Latest posts

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
23 Sept, 13:11
አቶ መሰለ አሰፋ የተባሉ ወላጅ አባት ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን ድጋፍ በማድረጉ መደሰታቸውን ገልጸው እነዚህ ልጆች የእናንተ ናቸው ልጆቻችን የመማሪያ ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው ወደ ት/ቤት ሲሄዱ ደስታችን ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ ከባድ ነው ። ወደፊትም ችግራችን ብዙ ነው ድጋፋችሁ አይለየን ይህንን ድጋፍ ላደረጋችሁልንም በያለችሁበት እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ እንደኛ ከመሆን ያድናችሁ ብለዋል።ድጋፍ ከተደረፈገባቸው ቦታዎች አንዱ የሆነው የኩታበር ወረዳ ማእከል ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተጠሪ ቀሲስ ዓለሙ አሰፋ ድጋፉ በአስፈላጊ ጊዜ የተደረገ መሆኑን ገልጸው ማኅበሩ አሁት ያደደረገላቸው ድጋፍ ካለባቸው ዘርፈ ብዙ ችግር አንጻር ችግራቸውን ሙሉ በሙሉ ባይቀርፍም መልካም እና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አያይዘውም ተማሪዎቹ ከአካባቢው ልጆች ጋር አብረው የሚማሩ በመሆናቸው የቦርሳና የዩኒፎርም ችግር እንዳለባቸውም ገልጸው በተጨማሪም ማኅበሩ እስካሁንም የተለያዩ የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ጠቁመዋል።በአጠቃላይ በመጠለያ ካምፕ እና ከካምፕ ውጭ ያሉ ተፈናቃዮች እንዲሁም በማኅበረሰቡ ውስጥም ረዳት የሌላቸው ብዙ ስላሉ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ደሴን ጨምሮ በሀገራችን ባሉ 14 ማእከላት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ሲሆን ይህም ማኅበረ ቅዱሳን ከሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክረስቲያንና ከሌሎች በጎ አድራጊ ወገኖች የተገኘ ነው፡፡ ለዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
23 Sept, 13:10
ማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ለመማር ዐቅም ለሚያንሳቸው ተማሪዎች ከ450 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡መስከረም ፲፫/፳፻፲፰ ዓ.ምሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ዘርፍ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራባቸው ግቦች አንዱ በመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን በየዓመቱ በድርቅ፣ በጦርነት፣ ወላጆቻቸውን በማጣትና በሌሎች ማኅበራዊ ቀውሶች ምክንያት ለመማር ዐቅም ለሚያንሳቸው የነገ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡በተመሳሳይ ለ2019 የት/ት ዘመንም በደሴና አካባቢው ባሉ 4 የተፈናቃይ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና ከዛም ውጭ በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ለሚገኙ 637 ተማሪዎች 450,398.77 ብር ወጪ የተደረገበት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 60ዎቹ የአብነቱን ከዘመናዊው ጋር አስተባብረው የሚማሩ ናቸው፡፡ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ተማሪ ማሪቱ ስለተደረገልን ድጋፍ በጣም ደስ በሎኛል ከጎናችን አይዟችሁ የሚል ወገን ስላለን በጣም ተደስቻለሁ ቤተሰብ ደብተር እስክርቢቶ ስንጠይቃቸው ይጨናነቁብናል፤ ትምህርት ቤትም የተለያየ የሞራል ጫና ይደርስብናል ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ተረድቶ ስላደረገልን ደጋፍ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን እያልኩ ቀጣይም ዩኒፎርም ሆነ የምግብ ችግር ስላለብን ድጋፋችሁ አይለየን በማለት ሐሳቧን ገልጻለች ።




ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
23 Sept, 10:56edited
የቅጥር ማስታወቂያ


ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
21 Sept, 13:14
"ልጆቻችን ሃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ኑሩ እርስ በእርሳችሁ ተደጋገፉ" ብፁዕ አቡነ እንጦንስመስከረም ፲፩/፳፻፲፱ ዓ.ምበማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ሲያስተምራቸው የነበሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ የቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን መስከረም ፲/፳፻፲፱ ዓ.ም የሽኝት መርሐ ግብር ማድረጉን አሳውቋል።በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል በዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ፣ የበገና ዝማሬ በቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን ከግቢ ጉባኤ ተመርቀው በወጡ ወንድሞች የግቢ ጉባኤ ሕይወትና የግቢ ፈተናን በተመለከተ ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።በመርሐ ግብሩ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ እንጦንስ “ለተማሪዎች ሃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ኑሩ እርስ በእርስ ተዋደዱ ፣ተደጋገፉ” በማለት አባታዊ መልእክትና ቡራኬ በመስጠት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የመጽሐፍ ሽልማት አበርክተዋል።በመጨረሻም ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት ሲሄዱ እንዳይቸገሩ የማእከላት የግቢ ጉባኤ አድራሻ ፣ውዳሴ ማርያም፣የ፳፻፲፱ ዓ.ም የእንኳን አደረሳችሁ ፓስት ካርድ የተሰጠ ሲሆን በዕለቱ የዋና ክፍሉ ኃላፊ አቶ አማረ ምትኩ ለተማሪዎች በምትሄዱበት ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን፣ ማኅበረ ቅዱሳንንና ግቢ ጉባኤን እንዲያገለግሉ የአደራ መልእክታቸውን በማስተላለፍ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል። በተመሳሳይ የማኅበረ ቅዱሳን ጅማ ማእከል ለቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የሽኝትና አደራ መስጠት መርሐ ግብር አከናውኗል።




ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
21 Sept, 09:14
ለዚህ ድጋፍ ከ363,000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ) ብር በላይ ገንዘብ ወጭ መሆኑን የጠቀሱት የማኅበረ ቅዱሳን ሰቆጣ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ፈንታ ዓለምሰገድ ድጋፉ በአሜሪካ ሀገር ከሚገኘው የሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን እና ከሌሎች በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ በጎ አድራጊ ወገኖች የተገኘ መሆኑን ገልጸው ፣ ስለድጋፍም በተማሪዎችና በማኅበረ ቅዱሳን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዞኑ ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉትን ጨምሮ ከ80 ሺህ በላይ ተማሪዎች አሁንም የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በድጋፍ ርክክብ ወቅት የተገኙት የመንግሥት ኃላፊዎች ተናግረዋል።በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተወካይ ኀላፊ ዲያቆን ሥዩም ገብረ ኪዳን ማኅበረ ቅዱሳን የዋግ ኽምራን ችግር ለዓለም በማሳወቅና መሰል ድጋፍ በማድረግ በኩል የዘወትር አጋዣችን ነው በማለት የተናግረዋል፡፡ እንዲሁም የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሥራ ኃላፊዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰቆጣ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት እና የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል።ለእነዚህ እና መሰል ማኅበራዊ ድጋፎችን ለማገዝ ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
21 Sept, 09:14
ማኅበረ ቅዱሳን በሰቆጣ ማእከል ለመማር ዐቅም ለሚያንሳቸው ተማሪዎች ከ363 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡መስከረም ፲፩/፳፻፲፱ ዓ.ምየማኅበረ ቅዱሳን በሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በኩል በማኅበራዊ ቀውሶች የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ዘርፍ ብዙ ማኅበራዊ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን በዚህም በድርቅ፣ በመፈናቀልና መሰል ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ማኅበራዊ ቀውሶች በመጎዳታቸው ምክንያት የትምህርት ቁሳቁስ አሟልተው ትምህርታቸውን መቀጠል ለሚቸገሩ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡በመሆኑም ለ2019 ዓ.ም የት/ት ዘመንም በመላ ሀገሪቱ በ14 ሀገረ ስብከቶች ለሚገኙ ተማሪዎች ይህ ድጋፍ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን በሰቆጣ ማእከል ሥር በሚገኙ በሰባት ወረዳዎች በተፈናቃይ ጣቢያዎች ለሚገኙ፣ ከአብነት ት/ት ጎን ለጎን ሳይንሳዊውን ት/ት ለሚማሩ ተማሪዎች በድምሩ 443 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ የዜማ ተማሪዎቹ ከአሁን በፊት የመማርያ ደብተር ባለማግኘታቸው እስከ ዛሬ ድረስ ትምህርት ቤት እንዳልተገኙ የተናገሩ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን አስተባብሮ የትምህርት ቁሳቁስ በመደገፉም ተስፋችን ለምልሟል ሲሉ ገልጸዋል።የስምንት ልጆች እናት የሆኑት ሌላኛዋ ወ/ሮ ዘነቡ ኪሮስ ልጆቻቸውን ለማስተማር ተቸግረው በነበረበት ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ድጋፍ በማድረጉ መደሰታቸውን በመግለጽ ለልጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ ለመግዛት ዐቅም በማጣታቸው የሁለቱ ልጆቻቸውን ትምህርት




ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
17 Sept, 06:23
የ2019 ዓ.ም የበረከት_ዕቁብ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ‼️ 👇👇👇👇 https://forms.gle/m8uwvizKM16azyUT9


ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
16 Sept, 13:12
በተጨማሪም «ትዝታዬ» በሚል ርእስ ከማኅበረ ቅዱሳን ምሥረታና የአገልግሎት አጀማመር በትውስታ ይቃኛል፡፡ v የነገዋ ቤተ ክርስቲያን «የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር ከማን የተገኘ ነው?» በተሰኘ ርእስ ኢትዮጵያ ከሕገ ልቡና ጀምሮ እግዚአብሔርን ስታመልክ የኖረች ሀገር መሆኗን፣ የዘመን አቈጣጠሯም የዘመን መለወጫ ወሯም ቀደም ሲል የነበረ መሆኑን ይተነትናል፡፡ v ክርስትና በማኅበራዊ ክርስቲያናዊ የሕይወት ለውጥን በተመለከተ ይተነትናል፡፡ v እናስተዋውቃችሁ የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል አመሠራረትና አገልግሎት በተመለከተ ይዘን የቀረብንበት ክፍል ሁለት ዝግጅት ይዳስሳል፡፡ v የጥያቄዎቻችሁ መልስ አቡሻክር (ባሕረ ሐሳብ) በተመለከተ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓዎቹ ዘመን አቆጣጠር እንዴት እንደተለየ እና አቡሻክር በተመለከተ ሌሎችም ጥያቄዎችን በማንሣት ከመምህር ተስፋ ማርያም ክንደ ጋር ያደግነውን ቆይታ ይዘን ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡ ሐመር መጽሔት #፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር ፱ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል ━━━━━༺✞༻━━━━
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
16 Sept, 13:11
የሐመር መጽሔት መስከረም ፳፻፲፱ ዓ.ም እትም የመስከረም ፳፻፲፱ ዓ.ም የሐመር መጽሔት እትም እነሆ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ በዚህ እትማችንም፡- v የማኅበረ ቅዱሳን መልእክት፡- «አንድ ልብ፣ አንድ ሐሳብ ለተናበበ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት» በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምን ጊዜውም በላይ የልጆቿ አንድነት፣ ኅብረት የምትሻበት ወቅት በመሆኑ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች መካካል መለያየትን አስወግዶ በአንድ ልብ በአንድ ሐሳብ ማገልግል እንደሚገባ ይተነትናል፡፡ v ዐውደ ስብከት፡- «አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም» (መዝ.፻፩፥፳፯) በሚል ርእስ እግዚአብሔር በባሕርይው መለወጥ የሌለበት፣ የሁሉ አስገኝ፣ ፍጥረቱንም በሥርዓት የሚመራ፣ ዓለምንም አሳልፎ የሚኖር፣ በዓመታት የማይገደብ አምላክ መሆኑንና ዘመናትን እያፈራረቀ ለሰው ልጆች እንደሚሰጥ ያስተምራል፡፡ v ትምህርተ ሃይማኖት «ምድርን ጎበኘሃት፥ አረካሃትም» (መዝ.፷፬፥፲፩) በሚል በክረምቱ እግዚአብሔር ምድርን በዝናብ እንዳረሰረሳት፣ ምድርም ለዘርና ለሚተከልባት ተክል ዝግጁ አደረግሃት፤ በልምላሜም አስጌጥሃት፣ ፍሬዋንም እንደምትሰጥ ሁሉ ክረምትን በብሉይ ኪዳን በጋውን ደግሞ በሐዲስ ኪዳን መስሎ ይተነትናል፡፡ v ዐቢይ ጉዳይ፡- «ከዐውደ ምሕረት ልመና ወደ ማእከላዊ ቋት» በሚል ርእሰ ጉዳይ በጥናት ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ጽሑፍ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ፡- ቤተ ክርስቲያናችን አሁን ካለችበት የተበታተነና ለውጥ የማያመጣ የሒሳብ አሰባሰብ ሂደት ወጥታ፣ ሐዋርያዊ መሠረቱን ወደጠበቀ፣ ዘመናዊና የተማከለ የሀብት አስተዳደር (Central


ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
16 Sept, 08:19
በመቅደላ ጦርነት የተወሰደውን የብራና መጽሐፍ ቅዱስ ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።በ1868 ዓ.ም. በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ የተወሰደውና የአጼ ቴዎድሮስ መጽሐፍ ቅዱስ ሊሆን እንደሚችል የሚገመተው ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ቅዱስ በ47.5 ሚሊዮን ብር ወይም 250 ሺህ ዩሮ ለሽያጭ መቅረቡ ይታወሳል።ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ ሙሉ የቅዱስ ሉቃስን ወንጌልና የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልንም ከመጨረሻዎቹ 16 ጥቅሶች በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደያዘ ተገልጿል።በ1730–1740 ዓ.ም. አካባቢ በጎንደር ውስጥ የተጻፈ እንደሆነ የሚገመተው መጽሐፉ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤና ሌሎች ተአምራትን የሚያሳዩ 235 ቅዱሳት ሥዕላትን እንደያዘ ታውቋል።መጽሐፉ ምንም እንኳን ለሽያጭ ቢቀርብም ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ኮሚቴ አባል ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።የሽያጩን ሂደት ለማስቆም ከኦስትሪያና ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር በዲፕሎማሲ በኩል መነጋገር እንደሚያስፈልግም ያነሡት ዶ/ር አሉላ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሕግና የዲፕሎማሲ ሂደቶችን እያከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል።




ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
16 Sept, 07:04
ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ሀገር የተመለሱ የብራና መጻሕፍትን ከኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ተረከበ።መስከረም ፮/፳፻፲፱ ዓ.ም በትናትናው ዕለት የኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ከሀገረ አሜሪካ በግለሰብ እጅ የነበሩና የተመለሱ 17 የብራና መጻሕፍን ለ7 ተቋማት የማስረከብ ሥነ ሥርዓት አከናውኗል።ከተረከቡት ተቋማት መካካል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ 2 መጻሕፍትን ተረክበዋል፡፡ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የባለሥልጣኑ ዳይሬክተር በንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት 5 እና 6 ዓመታት ቅርስ የማስመለሱን ሥራ በትኩረት እየሠራበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ለዘመናት ቅርሶችን ስናስመልስ ኖረናል ያሉት ዳይሬክተሩ በዚህም በትናትናው ዕለት ቅርሶቹን ለመረከብ የቻላችሁ ተቋማት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው ላለፉት 7 ዓመታት ቅርሶችን ለማስመለስ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብና ጥረት 67 ቅርሶች ወደ ሀገር መመለሳቸውን አንሥተዋል፡፡በብራና መጻሕፍቱ ውስጥ የተመዘገቡ ጽሑፎችና ስንኞች የኢትዮጵያን ሥልጣኔ፣ባህልና ታሪክ ለመረዳት የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡




ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
15 Sept, 18:19edited
የ2019 ዓ.ም የበረከት_ዕቁብ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ‼️ 👇👇👇👇 https://forms.gle/m8uwvizKM16azyUT9


ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
13 Sept, 09:24edited
እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን የዓመቱ የመጀመሪያ የዜና ገዳማት መርሐ ግብር በልዩ ዝግጅት ስለምናከብር በዚህ መርሐ ግብር ላይ ተሳታፊ ይሁኑ። ማክሰኞ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም 11:30 ጀምሮ

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
