gram news
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት channel avatar

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

@fdredefenseforc

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

ProjectsENMilitary

42,500subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    25 Sept, 15:50

    ሠራዊቱ የአርሶ አደሮችን ሰብል የማረም ድጋፍ አደረገ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ምበደቡብ ዕዝ ተወርዋሪው ኮከብ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና የሚገኙ አርሶ አደሮችን ሰብል በማረም ድጋፍ አድርጓል።የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ ሻለቃ ግርማ አሰፋ እንደገለጹት፣ ክፍለ ጦሩ ከግዳጅ ተልዕኮው ጎን ለጎን በሚሰማራባቸው አካባቢዎች ለህዝቡ የተለያዩ የድጋፍና የልማት ሥራዎችን ያከናውናል።አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖችን በገንዘብና በጉልበት መደገፍ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል መሆኑን የገለጹት ሻለቃ ግርማ፣ ይህም "ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር" የሚለውን የተቋሙን እሴት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት ሃምሳ አለቃ የሂኔስ አብራሌ እና ሃምሳ አለቃ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው፣ ከግዳጃቸው ጎን ለጎን ህዝቡን ማገዝ የደስታ ምንጫቸው መሆኑን ገልጸዋል። ዘጋቢ በቃሉ ክንዴ ነውየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    25 Sept, 12:37

    በቀጠናው የሚገኘው ኮር ከሰሜን ወሎ ዞን አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ምኮሩ ከሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ ከሚገኙ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በወቅታዊ የሠላም ሁኔታ ውይይት አካሂዷል።ውይይቱን የመሩት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ደጀኔ ደበሌ በቀጠናው ተሰማርቶ የሚገኘው የኮሩ የሰራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሉና ከመስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት በፅንፈኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ሰላም በዘላቂነት የማረጋገጥ ተግባር የመፈፀም ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።የፀረ ሰላም ሀይሎችን ፍላጎት ቀድሞ በመረዳትና የገቢ ምንጩን በማድረቅ ማንኛውንም ድጋፍ እንዳያገኝ በጋራ መስራት ይኖርብናል ያሉት ምክትል አዛዡ በህዝቡ ውስጥ ተደብቀው የፅንፈኞችን ፕሮፖጋንዳ የሚነዙና ዘረፍን የሚፈፅሙ ቡድኖችን ተከታትሎ በመያዝ እርምጃ በመውሰድ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል።የወልድያ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደርበው አዳነ መከላከያ ሰራዊታችን ቀን ከሌሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ በቀጠናው ሲንቀሳቀስ በነበረው የፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰዱ አሁን ላይ በዞኑ ሰላም መስፈን ችሏል ለዚህም የዞኑ የፀጥታ አካላት ከሰራዊቱ ጋር በመሆን የሰሩት የሰላምና ፀጥታ ስራ ውጤት ነው ብለዋል።የውይይቱ ተሳታፊ የፀጥታ አካላትም ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመቀናጀት ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመታገል የቀጠናውን ሰላም ለማረጋገጥ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።ዘጋቢ ጌትነት አስናቀው ፎቶ ግራፍ ዮናስ ካንቻማየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    2,6802951Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    25 Sept, 12:24

    አለም አቀፍ ህጎችን ያከበረ የግዳጅ አፈፃፀም ተመራጭና ለተሻለ ድል የሚያበቃ መሆኑ ተገለፀ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከማዕከላዊ ዕዝ ሁሉም ክፍሎች ለተውጣጡ ኦፕሬሽናል እና የስታፍ አመራሮች ወታደራዊ ኢላማዎችን በመለየት የሲቪሊያንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ስልጠና መሠጠቱን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ አስተባባሪ ሚስተር ስኖዊ ሊንተን ገልፀዋል።ከተጨባጭ ምልከታዎች በመነሳት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀገሪቱ የተስማማችባቸውን የጄኔቫ ስምምነቶች በማክበር ግዳጁን እየፈፀመ ነው። አሁን ላይ በሚከሰቱ ግጭቶች የተወሳሰቡ ስምሪቶችን በበሳል አመራር በመፍታት የሰላማዊ ዜጎች ከለላ ሊሆን ይገባል ሲሉ ሚስተር ስኖው አስገንዝበዋል።በማዕከላዊ ዕዝ የህዳሴ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል እያሱ ሀፍቱ ተቋሙ የሚመራባቸው ህጎች ሰራዊቱ የሚገነባባቸው፤ ከህገ መንግስቱ የተወሰዱ እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝን የሚቃወሙ በመሆናቸው የድል አድራጊነቱ ሚስጢር ናቸው ብለዋል።ስልጠናው በቀጥታ ወታደራዊ ስምሪትን ለሚመሩ አመራሮች መሰጠቱ በግጭት ቀጠና የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመለየት ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ ተቋማትን ከአላስፈላጊ አደጋ ለመታደግ ይረዳል ያሉት ከፍተኛ መኮንኑ ሰራዊቱ ዓለም አቀፍ የጦርነት ህጎችን እንዲረዳና በግዳጁ ላይ ግልፅ በመሆን በኃላፊነት ስሜት ተልዕኮዎቹን ማከናወን እንዲችል አቅም መሆኑን ተናግረዋል። የዘገበው መሀመድ አህመድ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    2,550212Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    25 Sept, 09:48edited

    የመከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነት አለኝታየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ምኢትዮጵያ በታሪኳ ለነጻነቷና ለሉዓላዊነቷ መስዋዕትነት ከፍላ ማንነቷን ያሥከበረች ሀገርጨናት። የዚህች ታሪካዊት ሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ሳይደፈር እስከ ዛሬ ሊዘልቅ የቻለው ደግሞ በየዘመናቱ በደሙና በአጥንቱ ሀገርን ባቆመው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሕልውና መሠረት፣ የሕዝብ ደኅንነት ዋስትና እና የሀገር ፍቅር መገለጫ የሆነ ኃይል ነው።የሠራዊቱ ታሪካዊ መሠረት ከሀገራችን የነጻነት ጉዞ ጋር በጥብቅ ተሳስሯል። ከዓድዋ የነጻነት ተጋድሎ እስከ ዘመናዊው የመከላከያ ግንባታ ድረስ፣ ሠራዊቱ የሀገርን ዳር ድንበር የማስከበር ተልዕኮውን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል።የውጭ ወራሪዎች የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለመድፈር ሲሞክሩ፣ ሠራዊቱ በተለያየ መልኩ ተደራጅቶና ተሰልፎ መስዋዕትነት በመክፈል ሀገርን አስከብሯል።ይህ ታሪካዊ አደራ ዛሬም ድረስ ቀጥሎ፣ ዘመናዊ የውጊያ ታክቲክን፣ ቴክኖሎጂንና ሳይንሳዊ አሰራርን በማቀናጀት የሀገርን የሰማይና የምድር ድንበር በጥንካሬ የመጠበቅ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።አንድን ሠራዊት በውጊያ ሜዳ ውጤታማ ከሚያደርጉት ዋና ዋና ነገሮች መካከል የወታደራዊ ሙያ እና የሞራል ልዕልና ግንባታ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሚያንፀባርቃቸው ቁልፍ የሞራል እሴቶች፣ ከግልና ከቡድን ጥቅም ይልቅ የሀገርን ሕልውና እና የሕዝብን ሰላም ማስቀደም፣ በከፍተኛ የሥነ-ምግባር ደንብ መመራት፣ ለህግ እና ለሰብዓዊ መብቶች ተገዢ መሆን እንዲሁም የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውክልና ያለበትና የጋራ ዓላማን አንግቦ የሚሰለፍ ጠንካራ ወታደራዊ ቤተሰብ መሆን ተጠቃሽ ናቸው።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በታሪክ የፃፋቸው የጀግንነት ገድሎች በሀገር ውስጥ ብቻ የተወሰኑ አይደሉም። በሀገር ውስጥ የሀገርን ሰላም ለማስከበርና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስጠበቅ ካደረጋቸው ተጋድሎዎች ጎን ለጎን፣ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችም የደመቀ ስም አለው።በአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የሀገር ሉዓላዊነት ከድንበር ጥበቃ ባለፈ ውስብስብ ጥቃቶችን እና የውስጥ ደኅንነት ስጋቶችን የመከላከል ሥራን ይጨምራል።በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገርን ለማፍረስና የሕዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚሰሩ እኩይ ኃይሎችን በመመከት የሀገርን ሕልውና ያረጋግጣል።ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት በሌለበት የኢኮኖሚ ልማትን ማሰብ ስለማይቻል፣ ሠራዊቱ የሚያስከብረው ሰላም ለሀገራችን እድገት መሠረት ነው።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገር ፍቅርን በተግባራዊ ጀግንነትና መስዋዕትነት የጻፈ፣ የሀገር ሕልውና የማዕዘን ድንጋይ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    3,7202812111Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    25 Sept, 08:07

    ከትናንት ስህተቱ መማር ያልቻለው ህወሃት ዛሬም ለዳግም ውርደት መዳረጉ ተገለፀ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ምየህገ-ወጡ ህወሃት ቡድን ከትናንት በስቲያ የሰሜን ምስራቅ ዕዝን በመተንኮስ ከደረሰበት ከባድ የሰብዓዊ ኪሳራ ሳያገግም ዛሬም የተረፉ ታጣቂዎችን በማሰባሰብ ለዳግም ትንኮሳ መንቀሳቀሱን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ኮር አዛዥ ገልፀዋል።ቡድኑ ከሞትና ከመቁሰል ተርፈው የተበታተኑ ታጣቂዎቹን በማሰባሰብ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የግዳጅ ቀጣና ማጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ መሆኑን የኮሩ አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል አዲሱ በድሩ ተናግረዋል የኮሩ ክፍለጦሮች በፈፀሙት የተቀናጀ የመከላከልና የፀረ-ማጥቃት ውጊያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ድል መቀዳጀታቸውንም ገልፀዋል።የቡድኑን ትንኮሳ መክተው ክፍለጦሮቹ ባካሄዱት ፀረ-ማጥቃት ዘመቻ 436 የጠላት ኃይል ተገድሏል፤ 44 ተማርኳል፤ 220 የጠላት ኃይል ቆስሏል። 04 ዲሽቃ፣ 18 መትረየስ፣ 06 ስናይፐር 83 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ ፣ 15 አይኮም የመገናኛ ራድዮ፣ 02 አይነት 77 ራድዮ እና 03 አርፒጂ የጦር መሳሪያ ከጠላት ተማርኳል።ከ5 ሺህ በላይ የመትረየስ እና 1590 የዲሽቃ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ መሆኑን ያስረዱት የክፍለጦር አዛዦቹ ሌሎች በርካታ መሰል ተተኳሾች እና የመሳሪያ አባሪ እቃዎችም መማረካቸውንም ገልፀዋል።በኮሩ የግዳጅ ቀጣና ጠላት 31ኛ ፣ 26ኛ ፣15ኛ እና 44ኛ እያለ የሚጠራቸውን አራት አርሚ ታጣቂዎችን ሙሉ ለሙሉ አሰልፎ የቀቢፀ- ተስፋ ሙከራዎችን የፈፀመ መሆኑን እና መመታቱን ብርጋዲየር ጀነራል አዲሱ በድሩ ተናግረዋል። ዘገባው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    1,80018171031Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    24 Sept, 16:52

    በ10ኛ ዕዝ አባይ ኮር የግዳጅ ቀጠና የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ ሰጡ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ምበሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ ዙሪያ በፀረ-ሰላም ተግባር ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች የተደረገላቸውን የሠላም ጥሪ ተቀብለው እጅ መስጠታቸውን የአባይ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሃሺም ኢብራሂም ገልፀዋል።ጀኔራል መኮንኑ በአካባቢው በተሰራው ጠንካራ የማግባባት ስራ በርካታ የፅንፈኛው ታጣቂዎች የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን አውስተው ሠራዊታችን በሰራው ጠንካራ ስራ በአካባቢው የነበረውን ስጋት ማስወገድ ተችሏል ብለዋል።የሰላም አመራጩን ተቀብለው በሠላም የገቡ ታጣቂዎች በበኩላቸው በተሳሳተ መንገድ ሀገራችንን እና ህዝባችንን በድለናል፤ አሁን ግን ከህዝባችን ጋር ሆነን ከኛ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    5,80037262Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    24 Sept, 15:56

    በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የሴክተር 3 መሃንዲስ ክፍል ግዳጁን በላቀ ብቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ምየመሃንዲስ ክፍሉ የሠፈረበት አካባቢ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በየጊዜው ጎርፍ የመከላከል ፈንጅዎችን የማፅዳትና ምሽጎችን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል፡፡የሴክተር ሶስት መሀንዲስ ክፍል ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል መስፍን አያሌው የመሀንዲስ ክፍሉ ከተሰጡት ሃላፊነቶች መካከል ሰራዊቱንና ለሰላም ማስከበር የተሰማራበትን የማህበረሰብ ክፍል ከሰው ሰራሽና ከተፈጥሮ አደጋ መጠበቅ በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የመሀንዲስ አባላቱ በተጨማሪ በወሰዱት የተቀነባበረ ፈንጂ የማምከን ስልጠና መሰረት በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች በበርደሬ፣ ገብረሃሬ፣ ቀንሰሃደሬ በመዘዋወር ፈንጅ የማፅዳትና የአልሸባብን ሴራ የማክሸፍ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።አልሸባብ በተለያዬ ጊዜ በስውር ክብደት ያላቸው የተቀነባበሩ ፈንጂዎችን አጥምዶ የነበረ ቢሆንም በአካባቢው ማህበረሰብ ጥቆማና ባልተቋረጠ የመሃንዲስ ክፍሉ ፍተሻ በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ሳያደርስ ማምከን መቻሉን ሌተናል ኮሎኔል መስፍን አያሌው ተናግረዋል።ዘጋቢ መዝገቡ ያረጋል ፎቶ ግራፍ ሙላቱ በየነየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    4,38019121Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    24 Sept, 15:28

    የኮሩ የሠራዊት አባላት በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኙ አረጋውያን የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም​የምስራቅ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኙ አረጋዊያን ማህበር አባላት የ107 ሺህ 900 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።​የምስራቅ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ሬድዋን ሬባቶ ፤ ሠራዊቱ የአገርን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር ለወገናቸው የቆሙና ለአገር ትልቅ ውለታ የዋሉ አረጋዊያንን መደገፍ የማህበራዊ ሀላፊነት አንዱ አካል ነው ብለዋል።የኮሩ ሠራዊት ሁልጊዜም ከህዝብ ጎን በመቆም አጋርነቱን የሚያሳይ ተግባራዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።​የምዕራብ ጎጃም ዞን የአረጋዊያን ማህበር ሰብሳቢ አቶ በፍቃድ ዲስሳ በበኩላቸው፤ ሠራዊቱ ላደረገው በጎና አርአያነት ያለው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።የሀገርን ሰላም የሚያስከብረው ሠራዊት በችግር ውስጥ ያሉ አረጋዊያንን በማሰብ ላደረገው እገዛ ማህበሩ ትልቅ ክብርና አድናቆት እንዳለው ገልጸው፤ ይህ ድጋፍ ለአረጋዊያኑ ትልቅ የሞራልና የማቴሪያል አለኝታ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።ዘጋቢ ሀብታሙ አወቀ ፎቶግራፍ አማኑኤል ግርማየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    4,03015121Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 18:20

    ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፥ ለሀገሬ የምሰስተው ነገር የለም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፥ ለሀገሬ የምሰስተው ነገር የለም ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወትና የውትድርና ጉዞ ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጀግኖችን ታሪክ በመፃፍ፤ ጀግኖችን በማወደስ ትውልድ ይገነባል፡፡ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፤ እኔም ለሀገሬ የምሰስተው አንዳች ነገር የለም ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ መጽሃፉ ለዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም ለታሪክ ተመራማሪዎች የሚጠቅም መሆኑን አንስተዋል፡፡ድል ቁርሱ መፅሃፍ ከኩየራ ወንዞች መሐል የፈለቀዉ የጦር ሊቅ በሚል ርዕስ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የህይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ነው።ወታደራዊ ሁኔታን ከማንበብ እስከ ውጤታማ የድል ምዕራፍ ድረስ በማያቋርጥ የአመራር ሰንሰለት ዉስጥ ያለፉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሁሉም በላይ ሀገር እና ህዝብን ላስቀደመ ዓላማ ዕምቅ ወታደራዊ ሙያቸውን ያለ መታከት ያበረከቱበት እውነተኛ ታሪክ በመፅሃፉ ተካቷል።በአማን ታደሰ ተፅፎ ለንባብ የበቃው መፅሃፉ ከጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ በጀግንነት የደመቀ ታሪክ ትውልድ እንዲማርበት በማድረግ
    1,330227421Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 18:20

    Image from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
    1,2501122Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 17:15

    https://youtu.be/yJEnKBmcCxc?si=RGPLpYfGNu2wQ270
    YouTube"ድል ቁርሱ" መፅሃፍ ተመረቀ።Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
    1,9102052211Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 16:22

    "ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተመረቀ።መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ የኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው።በዚሁ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አስፋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብራሃ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ደቦጭ በመጽሐፉ ላይ ምሁራዊ ሂስ እና ዳሰሳ አቅርበዋል።በመርሃ ግብሩ ላይ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሸዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0https://www.facebook.com/fdredefense.official
    3,3902918641Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 16:22

    Image from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
    3,1201621Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 14:33

    ለህዝቡ አለኝታ ለሃገሩ ኩራት የሆነ አይበገሬ የድል ሠራዊትየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምየቀኑን ሃሩር ተቋቁሞ ፣ የሌሊት ቁር ታግሶ ፣ በዳገቱ ከፍታ ጉልበቱ ሳይዝል ፣ በቁልቁለቱ ጥልቀት እግሩ ሳይሰናከል ፣ እንደ ሃረግ በተጠላለፈው ደን መሃል በስልታዊ ጥበብ ተጉዞ እያለፈ፣ አጋምና ቀጋው ሰውነቱን ወግቶ ቢያደማው ፣ የቆንጥሩ እሾህ ጠልፎ ሊያስቀረው ቢሻ ከአላማው ፅናት የተነሳ የጀመረውን ጉዞ ከግብ ሳያደርስ የማይቆም ክንደ ብርቱ ሠራዊት።በውጣ ውረድ መሃል እያለፈ ተልዕኮውን ለአፍታ ሳይዘነጋ አለም የደርሰበትን የሳይንስ ልህቀት በመገንዘብና አዳዲስ የቴክኖሎጅ ግኝቶችን በመተግበር ከዘመን ጋር ለመዘመን ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግና የረዥም ጊዜ ራዕይ ሰንቆ የሚሰራ ባለ ብሩህ ተስፋ።ከተገነባበት እሴትና ተላብሶት ከሚኖረው ህዝባዊ ባህሪ በመነጨ ፈታኞቹን አንበርክኮ ድል የሚያደርግበት ዋነኛ የአሸናፊነቱ ሚስጥር ፣ ሃያል ያደረገው ሃይሉ ፣ የህዝብ ድጋፍና አብሮነት መሆኑን ከልቡ የሚያምን ነው።የህዝብ ፍቅር ለሱ ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሪያና ከደረሰበት ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብ በላይ የሚተማመንበት አቅሙ ነው። ደግሞም የጠላትን እኩይ አላማ እያከሸፈ በፅናቱ ያሳለፋቸው የሞት ሽረት ጊዜያቶች ቁጥር ስፍር የላቸውም። በአይበገሬነቱ አያሌ ድሎችን አስመዝግቧል። በጥቅሉ ተልዕኮው በፈተና ውስጥ ማለፍን ግድ ስለሚል ከፅናት ጋር ያለው ቁርኝት ከፍተኛ ነው።በተለይም ለሃገር የሚከፍለውን ዋጋ ከተረዱ ዜጎች የሚያገኘው የሞራል ድጋፍ ፣ ውጣ ውረዱን በብቃት እንዲሻገር ፣ ፈተናውን
    2,940218631Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 14:33

    Image from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
    2,530216Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 13:08

    የወገንን ህይወት ለመታደግ ደም መለገስ እንደሚገባ ተገለፀ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምየኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ የሠራዊት አባላት ደም ልግሰዋል። ይህንኑ ፕሮግራም ያሥተባበሩት የኢትዮጵያ መከላከያ መረጃ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል እየሩሳለም ተገኝ "ደማችን ለሰራዊታችን" በሚል ሀሳብ ደሙን እና ላቡን ለሚያፈስና ምትክ አልባ ህይወቱን ለሚሰጥ ሰራዊት ደም መለገስ የሀገር ፍቅር ስሜት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ልገሳ ያደረጉት የክፍሉ አባላትም የጓዶቻቸውን ህይወት መታደግ የሚችል ደም በመለገሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ከለጋሾች መካከል ሻለቃ ታዬ ገብረ-ሚካኤል የሰራዊቱ ቁልፍ ተግባር የህዝቦችን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ነውና ህይወትን ለመታደግ የደም ልገሳ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡የመከላከያ ደም ባንክ ቡድን መሪ ኮሎኔል ፀሐይ ተስፋዬ በበኩላቸው ደም ልገሳ በበጎ ፈቃደኝነት የሚከናወን መልካም ተግባር መሆኑን አንስተው አንድ ሰው ደም ሲለግስ ዋነኛ ዓላማው የወገኑን ህይወት መታደግ ቢሆንም እግረ-መንገዱን የራሱን ጤንነት ማስተካከል የሚችልበትን መልካም አጋጣሚ ያገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ ፎቶ ግራፍ እፀገነት ዴቢሳየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
    2,99017611Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 13:08

    Image from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
    2,65018101Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 11:06

    ዕዙ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስረከበ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምየሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለበርካታ ዓመታት ሀገራቸውን በውትድርና ላገለገሉና አሁን ላይ የጤናና የአቅም ውስንነት ላጋጠማቸው ግለሰብ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን የመኖሪያ ቤት አስረክቧል።በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ መሐንዲስ ኃላፊ ኮሎኔል ዘሪሁን ሽፈራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከሕዝብ የወጣና ለሕዝብ የቆመ ኃይል መሆኑን ጠቅሰው ሀገርን ከጠላት የመከላከል ቀዳሚ ግዳጁን በብቃት ከመወጣት ጎን ለጎን ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በበጎ አድራጎት እያረጋገጠ የሚገኝ ሠራዊት መሆኑን ገልፀዋል።የቤቱን መስሪያ ቁሳቁስና ሌሎች ወጪዎችን የዕዙ ጠቅላይ መምሪያ ሙሉ ለሙሉ የሸፈነ ሲሆን የጠቅላይ መምሪያው ስታፍ የሠራዊት አባላት ደግሞ በጉልበት ስራው ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።የመኖሪያ ቤቱ የአፋር ክልል ለግለሰቡ በሰጠው 60 ካሬ ላይ ባለሶስት ክፍል ቤት ያረፈ ሲሆን ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ኪችን እና የአየር ማቀዝቀዣዎችን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።በዕዙ መሐንዲስ የኮንስትራክሽን ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጋዲሳ ሹመታ በበኩላቸው፣ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ሰርቶ ለማጠናቀቅ የዕዙ ኮንስትራክሽን ባለሙያዎች የአካባቢውን ሞቃታማ የአየር ፀባይ ተቋቁመው ስራውን በሚገባ ማከናወናቸውን አስረድተዋል።ድጋፉ የተደረገላቸው አቶ አሰፋ አያኑ የቤቱን ቁልፍ ከተረከቡ በኋላ በሰጡት አስተያየት ሠራዊቱ ለዋለላቸው ውለታና ላደረገላቸው
    3,3101514211Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 11:06

    Image from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትImage from a post by FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
    3,1401743Open in Telegram
  • FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

    22 Sept, 08:41

    የሬጅመንቱ ሠራዊት ህዝባዊነት በተግባርየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምበደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ የ11ኛ ዕዝ አንድ ሬጅመንት ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ሙሉ ቤት ገንብቶ አስረከበ።ሬጅመንቱ ከ600 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገነባውን ቤት ለቤተሰቡ ከተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ጋር በማስረከብ በችግር ውስጥ ላለ ወገን አብሮ መቆም የሠራዊቱ የህዝባዊነት ባህሪ አንዱ መገለጫ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።የክፍለ ጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ቴዎድሮስ ምትኩ በርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት የክፍሐጦሩ ሠራዊት ዋና ተልዕኮ ሀገርንና ህዝብን መጠበቅ ቢሆንም፣ ሠራዊቱ የህዝብ ልጅ በመሆኑ ህዝቡ በሚፈልገው ጊዜ ከጎኑ በመቆም በተለያዩ ድጋፎች ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።መቶ አለቃ መስፍን አደራው በበኩላቸው፣ የሬጅመንቱ ሠራዊት ጥንካሬ በግዳጅ ቀጠና በሚያከናውነው ተልዕኮ ብቻ የሚለካ እንዳልሆነ ገልጸው፣ ከህዝቡ ጋር ባለው ቁርኝትና ህዝቡ በችግር ውስጥ በሚገኝበት ወቅት በሚያደርገው ድጋፍም ጭምር ህዝባዊነቱ እንደሚገለጽ አንስተዋል።በርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ የወረኢሉ ወረዳ አስተዳደር አቶ ደለለኝ ቸርነት በበኩላቸው፣ መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ለህዝቡ ያለውን አጋርነት በተግባር እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2htt
    3,390141251Open in Telegram