gram news
Аватар канала YeneTube

YeneTube

@yenetube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

ПроектыENРазное

152,879подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • YeneTube

    25 сент., 13:29

    በትግራይ ክልል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መቛረጡን ተጠቃሚዎች አስታወቁ።አገልግሎቱ የታጎለው ከሕጋዊ ፓርቲነት የታገደዉ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣የግል የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ሰጭ ሳፋሪኮምና መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ነው ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ያላቸውን አራት ሰዎችና ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አንድ የሮይተር ምንጭ ህወሓት የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያዘዘው የመንግሥት ወታደሮች በውጊያ ድሮኖችን ሲጠቀሙ የሞባይል ኔትዎርኮችን እንዳያገኙ የተጠቀመበት ስልት አካል ሳይሆን እንዳልቀረ ተናግረዋል።ህወሓት አስተላለፈ ስለተባለው ትዕዛዝ ቢጠየቅም መልስ አልሰጠም ሲል ሮይተር ዘግቧል። ይሁንና ለቡድኑ ቅርበት አለው የተባለ ማንነቱ እንዲገለጽ ያልፈለገ አንድ ግለሰብ በአገልግሎቱ መቋረጥ ተጠያቂው ህወሓት አይደለም መንግስት እንጂ ማለቱ ተገልጿል። ዛሬ አርብ በኢትዮ ቴሌኮም መስመር የስልክ ጥሪዎችና መልዕክቶች ወደ ትግራይ ክልል እንደማይተላለፉ ኢንተርኔትም በክልሉ እንደማይሰራ ተጠቃሚዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ዶይቼ ቨሌ የኢትዮቴሌኮም የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊን ለማነጋገር ሙከራ አድርጓል።ኃላፊው ጥያቄያችሁን በፅሑፍ አቅርቡልን ባሉን መሰረት ጥያቄያችን በጽሑፍ ብናቀርብም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አላገኘንም።Via DW @YeneTube @FikerAssefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    25 сент., 12:25

    ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአፋር እና አማራ ክልል ባሉት አዋሳኝ አካባቢዎች ባሰማራቸው ታጣቂዎች፤ ባለፈው ማክሰኞ መስከረም 12፤ 2019 ከለሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ “ጥቃት መክፈቱን” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና ህወሓት “ባሰማራቸው ታጣቂዎች” መካከል በዋግ ኸምራ ዞን አካባቢዎች እና በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ግጭቶች መከሰታቸውንም” ኮሚሽኑ አስታውቋል።ኢሰመኮ ይህን ያስታወቀው በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ፤ ዛሬ አርብ መስከረም 15፤ 2019 ባወጣው መግለጫ ነው።በትግራይ እና በአማራ እንዲሁም በትግራይ እና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ስፍራዎች የነበረው “ውጥረት” “ከጊዜ ወደ ጊዜ” ሲባባስ መቆየቱን በመግለጫው ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ በእነዚህ አካባቢዎች “የትጥቅ ግጭቶች” “መቀስቀሳቸውን” ባሰባሰባቸው “መረጃዎች እና ማስረጃዎች” ማረጋገጡን ገልጿል።በአካባቢዎቹ ላይ በአሁኑ ወቅት “የትጥቅ ግጭቶች” “እየተካሄዱ” መሆኑንም መንግስታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቋም አመልክቷል።“እነዚህ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በትጥቅ ግጭት የተጎዱ እና በበቂ ሁኔታ ያላገገሙ በመሆናቸው፤ የትጥቅ ግጭት ዳግም መከሰቱ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ላይ ተደራራቢ ጉዳትን ሊያሳድር የሚችል በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው” ሲልም ኢሰመኮ በመግለጫው አስገንዝቧል።Via:- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር@Yenetube @Fikerassefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    25 сент., 12:13изменён

    የቀድሞው የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት የነበሩት ጀነራል ታደሰ ወረደ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል።የስልክ መስመር ከመቋረጡ በፊት የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ቤታቸው በህወሓት ታጣቂዎች ተከቦ መውጣትም መግባትም አይቻልም ነበረ።ጀነራል ታደሰ ወረደ የጊዚያዊ መንግስቱን እንዲመሩ በፌደራል መንግስት የስልጣን ጊዚያቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ቢያራዝምላቸውም ለጦርነቱ ምክንያት ነው በተባለለት ምርጫ የተመረጠ «ጅምር መንግስት ወደ ስልጣን መልሻለሁ» ያለው ህወሓት እሳቸውን በሃይል አውርዶ በዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መተካቱ ይታወሳል።ጀነራሉ ስለታሰሩበት ምክንያትም ሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸው የታወቀ ነገር የለም። ሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በቤታቸው ውስጥ በቁም መታሰራቸዉ አንዳንዶች ደግሞ ከሥራ መታገዳቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።@Yenetube @Fikerassefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    9,31018822Открыть в Telegram
  • YeneTube

    25 сент., 09:59

    #እንድታውቁት፡- የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ተደረጉበአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ ተደረጉመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡በከተማው ከዛሬ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሃ ግብሩ ፍጻሜ የሚዘጉት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግበመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል። ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ መከልከሉንም አመልክቷል።ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ0111-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻልም ተጠቁሟል።መስከረም 15/2019 ዓ.ም
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    25 сент., 09:29

    переслано из @kelematadshub

    🚨 ሰበር ዜና! 🔥 ከቴምር ፕሮፐርቲስበወር 1% ብቻ እየከፈሉ የሱቅ ባለቤት የምትሆኑበት እድል እንደቀጠለ ነው::በሳርቤት,በቡልጋሪያ እና በገላንከ10ካሬ ጀምሮ እስከ 861ካሬ በፈለጉት የካሬ አማራጭከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ባለባቸው ቦታዎች፣ ለሬስቶራንት፣ ካፌ እና የንግድ መደብሮች የተመቸ።ከ1.8 ሚሊየን ብር አጠቃላይ ክፍያ ጀምሮ ወይም በ25% ቅድመ ክፍያ የሱቅ ባለቤት መሆን ይችላሉይህ እድል ለአጭር ጊዜ ስለሆነ ቀድመው ያናግሩን።+251998878106ከ 80 በላይ አፓርትመንቶች፣ የንግድ ሱቆች እና ቢሮዎች ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን መተግበሪያ ይጠቀሙ። 👇http://t.me/realtorbisrat_bot/realtorbisrat
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    25 сент., 06:19

    ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለከለከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ።አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያ እና የስርቆት ወንጀል ሲፈጽሙ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸውም ይገኛል።ወንጀል ፈጻሚዎች ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር እና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቡን እንደማያከብሩ በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።ወንጀልን ለመከላከል እና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸምን የደንብ ጥሰት ለመቆጣጠር ከዛሬ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌት ውጭ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እና ባለ ንብረቶች አስፈላጊውን እንዲፈጽሙ ፖሊስ አሳስቦ ነገር ግን ይህንን ማሳሳቢያ በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።@Yenetube @Fikerassefa
    10,700291141Открыть в Telegram
  • YeneTube

    24 сент., 17:03

    переслано из @yenetube

    🌟 በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ!✅በአዲስ አበባ prime location ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣✅ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር!✅ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጋር በጋራ (70/30) በፍጥነት እየተገነባ ያለ እጅግ ዘመናዊ compound አፓርታማ ✨ ልዩ ጥቅሞች፦ ✅Fixed Rate፦ ቤቱን እስኪረከቡ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም! ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት (progress )የሚከፈል ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ በኃላፊነት የሚስተናገዱበት 🚪 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ) 🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር🛏 ባለ 3 መኝታ (95 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 10,070,665 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,510,600 ብር🛏 ባለ 4 መኝታ (160 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 16,961,120 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 2,544,168 ብር💥ዛሬ ነገ እያሉ እድሉ እንዳያመልጥዎት ❗️አሁኑኑ ይደውሉ — ሳይቱን ይጎብኙ! 📱 ስልክ፦ +251923047904 👤 የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪና ኃላፊ 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251928579029📲Telegram :@abel211227
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    24 сент., 15:34изменён

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ-ጅቡቲ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ ቱቦ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ በጅቡቲ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።FMC @Yenetube @Fikerassefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    12,9004532772Открыть в Telegram
  • YeneTube

    22 сент., 13:47

    በኢትዮጵያ ያለው የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት እና የድሮን ጥቃቶች አስቦኛል - የተባበሩት መንግስታትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዲሱን የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት መመሥረት፣ የቀጠለውን የጸጥታ ችግር እና የድሮን ጥቃት ዘገባዎችን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ።ትላንት በተካሄደው የተመድ ዕለታዊ የዜና መግለጫ ላይ የተቋሙ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ እንደተናገሩት፣ ተመድ በኢትዮጵያ ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ወቅት በተከሰቱ አዳዲስ ኩነቶች «ጥልቅ ስጋት» እንደገባው አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ «ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን» ብለዋል።አክለውም «ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም፤ ወይም መሠረታዊ ቅሬታዎችን አይመልስም» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ወገኖች ለውይይትና ለንግግር ዳግም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።@Yenetube @Fikerassefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    6,76024222Открыть в Telegram
  • YeneTube

    22 сент., 13:34

    🌟 በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ!✅በአዲስ አበባ prime location ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣✅ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር!✅ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጋር በጋራ (70/30) በፍጥነት እየተገነባ ያለ እጅግ ዘመናዊ compound አፓርታማ ✨ ልዩ ጥቅሞች፦ ✅Fixed Rate፦ ቤቱን እስኪረከቡ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም! ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት (progress )የሚከፈል ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ በኃላፊነት የሚስተናገዱበት 🚪 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ) 🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    22 сент., 08:18

    በአዲስ ምዕራብ ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመ ብልሽት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠበአዲስ ምዕራብ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።በዚሁ ብልሽት ሳቢያ• በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው• በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው• አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው• ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው• ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው• ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው• ሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    21 сент., 15:50

    переслано из @yenetube

    ⚽️ MANO FANTASY — እንዴት መጫወት ይቻላል? 1️⃣ ቡድንህን ፍጠር ⚽️ 2️⃣ 100 ETB ክፈል 💰 3️⃣ ሊጉን ተቀላቀል 🏆 4️⃣ በየሳምንቱ ነጥብ ሰብስብ 📈 5️⃣ Chips-ህን በጥበብ ተጠቀም ⚡️ 6️⃣ TOP 30 ውስጥ ግባ እና ተሸለም! 🎁 💰 Prize Pool: 25,000 ETB 👉 @ManoFantasy_bot ቡድንህን ፍጠር። ተወዳደር። አሸንፍ! ⚽️🏆
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    21 сент., 11:00

    የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥን መታገዱን አስታወቀበኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት ተከተሎ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነት መሠረት፣ ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱ ይታወቃል።ከዚህም በተጨማሪ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ-መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፤ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነት የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ እየተላለፉበት እንደሚገኝ የሚዲያ ይዘት ክትትል ግምገማችን ውጤት ያረጋግጣል፡፡በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ፣ ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ይገልጻል።ማንኛውም ዲጂታል፣ የብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በህገወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ ወይም አስተጋብቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    10,5003518142Открыть в Telegram
  • YeneTube

    21 сент., 09:59

    🌟 በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ!✅በአዲስ አበባ prime location ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣✅ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር!✅ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጋር በጋራ (70/30) በፍጥነት እየተገነባ ያለ እጅግ ዘመናዊ compound አፓርታማ ✨ ልዩ ጥቅሞች፦ ✅Fixed Rate፦ ቤቱን እስኪረከቡ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም! ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት (progress )የሚከፈል ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ በኃላፊነት የሚስተናገዱበት 🚪 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ) 🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    21 сент., 09:04

    переслано из @kelematadshub

    🚨 ሰበር ዜና! 🔥 ከቴምር ፕሮፐርቲስበ1% ወርሃዊ ክፍያ በሳርቤት፣ ቡልጋሪያ እና ገላን ደንበኞቻችንን የሱቅ ባለቤት እያደረግን ነው።ከእርስዎ የሚጠበቀው 25% ቅድመ ክፍያ ቦታውን ማስያዝ ብቻ ነው፤ ቀሪውን በወር 1% ብቻ እየከፈሉ በ2 ዓመት ውስጥ የሱቅ ባለቤት ይሆናሉ።ግልጽ የሆነ የ ግንባታ ሂደት ስላለን ግንባታው በምን ደረጃ ላይ እንዳለ እየተመለከቱ የሚከፍሉበት የአከፋፈል ሁኔታም አለ። ይህ እድል ለአጭር ጊዜ ስለሆነ ቀድመው ያናግሩን።+251998878106ከ 80 በላይ አፓርትመንቶች፣ የንግድ ሱቆች እና ቢሮዎች ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን መተግበሪያ ይጠቀሙ። 👇http://t.me/realtorbisrat_bot/realtorbisrat
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    21 сент., 08:59

    "የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ኤርትራ አሰልፋቸዋለች !" - አቶ ጌታቸው ረዳየቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የኤርትራ መንግሥት ከግብፅ ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካን ሰላም ለማናጋት እና ቀጣናውን ለማተራመስ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።ይህን ያሉት ከ"Pulse of Africa" ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።በኤርትራ ያለው ከባድ የኑሮ ውድነት እና መጥፎ የፖለቲካ ሁኔታ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጉን ያነሱት አቶ ጌታቸው "የሀገሪቱ ሠራዊትም ሀገር ለመጠበቅ ሳይሆን ፕሬዚዳንቱን ለመጠበቅ ብቻ የቆመ ነው" ብለዋል።በዚህም ምክንያት ኤርትራ ራሷ በቀጥታ በጦርነት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ ሌሎች ታጣቂዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ግጭቶችን ከድንበሯ ራቅ ባሉ ቦታዎች ለማቀጣጠል እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።አቶ ጌታቸው እንዳሉት፤ እንደ ፋኖ፣ ኦነግ ሸኔ እና አሁን ደግሞ ሕወሓት ያሉ አካላት የኤርትራን ዓላማ ለማሳካት እና የጦርነቱን ሸክም እንዲሸከሙ ተሰልፈዋል።በተለይም ሕወሓት እና የኤርትራ መንግሥት አብረው መሠለፋቸው እጅግ አደገኛና የትግራይንና የአማራን ሕዝብ ለከፋ ሁኔታ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል።@Seledadotio @Seledadotio
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    21 сент., 08:44

    ቀን 11/01/19 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ 📞09 03 01 00 06 📞09 57 97 40 82 🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption ✨ደመወዝ===150dollar ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የት/ት ደረጃ===10&12 🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/ ✨ደመወዝ===200-600 dollar ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ ልምድ===0-5አመት ✨የት/ት ደረጃ= 30000+ 🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport ✨ደመወዝ===13500+ ✨ፆታ===ወ/ሴት ✨ልምድ===0አመት ✨የ/ት ደረጃ===10 🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
  • YeneTube

    21 сент., 08:32

    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናት እንደሚጨምር በሚጠበቀው የዝናብ ሁኔታ ሳቢያ የኮሌራ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።በክልሉ “ሁሉም አካባቢዎች” ይህንኑ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ “የመከላከል እና የዝግጁነት ስራ” እንዲጠናከርም ኢንስቲትዩቱ መልዕክት አስተላልፏል።ተቋሙ የኮሌራ ወረረሽኝ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክቱን ያስተላለፈው፤ በክልሉ ስር ለሚገኙ 12 ዞኖች ጤና መምሪያዎች እንዲሁም ለሶዶ፣ ዲላ እና አርባ ምንጭ ከተሞች በጻፈው ደብዳቤ ነው።ባለፈው አርብ መስከረም 8፤ 2019 የተጻፈው ይህ ደብዳቤ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከዓመታት በፊት የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ፤ “ቀላል የማይባል” ህመም እና ሞት ማስከተሉን አስታውሷል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሁኑ ወቅት የኮሌራ ወረረሽኝ “በየትኛውም አካባቢ” ያልተከሰተ መሆኑንም የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በደብዳቤው ጠቅሷል።ሆኖም ለበሽታው መከሰት “ምቹ ሁኔታዎች ሲፈጠር”፤ ወረረሽኙ “ዳግም ሊከሰት የሚችልበት” አጋጣሚዎች እንዳሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።ተቋሙ ለዚህ በማስረጃነት ያቀረበው፤ በኢል-ኒኖ የአየር ንብረት ክስተት ምክንያት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዝናብ ሁኔታ እንደሚጨምር የሚቴዎሮሎጂ የትንበያ መረጃዎች ማመልከታቸውን ነው።Via Ethiopia Insider @YeneTube @FikerAssefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
  • YeneTube

    20 сент., 15:37изменён

    የአሜሪካ አስቸኳይ መግለጫ❗️👉የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ሪያድ፣ አቡ ዳቢ፣ ዶሃ፣ እየሩሳሌም እና ሌሎችም ከትናንት ጀምሮ ያወጡት የተቀናጀ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።በየመኑ ሁቲዎች እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭትና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃቶች ማሻቀባቸው ግጭቱ በፍጥነት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊስፋፋ እንደሚችል ተስጋቷል።👉 የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ የሲቪል አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ከዚያ ውጭ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን እና ዜጎችን ኢላማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ኤምባሲዎቹ አሳስበዋል።👉በአካባቢው የሚገኙ የአየር ክልሎች በድንገት ሊዘጋጉ ስለሚችሉ፣ የበረራ ስረዛዎች እና ከፍተኛ የመንገድ መስተጓጎሎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።👉 በዱባይ፣ ዶሃ፣ አቡ ዳቢ፣ ሪያድ እና ጅዳ አየር ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የበረራ ሁኔታቸውን ከአየር መንገዶቻቸው ጋር በቀጥታ እንዲያረጋግጡ ታዟል።👉 በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የሌሉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ አካባቢውም ሆነ በአካባቢው አየር ክልል አቋርጠው የሚያደርጉትን ጉዞ "በድጋሚ እንዲያጤኑት" ምክር ተሰጥቷል።@Yenetube @Fikerassefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    12,6003431Открыть в Telegram
  • YeneTube

    20 сент., 14:56

    በኢትዮጵያ “አካታች የሽግግር መንግስት” ለመመስረት ያለመ የሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ።“የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን ትብብር ከመሰረቱት ውስጥ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደሚገኙበት ተገልጿል።ይህ የተገለጸው ዛሬ እሁድ መስከረም 10፤ 2019 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዜና ማሰራጫዎች በኩል በተላለፈ መግለጫ ነው።መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን አፋብንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው።አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውም በቪዲዮ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ተመልክቷል።የእዚሁ ትብብር ሌሎች መስራች አባላት የኦጋዴን ህዝብ ነጻነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ እና የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንደሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @YeneTube @FikerAssefa
    Иллюстрация к посту канала YeneTubeИллюстрация к посту канала YeneTube
    12,6005946108Открыть в Telegram