Последние посты

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
23 сент., 14:01
• ስለ ሌላው አይመለከተኝም…ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ"…ዘመነ ካሤ ለምን ኮፍያ አድርጎ መግለጫ ሰጠ? እሱ መግለጫ ሲሰጥ ሌሎቹ የትአሉ? ስለዚህ ዘመነ ብቻውን ነው ማለት ነው የሚዋጋው? እንዴት ዐማራ ከትግሬ ጋር ይስማማል? ኦሮሞ፣ ዐማራ እና ትግሬ እንዴት አንድ ላይ ይቆማሉ? እንትና እኮ ዐማራን እንዲህና እንዲያ ያደረገ ነው። ዐማራ እንዴት ትግሬ ያደረሰበትን በደል ይረሳል? ቆይ እሺ አሸንፈው ቢመጡ እንኳ እንዴት ሆነው ተስማምተው ሊሠሩ ነው? ኧረ ምንም አያመጡም። ደግሞም የትም አይደርሱም። ጠንክረው ገፍተው ከመጡም አንፋታቸውም። አንለቃቸውም። ብላ ብላ እያሉ 24/7 ቲክቶክና ዩቲዩብ ላይ ተወዝፎ መተንተኑ አሁን ላይ ምን ይጠቅማል? ምንም አይጠቅምም እኮ።"…ወዳጄ የትንተና ዘመን፣ የማንቃት፣ የማደራጀት ዘመን ትናንት አልፏል። አልፏል አልኩህ አባቴ። እንቅልፍ አጥተን፣ ሌት ተቀን እየተሰደብን፣ እየተረገምን፣ ማድያት እስክናወጣ ድረስ ኡኡ ያልንበት ዘመን አልፏል። ማንን ለማንቃት ነው በየቲክቶኩ 300 ሰው ይዘህ ዋይዋይ የምትለው? ከእንግዲህ ማነው በኤርሚያስ ዋቅጅራ የሚነቃው። ለራሱ እምነት የሌለው፣ ያ የድሮውን ሳንቲም አስገብተውበት እንደፈለጉ የሚያናግሩበትን የቴሌ የግድግዳ ስልክ የመሰለ ሶዬን ምን ልሁን ብለህ ነው ልስማው ብለህ የምትደክመው? ሳንቲም ለከተተበት ሁሉ የሚለፈልፍን ሶዬ፣ አስር የዐማራ ፋኖ አስር ሺ የኦሮሞ ወታደር እንደ በግ ይነዳል፣ ኦሮሙማ ማለት እንዲህ እና እንዲያ ነው በማለት ኦሮሞን በሁሉ ዘንድ መሳቂያ መሳለቂያ ካደረገ በኋላ በ11ኛው ሰዓት አሁን ደርሶ የኦሮሞ አዳኝ ለመሆን ፍዳ መከራውን የሚበላ፣ የአቢይ አሕመድ 196,666 ውሸቶች እያለ ሌክቸር ሲሰጥ፣ የአቢይ አሕመድን ስብእና በገጀራ ሲከካ የከረመ ሶዬ አሁን መጥቶ አቢይ ጻድቅ ነው ሲለኝ እንድሰማው ነው የምትፈልገው? ኧረ ተፋታኝ አባው።"…ወዳጄ የዐማራ ሕዝብ ኩሩና ጨዋ ሕዝብ ነው። የዐማራ ፋኖ አሁን የሚኮነንበት፣ የሚከሰስበት ምንም አይነት ምክንያት እና ወንጀል የለም። ዐማራ ሲጀምር የለውጡ ተቃዋሚ አልነበረም። እንደ ዐማራ ለውጡን የተቀበለ፣ የደገፈም አልነበረም። ነገር ግን በዚህ ድርጊቱ አልተወደሰም ተናቀ፣ ተገደለ፣ ተዘረፈ፣ ተፈናቀለ፣ ታሰረ እንጂ። ዐማራ አኩርፎ ፈጥኖም ወደ ጫካ አልገባም፣ መጀመሪያ ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄን መልሱልኝ እያለ ነበር የወተወተው። ይሄም ተግባሩ እንደፈሪ አስቆጠረው? ዛሬም ሰልፍ? ዘሬም እዬዬ? ዐማራ እንደ አዝማሪ መሰንቆ እየገዘገዘ መሸለል እንጂ ክላሽ ይዞ ተኩስ አያቅም እያሉ እነ እስታሊን ገብረ ሥላሴ ሳይቀር ዛሬ ከእነ ጌትነት አልማው፣ ቶማስ ጃጃው ተሽለው የዐማራ ፋኖ ቋሚ የ24/7 አክቲቪስት ከመሆናቸው በፊት ኢንዶሚን እያሉ ሲሰድቡት የነበረ ነው። ዐማራ ግን ሙያ በልብ ብሎ ከሰልፍ ወደ ሰይፍ ተሸጋግሮ ዛሬ ያ የናቁት የት ይደርሳልም ያሉት አነ ብራኑ ጁላ በሳምንት ቀበቶውን አስወልቀን ልክ እናገባዋለን ያሉት ፋኖ በሦስት ዓመት ፈርጥሞ፣ ሌሎችንም ነገዶች አስተባብሮ ከባድ ሚዛን ሆኖ ሲመጣ ተሰብስበህ ብትተነትን ምንም አባክ አታመጣም። እየነገርኩህ ነው።"…አሁን ላይ አየር ይዞ ፋኖን ማውገዝ፣ እንዲህና እንዲያ ብሎ በብላኔ መተንተኑን አይጠቅምም። እከሌ ከእከሌ ጋር እነ እገሌም ከእነ እገሊት ጋር እንዴት ትብብር ይፈጥራሉ? እያልክ ማላዘኑን ተወውና ይልቅ የሚበጀው እንዲህ እያልክ ራስህን መጠየቁ እና ሥልጣኑን እንዴት ላስረክብ ብለህ መጀገኑ፣ መድፈር፣ መቁረጡ ላይ ነው። ጠይቅ ራስህን አንድ የነበረው ጠላቴ ፋኖ እንዴት ሰባት ጠላቶች አደራጅቶ፣ አፍርቶብኝ አስተባብሮ ነቀነቀኝ? እነሱስ እንዴት አምነው ተከተሉት? ምን አይነት የድንክ ፓለቲካ አራማጅ ብሆን ነው ከሁሉም ጋር ጦርነት የከፈትኩት ብለህ የራስህን ስንፈተ ፖለቲካ ገምግም። የአውርቶ አደር ፋርሴ ቡላ ካድሬዎችህን እና ጭፍን ደጋፊዎችህን አሰልፈህ እየዬ ብትል ሰሚ የለህም። ስለዚህ የሚሻልህ እንዲያ ማድረግ እንጂ አሁን ትንተናህን ማን ይሰማል። እኔ ራሱ ርእሰ አንቀጽ መጻፍ ካቆምኩ ስንት ጊዜዬ።"…እኔና እኔን መሰል ጓደኞቼ ሰኔ ግም ሲል የዛሬ ሦስት ዓመት ጀምሮ በሬ ጠምደን፣ ሞፈር ቀንበራችንን በትከሻችን ተሸክመን፣ እርሻችን ስናርስ፣ በዚያ በክረምት፣ በዚያ ቁር፣ በቆፈን፣ ውርጩ እየመታን፣ በረዶ እየወቀጠን፣ በጭቃ መከራ ስናይ እናንተ እኮ ሃኒሙን ላይ ነበራችሁ። በሸነና እያላችሁ። እኛ ሦስት መስከረም የእርሻችንን አረም ስንኮተኩት፣ ስንነቅል፣ ፀረ ተባይ ፀረ አረም መድኃኒት ስንረጭ፣ ሰብሉ አብቦ፣ ለፍሬ ደርሶ ከጦጣ፣ ከዝንጀሮ፣ ከአይጠ መጎጥ፣ ከጃርት ስንከላከል ስንጠብቅ እናንተ እኮ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳር አበባ፣ በሪዞርቶቹ በሸነና ስትሉ ነበር። አሁን ግን ማነህ ይሰማል? እኔ እና ገበሬዎቹ ለፍሬ የደረሰውን ሰብላችንን እሸቱን መቅመስ ጀምረናል። እንኩቶ እያነከትኩ በምበላበት ሰዓት አስሬ መጥተህ ትንተና እያልክ ትን እስኪልህ ተንትን። መብትህ ነው። እኔ ግን አልሰማህም።"…ያነዜ ብልግና ዐማራን በጋራ እንውጋ ብሎ ኤርትራ ሄዶ ደጅ ሲጠና ፋኖ ዝም ነው ያለው። አንተ ኢሱ ጀግና ስትል ነበር። ብልግና ሕወሓትን ፕሪቶሪያ፣ ኦነግን ጃልመሮን ታንዛኒያ ድረስ ወስዶ ሲጀነጅናቸው፣ ዐማራን እስከመጨረሻው ከምድረገፅ እንጥፋው ብሎ ሲወተውታቸው፣ ሱዳን ሄዶ አልቡርሃንን እግሩ ስር ወድቆ ቅበረን ሲለው ዐማራ ምንም አላለም። በብልግና የተጠየቁት ሁላቸውም የኦሮሙማው ቁማር ገብቷቸው ዐማራን አንወጋም ሲሉ እና እንዲያውም ከዐማራ ጎን ነው የምንቆመው ሲሉ ደርሰህ ለምን? እንዴት ይሆናል? ብሎ መጮህ ልክ አይሆንም። ልክም አይመጣም።"…የዐማራ ልጆች ግን አሁንም ደግሜ እላለሁ። የዐማራ ፋኖ ገበሬዎች፣ ደጋፊዎች፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብራችሁ የነበራችሁ በሙሉ የዐማራ ፋኖን አሁንም ተቹት። መሪዎቹን ገምግሙ፣ ምቾት ተሰምቷቸው እንዳይዘናጉ፣ በለሆሳስም፣ ከፍ ባለ ድምጽም ውቀሷቸው። ገስጿቸው። ሓሳብ ሽጡላቸው። ታዲያ ይሄ ሲሆን እንደ ስኳድ፣ እንደ ፖለቲካው ቅማንት፣ እንደ ሸንጎ፣ እንደ ብአዴን፣ እንደ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ እንደ ኦሮሙማው ብልግና ካድሬዎች አይደለም። በፍቅር ጩሁባቸው። ምንአባክ? የትአባክ ብላችሁ አስጠንቅቋቸው። የወያኔን የማይታመን፣ የእባብነት፣ የኮብራ፣ የመርዛምነት የኋላ ታሪክ እያመጣችሁ አስጠንቅቋቸው። አትፈሩአቸው። አትሽኮርመሙ። የድሮን ቦንብና መድፍ ታንክ የማይፈሩ ጀግኖች የወዳጅ ምክር አይፈሩም። አይፈሩም ደግሞም አይኮሩም።"…ለምሳሌ እኔ አርበኛ ዘመነ ካሤን የምቆጣው፣ የምወቅሰው፣ ከፍ ሲልም ምንአባክንስና ነው፣ እረፍ፣ ዋ የምልበት መንገድ እና ኤርሚያስ ዋቅጅራ፣ ፓስተር ምስጋናው፣ አያሌው መንበር፣ ሞጣ ቀራንዮ ወዘተረፈ የሚሉበት መንገድ አንድ አይደለም። የእኔ ቅቤ ነው። አንጀት አርስ የወዳጅ ቁጣ ነው። የሌሎቹ ግን የቅናት፣ የብልግና፣ የመደዴነት ነው፣ የባንዳነት ነው። ምክርና ወቀሳ፣ ቁጣና ምርቃትም ልዩነት አለው። እደግመዋለሁ በትብብሩም ሆነ በምኑ ቅሬታ ያላችሁ፣ ያልጣማችሁ ነገር ያለ ዐማሮች አሁንም የህልውና ጉዳይ ነውና ጎሽ፣ ጎሽ በርቱ አንበሶች ምናምን ብቻ ሳይሆን ባልኳችሁ መሠረት እንደ ብረት ቀጥቅጡአቸው፣ በሁለት ወገን እንደተሳለም ሰይፍ እንዲሆኑ አድርጓቸው።"…በተረፈ
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
23 сент., 14:01
• ልመክራቸው ነኝ። በርበሬ በሚጥሚጣ ላጥናቸው ነኝ።


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
23 сент., 12:17изменён
• ምክሩ ይቆይ እና በርግቦቼ ሪፖርቶች ልጀምር…"…ፊልድ ማረሻው ሃኒባጀር ዘመዴ ሆይ ‼ በሁሉም የራያ አካባቢዎች ጦርነቱ ተጀመሯል።"…ትናንት እንደነገርኩህ የትብብር ኃይሎቹ ጦርነቱን ከመስቀል በኋላ ለማድረግ አስበው የነበረ ቢሆንም ፀረ መስቀል፣ ፀረ የዐማራ እስላም የሆነው የፅንፈኛው የኦሮሞ ወሀቢይ እስላም እና የጽንፈኛው የደቡብ ጴንጤ ስብስብ የሆነው አገዛዙ ግን ለበዓሉም፣ ለዐማራና ለትግሬም ሕዝብ ደንታ ስለሌለው ትናንትናውኑ የከባድ መሳሪያና በድሮን ድብደባ ጦርነቱን ጀምሮታል። ትምህርት ቤት አውድሟል። ምስኪኖችንም ገድሏል። ሕዝብ ላይ መተኮስ ከጀመርክ አለቀልህ። እንደሞትል ቁጠረው።"…በነገራችን ላይ በጦርነት ወቅት ወታደር ለወታደር ተታኩሶ በጦርነቱ የሚሞት፣ የሚገደል ካለ ማንም አይከሰስም። ምክንያቱም ጦርነት ነዋ። ክስ የሚመጣው ሲቢሎችን እና ተቋማትን ማውደም ስትጀምር ብቻ ነው። አገዛዙ ብቻ ሳይሆን የትብብር ኃይሎችመ ቢሆኑ እንደዚያው ነው። የሚወጋቸውን መውጋት፣ ማውደም፣ መደምሰስ የጦርነት ሕጉ ይፈቅዳል። በድሮን በለው በታንክ፣ በክላሽ በለው በፍልጥ ባገኘኸው ተናረት። ግን ወታደር ለወታደር። ሕዝብ አይነካም። ምርኮኛም አይነካም። ቁስለኛ በተቻለ መጠን ይታከማል። በተረፈ ሃቅ አለኝ ካልክ ተባባል። ውቃው፣ ይውቃህ። ያሸነፈ ይነግሣል። አለቀ።"…እናም ዘመዴ የትናንቱን ጦርነት ተከትሎ ቆንጆዎቹ ዛሬ ወደ ንጋቱ አካባቢ በተኩለሽ በኩል ጀምረውታል። በእስከአሁኑ መረጃ መሠረትአይና ቡግና የሚገኘው የአገዛዙ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። አይና ቡግና አሁን በቆንጆዎቹ ቁጥጥር ስር ገብታለች። 💪💪💪👉 በተኩለሽ በኩል የገባው የቆንጆዎቹ ጥምረት የአገዛዙን ሠራዊት እየለበለበው ነው። የተኩለሹ ከተደመሰሰ በቀጥታ ቆቦ እና አካባቢዋ ላይ እንደ አንበጣ የሰፈረው የአገዛዙ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ይቆረጣል። ቆንጆዎቹ የተኩለሹን ከደመሰሱት በአርበት አድርገው በአራዱም በኩል ካለው ትልቁ የመከላከያ ካምፕ ነው ብቅ የሚሉት !!!• ጠዋት 12:51 ደቂቃ ላይ👉 ከቆቦ - ደሴ ያለው የፌደራል መንገድ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል !• ጠዋት 1:45👉 ቆንጆዎቹ የሰቆጣ ከተማን ከበባ ውስጥ አስገብተው ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እያስባሉት ነበር። ቆንጆዎቹ እዚያው ሰቆጣ ከተማ የሚገኘውን የመምህራን ኮሌጁን እና ዙሪያውን ተቆጣጥረውታል። በአጠቃላይ ከትንሽ ሰዓታት በኋላ ሰቆጣ ገቢ ትሆናለች። ልጆቿንም ናፍቃለች !!! 💪💪💪• ጠዋት 3:09👉 ከደብረ ጀመዶ ወጣ ብሎ ጥራሪ የሚባል ቦታ ላይ አገዛዙ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል። የደረሰ የጉዳት አልተዘገበም።• ረፋድ 5:12👉 1ኛ፦ ከወልዲያ- ጋሸና የሚወስደው ወሳኝ ቦታ ጥቁር ውኃ ላይ በቆንጆዎቹ ተከርችሞ ተዘግቷል።2ኛ፥ ስሪንቃ፥ መሃል አምባ እና በዚሁ አካባቢ የሚገኙ ከወልዲያ -ደሴ የሚወስደው የፌደራሉ መንገድ በቆንጆዎቹ ተከርችሟል፥ የአገዛዙ ሠራዊት ውጭ ነፍስ፣ ግቢ ነፍስ እያለልህ ነው !!!💪3ኛ፥ ደብረ ጀመዶ፣ በረሃ ማሪም በቆንጆዎቹ እጅ ገብተዋል።• ረፋድ 5:53 ላይ👉 የአገዛዙ ሠራዊት ከጎብየ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ካራይንሳ የምትባል ቦታ ላይ ባከማቸው ከባድ መሳሪያ ወዳገኘበት እየተኮሰ ይገኛል !• በመጨረሻም አድንደ ሰበር ቁጠረው።👉 የላስታ ላሊበላ የሰላም እና ደህንነት ሐላፊው እስከ አጃቢዎቹ ተሸኝተዋል ! 💪 የነበሩባት ፓትሮልም ተቃጥላለች።


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
23 сент., 11:42
መልካም…"…የወፎቼ አጫጭር ሪፖርቶች ደርሰውኛል። ከዚያ በፊት ግን ዛሬ ቀኝ ትከሻዬን እየሸከከ፣ እየሸከከኝ "ዘመዴ ምከር፣ ምከር፣ ምክር ስጣቸው፣ ስጣቸው" አሰኘኝ።• እኔ ፊልድ ማረሻው ሃኒባጀር ዘመዴ ልምከር አይደል? 😁 ያው የእኔ ምክር ደግሞ የታወቀ ነው። ቃሪያ በሚጥሚጣ በዳጣ፣ ሬት በግራዋ በጌሾ የሆነ አቃጣይ ግን ፈዋሽ የሆነ ምክር ነው።• ልምከር አይደል?



Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
23 сент., 07:26
• መስክረም 13/2019 ዓመተ ምሕረት"…በነገራችን ላይ እኔ ትብብሩን አልነቅፍም፣ አልቃወምም፣ ስሕተትና ልክ ያልሆነ ነገር ሳገኝ፣ ሳይ ስመለከት እንደተለመደው "በመጽሐፈ ፋኖ አንቀጽ 12 ንዐስ አንቀጽ 7/4 ላይ የተጻፈውን የተቹዎች መብትና ግዴታ የሚለውን አንቀጽ በመጠቀም ያንኑ እሳት የሚተፋ ብዕሬን እና የጭቃ ዥራፌን በማንሳት እለበልበው ዘንድ ሕጉ ይፈቅድልኛል። እንደዚያ ነው የማደርገው።"…አሁንም ግን እኔ ዘመዴ ሙሉ ትኩረቴ ጥምረቱ ላይ ሳይሆን የደከምኩለት፣ የተሰደብኩበት፣ ብዙ ወዳጅ ያጣሁበት፣ አሸባሪ የተሰኘሁበት፣ ማዲያት ያወጣሁበት፣ እንቅልፍ አጥቼ የኖርኩበት የዐማራ ፋኖ ላይ ብቻ እና ብቻ ላይ ነው። ጥምረቱን በተመለከተ ከድል ዜና በቀር ዝብዘባ ውስጥ አልገባም። አይመለከተኝም። ለጥምረቱ ሺ ምንተሺ አዲስ ምልምል አይደክሜ፣ አይሰለቼ ፕሮፓጋንዲስቶች አሉት። ትናንት በፋኖ፣ በዐማራ ምክንያት እኔንም ሆነ ዐማራን እንደ ሕዝብ፣ ፋንኖን እንደ ድርጅት ሲያንቋሽሹ፣ ሲሰድቡና ሲረግሙ የነበሩ አዲስ ገቢ ቱክቱካዎች ስላሉለት አልጨነቅበትም።"…የእኔ ትኩረት ፋኖ ነው። ልጄ፣ አለኝታዬ፣ መከታዬ ፋኖ ነው። እጸድቅበታለሁ፣ መንግሥት ሰማያት እገባበታለሁ፣ ሀገሬን ያድንልኛል፣ ሰንደቅ ዓላማዬን ከፍ ያደርግልኛል ብዬ ተስፋ ሳይሆን እምነቴን የጣልኩበት ፋኖ ላይ ነው። እንደዚያ ነው።"…አሁን አብዮቱ ለመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል። ክለብ ፋኖ አስቀድመው የነበሩት ግብ ጠባቂዎች፣ ተከላካዮችና አማካዮቹ ከአጥቂዎቹ ጭምር እንዳሉ ናቸው። ፋኖ ቡድኑ ላይ የጨመረው የግራና ቀኝ መስመር አጥቂዎች፣ ተመላላሽ እና ተከላካዮቹን አጋዦችን ነው። የቡዱን ቁመና ስገመግመው ዘንድሮ ሻምዮን መሆኑ እርግጥ ይመስላል። እኔ ስለደመገጡ፣ 24/7 ቁጭ ብለው ስለ ፋኖ ቡድን ስለሚንጫጩ የሌላ ቡድን ደጋፊዎች አያገባኝም። አይመለከተኝምም። እነሱ ላይ የማየው ጠባይ እኔን ድሮ ያደርገኝ እንደነበረው አይነት ነገር ነው። አሁን እኔ ስለ ፋኖ እንቅልፍ የማጣበት ሰዓት አይደለም። ፋኖ ልጄ ነው። ለአቅመ አዳም ደርሷል። ጭቅጨቃ አያስፈልገውም። ምክር ግን አይቋረጥበትም። አሁን እኔ ፋኖን ድሉን በጉጉት የምጠብቅበት ሰዓት እንጂ እንደነ ጃዋር፣ አሉላ፣ ኤርሚያስ እንቅልፍ የማጣበት ሰዓት አይደለም። ገባችሁ ኣ?• ለማንኛውም እናንተ ግን እንደምን አደራችሁልኝ።


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 16:44изменён
👆②✍✍✍ "…በአላማጣ ዙሪያ ዛሬ ውሎውን ይልማ መርዳሳ አቢይ የፈረመበትን ከ17 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል። በዚህም ወያኔ የተለያዩ ተተኳሾችን እና አንዳንድ ነገሮችን ትሸከማላችሁ ብላ በአንድ ቦታ ላይ ያስቀመጠቻቸው የቀን ሠራተኞች፣ ለሸክም ይሆናሉ ብላ የገዛቻቸው አህያ፣ ግመል እና የተለያዩ እንስሳት በአንድ ላይ አከማችተውት የነበረ የተለያዩ ተተኳሾች እና መሳሪያዎች በድሮን ተመትቷል። በነገራችን ላይ ዘመዴ ሕወሓት መችም አትማርም። እንዴት ብትለኝ ፋኖን ተመልከተው ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ በዚህ መጠን በድሮን ተመትተው አያውቁም። እነዚህ ግን ሁሌም በጅምላ እንደተጨፈጨፉ ነው። ለምን ከፋኖ እንደማይማሩ አይገባኝም? ሌላው ደግሞ ዐማራ ጥብቅ ዲሲፕሊን ስላለው ምስጢር ጠባቂ ሆኗል፣ ትግሬ ግን ስለተከፋፈለ አስተኳሹ የትየለሌ ሆኗል። ለዛሬ ይኸው ነው በቀጣይ ነገሮችን እየተከታተልኩ አሳውቅሃለሁ። ሰላም እደር ፊልድ ማርሻል ሃኒ ባጀር ዘመዴ ብላኛለች።"…እሺ የርግቤን ሪፖርት እንዴት አያችሁት። ሪፖርት መረጃዋ ከተመቻችሁ አስተያየታችሁን ጻፉላት። ቤተ መንግሥት እና መከላከያ፣ ብሔራዊ መረጃ አገልግሎት የሄዱት ወፎችና እርግቦቼም በስራ ላይ ተጠምደዋል። በተለይ ኮምፒዩተር አካባቢ ያሉቱ ጉድ ነው እያሳዩኝ ያሉት።• ስምምነ ‼
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 16:44изменён
• ወቅታዊ የሸዋና የራያ ሁኔታ፦"…ፊልድ ማርሻል ሃኒባጃር ዘመዴ ሆይ ! እኔ ወደ ወሎ ወደ ቤተ ዐምሓራ ከመሄዴ በፊት ገና መንገድ ስጀምር ብዙ መኪና ከቤተ ክህነት ሲወጣ ስላየሁ ወዴት ነው የሚሄዱት ብዬ እስቲ ልከተላቸው ብዬ መከተል ጀመርኩ። የምሥራቁን አዲስ አበባ በር ይዘው መጓዙ ጀመሩና ሞጆ ላይ ወደ ዝዋይ መስመር ሲሄዱ ተከተልኳቸው። ከሰዓታት በኋላ ሻሸመኔ ደረሱ። ዝቅ ብዬ ሳይ የቤተ ክርስቲያን ምረቃ ነው አሉኝ። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቀል የኦሮሞ ወሀቡያ እስላሞች እና የኦሮሞ ጴንጤና ዋቄፈና ባለ ሥልጣናት መከልከላቸውን፣ የተሰቀለውንም ማውረዳቸውንም ሰማሁ።"…ቆይቶም የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ነፍሰ ገዳዩ አቡነ ዜና ማርቆስ እኔም እኮ እሮሞ ነኝ፣ ስለዚህ ሰንደቅ ዓላማው መሰቀል አለበት ብለው ቆመው ቢያሰቅሉም እስላሞቹ ባለ ሥልጣናት፣ አንተ ኦሮሞ ብትሆንም የቱለማ ኦሮሞ ነህ። ከኦሮሞነትህም ዐማራነትህ ነው የሚጎላው። የቱለማ ኦሮሞ የኦሮሞነትንም መስፈርት አያሟላም። የዓለም ስምህም አሰፋ ነበር። አሰፋ ደግሞ የኦሮሞ ስም አይደለም። የጵጵስና ስምህም ዜና ማርቆስ ነው። ዜና ማርቆስ ደግሞ የቡልጋ ሰው ናቸው። እናም በኦሮሞ ጉዳይ አያገባህም። መብቱ የእኛ ነው። የፋኖ ባንዲራ አንሰቅልም። የኦሮሞ ባንዲራ የእኛን የአባ ገዳንም ባንዲራ አንስቀልም፣ የግድ ጨርቅ መሰቀል አለበት ካላችሁ የአርጀንቲናነ እና የእስራኤልን ሰማያዊና ነጭ ስንሰቅልላችሁ ነበር። እሱ ደግሞ እስራኤል ፍልስጤምንና ኢራንን ስለደበደበች ድጋሚ በኦሮሚያ እኛ የወሀባ እስላሞች እያለን አይሰቀልም። ባይሆን የስልጤ ባንዲራ
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 15:05
• ዴየሞ።መጣች…"…የሸዋና የራያ ወቅታዊ ሪፖርት ይዣለሁ ነው የምትለው። እኔ በሰሜን በኩል በሱሉልታ በደራ መስመር ወደ አምባሰል ስሔድ ርግቤ ደግሞ በሸዋ ለ ወደ ራያ ነበር የበረረችው። ያየችውን እና የታዘበችውን እያስረከበችኝ ነው።• መልእክቷን ከፍቼ ላንብበውና ቀሽሬ እንደወረደ ላቅርብላችሁ አይደል?


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 13:50
• ግሸን ደርሻለሁ…"…ግሸን ከአዲስ አበባ ደሴ 400 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ከደሴ 82 ኪሎ ሜትር ተጉዘው በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ በ482 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የጌታችን የአምላካችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀሉ የሚገኝባት ተራራ ናት።"…በአሁን ሰዓት የግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ ዐምሓራ ምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ነው። ባለፈው ሳምንት የአገዛዙ አንድ ሙሉ ክፍለጦር በደቡብ ወሎ በዳውንት ያለቀው እና የተደመሰሰው በቆረጣ ገብቶ ግሸንን አስለቅቆ አለሁ፣ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ነው ለማለት ነበር። ግን አልተሳካም። አሁን ግሸን በቆንጆዎቹ ቁጥጥር ስር ናት።"…የኦሮሙማው መንግሥት በትእቢት ተሞልቶ፣ በእብሪት አብጦ፣ ያጎረሱትን እጆች በሙሉ ነክሶ፣ ውለታ ቢስ ሆኖ፣ የበላበትን መሶብ ገበታ ገልብጦ፣ ወጪት ሰባሪ ሆኖ ተወጣጥሮ በዐማራ ላይ የሠራው ግፍ አሁን ተግባራዊ ዋጋ ወደማስከፈሉ ገብቷል። በሀገረ ኢትዮጵያ ብዞ ሚልዮን ሰዎች ከሚሳተፉባቸው ክብረ በዓላት በቁጥር ጥቂት እንደሆኑ ይታወቃል። የቁልቢው ቅዱስ ገብርኤል፣ የአክሱም ጽዮን፣ አዲስ አበባ የመስቀል ደመራ፣ የጎንደር እና የአዲስ አበባ የጥምቀት በዓል፣ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ እና ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ናቸው።"…ከእነዚህ ውስጥ ሙሉ ክልል ትግራይ በትግሬዎቹ እጅ ነው። ብልፅግና ምንም ዓይነት ቁጥጥር የለበትም። ግሸን ደብረ ከርቤም ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ ነው። የአካባቢውንም፣ የገዳሟንም ፀጥታ የሚያስከብረው የዐማራ ፋኖ ነው። ይሄ ማለት ለአገዛዙ
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 12:34изменён
ማስታወሻ…"…እኔና ወፎቼ በነበረን ስብሰባ በጊዜ የተገደበ ሹመትም እንደተሰጠኝ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። ከዛሬ መስከረም 12/2019 ዓመተ ምሕረት ከዕለተ ቅዱስ ሚካኤል ጀምሮ አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ ወደ አጎት ሀገር ጀርመን ወደ መጠለያ ዋሻዬ እስክመለስ ድረስ በኢትዮጵያ ቆይታዬ አዲሱ መጠሪያ ስሜ የሚከተለው ይሆናል።• ፊልድ ማሽራል ሃኒ ባጀር ዘመዴ• አከተመ።"…ከተቻለ እንዲያው ደስስ እንዲለኝ ለበአሉ ድምቀትም ሲባል በአዲሱ ማእረጌ አሁኑኑ መጥራት ብተጅምሩ ብዬ አሳስባችኋለሁ። ማን በጀር ነበር ያሉኝ እኔኑ ጠፋኝ ስሜ። አዲስ ስም ስለሆነ እስክትለምዱት ድረስ ብትቸገሩ ነው።• ዘመዴ ከራየን ወንዝ ማዶ ስመለስ ነው ይሄኛው ማን ባጀር የሚለው ግን በሃገር ቤት ቆይታዬ ወቅት የምጠራበት ስሜ ነው። ሰምታችኋል። 😂 …ዘና ፈታ እያልን ነው የምንዘግበው። መጨናነቅ ብሎ ነገር የለም።• እንዴት ነኝ ግን ፊልድ ማረሻነቱ ተስማምቶኛል?


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 11:55
• መልካም…"…የተወደዳችሁ የቴሌግራም መንደር ነዋሪዎች ሆይ! እኔ ተወዳጁ፣ ተናፋቂው፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከሩ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ ባለ ማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ የተነከሩት ፊልድ ማረሻ ዘመዴ እና ተወዳጆቹ ታማኞቹ ወፎቼ እንደተለመደው ለእናንተ ትኩስ፣ ትኩስ የሆኑ መረጃዎችን ልናካፍላችሁ በማሰብ ረዘም ካለ የእረፍት ጊዜ በኋላ አሁን ወደ እናንተ ተመልሰናል።"…እኔና ወፎቼ ረዘም ላሉ ቀናት በመጪው ጊዜ ለሚጠብቀን ከፊታችን ላለው የጦርነት እና የራብ ጊዜ ሕዝብ መረጃ በሚያገኝበት አግባብ ላይ ለመመካከር በማሰብ ሌት እና ቀን ግሩም የሆነ ስብሰባ እና ውይይት ስናደርግ ከርመን ሁላችንም ለእረፍት ከሄድንበት ተመልሰን የሥራ ስምሪት ወስደን ወደ መሬት ወርደን ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴ ጀምረናል። ንስሩ ብቻ ነው ለጊዜው አሜሪካ ላይ በምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረን ነውር ለማጽዳት፣ ሴራ ለማክሸፍ የሚቆየው እንጂ ሌሎቹ ወፎቼ እና ርግቦቼ በሙሉ የሥራ ስምሪት ወስደው በየቦታው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የቤተ መንግሥቱ ሌባም መረጃ ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሷል።"…እኔም ከነ ሙሉ የፊልድ ማረሻ የማእረግ ልብሴ በቀጥታ በርሬ ዛሬ ንጋት ላይ አዱ ገነት አዲስ አበባ የገባሁ ሲሆን፣ መንገዱም፣ መንደሩም ፍርስርስ ብሎ አበባና ሳር ብቻ ሆኖብኝ ቅብዥርዥር ቢልብኝም ለትንሽ ሰዓት ዞር ዞር ብዬ አዱ ገነትን አይቼ፣ ከመስቀል በዓል በፊት ለጠቋር ዋቃ ጉራቻ በአል የቱለማ ኦሮሞዎቹ ከወርሀ ነሐሴ ጀምረው በ4 ቢልዮን ብር የኦሮሙማው በጀት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚጨፍሩ




Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
22 сент., 09:09
"…የእኛ እግዚአብሔር በተለይ ደግሞ የእኔ እግዚአብሔር ይችላል። አምላኬ ይችላል። የእውነት፣ የሐቅ፣ ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ሁሉን ማድረግ ይችላል። እግዚአብሔር አሸናፊ ነው።"…ዘወትር ከፊት ከኋላዬ ቅደሚ የምላት የእኔ አማላጅ፣ የእኔ እናት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድግል ማርያም ለአፍታም ያህል ለሰከንዶች ተለይታኝ የለማወቋነ የማረጋግጠው በዚህ በዚህ ጊዜ ነው።"…የተወረወረብኝን ጦር አምላኬ አበባ አደረገልኝ። አዲስ ዘመንም፣ አዲስ የሥራ በርም ከፈተልኝ። የተወረወረብኝን ድንጋይ ሰብስቤ ምርጥ ቪላ፣ ምርጥ ሃውልት እንዳንፅም ሁሉን አመቻቸልኝ። ወጥመድ ተሰበረ። እኔም አመለጥኩኝ። እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ ሁሉም ነገር ይለወጣል። እግዚአብሔር ይመስገን። ዳይ ወደ ሥራ ተንቀሳቀስ። ይቅርታ ነገሩን ሁሉ ከትቶታል። አለቀ፣ ሃላስ።• እናንተ ግን እንደምን አደራችሁ?



Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
21 сент., 20:02изменён
• ልዩ ዝግጅት…• በዮፍታሔ ሾው የቲክቶክ አዳራሽ https://www.tiktok.com/t/ZTy1mV8UR/• ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ… https://www.youtube.com/live/gAGwW9brldw?is=XEOhWZZH8Ky44hGS"…ሁላችሁም ተጋብዛችኋል


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
21 сент., 08:41
መስከረም 11/2019 ዓመተ ምሕረት"…የጥምረቱ ክርክር፣ ሙግት ይቀጥል። የአገዛዙም ሆነ የተቃዋሚው ኃይል ደጋፊዎች ጎራ ለይታችሁ በቃላት መጠዛጠዙን ቀጥሉ። ይበጀኛል ያላችሁትን ደግፋችሁ የራሳችሁን ጻድቅ፣ ሌላውን ኃጥእ፣ ቡልጉ፣ ጭራቅ አድርጋችሁ ኡኡ፣ ወየው ወየው ማለታችሁማለታችሁም ሆነ ለምትደግፉት አካል ሽንጥን ይዞ መከራከር ተፈጥሮአዊ ነው ቀጥሉበት። ሄዶ ሄዶ አንደኛችሁ በፈሊጥም ሆነ በፍልጥ ማሸነፋችሁ አይቀርም። እናም ተሟገቱ። ግን ደግሞ የድርቁ ነገር እንዳይረሳ።"…ድርቁ ከመጣ፣ ከሰፋ መከላከያም ፋኖም፣ ጥምረቱም ሊያስቆመው አይችልም። ለመዋጋትም፣ ለመከራከርም ምግብ ወሳኝ ነው። ያለምግብ ክርክርም፣ ጦርነትም ዋጋ የለውም። ለመዋጋትም ሆነ ለመከራከር በቅድሚያ መብላት አለብህ። በባዶ ሆድ ጦርነትም ክርክርም ከንቱ ነው። የራበው ሰው አቅመቢስ ነው የሚሆነው። እናም ተዋጊዎችም፣ ተከራካሪ ደጋፊዎችም ከውጊያችሁ እና ከክርክራችሁ ጎን ለጎን ስለ ድርቁ፣ ስለራቡ እየጸለያችሁ ቢሆን ይመከራል።"…እግዚአብሔር ሊቀጣን የመጣበት መንገድ እየገረመኝ ነው። ከመላ ሀገሪቱ የሚደርሱኝ መረጃዎች እያስደነገጡኝ ነው። ተመስገን እዚህ እዚህ ቦታ እንኳን ቢሆን ድርቁ እዚህ እዚህ አከባቢ ምርት ስላለ ይካካሳል ብዬም እንዳልፅናና የሚያደርግ ነገር ነው እያየሁ ያለሁት። እናም አገዛዙም ቅድመ ዝግጅት ቢያደርግ፣ ሕዝቡም ቢጸልይ መልካም ነው።"…ወለጋ ኦሮሞዎቹ ዐማራን ጎዳን ብለው እህል ከጎተራ፣ ለንግድ የሚሄደውን ከመኪና አውርደው እሳት ለቀቁበት። የዐማራ አምላክ ደግሞ በሌላው የኦሮሞ ግዛት፣ ትርፍ አምራች


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 21:05
መልካም…"…ዛሬም እንደ ወትሮው በቲክቶክ መንደራችን ከ60 ሺ በላይ ሕዝብ መርሀ ግብራችንን ተከታትሎዘል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🙏🙏🙏• ምሽቱ እንዴት ነበር?


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 16:08изменён
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 01:30 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።• ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html• በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1OGwbnAbbLPKB• በራምብል 👉 rumble.com/v7fqulu--zemede-september-20-2026.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a• ቲክቶክ 👉 tiktok.com/@zemedkun.b• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Zemed TV Yahsat 52.5° East 11977 H 27500• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Mereja TV Niesat / Eutelsat 8 B Freq. 11.636 Vertical SR: 27.500


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 15:20
• በዛሬው መርሀ ግብራችን…"…ልጅቷ " ፀረ ኢትዮጵያ የጨረቃ ጳጳሱን ለምን ራሷን ለአደጋ አጋልጣ እንደቀረጸቻቸው ከራሷ ከልጅቷ አንደበትም ትሰማላችሁ" ።• ዛሬ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ቃሪያ በሚጥሚጣ የመሰለ ዝግጅት ነው።• ዝግጁ?


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 14:28
ሰበር ዜና…• ጥምረቱ ይፋ ሆኗል። አዲዮስ…ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) የተሰጠ መግለጫኢትዮጵያ በብልጽግና ግለሰባዊ አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ እጅ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ ዋነኛ መገለጫዋ፡ ጦርነት፣ የዘር ፍጅትና እልቂት እንዲሁም ፍፁም ድህነት ሆነዋል። ሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት የፈረሰባት፣ ሚሊየኖች የከፋ ድህነት ውስጥ የወደቁባትና የተፈናቀሉባት፣ ለዜጎቿ የሚሆን ተስፋ የጠፋባት፣ ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ሀገር አጥፊ ጦርነቶች የሚታወጁባት፣ አምባገነናዊ አገዛዝ የተጫነባት እና እንደሀገር ከወደቀ ሀገረ-መንግስትነት አልፋ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባት እንዲሁም በቀጠናውና በዓለም አቀፍ ደረጃም በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚዊ እና በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ወደጠርዝ የተገፋችና ተሰሚነቷን ያጣች ሀገር ሆናለች።አገዛዙ በተዛባ ትርክትና በፀረ-ሕዝብ መንግስታዊ መዋቅር ላይ የቆመ፣ ከምክንያትና ከእውነት፣ ከእኩልነትና ከሕዝቦች አሳታፊነት፣ ከፍትሕና ከነጻነት፣ ከሕዝብ ክብርና ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የተጣላ ሰላማዊና ገንቢ መንገዶችን የማይከተል ስለሆነ ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን እየበላ ያለውን ጦርነት የመግታት፣ ዘላቂ ሰላም የማምጣት፣ የዜጎችን መብትና ነጻነት የማረጋገጥ፣ ሕግና ሥርዓትን የማስፈን፣ የሕዝቦችን መከራና ሰቆቃ እንዲሁም ድህነትንና ኋላቀርነትን የማስቆም ፍላጎትና አቅም የለውም። ይህ አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት ለውጭ ኃይላት ቅጥረኛ በመሆን የሕዝቦችን ጥቅም በመሸጥ ሀገሪቱን ተላላኪና ጥገኛ ሀገር አድርጓት ይገኛል።በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝቦች




Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 13:35изменён
"…በኢትዮጵያዊው ሥነ ፈለክ ሳይንቲስት በመምህራችን በመጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ በዕለቱ ሰርግ ላይ በብቸኝነት የታየው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይሄ ከመሪጌታው ጥምጣም ላይ የታሰረው ባንዲራ ነው።• የኢትዮጵያዊው ሊቅ ሰርግ በየት ሀገር ሰርጉ እንደተደረገ የውጭ አገር አድናቂዎቹ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።"…አይደለም ይሄን የሚያክል ለሰማይ ለምድር የከበደ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ይቅርና በሀገሬ ገጠር በደሀ ገበሬ ሰርግ፣ ሞቱ ቀብሩ ሳይቀር ሰንደቅ ዓላማ አይለይም። አሁን ግን በአዲስ አበባ ኦሮሙማው በጀመረው የፀረ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዘመቻ ላይ ቤተ ክህነቱን ተጠቅሞ በቤተ ክርስቲያን የትኛውም አገልግሎት ላይ ሰንደቅ ዓላማው እንዳይታይ አድርጓል። አድናቂው ነኝ የኦሮሙማው።"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምትገኝበት ስፍራ ሁሉ አሁን ከኦሮሚያ እና ከትግራይ ውጪ አይደለም አሜሪካ፣ ካናዳና አውሮፓ ጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በየትኛውም የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ላይ ይሰቀላል። ይውለበለባል። በአዲስ አበባ ግን ኢንጂሩ።"…ለነገሩ አንደኛ ሚዜው ሄኖክ ኃይሌ አይደለምን? ሄኖክ ኃይሌ ባለበት ስፍራ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ማየት ዘበት ነው። ሄኖክ ለዶላር ቅፈላው ሲባል ብቻ ወደ አውሮጳ፣ ካናዳና አሜሪካ ሲሄድ ብቻ ነው የግዱን ሰንደቅ ዓላማው ከዐውደ ምህረቱ ላይ የሚታየው።• ሮዳስ ምክር ስለሚሰማ ይሄንንም በምሽት መርሀ ግብራችን ላይ አንስተን እንደ ኮሶ፣ እንደመተሬ ያለ ምክር በነጭ ነጯን ከዘመዴ መርሀ ግብር ላይ አንስተን በዘመድ ቴቪ እና በመረጃ ቴቪ ላይ በሰፊው


Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
20 сент., 11:39
መልካም…• ዛሬ በዘመድ ቴሺ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ስናወጋ ከምናመሽባቸው አጀንዳዎቻችን መካከል አንደኛው የአይተ አሮን አፅብሃ ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነው። አበጥረን እንነጋገርበታለን።• በዚህ ጉዳይ ብዙ ነገሮችን እናጠራለን።• በትግራይ ላይ በጉልበት የተጫነን ወንበዴ ወንጀል እና የግል ኃጢአት እንደ ሕዝብ የትግራይ ሕዝብ የሚሰደብበት ምክንያት እንደሌለም እንሞግታለን።• በዚህ ሰውዬም ሆነ በትግራይ ባለችዋ የሻአቢያ እና የምዕራባውያን ኤጀንቶች ባቋቋሙት በትግራይ የጨረቃ ጳጳሳት ጉዳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትወቀስበት ምክንያት እንደሌለም አበክረን እንወያያለን• አይደለም ከእንግሊዝ ተልእኮውን ተቀብሎ ከጁንታው ጋር ሆኖ ጦርሜዳ ከርሞ፣ ሀገረ ትግራይን እመሰርታለሁ ሲል የከረመ ፍንዳታ ሻአቢያ መነኩሴ ነኝ ባይ ይቅርና በሥጋ ዓይን እንደ ቅዱስ የምናያቸው ቢስቱ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ለሳተው ሰው እንጸልያለን እንጂ ከሃይማኖታችን እንደማንናወጽም አስረግጠን እንወያያለን።• አንዳንድ አስላሞችንም ቀይ መስመር እንዳያልፉ፣ በማያገባቸው ገብተው እንዳይፈተፍቱ ኮስተር፣ ቆፍጠን ያለ መልእክት እናስተላልፋለን። በእኛ ሓይማኖት መነኩሴ ሆነ፣ ጳጳስ፣ ወዛደር ሆነ ወታደር ዶክተር ኢንጂነር፣ የፈለገ ይሁን የፈለገ መድፈር፣ መድፈር ነው፣ ወንጀል ነው። በኃይማኖታችን የተከለከለ ነው። የተከለከለውን ሕግ የጣሰ ደግሞ ይቀጣል። ሕግም፣ ሥርዓትን አለን።"…እናም በአንድ ሃይማኖትን ለማርከስ፣ ሃገርን ለማፈረስ፣ እንግሊዝ ከርሞ፣ ከእንግሊዝ የአክሱም ልጅ ደፍሮ፣ ወደ ትግራይ ሄዶ በዚያም

