Последние посты

Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 17:30
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሳምሶን መለሰ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መማክርት ጉባኤ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ገልጸው፤ አደረጃጀቱ ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ ሲደረግ የነበረ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ግብረመልስ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና መማር ማስተማሩ በጥራት እንዲካሄድ ድርሻውን መወጣቱን ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳምሶን አክለውም በ2019 ትምህርት ዘመን በነበረው የትምህርት አከፋፈት ሂደት የመማክርት ጉባዔው አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው፤ የበለጠ ለስራው ዝግጁ በመሆንና በ2019 ትምህርት ዘመን የሚገጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ምንጭ በመለየት ማን መፍትሄ ይሰጥ የሚል ጥቆማ በመስጠትና የመፍትሄ ሀሳቦች በማቅረብ ድጋፋችውን መቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና ሪፎርም ዘርፍ አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው የመማክርት ጉባዔ ( ተገልጋይ ካውንስሉ) ከ2018 ትምህርት ዘመን መክፈቻ ጀምሮ በትምህርት ተቋማት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ እንዲሆን ሰፊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸው ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ የረካ የትምህርት ማህበረሰብ ከመፍጠር አንጻር ልንከተላቸው የሚገቡ የመልካም አስተዳደርና የደንበኛ አያያዝ ስነምግባሮች ላይ ግንዛቤ መያዝ ይገባል በማለት በ2019 ትምህርት ዘመንም በትምህርት ሴክተሩ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እየተመዘገበ የቆየው ውጤት ላይ ተደማሪ ውጤት እንዲመጣ አቅም ሆኖ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!https://linktr.ee/aacaebc
Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 17:30
የመማክርት ጉባኤ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ተገለጸ፡፡( መስከረም 13 /2019 ዓ.ም ) የከንቲባ ፅ/ቤት መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር የመልካም አስተዳደር መርሆችን በመተግበርና ለትምህርት ስራ ትክክለኛ ፖሊሲ፤ አሰራር መመሪያዎችና ደንቦች ላይ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ከቅሬታ የጸዳ ቀልጣፋ የአገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል።




Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 12:11
ማስታወቂያ! / BEEKSISA!(መስከረም 13/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc


Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 11:36изменён
ማስታወቂያ! / BEEKSISA!(መስከረም 13/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc


Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 11:14
https://youtube.com/shorts/8Lq_l-nViBU?feature=shareYouTubeበመዲናችን አዲስ አበባ የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች ከ20 5,500 መድረሳቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋልEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 10:30
ማስታወቂያ! 3(መስከረም 13/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 10:29
ማስታወቂያ! 2(መስከረም 13/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
23 сент., 10:29
ማስታወቂያ! 1(መስከረም 13/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 14:37
ማስታወቂያ! 2(መስከረም 12/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 14:37
ማስታወቂያ! 1(መስከረም 12/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 13:31
ማስታወቂያ!(መስከረም 12/2019 ዓ.ም )ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc




Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 10:35
መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ የትምህርት ሴክተሩ አመራርና አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡(መስከረም 12/2019 ዓ.ም ) የመልካም አስተዳደር ምንነትን መርሆችና መለያ መስፈርቶች በመገንዘብ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የትምህርት አመራርና አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የሪፎርም ዘርፍ አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የትምህርት ሴክተሩ አመራር በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ሚና በአግባቡ መወጣት እንዲችልና ከታች ጀምሮ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአግባቡ ለይቶ በመፍታት በአገልግሎት አሰጣጥ የረካ የትምህርት ማህበረሰብ ከመፍጠር አንጻር ልንከተላቸው የሚገቡ የመልካም አስተዳደርና የደንበኛ አያያዝ ስነምግባሮች ላይ ግንዛቤ በመጨበጥ ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዴት መለየትና መፍታት እንደሚገባ ቀደም ሲል ባለው እውቀት ላይ ተጨማሪ ግንዛቤ በመያዝ ብሎም መነቃቃት በመፍጠር በ2019 ትምህርት ዘመን በትምህርት ሴክተሩ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እየተመዘገበ በቆየው ውጤት ላይ ተደማሪ ውጤት እንዲመጣ አቅም መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡አማካሪዋ በተጨማሪም የከተማችን ነዋሪ ለትምህርት አገልግሎት ሲመጣ የሚያገኘው የትምህርት አመራሮችን መሆኑን አስታውሰው፤ ተገልጋይ ማህበረሰቡን በአግባቡ ለማገልገል ተጨማሪ ግንዛቤ በመውሰድ የሚፈቱ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት እንዲሁም መፈታት ለማይችሉ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አቅምን ማጎልበት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! htt




Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 04:50
ይህ የተቀናጀ የትምህርት ስርዓት ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመና የነገዋን አገር በብቃት መሸከም የሚችል አዲስ ትውልድ ማፍራት እንደሚያስችል ታምኖበታል። ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወነው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ አማካኝነት በገንዘብና በአይነት በርካታ ሀብት ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ተስብስባል። ይህ ንቅናቄ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የመንግሥት ጥረት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡና የወላጆች ንቁ ተሳትፎ የታየበት ትልቅ እርምጃ ነው።የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማስጠበቅ ስራዎች በዘላቂነት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት ያላቸው ተነሳሽነትና ክትትል መጨመሩ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Addis Ababa Education Bureau
22 сент., 04:50
ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው፡፡(መስከረም 12/2019 ዓ.ም) የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ፣ ብቃት ያለውና አገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት በማሳየት ላይ ይገኛሉ።የትምህርት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል በተጀመረው ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እና በአዲሱ የትምህርት ስርዓት አተገባበር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።ከቅድመ-መደበኛ ፣ ከ1ኛ ደረጃ እና ከ2ኛ ደረጃ ጀምሮ በራስ መተማመን ያለው፣ ጥራትና ሙሉ አቅም ያለው አዲስ ትውልድ መገንባትን መሰረት በማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ለማየት ተችላል።የትምህርት ልማት ስራ ውጤት በሂደት በመታየት ላይ የሚገኝ ሲሆን በተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የትምህርት ጥራት እየተሻሻለ በመምጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትክክለኛ አቅም ያላቸው ተማሪዎችም ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚናቸዉን ማበርከት የጀመሩት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡በዚህም በአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የተደረገው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም የተማሪዎችን ውጤትና አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲመጣ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።በቀጣይም ተማሪዎች ከዚሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትኩረት መስራት የሚገባ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን የቴክኒክና ሙያ ትምህርቶችንም ጭምር እንዲያስተምሩ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።




Addis Ababa Education Bureau
21 сент., 14:34
3. የስራ እና የግል መረጃን መለየት (Keep Professional & Personal Separate)፦ለትምህርት ክፍሉ የተሰጥዎትን ይፋዊ ኢሜይል (Institutional Email) ለሥራ እና ለምርምር ጉዳዮች ብቻ ይጠቀሙ። የግል ማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በዚህ ኢሜይል አይክፈቱ።4. ከሳይበር ማታለያዎች ይጠንቀቁ (Don’t Take the Bait)፦"የነፃ ምርምር መጽሐፍት"፣ "የነፃ ሶፍትዌር ማውረጃ" ወይም "የኮንፈረንስ ጥሪ" በሚል በኢሜይል ወይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን (Phishing Links) ከመክፈት ይቆጠቡ። ትክክለኛነታቸውን ሳያረጋግጡ መረጃዎችዎን አያስገቡ።5. ሀገር በቀል እና አለምአቀፍ ዲጂታል መድረኮችን መጠቀም፦የኢ-ለርኒንግ መድረክ (e-SHE) እና Google Workspaceን የመሳሰሉ መድረኮችን ለተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት ይጠቀሙ።6. ዲጂታል አርአያ ይሁኑ (Be a Cyber Security Role Model)፦ለተማሪዎችዎ ስለ ዲጂታል ደህንነት እና ጤናማ የኢንተርኔት አጠቃቀም በማስተማር፣ ልጆች እና ወጣቶች የተጠበቀ የሳይበር ምህዳር ባህል እንዲያዳብሩ አርአያ ይሁኗቸው።ቴክኖሎጂ መምህራንን መቼም ሊተካ አይችልም፤ ነገር ግን በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል የመማሪያ ክፍሎችን እና የትምህርት ስርዓቱን ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል፡፡ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
