Последние посты

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
18 сент., 17:44
переслано из @yaregalabegaz
የክርስቶስን ስጋ እና ደም ለመቀበል የሚበቃው ማነው?#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
13 сент., 07:42

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
12 сент., 02:57
переслано из @finotebooks1623
📚#ኢቮሊዩሺን የተረጋገጠ ሳይንስ ወይስ እምነት?#በመምህር_ያረጋል _አበጋዝ_የተዘጋጀ➥ይህ የመምህራችን የመምህር ያረጋል አበጋዝ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ ሥራቸው፣ በተለይ ትንሽ አስኳላ ትምህርት ለዘለቀው ማኅበረሰብ ሕሊናውን የሚያነቃበትና ራሱን የሚፈትሽበት ጠቃሚ መጽሐፍ እንደሆነ አምናለሁ። መምህራችን ከዚህ በፊት “ሳይንሰ እና ሃይማኖት” በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ያቀረቧቸውን ግሩም ሐሳቦች አጣጥመን ሳንጨርስ ይህን ጥልቅና የብዙዎቻችንን ጥያቄ የመለሱበትን ጠቃሚ መጽሐፍ በማበርከታቸው እግዚአብሔር ይስጥልን፣ በዕድሜ በጸጋ ይጠብቅልን፣ በቀጣዩስ ምን እንጠብቅ? እያልኩ ለአንባብያን መልካም ንባብ እላለሁ።[ዲ/ን ዶ/ር ዮሴፍ አጥላው]📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]ይደውሉልን!📞፦0913083816Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623


ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
11 сент., 15:47
переслано из @emmauset
ኦርቶዶክሳዊ የተልዕኮ ትምህርት ስንል በትክክል ምን ማለታችን ነው?https://vt.tiktok.com/ZSqPG97Ku/
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
10 сент., 15:02
መልካም አዲስ አመት


ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
9 сент., 09:52
переслано из @yaregalabegaz
#መድሎተ_አሚን#መልአከ_ብርሃን_አድማሱ_ጀምበሬ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
8 сент., 16:07
https://youtube.com/shorts/aV3Nw-7p7IQ?si=tJazMK3HegZgKY_8YouTube"ሰው ሃጢያትን አስቦ አቅዶ የሚሰራ ከሆነ እንዲህ አይነት ሰው ንስሐ ለመግባት እድሉንም ላያገኝ ይችላል" ዲ/ን ያረጋል አበጋዝEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
8 сент., 03:07
በዓለ ቅዱስ ሩፋኤልበወርኀ ጳጉሜን ከሚታሰቡ እና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በዓሉ የሚከበርባቸው ምክንያቶችም ሁለት ናቸው፤ እነርሱም አንደኛው በዓለ ሢመቱን ምክንያት በማድረግ ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤቱ ነው፡፡ ‹ሩፋኤል› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ‹ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ› ማለት ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› እንዲል (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ ‹‹በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል (ሄኖክ ፲፥፲፫)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዳለ ሄኖክ፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው፤ ላረገዙ ሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ (ኗ በማኅፀን እያለ (ች) ተሥዕሎተ መልክዕ (በሥላሴ አርአያ መልኩ /ኳ/ መሳል) ከጀመረበት
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
7 сент., 12:01
https://youtube.com/shorts/dJhyx7h9srQ?si=FCEPJ8oEI1PnzzbSYouTubeበስንፍናችን ነው እንበል ! - መምህር ያረጋል አበጋዝ #ethiopiaEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
4 сент., 04:58
በብሕትውናው ቦታ ፈጽሞ እንዳይለቅ ከመሬት በላይ ቤት ሠርቶ እንዳይኖር፣ ፀጉሩን እንዳይላጭ፣ ጥፍሩንም እንዳይቆረጥ ሚስትም እንዳያገባ ሥርዓት ሠርቶለታል፡፡ በመላከ እግዚአብሔር እየተረዳ ምግቡን መላእክት እየመገቡት እስከ አብርሃም ድረስ በፍጹም ብሕትውና ለማንም ሳይገልጥ ኑሮአል፡፡ አብርሃም የወንድሙ ልጅ ሎጥን ያስጨንቁና ንብረቱን የዘረፉ አምስቱን ነገሥታት ኮሎዶጎሞርን ድል ነሥቶ ሲመለስ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ በዘመኑ የሚፈጸም መሆኑንና አለመሆኑን ለማወቅ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቆ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ምሳሌውን ካህኑ መልከጼዴቅን ከተሰወረበት ቦታ ሄዶ እንዲመለከት ፈቀደለት፡፡ አብርሃምም የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ኅብስተ አኮቴት ጽዋ በረከት ይዞ ወደ ማዕከለ ምድር ቀራንዮ ሄደ፤ መልከጼዴቅም ተገልጦለት ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ፤ አየም ደስም አለው ….›› እንዳለው ጌታችን (መልከጼዴቅ የእግዚአብሔር ወልድ የመድኅን ዓለም ክርስቶስ) ምሳሌ ነበር፡፡ (ዮሐ.፰፥፶፰) ለዚህ ነው ጌታችን ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ አየም ማለቱ) አብርሃም ኅብስት አኮቴት ጽዋ በረከት ለመልከጼዴቅ የሰጠው፤ (ዘፍ.፲፬፥፲፰) ትውልድ ከእርሱ የማይቆጠር ግን አብርሃም ዐሥራትን አውጥቶ ሰጥቶታል፤ የአብርሃምንም መሥዋዕት አስታኮቶለታል፤ አብርሃምንም ባርኮታል፤ የጌታችን ምሳሌ የሆነው የኦሪቱ ሊቀ ካህን መልከጼዴቅን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ታስበዋለች፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም ሊቀ ካህን የመልከጼዴቅ ጸሎት ይጠብቀን፤ አሜን!!!ጾመ ዮዲትበወርኃ ጳጉሜን
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
4 сент., 04:58
ወርኃ ጳጉሜንዕለተ ምርያወርኃ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ የምትገኝ በአገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዐሥራ ሦስተኛው ወር የምትቆጠር ናት፤ ወርኃ ጳጉሜን አምስት ቀናት ያሏት ስትሆን በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ሉቃስ መውጫ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ያለው ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላታቸው ጳጉሜን እንዲህ ይተረጉሟታል፤ ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ተውሳክ፣ አምስት ቀን፣ ከሩብ፣ ከዐውደ ወር ተርፎ በዓመቱ መጨረሻ የተጨመረ ስለሆነ ትርፍ ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፱፻፭)በወርኃ ጳጉሜን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተከብረው (ታስበው የሚውሉ በዓላት አሉ፤ በሌላ ስያሜም ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች፤ ምርያ ማለት ከቀን ወደ ቀን የሚያሻግር፣ አንድም ዕለተ ኅሪት ዕለተ መድኃኒት ማለት ነው፤ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፮፻፰) ምእመናን በዚህች ወቅት ጸበል ይጠበሉባታል (ይጠመቁበታል)፡፡ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤልጳጉሜን ሦስት ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ የሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዚህች ዕለት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ በድርሳነ ቅዱስ ሩፋኤል እና በወርኃ ጳጉሜን ሦስት ቀን የሚነበበው ስንክሳርና የተጻፉት ድርሳናት እንዲህ ያስተምሩናል፤ አንዲት ክርስቲያን ሴት በቅዱስ ሩፋኤል ሰም በባሕር መካከል ባለች ደሴት ቤተ ክርስቲያን አሳነጸች፤ ሊቀ ጳጳሱ አባ ቴዎፍሎስ በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱን አከበረ፤ ከደሴቲቱ ሥር የነበረ ግዙፍ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
3 сент., 17:15
переслано из @yaregalabegaz
"የተጠራነው እንድንቀደስ ነው"#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
31 авг., 19:07
переслано из @yaregalabegaz
መታገል#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
30 авг., 14:12
переслано из @emmauset

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
29 авг., 20:01
переслано из @emmauset
ጌታን ሲከተሉት የነበሩ አይሁድ "ከሰማይ የወረደ እውነተኛ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ" የሚለውን የጌታ ቃል በሁለት ምክንያት ለመቀበል ተቸግረው ነበር። ለጊዜው ፍላጎታቸው ምድራዊውን ምግብ አበርክቶ የሚያበላቸው ሰው ነው፡፡ ሁለተኛው እንዴት ሥጋውን ለመብልነት ሊሰጣቸው እንደሚችል ማሰብ አልቻሉም። በዚህ ትምህርቱ " እንዴት ልንከተው እንችላለን" ብለውም ጥለውት ሄዱ። ይኼንን የወንጌል ክፍል ለማየት ሞክረናል። አድምጡትhttps://youtu.be/Dt2XogkyzFk?si=m15uIes48_xP5kNO
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
29 авг., 14:55изменён
ተአምራትየአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው:: ሙት አንስተዋል፤ ድውያንን ፈውሰዋል፤ አጋንንትን አሳደዋል፤ እሳትን ጨብጠዋል፤ በክንፍ በረዋል፤ ደመናን ዙፋን አድርገዋል፤ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መስርተዋል፤ በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕፃናት አብረው ኑረዋል፤ በዘመናቸው ሰይጣን ታስሯልና::ዕረፍትጻድቅ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው፣ መከራን በብዙ ተቀብለው፣ እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው በተወለዱ በ፺፱ ዓመት: ከስምንት ወር ከ አንድ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬ ቀን በ፲፻፫፻፮ ዓ.ም ዐርፈዋል:: ጌታችን፣ ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል፤ ፲ ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::የጻደቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከታቸው ይደርብን፤ አሜን፡፡ምንጭ፡- ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
29 авг., 14:55изменён
በዓለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትአምላካችን እግዚአብሔር ለነቢዩ ኤርምያስ “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሸሃለሁ” በማለት እንደተናገረ የገናናው ጻድቅ የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዜና ሕይወቱን እንዘክራለን፡፡ (ኤር.፩፥፭)ልደትደጋጎቹ ካህኑ ጸጋ ዘአብና እግዚእኃረያ የእግዚአብሔር ሰዎች ነበሩ፡፡ እነርሱም እንደሌሎች ቅዱሳን እናት እና አባቶቻቸው ልጅ አተው ኖረዋል፡፡ እንደነ አብረሃም እና ሣራ፣ እንደ እነ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ማለት ነው። እግዚኃርያም ሁል ጊዜም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ታመለክት ነበር። ከዕለታት አንዲት ቀን መላኩ ተግልጾ ልጅ እንደሚወልዱ ነገራቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመጋቢት ፳፬ ቀን ፲፻፪፻፮ ዓ.ም ተፀንሰው በሸዋ ክፍለ ሀገር በጽላለሽ ወይም በዞረሬ አካባቢ ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከእግዚኃርያ በታኅሣሥ ፳፬ ቀን በታኅሣሥ ፳፬ ቀን በ፲፻፪፻፯ ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ሲወለዱም ሥላሴን “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ” ብለው አመስገነዋል። ጻድቁ በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጿል፤ ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::አባታችን ተክለ ሃይማኖት ክርስትና ወይም የሥላሴን ልጅነት ሲቀበሉ አባቱ ጸጋ ዘአብ ሲቀድስ ያመሰግን ነበር፡፡ እናቱም ደግሞ “አንተ ልጅ አሁን ጡጥ ጥባ እንጂ” እያለች ትሞግተው ነበር። የካህን ልጅ ካህን እንዲሉ ገና ሲወለድ ጀምሮ “ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ምስጋና
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
28 авг., 14:49
переслано из @sardinon
ታላቅ የምሥራች የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች በዮሐንስ አፈወርቅ በመምህር ሽመልስ መርጊያ ተተርጉሞ ጀምሮ ገበያ ላይ ውሏል።በሰርዲኖን መጽሐፍ መደብር ታገኙታላችሁ።




ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
27 авг., 15:13
https://youtu.be/5VGAbdNmosU?si=M31d3BkqFlTD-tiSYouTubeበየቀኑ እንዲህ አድርጉ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ Yaregal Abegaz sibket ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Ethiopia Orthodox tewahdoበየቀኑ ይህን አድርጉ። በ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ Yaregal Abegaz የተሰጠ ትምህርት። #deacon #ethiopia #yaregal_abegaz #ያረጋል_አበጋዝ #ዲያቆን #tewahedo #sibket
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
27 авг., 06:41
переслано из @emmauset
https://youtu.be/jCaa_Q-auC4?si=HUJmQ49Sqcmx5H9a
