gram news
Аватар канала ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

@zena24now

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

ПроектыENНовости

40,957подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 16:43

    ለበርካታ አመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት የምናውቀው የአባይ ቲቪ ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ ከከባድ ህመም ጋር እየታገለ ይገኛልጋዜጠኛው የኩላሊት ህመም ገጥሞት በህክምና ተቋም በመተኛት እንዲሁም እየተመላለሰ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል።ህመሙ የማንኛውንም ሰው አቅም እንደመፈታተኑ ብሎም እስከ ንቅለ ተከላ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚፈልግ ለጋዜጠኛው የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል።ጋዜጠኛ ዮሴፍ ለሀገር ውስጥ ስፖርት ብሎም ለሙያው የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው።የድጋፍ ገንዘቡ ገቢ የሚደረገው በባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃን በክረፂዮን የሂሳብ ቁጥር አካውንት ነው።ኢ/ን/ባንክ :- 1000729159895 - ወይዘሮ ብርሃን በኩረፅዮን#ዳጉ_ጆርናል
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 16:07

    ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 70 በመቶ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው አያውቁም ተባለ👉የዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን በዓለም ለ35ኛ ጊዜ ተከበረ35ኛው የዓለም አቀፍ የስኳር ህመም ቀን «በስኳር ሕመም ላይ ቀድመን እርምጃ እንውሰድ» በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል።በኢትዮጵያ ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ ህመሙ እንዳለባቸው እንደማያውቁ የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ጌታሁን ታረቀኝ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ህመሙ እንዳለባቸው ከታወቀባቸው ሰዎች መካከል መድኃኒት የሚወስዱት ከ20 በመቶ በታች ሲሆኑ በአግባቡ መቆጣጠር የቻሉት ደግሞ ከ4 በመቶ እንደማይበልጡ ተገነግሯል።የስኳር ህመም በዓለም ዙሪያ ስርጭቱ እየጨመረ ከመጡ የጤና ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።በ2024 በተደረጉ ጥናቶች መሠረት በዓለም ከ587 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር እየኖሩ ሲሆን ከ600 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ ቅድመ ስኳር በሽታ በሚባለው የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።በተለይም በታዳጊ ሀገራት የሰዎች አኗኗር ዘይቤ መለወጥን ተከትሎ የስኳር ህመም ስርጭት በቀጣይ ዓመታት እየጨመረ እንደሚሄድ ተገምቷል።በኢትዮጵያም የስኳር ህመም ከተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ ሲሆን ስርጭቱ እያሳሰበ መምጣቱ ተጠቁሟል።የዓለም አቀፍ የስኳር ሕመም ቀን ከ1991 ጀምሮ በየዓመቱ ህዳር 5 ቀን (ኖቬምበር 14) የሚከበር ሲሆን ቀኑ ኢንሱሊንን የተባለውን መድሃኒት ያገኙትን ሳይንቲስት የልደት ቀን ለማስታወስ ነው።በተስፋዬ ክንዴ#ዳጉ_ጆርናል
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 13:49

    ጃፓን ብራዚልን አሸንፋለችበአለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ጃፓና ብራዚልን 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።የጃፓንን የማሸነፊያ ግቦች ሳካሞቶ ፣ ናካሙራ እና ኩቦ ማስቆጠር ችለዋል።ቪንሰስ ጁኒየር የብራዚል ብሔራዊ ቡድንን ሁለት ግቦች ከመረብ አሳርፏል።በጨዋታው ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ራፊና እና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።ራፊና ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቀጣይ ከ ሲንጋፖር ጋር በሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ አይሳተፍም።#ዳጉ_ጆርናል
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 13:30

    የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ልጅ በታጣቂዎች ተገደለ ‼️​የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ዋና አስፈጻሚ ብርጋዴር ጀነራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ልጅ የሆነው ወጣት መዋእል ገብረእግዚአብሔር መንገድ ላይ በታጣቂዎች መገደሉን የቅርብ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ አረጋግጠዋል።​ምንጮቹ እንደገለጹት፤ ወጣቱ ትናንት አመሻሽ ከመቐለ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ደጉዓ ተምቤን ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱበት ጥቃት ሕይወቱ አልፏል።በ1995 ዓ/ም የተወለደው የ24 ዓመቱ ወጧት መዋእል ገብረእግዚአብሔር የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 5 በመቐለ ከተማ ይፈጸማል ተብሏል።ሟቹ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2017 ዓ.ም የቲዲኤፍ አባል የነበረ ሲሆን ጥር 2017 ዓ.ም የኮር እና ከኮር በላይ አመራሮች በእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ሲመራ ለነበረው ህወሓት እውቅና እንደሚሰጡ የወሰኑትን ውሳኔ ተከትሎ ወደ ትግራይ የሰላም ኃይል መቀላቀሉ የትግል ጓዶቹ ያጋሩት መረጃ አመልክቷል።#ዳጉ_ጆርናል
    2,8108622Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 09:49изменён

    ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለ32 ሰዎች የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት ሰጡፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለ32 ሰዎች የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ፕሬዚዳንቱ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት:-1. አቶ ታገሰ ጫፎ 2. አቶ አገኘሁ ተሻገር 3. አቶ ዛዲግ አብርሃ4. አምባሳደር ሲራጅ ራሺድ ጁንዲ 5. አምባሳደር መለስ ዓለም ተክዔ 6. አምባሳደር አንተነህ አለሙ ሰንበቴ7. አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ይግዛው 8. አቶ መላኩ አለበል 9. ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)10. ስንታየሁ ወ/ሚካኤል (ዶ/ር) 11. ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) 12. መስፍን አርአያ (ፕ/ር)13. ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) 14. ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) 15. አቶ አዳም ተስፋዬ አበራ16. አቶ አምሐ ኃ/ጊዮርጊስ አየለ 17. አቶ ሳሙኤል አዲስ አለማየሁ 18. አቶ በላቸው አንሺሶ ኬምበጫ19. አቶ አበበ መብራቱ ክብረት 20. አቶ መላኩ በዳዳ ሰንበታ 21. ወ/ሮ ዑባህ መሐመድ ሁሴን22. አቶ ዳንኤል ጠንክር አረጋ 23. አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) 24. ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ25. ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) 26. አቶ መላኩ ፈንታ ባልቻ
    3,71021125Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 09:33

    በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡበአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9፣ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚያመራው መንገድ ላይ በሚገኘው ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ ኅዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ገደማ በደረሰ የሥራ ላይ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ።አደጋው የደረሰው ሠራተኞቹ በግንባታ ላይ ባለ አንድ ሕንጻ ላይ የዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ፣ ቆመውበት የነበረው ርብራብ በድንገት በመፍረሱ ከ12ኛ ፎቅ ላይ በመውደቃቸው ነው። በስፍራው የነበሩ ነዋሪዎችና መንገደኞች በድንገተኛው ክስተት ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ መውደቃቸው ተገልጿል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለኤኤምኤን በሰጡት መግለጫ፣ ሦስቱም ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ በመውደቃቸው ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠዋል።አያይዘውም የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር ሁኔታ ለማጣራት ምርመራ እያካሄዱ መሆኑን ጠቁመው፣ የምርመራው ውጤት ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን።©️AMN #ዳጉ_ጆርናል
    3,4502384Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 09:02

    ያንጎ ግሩፕ ከ12ሺ 500 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና ሰጠመቀመጫውን በዱባይ ያደረገው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ፤ ከሴቭ ዘ ኔሽን እና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመላው አፍሪካ እየተተገበረ ያለውን "ደኅንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ቤት ጉዞ" (Safer Journeys to School) የተሰኘውን ተነሣሽነት በኢትዮጵያ በይፋ ማስጀመሩን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ12ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተግባራዊ የመንገድ ደኅንነት ትምህርት ለ25 ቀናት የሰጠ ሲሆን፣ በትምህርት ቤቶቹ አካባቢ የመንገድ ደኅንነትን የሚያጠናክሩ የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን ማከናወኑ ተገልጿል።የያንጎ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር የቀናለም አበበ እንደገለጹት፣ ደኅንነት ለያንጎ ሁሌም ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ሕጻናት በየዕለቱ ወደ ትምህርት ቤት በሚያደርጉት ጉዞ የበለጠ በራስ መተማመን እንዲኖራቸውና በደኅንነት እንዲንቀሳቀሱ ለማገዝ እየተሰራ ነው።በኢትዮጵያ የሴቭ ዘ ኔሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ቢምረው በበኩላቸው፣ ፕሮግራሙ ተማሪዎች የክፍል ውስጥ የመንገድ ደኅንነት ሕጎችን እንዲገነዘቡ ከማድረጉም በላይ በመንገድ ላይ በተዘጋጁ ተጨባጭ ማሻሻያዎች ህጻናትን ከአደጋ ለመጠበቅ እንደረዳ ገልጸዋል።ይህ አህጉራዊ ተነሣሽነት ከዚህ ቀደም በዛምቢያና በሴኔጋል ከ34ሺ በላይ ሕጻናትን ያዳረሰ ሲሆን ያንጎ ግሩፕ ከዚህ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብር ማከናወኑን እና የወጣት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተሰጥኦዎችን የሚደግፍ የፌሎውሺፕ ፕሮግራም ማስፋፋቱ ተመላክቷል።በሚኪያስ ፀሐዬ#ዳጉ_ጆርናል
    3,540991Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    14 нояб., 06:19изменён

    ኢትዮጵያ የ2027 የአፍሪካ ንግድ ማርኬቲንግ ጥምረት ጉባኤን (ACCS 2027) ለማስተናገድ የሚያስችላትን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች።👉ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምታስተናግደው አህጉራዊ የንግድና የማርኬቲንግ ጉባኤ የአጋርነት ጥሪ ከአዘጋጆቾ ቀርባል።ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2027 የሚካሄደውን የአፍሪካ ንግድ ጥምረት ጉባኤ ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ፣ የዝግጅቱን አጋርነት በይፋ የሚያስጀምር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ማኅበር (EMPA)፣ የኢትዮጵያ አይሲቲ ማኅበር (ICT-ET) እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ባለሙያዎች ማኅበር (ELSA) ከአፍሪካ አቻዎቻቸው ማለትም ከአፍሪካ ማርኬቲንግ ኮንፌዴሬሽን (AMC)፣ ከቲኮን አፍሪካ (TICON Africa) እና ከአፍሪካ ሰፕላይ ቼይን ኮንፌዴሬሽን (ASCON) ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከ1,000 በላይ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ታላቅ ጉባኤ ዙሪያ በተዘጋጀው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከዛምቢያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጋና፣ ከኬንያ እና ከእንግሊዝ የመጡ ልዑካን መገኘታቸውን ብስራት ሬድዮ ተመልክቷል።ይህም ጉባኤው በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ድንበር ተሻጋሪ ትብብር ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ የኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ፋና አብርሃም ተናግረዋል። የ2027 የአፍሪካ ንግድ ጥምረት ጉባኤ (ACCS 2027) አራት እርስ በርስ የተሳሰሩ የሙያ ዘርፎችን ማለትም ማርኬቲንግን፣ ቴክኖሎጂን፣ ሰፕላይ ቼይንና ሎጂስቲክስን እንዲሁም የፈጠራ ኢኮኖሚውን (Creative Economy) በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነውም ተብሏል።መድረኩ የአፍሪካ የንግድ መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የፈጠራ ባለቤቶች ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የንግድ ትስስር የሚፈጥሩበት እንዲሁም የኢንቨስትመንትና የንግድ ዕድሎችን የሚያስፋፉበት ይሆናል።ገበያን የሚያለሙ፣ ቴክኖሎጂን የሚያስፋፉ እና ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ድንበር ተሻግረው የሚያንቀሳቅሱ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ላይ ማምጣቱ፣ የአፍሪካን እምቅ የሥራ ፈጠራ አቅምና ሙያዊ ክህሎት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ እሴት ለመቀየር፣ የአህጉሪቱን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና ገበያዎችን በማስተሳሰር የጋራ ዕድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።ጉባኤው ለኢትዮጵያ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የጠቀሱት ፕሬዝዳንቷ፣ ዝግጅቱ በዋናነት በግሉ ዘርፍ ተነሳሽነት የሚመራ በመሆኑ ድርጅቶችና ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነትና በአጋርነት አብረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ዝቅተኛ የንግድ ትስስር ለማሳደግና የአህጉሪቱን ባለሙያዎች በቴክኖሎጂና በዕውቀት ለማስተሳሰር ያለመ ሲሆን፣ በቀጣይ ዓመት የሚካሄደው ስድስተኛው ዙር ጉባኤ መሆኑ ተገልጿል።#ዳጉ_ጆርናል
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 19:06

    "ከንቲባው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ነው ያረፈው። ሾፌሩ ግን የመኪና አደጋ በተከሰተበት እለት ወዲያው ነው ሕይወቱ ያለፈው" - አቶ ኃይሉ አዱኛበኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መተሃራ ከተማ፥ የከተማው ከንቲባና አሽከርካሪ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪ እና የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደነገሩንና ከአካባቢው በወጡ መረጃዎች መሰረት፣ የመተሃራ ከተማ ከንቲባ አቶ አዲሱ ዋቆ እና አንድ ሹፌር በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፏል።ነዋሪው የሞታቸው ምክንያት ሲያስረዱ፣ "የመኪና አደጋ ነው፤ አረጋግጫለሁ። ከንቲባው አቶ አዲሱ ዋቆ ይባላል፤ በጣም ጥሩ ሰው ነበር። ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ነበር የመኪና አደጋው የደረሰው 'ኢላላ' አካባቢ ከሹፌሩ ጋር እየተጓዙ በነበረበት ወቅት። ሹፌሩ ወዲያውኑ ሞተ፤ ከንቲባው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሞተ" ብለዋል።የአካባቢውን አመራሮች ለጊዜው ማግኘት ባይቻልም፤ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ከንቲባው እና ሹፌሩ በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።የመኪና አደጋ የደረሰው ጳጉሜ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ "ከንቲባውና ሾፌሩ ሞቱ በመባሉ ትክክል ነው፤ ከዞኑም አጣርቻለሁ" ብለዋል።"ከንቲባው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ነው ያረፈው። እኔም በአካል ሂጄ ጠይቄው ነበር። ኢትዮ ኢስታንቡል ነበር የተኛው። አደጋው ያጋጠማቸው ከመተሃራ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር በማይሞላ ቦታ ነው" ሲሉ ነግረውናል።
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 19:06

  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 17:24

    ቻይና በኢራን አየር መንገድ ኩባንያዎች ላይ የተጣለውን ህገ-ወጥ የአሜሪካ ማዕቀብ ተቃወመችየአሜሪካ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት እርምጃ እንደሚወስዱ ካስፈራሩ ከአንድ ቀን በኋላ፣ ቻይና በኢራን የአየር መንገድ ኩባንያዎች ላይ የተጣለውን "ህገ-ወጥ" የአሜሪካ ማዕቀብ እንደምትቃወም አስታወቀች።የትራምፕ አስተዳደር በቴህራን ላይ የሚያደርሰውን የኢኮኖሚ ጫና ለማሳደግ በሚጥርበት በዚህ ወቅት፣ ቤሰንት ሰኞ ዕለት ለ CNBC እንደተናገሩት፣ "በአሜሪካ ማዕቀቦች ጫና ምክንያት በመላው ዓለም የሚገኙ ሁሉም የኢራን የአየር መንገድ ኩባንያዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ስራቸውን ያቆማሉ" ብለዋል ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ “ቻይና በዓለም አቀፍ ህግ ወይም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እውቅና ላይ ያልተመሰረቱ ህገ-ወጥ ማዕቀቦችን በጽኑ ትቃወማለች” ብለዋል።ይህ ወቀሳ የተሰማው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ሀሙስ ዕለት ከሚያደርጉት ስብሰባ አስቀድሞ ነው።በሚኪያስ ጸሐዬ #ዳጉ_ጆርናል
    2,9001761Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 16:38изменён

    ንብ ባንክ ግብይት ሲፈፀም በድምፅ ማወቅ የሚያስችል አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከያጉት ፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያስጀመረዉ "NIB ETHQR sound box platform " ግብይትን አስተማማኝ ፣ፈጣን ፣ቀልጣፋና ደህንነቱ በተጠበቀ ለማድረግ የሚያበረክተዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።ይህም ሳዉንድ ቦክስ በንግዱ ዓለም ላይ የተሠማሩ ሰዎች ደንበኞቻቸዉ ላደረጉት ግብይት ክፍያ ሲፈፅሙ ወዲያዉኑ በድምፅ እንዲያዉቁት ያስችላቸዋል ተብሏል ።ይህም የባንኩን ዲጂታል ክፍያ ለማዘመን እና ለደንበኞች ፈጣንና አስተማማኝ ክፍያ ለመፈፀም እንደሚያስችል የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮዮ ሠምቷል ።ዋና ስራ አስፈፃሚዉ አክለዉም ባንኩ በቀጣይ የደንበኞቹን ተሞክሮ የሚያሻሽሉና የዲጂታል ኢኮኖሚን የሚያጠናክሩ አዳዲስ የዲጂታል ባንኪንግና የክፍያ መፍትሄዎችን ለደንበኞች ለማቅረብ ይሠራል ብለዋል ።የያጉት ፔይ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ ዓለማየሁ እንደተናገሩት ኩባንያዉ በቀጣይም ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ቀላል ፣አስተማማኝና ዘመናዊ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ለማቅረብ ይሠራል ።ዛሬ ወደ ስራ የገባዉ ሳዉንድ ቦክስ የባንኩ እና የኩባንያዉ የመጨረሻ ስራ ሳይሆን በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ከተተገበሩት የኦንላይን ክፍያ ትስስር መፍጠር ፣የስማርት ፖስና የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አገልግሎት ፣የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ማኔጅመንት ፣የንብ ተራ አስኳላ እና የንብ ተራ ቢዩልዲንግ የክፍያ አማራጮችን የማዘመን አካል ነዉ ተብሏል ።ያጉት ፔይ ፋይናንሺያል
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 15:08

    የጓደኛውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥር በመውሰድ 20ሺህ ብር ያወጣው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።ግለሰቡ ወንጀሉን የፈጸመው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።ጉታ ገመዳ የተባለው ግለሰብ ከግል ተበዳይ ጋር በጓደኝነት አንድ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ የግል ተበዳይ ቤት ውስጥ ያስቀመጠውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥሩን በመውሰድ ከግል ተበዳይ የሂሳብ ደብተር ፊርማ ጋር በማመሳሰል በክ/ከተማው ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ 20ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡ግለሰቡ ገንዘቡን ካወጣ በኋላ የግል ተበዳይ በደረሰው መልዕክት አማካኝነት ባንኩን በመሄድ ይጠይቃል።ገንዘቡ ወጪ መደረጉን ምላሽ የተሰጠው የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለአቅራቢያው ሙገር ፖሊስ መምሪያ አመልክቷል፡፡አቤቱታው የደረሰው ፖሊስም ምርመራውን በማጣራትና ባንኩ ውስጥ የነበረን ካሜራ በመጠቀም ወንጀል ፈጻሚውን በመለየት ከነ ኤግዚቢቱ ማስመለሱን የመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኢ/ር ዮሴፍ ገረመው ተናግረዋል።ወንጀል ፈጻሚው ክስ እንደተመሰረተበትም ኃላፊው ገልፀዋል።ግለሰቦች የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥራቸውን ከራሳቸው ውጪ ለየትኛውም አካል አሳልፈው መስጠት ወይም በግዴለሽነት ለወንጀል ተጋላጭ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እንደሌለባቸው የገለጹት ኃላፊው ደንበኞች ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄዱም የባንክ ባለሙያዎች የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ትክክለኛ ማንነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡#ዳጉ_ጆርናል
    3,9701541Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 14:34

    "ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር" - ሮዛየኢትዮጵያ Vs የግብፅ አየር መንገድ ትንቅንቅhttps://youtu.be/n90UVW5u-6o?is=BVmd-oSOaHworTpg
    3,7701372Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 14:24

    በቀጣይ 4 ዓመታት በወሊድ ምክንያት የሚሰትን የእናቶች ሞት ወደ 70 ዝቅ ለማድረግ እየተሰራ ነዉ ተባለበኢትዮጵያ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም አሁንም የእናቶች ሞት አሳሳቢ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል ።በተለይም ደግሞ ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ለእናቶች ሞት ቀዲሚዉ ምክንያት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ። ቀደም ባሉት ዓመታት ከ100 ሺህ እናቶች በወሊድ ምክንያት 871 የሚጠጉ እናቶች ህይወታቸዉ ያልፍ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ወደ 141 ዝቅ ማድረግ መቻሉን የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።በ2030 የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ከ141 ወደ 70 ለማድረስ የሚረዱ የፖሊሲ ዶክመንቶች ተቀርፀዉ በዛሬዉ ዕለት ይፋ ሆነዋል ።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ አጋር አካላት እና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን ይፋ የሆኑትን የፖሊሲ ዶክመንቶች ወደ መሬት በማዉረድ በ2030 የእናቶችን ሞት ወደ 70 ለማድረስ በሚቻልባቸዉ መንገዶች ላይ ዉይይት አድርጓል ።በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
    3,810431Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 13:12

    በዓለም ዙሪያ ከ57 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የመርሳት የአእምሮ ሕመም ወይም ዲሜንሽያ ሰለባ መሆናቸው ተገለጸ፡፡​እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በዓለም ዙሪያ ከ57 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዲሜንሽያ ወይም የመርሳት የአእምሮ ሕመም እየተጠቁ የሚገኙ ሲሆን፣ በየዓመቱ 10 ሚሊዮን አዳዲስ ታካሚዎች ይመዘገባሉ።​በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲሜንሽያ ተጋላጮች ቁጥር በፈረንጆች 2030 ወደ 78 ሚሊዮን፣ እንዲሁም በ2050 ወደ 139 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከእነዚህም መካከል ከአልዛይመር ጋር የተያያዙት ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ።​እስከ 45 በመቶ የሚሆነው የዲሜንሽያ ተጋላጭነት ሊሻሻሉ ከሚችሉ እንደ ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም፣ አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ከፍተኛ የደም ግፊት ካሉ ምክንያቶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተጠቅሷል።በሰላማዊ ነጋሲ #ዳጉ_ጆርናል
    3,950421Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 12:21

    ከመኖሪያ ቤቷ ጀርባ ወስደው የ15 ዓመት ታዳጊን የደፈሩ ሁለት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ከመኖሪያ ቤቷ ጀርባ ወስደው የ15 ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድር ወንጀል የፈፀመሙ ሁለት ተከሳሾች በእስራት መቀጣታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ተከሳሾቹ ማረከኝ ድንበሩ እና አማኑኤል መኩሪያ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ታዳጊዋን ከምትኖርበት ቤት ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ ይዘዋት በመሄድ አንደኛ ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩ ታዳጊዋን ከመኖሪያ ቤቱ ጀርባ እንሰት ስር በማስገባት ኃይል በመጠቀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡2ኛ ተከሳሽ አማኑኤል መኩሪያ ደግሞ የወንጀሉ ተባባሪ በመሆን ወንጀሉ እንዲፈጸም ማመቻቸቱ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ተረጋግጧል ተከሳሾቹ ጥፋተኛ የተባሉት በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 620(2)(ሀ እና መ) እንዲሁም አንቀጽ 37(1 እና 4) ሥር በተደነገገው ድንጋጌ መሠረት መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል።በዚህም የወረዳው ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩን በ13 ዓመት ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ አማኑኤል መኩሪያን ደግሞ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል።በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
    4,1401443Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 11:09

    አሜሪካ፣ ዴንማርክ እና ግሪንላንድ የእርስ በእርስ የደህንነት ስምምነት ሊፈራረሙ ነው፡፡​አሜሪካ፣ ዴንማርክ እና ግሪንላንድ በአርክቲክ ግዛት ላይ ያለውን የዴንማርክን ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ እና የአሜሪካን ተሳታፊነት በግሪንላንድ መከላከያ ላይ የሚያሰፋ የደህንነት ስምምነት ማክሰኞ ዕለት ሊፈራረሙ እንደሆነ ተገልጿል።​የዴንማርክ መንግስት እንዳስታወቀው አሜሪካ፣ ዴንማርክ እና ግሪንላንድ ቀደም ሲል ይፋ የተደረገውን የአሜሪካ እና የግሪንላንድ የደህንነት ስምምነት ማክሰኞ ዕለት በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ይፈራረማሉ።​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው አርብ እንደተናገሩት፣ ይህ ስምምነት አሜሪካ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በምትመኛት እና በአርክቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በሚገኘው የዴንማርክ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ግሪንላንድ የደህንነት ጉዳይ ላይ ቋሚ ቁጥጥር እንዲኖራት ያስችላታል።​የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬደሪክሰን ጽህፈት ቤት እንደገለጸው እሳቸው፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ-ፍሬደሪክ ኒልሰን ስምምነቱን በኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህንፃ ውስጥ ይፈራረማሉ።​ፍሬደሪክሰን ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት እስካሁን ይፋ ያልተደረገው ይህ ስምምነት የዴንማርክን ግዛት ሉዓላዊነት እና አንድነት፣ እንዲሁም የግሪንላንድ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብትን ዕውቅና የሚሰጥ ነው።በሰላማዊ ነጋሲ #ዳጉ_ጆርናል
    4,210931Открыть в Telegram
  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 11:09

  • ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

    22 сент., 10:21

    በ140 ብር መነሻ መዋጮ የተጀመረው አሚጎስ የቁጠባና ብድር ማህበር ሀብቱ 10 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀማህበሩ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የህብረት ሥራ ማህበራት ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን ከወረቀት ነፃ የስማርት አገልግሎት ማዕከል አስመርቋል።አዲሱ የስማርት አገልግሎት ማዕከል የአባልነት ምዝገባን ማከናወን፣ መረጃ መጠየቅ፣ የብድር ሂደትን መከታተልና አስፈላጊ ሰነዶችን ማሟላት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።ማህበሩ የአባላቱን ተደራሽነትና የአገልግሎት ፍጥነት ለማሻሻል ከሚያቀርባቸው ዲጂታል አገልግሎቶች መካከል ኮር ባንኪንግ፣ ዌብ ቤዝድ ሰርቪስና የሞባይል መተግበሪያ ይገኙበታል።አሚጎስ በመጀመሪያ በሶስት ጓደኛሞች 140 ብር መዋጮ የተጀመረ ሲሆን በ2005 ዓ.ም ደግሞ በ20 አባላትና በ9 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ተመስርቶ የቤት ለቤት የቁጠባና የብድር አገልግሎት ጀምሯል።በ13 ዓመታት የሥራ ጉዞው ከ20 ሺህ በላይ አባላትን ማፍራቱንና እስካሁን ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለአባላቱ መስጠቱን የአሚጎስ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ወ/አማኑኤል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ማህበሩ በፌዴራል ደረጃ ፈቃድ በማግኘት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች 28 ቅርንጫፎችን ከፍቶ እየሰራ ሲሆን በቀጣይ ወራት ተጨማሪ 23 ቅርንጫፎችን ለመክፈት እየተሰራ ነው ።ከቁጠባና ብድር አገልግሎቱ ባሻገር፣ ማህበሩ ለባለአክሲዮን አባላቱ ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ከ50 በመቶ በላይ ትርፍ ማከፋፈሉን ገልጿል።በማህበራዊ ኃላፊነት በኩልም በከተማ ልማት፣ በበጎ አድራጎትና በተለያዩ ማህበራዊ ሥራዎች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ
    4,26014721Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота