ፡፡ ዋዜማ የተመለከተችው መመሪያ፤ በዲሲፕሊን ውሳኔ ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ ሠራተኞች የቅጣት ጊዜያቸውን እስኪያጠናቅቁ ባሉበት ደረጃ ይቆያሉ ይላል። በዲሲፕሊን ክስ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች ግን ከምደባ ውጭ እንደማይደረጉ ተደንግጓል። የኮንትራት፣ የጊዜያዊ፣ በትውስት፣ በውክልና ወይም በተጠባባቂነት የሚያገለግሉ ሠራተኞችን በድልድል ማወዳደርና መመደብ በመመሪያው ተከልክሏል፡፡ መመሪያው፤ የቋሚ ሠራተኞችን ሕጋዊ መብትና የሥራ ዋስትና ማረጋገጥን እንዲሁም በፍትሐዊነትና በግልጽነት መልሶ መመደብን ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል።4፤ የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የኤፈርት የቦርድ አባላትን በማገድ፤ በምትኩ አዳዲስ የቦርድ አባላትን ሾመ፡፡ አስተዳደሩ፤ የቀድሞዎቹ የቦርድ አባላት "ሕገወጥ" ሲል ከጠራቸው አካላት ጋር በመተባበር ኩባንያውን አደጋ ላይ ጥለዋል በማለት ከሷል። ርምጃው የተወሠደው፤ ኩባንያውን ከውድቀት ለማዳን፣ ሠራተኞቹንና ንብረቶቹን ለመጠበቅ እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ሲባል እንደሆነ ዋዜማ ከአስተዳደሩ ደብዳቤ ላይ ተመልክታለች። አዲስ የቦርድ አባል ኾነው የተሾሙት፤ የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊው ገብረሕይወት ገ/ማርያም፣ የፋይናንስና ሀብት ትብብር ቢሮ ኃላፊ ሓሰና ተክለ፣ የቴክኖሎጂና መገናኛ ቢሮ ኃላፊ ታደለ መንግስቱ፣ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ተናሄ ወርቅዬ እና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ገብረመድኅን ኃይሉ ናቸው።5፤ የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ የስድስት ወራት ገቢ የ40 በመቶ እድገት አስመዘገበ። የኩበንያው ገቢ የጨመረው፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ኪሳራ በመቀነሱ እንደሆነ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው በተጠቀሠው ጊዜ ውስጥ 701 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ጠቅሷል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ብቻ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር የደረሠ ሲሆን፤ ኩባንያው ለእናት ኩባንያው ሳፋሪኮም አጠቃላይ የአገልግሎት ገቢ 17 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተገልጧል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ዕድገት በማሳየት፤ ባሁኑ ወቅት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለሦስት ወራት ንቁ የሆኑ ደንበኞች እንዳሉት ተገልጧል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመጋቢት ገደማ ኪሳራውን ሸፍኖ ወደ ትርፍ ሊሸጋገር ይችላል ተብሏል።እንዲሁም፤1፤ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የ"ነገረ መጽሐፍት" ውይይት ላይ እንዳልካቸው ለማ በእንግድነት ተጋብዟል። ለውይይት የተመረጡት ፣ "ሽሽግ ወግ" እና "የጀበና ፖለቲከኞች እና..." የተሠኙ መጽሐፍት ናቸው። ውይይቱ የሚካሄደው፣ ቀበና አካባቢ በሚገኘው የማኅበራዊ ጥናት መድረክ አዳራሽ ነው።2፤ የ"ቃል ፌርማታ" መጽሐፍ አዘጋጅ ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ከመጽሐፉ አንባቢዎቹ ጋር የሚገናኝበት የመጽሐፍ ፊርማ መርሃ-ግብር ለገሐር በሚገኘው ጃፋር መጽሐፍት መደብር ይካሄዳል። [ዋዜማ]
    10,6005453Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    22 сент., 17:11

    ለቸኮለ! ማክሰኞ፣ መስከረም 12፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የዓለም አገራት የሰላም አመላካቾች ከ163 አገራት 138ኛ ደረጃ ተሠጣት። ኢትዮጵያ፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ ዘንድሮ አንድ ደረጃ አሻሽላለች። ለአገራት የሰላም ጠቋሚ ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የኢኮኖሚክስና ሰላም ኢንስቲትዩት፣ ከ5 ከያዘው ነጥብ ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 6 ነጥብ ሠጥቷታል። አገሪቱ ዝቅተኛ ነጥብ ያገኘችባቸው ጠቋሚዎች፣ ፖለቲካዊ ሽብር፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላት ግንኙነት፣ ውስጣዊ ግጭቶች፣ የውስጣዊ ግጭቶች አስከፊነት እና የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች ተደራሽነት ናቸው። ኢትዮጵያ በደረጃው ከተካተቱ 44 የአፍሪካ አገራት ያገኘችው 35ኛ ደረጃ ነው።2፤ ተመድ፣ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለጠ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቲፋኒ ዱጃሪክ፣ በአገሪቱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መፍጠራቸውን፣ የድሮን ጥቃቶች መደጋገማቸውንና የጸጥታ ችግሮች መቀጠላቸውን ጠቅሠው፣ ድርጅቱ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ትናንት ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዱጃሪክ፣ የአገሪቱ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የጸጥታ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ ከሚያደርጉ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል። ወታደራዊ ርምጃ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ወይም ነባር ቅራታዎችን አይፈታም በማለት ጭምር ዱጃሪክ አጽንዖት ሠጥተዋል።በተያይዘ፣ በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኦዞኒያ ኦጄሎ፣ በኢትዮጵያ ሰላም፣ መተማመንና
    4,11044321Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    21 сент., 17:08изменён

    ለቸኮለ! ሰኞ፣ መስከረም 11፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ፖለቲከኞች፣ ፋኖን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትንና ሕወሃትን ጨምሮ ሰባት የታጠቁ ቡድኖችና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ትናንት በይፋ በመሠረቱት "ትብብር" ዙሪያ ለዋዜማ በሠጡት ቃል የተለያዩ አስተያየቶችን አንጸባርቀዋል። የኢሕአፓ ፕሬዝደንት አብርሃም ኃይማኖት፤ ፓርቲያቸው ለአገሪቱ ችግር ብቸኛው መፍትሄ ውይይትና ድርድር መኾኑን እንደሚያምንና ማንኛውንም የትጥቅ ትግል እንደማይደግፍ ነግረውናል። የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት አስተባባሪ ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በበኩላቸው፣ የትብብሩ ዋነኛ ዘዋሪ የኤርትራ መንግሥት ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ባንጻሩ፤ ፓርቲያቸው በትብብሩ ላይ ገና አቋም እንዳልያዘ በመጥቀስ፣ ለጊዜው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የፈረመው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ክንፍ ተወካይ ማስረሻ ሠጤ ደሞ፣ ትብብሩ የፋኖ መሪዎችን ጨምሮ ከሕወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸውና በ"ኢትዮጵያዊነት ስም" ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሰዎችን ማንነት ያጋለጠ ክስተት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሠጥተዋል፡፡የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሠን አስመላሽ ኮሚቴም፣ "በትብብር" ስም የአማራን ታሪካዊ ግዛቶችና ማንነቶችን ለመንጠቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እቃወማለሁ ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል። ኮሚቴው፣ ትናንት ፋኖ እና ሕወሃትን ጨምሮ ሰባት
    8,8408919532Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    21 сент., 02:35

    የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ የሕዝብ አሰፋፈር ጥናት እየተካሄደ ነውበአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች ያሰማራቸው ባለሞያዎች ቤት ለቤት በመዘዋወር ፤ በአንድ ቤት የሚኖሩ የቤተሠብ አባላትን ብዛት፣ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ የትምህርት ደረጃ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እንዲሁም ወርሃዊ ገቢን የተመለከቱ መረጃዎችን እያሰባሰቡ እንደሆነ የዳሰሳ ጥናት ጥያቄ የቀረበላቸው ነዋሪዎች ገልጸውልናል። በአንዳንድ መንደሮችም፤ መኖሪያ ቤቶቹ ያረፉበት መሬት ልኬት መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡ የዋዜማን ዝርዝር ዘገባ ያንብቡ- https://cutt.ly/pycVqs55
    11,00071201142Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    20 сент., 16:01

    #NewsAlert ሰባት አማፅያን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት አስወግደው የሽግግር መንግስት ለመመስረት ያስችለናል ያሉትን አዲስ ጥምረት "ትብብር" ይፋ አድረጉ።በትግራይ ክልል በሚገኙ የሚዲያ አውታሮች በኩል የተሰራጨውን የ"ትብብር" መመስረት ይፋ ያደረጉት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሰብሳቢ አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው። አቶ ዘመነ የትብብሩ ሰብሳቢ መሆናቸውም ተገልጿል።አፋብን፣ ሕወሓት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ህዝብ ነፃነት ግንባርና የአፋር ብሄራዊ አንድነት ግንባር የ"ትብብሩ" አባላት መሆናቸው በመግለጫው ላይ ተነግሯል። "ትብብሩ" በስልጣን ላይ ያለውን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት በመጣል "ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት" ለማቋቋም ትልም እንዳለውም አቶ ዘመነ ካሴ በመግለጫው አብራርተዋል። [ዋዜማ]
    11,70013847423188Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    20 сент., 06:05

    https://youtu.be/8SfZAD0NHcQ?is=Wuge_c0KtBFAE0II
    YouTubeአዲስ አበባ የንባብ ነውጥ........ከፌቨን ኤልያስ ጋርዋዜማ ሐሳብ ያላቸውን ፣ ሙግት የሚወዱትንና አብነት የሚሆኑትን መሰሎቻችንን እንግዳ አድርገን እንጋብዛለን፣ ያወሩናልም። ይህን ወግ ተጋበዙልን
  • Wazema Media / Radio

    19 сент., 18:17

    ለቸኮለ! ቅዳሜ፣ መስከረም 9፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር፣ በኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ባለው የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሠራጩ ይገኛሉ አለ። ሚንስቴሩ፣ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ እንደተዘጋ፣ ዜጎች ለሥራ እየተሠማሩ እንዳልኾነና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ለጥቂቶች ብቻ እንደተዘጋጀ በማስመሰል በመሠራጨት ላይ ያሉ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ "መሠረት የለሽ" ናቸው ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚንስቴሩ፣ ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት ሂደቱ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ አማካኝነት አሁንም እየተካሄደ ይገኛል ብሏል። "መሠረት የለሽ" እና "አሳሳች" መረጃዎችን የሚያሠራጩ አካላትን በማጣራት ሕጋዊ እርምጃ ለመውሠድ በዝግጅት ላይ መኾኑንም ሚንስቴሩ ጠቅሷል።2፤ አፍሮ ፒክስ፤ በድረ ገጽ ለዕይታ በሚያቀርባቸው የኢትዮጵያ ፊልሞች 100 ሺሕ ዕይታ ለሚያገኙ 3 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር ለመክፈል ከፊልም ሠሪዎች ጋር ውል እየገባ ይገኛል። ድርጅቱ፣ ለአንድ የፊልም ዕይታ 0 ነጥብ 03 ዶላር እንዲሁም ለ10 ሺሕ ዕይታ 300 ዶላር ክፍያ ይፈጽማል። የድርጅቱ አሠራር፣ ፊልም ሠሪዎች ፊልማቸውን በሌሎች አማራጮች ጭምር ለዕይታ የማቅረብ መብት የሚሠጥና የፊልሞች የቅጂ መብት የባለቤቶቻቸው ኾኖ እንዲቀጥል የሚፈቅድ መኾኑንም ዋዜማ ተረድታለች። በድረገጹ ላይ ፊልሞችን ለዕይታ ለማቅረብ፣ ፊልሙ የእንግሊዝኛ የትርጉም ጽሑፍ ያለው መኾኑ አንዱ መስፈርት ነው። ድርጅቱ፣ በድረገጹ በወር ከሦስት እስከ አምስት የሚደርሱ ፊልሞችን ለዕይታ ለማብቃት ማቀዱንም ሠምተናል።3፤ ደቡ
    12,300467411Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    19 сент., 03:11

    በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የድርቅ ቀውስ እየተባባሰ ነውበተጠናቀቀው አመት የክረምት ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታየው የዝናብ መዘግየትና እጥረት በሰው፣ በእንስሳት እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያሰከተለ ይገኛል። አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ በርካታ ዞኖችና ወረዳዎች ድርቁ አስከፊ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እና ተጓዳኝ ችግሮች መዳረጉን ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት ተረድታለች።ድርቁ ከተባባሰባቸው ክልሎች መካከል አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና አፋር የሚገኙበት ሲሆን፤ የዋዜማ ባልደረቦችም ከእነዚሁ ክልሎች ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የተመለከተ መረጃ አሰባስበዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡት https://cutt.ly/vyckSL4a
    12,50024161Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    18 сент., 17:15

    ለቸኮለ! ዓርብ፣ መስከረም 8፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ በአማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች የተከሠተው ድርቅ በአስር ሺዎች በሚገመቱ እንስሳትና ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሠ መሆኑን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በሦስቱ ክልሎች በርካታ ወረዳዎች በድርቁ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ከቀያቸው መፈናቀላቸውንና በርካታ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ካሠባሠብናቸው መረጃዎች ተረድተናል።በአማራ ክልል ድርቅ ከተከሠተባቸው መካከል፣ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን እና የሰሜን ጎንደር ዞን ቆላማ አካባቢዎች ተጠቃሽ ሲኾኑ፣ በኦሮሚያ በምሥራቅ ሸዋና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች በርካታ ወረዳዎች የክረምት ዝናብ እጥረት በተለይ በሰብል ላይ መጠነ-ሰፊ ጉዳት ማድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በትግራዩ ጭላ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸውንና "አጋራሌ" በተባለች ቀበሌ በቅርቡ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል።2፤ አማጺው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ ከ"ጽምዶ" ጥምረት ጋር ግንኙነትም ሆነ ትብብር የለኝም አለ። ኾኖም "ትብብሩ" በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ኃይሎች የጋራ ስምምነት መሆኑንና ምሥረታውም በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ እንደሚያውቅ ቡድኑ ገልጧል። ቡድኑ፣ የ"ትብብሩ" ትኩረት ተቃዋሚ ኃይሎች የውስጥ ሽኩቻዎችን አቁመው በመንግሥት ላይ እንዲያተኩሩና ሠፊ መሠረት ያለው የሽግግር መድረክ መፍጠር መሆኑን ጠቅሷል፡፡3፤ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ አቡዳቢ ውስጥ በዓለማቀፍ የመጽሃፍት ሽያጭ አውደ ርዕይ ላይ በ250
    13,9007662Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    18 сент., 01:39

    ክልሎች ከሰራተኞቻቸው ደሞዝ የአደጋ ስጋት ፈንድ መሰብሰብ ጀመሩበአብዛኞቹ ክልሎች ከመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን ተመሳሳይ ቢሆንም፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ክልሎች ከፍ ያለ መጠን የሚሰበስብበትን አሠራር ዘርግቷል። ክልሉ «ሀልዋ» ብሎ በሰየመው የገንዘብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 187/2018 መሠረት፤ ከመንግሥት ሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ከ1 እስከ 2 በመቶ እንዲቆረጥ ይደነግጋል። የዋዜማን ዝርዝር ያንብቡ- https://cutt.ly/IycqN2ev
    14,800252318542Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    17 сент., 17:09изменён

    ለቸኮለ! ሐሙስ፣ መስከረም 7፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ ዛሬ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን "ጸሊሞይ" በተባለ ሥፍራ በትግራይ ኃይሎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በከባድ መሣሪያ የታገዘ ግጭት መካሄዱን ዋዜማ ሠምታለች። ከማለዳው 1 ሰዓት ተኩል ጀምሮ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ድረስ የዘለቀው ግጭት ቢቆምም፣ በአካባቢው ወታደራዊ ውጥረት መኖሩ ታውቋል፡፡ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ወደ ወልቃይት በሚወስዱ ሦስት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ማለትም በሽረ - አዲ ረመፅ፣ በማይፀብሪ - ዳንሻ እና በሽረ - ፀለምት - ሶሮቃ መስመሮች ላይ ከረቡዕ መስከረም 6 ጀምሮ መጠነ-ሠፊ የሠራዊትና የጦር መሣሪያ እንቅስቃሴ በስፋት ይስተዋል እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል።2፤ የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከዜሮ ነጥብ 5 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበትን አሠራር መዘርጋታቸውን ዋዜማ ሠምታለች፡ ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ግን ቀሪ መደረጉ ይታወሳል። ክልሎች ለመሠብሠብ የወሠኑት መዋጮ ተመሳሳይ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ መጠን ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።3፤ ዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ፤ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ ጫና ሳያደርጉ ገቢያቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን የፖሊሲ ጥናት ይፋ አደረገ። ባንኩ፣ የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ ከአገር ውስጥ
    14,2007694Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    16 сент., 17:05

    ለቸኮለ! ረቡዕ፣ መስከረም 6፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ ትምህርት ሚንስቴር፣ ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል 70 በመቶዎቹን ከተወለዱበት ወይም ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መመደቡን ማምሻውን አስታወቀ። ሚንስቴሩ፣ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ደሞ በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸው መድቤያለሁ ብሏል። ከተማሪዎች የምደባ መስፈርቶች መካከል፣ የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤትና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፣ የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም እንዲሁም የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የትምህርት ቤት ሥርጭት እንደሚገኙበት የጠቀሠው ሚንስቴሩ፣ የተማሪዎችን አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት አድርጎ መውሠዱንም ገልጧል።2፤ የዓለም ጤና ድርጅት፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የድንገተኛ የሕክምና እርዳታ ቡድን በአፍሪካ የመጀመሪያ የኾነውን ማረጋገጫ ሠጠ። ድርጅቱ፣ የአገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ የሕክምና ቡድን የማረጋገጫ እውቅና ያገኘው፣ ለጥራት፣ ለዝግጁነት፣ ለሥምሪት አቅም እና ለድንገተኛ የሕክምና ምላሽ አሠጣጥ የወጡ ዓለማቀፍ እውቅና ያላቸውን መስፈርቶች በማሟላቱና የድርጅቱን ጥብቅ የማረጋገጫ ሂደቶች በማለፉ መኾኑን ጠቅሷል። ምደባው፣ አገሪቱ የድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ አሠጣጥ ሥርዓቶችን ለማጠናከር እየሠሩ ላሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እውቀቷንና ልምዷን እንድታካፍል በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚያስቀምጣት ድርጅቱ ገልጧል።3፤ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ የኢትዮጵያ
    15,0007411322Открыть в Telegram
  • Wazema Media / Radio

    15 сент., 17:00

    ለቸኮለ! ማክሰኞ፣ መስከረም 5፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1፤ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ምክክር መክፈቻና መዝጊያ ላይ የኢትዮጵያ የኮፕ-32 ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ሳይገኙ መቅረታቸውን ዋዜማ ሠምታለች። ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ፣ም "ከቃል ወደ ተግባር" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረትና ልማት ጉባዔ ዓላማ፣ ቱርክ በቀጣዩ ኅዳር በምታስተናግደው ዓለማቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝና በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያ የምታስተናግደገውን ጉባኤ ለአፍሪካዊያን የተሳካ ለማድረግ ያለመ ነበር። በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያዊ አንጋፋ ባለሞያ ግን፤ ስብሰባው የኮፕ-32 አዘጋጅ ኮሚቴ ስብሰባ ባለመኾኑ የከፍተኛ አመራሮች መገኘት ግዴታ እንዳልነበር ገልጠው፣ የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ የሥራ ጫና ለባለሥልጣናቱ አለመገኘት ምክንያት ሊኾን እንደሚችል ጠቁመዋል። ኾኖም የፕላንና ልማት ሚንስቴር ተወካዮቹን ለስብሰባው መላክ እንደነበረበት ባለሙያው ገልጸዋል።2፤ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር፣ ከኩዊሃ መለስ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ውጪ ያሉት ስድስቱ ካምፓሶቹ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ደኅነታቸው የተጠበቀ መኾኑን ገለጠ። ኩዊሃ ካምፓስ የቀድሞ ተዋጊዎች መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል በመኾን ላለፉት አምስት ዓመታት ከቁጥጥሩ ውጭ መቆየቱን የጠቀሠው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር፣ ኾኖም ካምፓሱን ለማስመለስ ጉዳዩ
    15,7008594Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота