Последние посты

ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
22 сент., 18:58
Are you ready to watch the discussion? 😁The reason I want to delete the channel is that I am struggling with many health issues, both mental and physical. I still need your prayers since the medication is not helping much. We will see what happens with the channel in the future, but I don't think I am capable of continuing.


ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
22 сент., 18:41

ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
22 сент., 07:43
In the next 5 days, I will either delete the channel or transfer ownership to another person. Alternatively, I might only post articles within one or two weeks.So please pray for me, and I will do what is best for this channel.
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
20 сент., 06:27изменён
በቅርቡ በአቡ እና ዴቭ መሐከል “ሃይማኖት በዚህ ዘመን ያስፈልጋል ?” በሚል ርዕስ የተደረገው ውይይት ላይ የራሴን አስተያየት እንዲሁም የእያንዳንዳቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን የገለጽኩበት ነው። በደንብ ኮፒ ሊንክ ፣ ሼር ፣ ላይክ እና ሪፓስት እያደረጋችሁ እዩት።https://vt.tiktok.com/ZSqvtgda4/
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
18 сент., 15:32изменён
POV :- በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ሊያውም ኢንተርኔት ባለበት ዘመን አንድ ኤቲስት “በዓለም ላይ ከ 4000 በላይ አማልክት አሉ ፥ አንተ 3999 ን በተመለከተ ኤቲስት ስትሆን አንዱን ትቀበለህ። ስለዚህ እኔ ማምነው ከአንተ በአንድ አምላክ ያነሰ ነው።” ሲል ስሰማ My honest Reaction be like ...
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
15 сент., 12:35
አስባብ አል-ኑዙልእስልምናን በምዕራብ ምሁራዊነት (Western Scholarship) ወይንም ኦሪየንታሊዝም (Orientalism) ጥናት መነጽር መመልከት እና ማጥናት ስትጀምሩ የምታስተውሉት ነገር ፣ ለየትኛውም በእስልምናው ውስጥ ለሚታመኑ እንዲሁም ለቁርዓን የመገለጥ ሂደት “ታሪካዊ” ትረካ ለሚሰጡ ትውፊታዊ ምንጮች ቅንጣት ያህል ቦታም ሆነ ጊዜ የማይሰጡ መሆናቸው ነው፤ ይኸውም ከአንድ ልበ ወለድ የማይታናነስ ታሪካዊ ተአማኒነት ስላላቸው ነው። ለአብነትም «The Function of Asbāb Al-nuzūl in Qurʾānic Exegesis» በተሰኘ ምሁራዊ መጣጥፉ ፕሮፌሰር እንድሪያስ ሪፒን (Andrew rippin) የተለያዩ የቁርዓን አንቀጾች የተገለጡበት ሰበብ እየተባሉ የሚነሱ ታሪኮች ምንም ዓይነት ታሪካዊ ተአማኒነት እንደሌላቸውና ከሥነ-መለኮታዊ ምክንያት በሚመነጭ ተነሳሽነት ፣ በሰዎች ቁርዓን መለኮታዊ መገለጥ እንዳለውና ይህም መገለጥ ታሪካዊ እንደሆነ ለማሳየት የተፈጠረ ልበ-ወለድ እንደሆነ በብዙ ማስረጃዎች እና ምሁራዊ ትንተናዎች አሳይቷል።አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ



ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
14 сент., 05:21изменён
ፈላስፎች :- “አንድ ነገር የተፈጠረ ነው የሚባለው ህልውናው የጀመረ ከሆነ ወይንም ያልነበረበት ጊዜ ካለ ነው አይደል ?”ኢብኑ ተይሚያ be like ...
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
10 сент., 18:01изменён
ከዚህ በፊት «ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመው ምንም ዓይነት መሲሓዊ ትንቢት የለም» የሚለውን ሙግት በኢብኑ ተይሚያ ጽሑፍ እንደገደልነው ሁሉ ፣ አሁን ደግሞ በኢብኑል ቀይም ጽሑፍ መቃብሩ ላይ 12 ቁጥር ሚስማር የምንመታ ይሆናል።https://www.sonsofathanasius.com/am/articles/ibnul-qeym-ena-mesihawi-tnbitochSonsofathanasiusደቂቀ አትናቴዎስ | Sons of Athanasius — Orthodox ApologeticsEthiopian Orthodox Tewahedo Church apologetics, patristics, and digital library.
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
10 сент., 13:19изменён
የምን ነቃ ደንገጥ ነው ኡስታዝ 😭“ነቅዕ” የሚለውን “ነቅዐ” እያለ ማንበብ ከየት ነው የተማርክ ? ግሪኩ ላይ ዝም ብለነው ነው ወደ ግእዝ የመጣው ፣ “ምነው እናቴ በዕንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ” ማለት አሁን ነው።
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
9 сент., 09:42изменён
ትዕይንተ ግብረ ዝሙት (Pornography) መመልከት በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል እንደ ተንሰራፋ እንዲሁም መፍትሔ እንደሚያስፈልገው በጥናታዊ ሥራዎች ላይ ተመርኩዞ የሚያብራራ መጣጥፍ ነው።https://www.sonsofathanasius.com/am/articles/teynte-gbre-zmut-pornography-chgrochu-ena-mefthew-kfl-1
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
8 сент., 15:10изменён
ለአዲሱ ዓመት ክህዶተ አምላክ (Atheism) ላይ ጥሩ ጽሑፍ ለእናንተ የማጋራት ዕቅዳችን ምን ያህል እንደሆነ የምታውቁት የተለያዩ የፍልስፍና እና የአመክንዮ ቃላትን በአማርኛ ለመተርጎም የሚያግዙ መጻሕፍት (በተለይ የዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌን) በእግር በፈረስ እያልን ስንገዛ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር በ 2019 ዓ.ም የአምላክ መኖር ላይ ጥያቄ የሚፈጠርባቸው ወጣቶች በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀላሉ ፈልገው የሚያነቧቸው እና የሚማሩባቸው መጣጥፎች እንደምንጽፍ ተስፋ አደርጋለሁ።አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ


ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
7 сент., 07:03изменён
ሙስሊሞች አምላክ የሚሉት አላህ የአምላክነትን መስፈርት እንደማያሟላ በዚህም አምላክ ሊሆን እንደማይችል የሚሞግት መጣጥፍ ነው ፥ በእርግጠኝነት አዲስ ነገር ታገኙበታላችሁ።አንብቡ ፥ አስነብቡ !https://www.sonsofathanasius.com/am/articles/alah-yeamlaknetn-mesfert-ayamwalam-kfl-1
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
6 сент., 14:18изменён
አንዳንድ ነገሮችከሳምንታት በፊት ድረ-ገጻችን ችግር እንደገጠመውና ለማስተካከል እየሞከረን እንደሆነ ነግሬያችሁ ነበር። እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሊያግዙን የመጡት ልጆች በአዲስ መልኩ እንዲሰራና ለአንባቢያን ምቹ እንዲሆን ሃሳብ ስላቀረቡ በአዲስ መልኩ ሲዘጋጅ ቆይቷል። አዲሰ ዓመት ሳይገባም ሥራ ይጀምራል የሚል እምነት ያለኝ ሲሆን እስከዛው ድረስ አንዳንድ አዳዲስ ነገሮች ላይ ጥቂት ለማለት አሰብኩ።በመጀመሪያ ከዚህ ቀደም በነበረው ድረ-ገጽ እስልምና ክርስትና ተዋሥኦ ላይ ብቻ አተኩረን የምንጽፍ የነበረ ሲሆን በዚህኛው ድረ-ገጽ ግን ሌሎች ሦስት ዐበይት ርዕሶች ጨምረን ለመጻፍ የምንሞክር ይሆናል። እነርሱም ኤቲዝም ፣ ፕሮቴስታንቲዝም እና መንፈሳዊ ህይወት ናቸው። በእርግጥ ዋና ትኩረታችንን የምናደርገው የእስልምና ክርስትና ተዋሥኦ እንዲሁም ኤቲዝም ላይ ሲሆን ፕሮቴስታንቲዝም እና መንፈሳዊ ህይወትን በተመለከተ ግን ወቅታዊ በሆኑ እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ብዙ የተጻፈ ምንጭ በማያገኝባቸው ርዕሶች ላይ ብቻ የምንጽፍ ይሆናል።መጣጥፎች ሳምንታዊ መርሐ ግብር ይዘው እንዲጻፉ ያቀድን ሲሆን ይህን ለማሳካት በየርዕሱ ከአንድ በላይ ጸሐፊ እንዲኖር እንጥራለን። እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ የሆነ መጣጥፍ ጽፈው በድረ ገጻችን እንዲለቀቅ የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ ተገቢውን ግምገማ ተደርጎላቸው ካለፉ መጣጥፎቹን የሚንለቃቸው ይሆናል።በተረፈ አቅደን ከመቅረት ፣ አስበን ከመተው ልዑል እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ በጸሎታችሁ አግዙን !አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
29 авг., 21:41
«Icons were intimately connected with the origins and growth of Christianity itself.»The Dawn of Christian Art in Panel Paintings and Icons by Norman E. Muller and Thomas Mathews



ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
29 авг., 21:28
Iconoclasm as Discourse: From Antiquity to Byzantium By Jas Eisner


ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
28 авг., 10:45
በአንድ ራስ ሁለት ምላስዛሬ የተናገሩትን ነገ የሚያጥፉት ሙስሊም የእምነት ጠበቆች አሁንም በአንድ ራስ ሁለት ምላስ መሆናቸውን ቀጥለውበታል። ኡስታዝ ወሒድ ስለ የጥበብ ነገረ ክርስቶስ (Wisdom Christology) በሚያብራራበት አንድ ቪዲዮ “ ... ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።” (ማቴ 11፥19) የሚለው ኃይለ ቃል ክርስቶስን አያመለክትም በማለት የተናገረ ሲሆን ይህም ንግግሩ “እውን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነውን ?” በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ.29 ላይ ጥበብ በልጆችዋ ጸደቀች የተባለው ክርስቶስ በሥራው መገለጡን እንደሚያሳይ በመግለጽ በቀጥታ ክርስቶስ ራሱን በሦስተኛ መደብ ጥበብ እያለ ስለ መጥራቱ ከጻፈው ጋር ይጋጫል።መቼም አንድ ሰው መጽሐፍ ሲጽፍ የሚያምንበትን እና የሚቀበለውን ነገር ለሰዎች ለማስገንዘብ ነው ፥ ታዲያ ኡስታዙ እንዴት እዩልኝ ስሙልኝ ብሎ ባሳተመው መጽሐፍ ያሰፈረውን ሊክድ ቻለ ? ወይንስ እንደ አየሩ ሁኔታ የእርሱም አቋም ይለዋወጣል ? እንዲያስ ከሆነ ከእርሱ የተማሩ እና መጽሐፉን ገዝተው ያነበቡ ሰዎች ስላስተማራቸው እና ስላስነበባቸው ነገር እንዴት እርግጠኛ ሊሆኑ ይችላሉ ? የሚለውን ጥያቄ ለህሊና ትቼዋለሁ።አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ



ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
28 авг., 10:45

ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
24 авг., 08:09изменён
መሲሓዊ ትንቢት እና ኢብኑ ተይሚያየራሳቸውን እምነት የሚጻረር ቢሆንም እንኳ የክርስትና አስተምህሮን ከተቃወመላቸው ከይሖዋ ምስክሮች አንስቶ እስከ ሥዝም ሰብአዊ ምሁራን ሙግቶች ድረስ የሚቃርሙትና የሚያግበሰብሱት ሙስሊም ዐቃቤያነ እምነት አሁን ደግሞ “ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድም ትንቢት አልፈጸመም” በማለት መሞገት ጀምረዋል። ይህ ዓይነቱ የሙግት መስመር በታሪክ ውስጥ የአይሁድ ሊቃውንት በክርስቲያኖች ላይ የሚያቀርቡት ዋና መከራከሪያ ሲሆን ትክክለኛ ባይሆንም እንኳ ክርስቲያኖች እንደ ማስረጃ ለሚያቀርቧቸው ጥቅሶች አጸፋዊ ምላሽ እና ተለዋጭ ትርጉም ሲሰጡ ኖረዋል። ዘግይተውም ቢሆን በመሲሓዊ ትንቢቶች ላይ የአይሁድ ሊቃውንት የሚያቀርቡትን ሙግት እንዲሁም አጸፋዊ ምላሽ ማንበብ የጀመሩት ተንባላት እነዚያ ያረጁ እና ያፈጁ እንዲሁም በተደጋጋሚ የተረ’ቱ ሙግቶችን እንደ በቀቀን በመደገም ላይ ይገኛሉ።ሆኖም ዐቃቢያኑ ከአይሁድ ሊቃውንት በቃረሙት ሙግት በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሊቃውንት ጋር እየተቃረኑ እንደሆነ የሚያውቁ አይመስልም። ስለሆነም በዚህ አጭር መጣጥፍ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ “አል-ጀዋብ አስ-ሰሒሕ” በተሰኘ ሥራው በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች የሚስማሙባቸው በአይሁድ ግን ተቃውሞ የሚቀርብባቸው የክርስቶስን መሲሕነት የሚያሳዩ መሲሓዊ ትንቢቶች መኖራቸውን ስለመግለጹ በአጭሩ የምንጽፍ ይሆናል - መልካም ቆይታ !ኢብኑ ተይሚያ “አል-ጀዋብ አስ-ሰሒሕ” በተሰኘ መጽሐፉ የቀደሙ ነቢያት የሙሐመድን መምጣት መተንበያቸውን ያነሳና ፣
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
24 авг., 08:09





ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ
21 авг., 07:33
W Ibn rushdኢብኑ ተይሚያ የኢብኑ ሩሽድን ሙግት እንዴት አጣጥሎና አጣሞ በማቅረብ በቂ ምላሽ ሳይሰጥ እንደሚያልፍ ወይንም ቁልምምተ ወገራ (Straw man fallacy) የተሰኘ አመክንዮአዊ ሕጸጽ እንዴት እንደሚሰራ ተመልከቱ ፤ ዕውቁ የኢብኑ ተይሚያ ምሁር ዮሐንስ ሁቨር (John Hoover) ራሱ «Ibn Taymiyya’s contention is of course disingenuous.» ብሎ እስኪጽፍ ድረስ ማለት ነው። ሆኖም “አባይን ያላየ ምንጭን ያመሰግናል” እንዲሉ ክርስትና እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የጻፈውን መጽሐፍ ስትመለከቱ ደግሞ “ኢብኑ ሩሽድን ምን አደረገው ?” ያስብላችኋል። በነገራችን ላይ አንዳንድ ድኩማን አብዱሎች ኢሳይያስ 9:6 ለሙሐመድ ነው የሚሉት ከእርሱ አንብበው ነው - የሆነው ሆኖ ባለ ምጥቁ አዕምሮ ፈላስፋ መሆኑን ግን መካድ አይቻልም።ለማንኛውም አንድ ዐቃቤ ነኝ የሚል አብዱል ኢብኑ ተይሚያ በምሁራዊ ጥናት ውስጥ እያገኘ ያለውን ቦታ አንስቶ እንዲሁም በክርስትና ላይ የጻፈውን መጽሐፍ ጠቅሶ የሰራውን ቪዲዮ እያየሁ ነበርና ኢብኑ ተይሚያ በ Al-Jawab As-Sahih ለሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ መተንበይ ያነሳቸው ሁሉም ሙግቶች Valid and sound ናቸው ብሎ ካመነ ይህን እምነቱን ይከላከል ዘንድ የውይይት ጥሪ አቅርቤለታለሁ።አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ



