gram news
የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ channel avatar

የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

@amharic_hadith

በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ላይ የነቢያችንን ﷺ ሶሂህ ሐዲሶችን የምንለቅበት ይሆናል። ኢንሻ አላህ!!!

ProjectsENReligion

3,580subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    21 Sept, 02:59

    اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ያ ጀመዓ ዐፉወን ከዚህ በኋላ ለብዙ ጊዜ ያሕል ሐዲስ መልቀቅ አልችልም። ዒልም ፍለጋ ከሚዲያው አለም ለብዙ ጊዜያት ስለምርቅ ማለት ነው። እና ከዚህ በፊት ብዙ ሐዲሶችን መልቀቄ ይታወቃል። እና ወደኋላ በመመለስ ከዚህ ጀምራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። 👇 Amharic_Hadith Amharic_Hadithየአላህ ፍቃድ ከሆነ ለወደፊቱ በተሻለ መልኩ ለመምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላህ!!እና ይህን ደካማ ወንድማችሁን በዱዓ አትርሱት። ባረከላሁ ፊኩም።የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    20 Sept, 02:50

    ምድርን የሞላ ምህረትከአነስ ኢቢኑ ማሊክ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿يقولُ: قال اللهُ: يا ابنَ آدَمَ، إنَّك ما دَعَوْتَني ورجَوْتَني غفَرْتُ لك على ما كان فيك ولا أُبالي، يا ابنَ آدَمَ، لو بَلَغَتْ ذُنوبُك عَنانَ السَّماءِ ثمَّ استَغفَرْتَني غَفَرْتُ لك ولا أُبالي، يا ابنَ آدَمَ، إنَّك لو أَتَيْتَني بقُرابِ الأرضِ خَطايا ثمَّ لَقيتَني لا تُشرِكُ بي شَيئًا، لَأَتَيْتُك بقُرابِها مَغفرةً.﴾“የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ የኣደም ልጅ ሆይ! ከለመንከኝና ከከጀልከኝ ባንተ ላይ ላለው (ወንጀል) ደንታ አይኖረኝም እምርልሃለሁ፡፡ የኣደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመናን ቢደርሱ ከዚያም ምህረትን ከጠየቅከኝ እምርልሃለሁ፡፡ የኣደም ልጅ ሆይ! አንተ ምድርን ሊሞላ የቀረበ ወንጀል ጋር ብትመጣኝ፣ ከዚያ በኔ ላይ ምንም ሳታጋራ ካገኘሀኝ እሷኑ ሊሞላ የቀረበ ምህረትን ይዤ እመጣሀለሁ፡፡”(📚ቲርሚዚ ሀሰን ብለውታል 3540)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    19 Sept, 02:50edited

    ለሰላምህ ስትል ሰላምታን አብዛረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿السلامُ اسمٌ من أسماءِ اللهِ وضَعَهُ اللهُ في الأرضِ، فأفْشُوهُ بينَكمْ، فإنَّ الرجلَ المسلمَ إذا مَرَّ بقومٍ فسلَّمَ عليهم، فردُّوا عليه؛ كان لهُ عليهم فضلُ درجةٍ بتذكيرِهِ إيّاهُمُ السلامَ، فإنْ لمْ يرُدُّوا عليه رَدَّ عليه مَنْ هوَ خيرٌ مِنهمْ وأطْيبُ﴾“አስ-ሰላም ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ስም ነው። አላህ በምድር ላይ (ሰላምታን ትለዋወጡበት ዘንድ) አስቀምጦታል። በመሆኑም በመካከላችሁ (ሰላምታን) አብዙ። አንድ ሙስሊም ሰው በሰዎች አጠገብ ሲያልፍና ቀድሞ ሰላምታ ሲያቀርብላቸው፣ እነሱም መልስ ከሰጡት፤ ሰላምታን በማስታወሱ ብቻ በእነሱ ላይ የአንድ ደረጃ ብልጫ (ተጨማሪ ምንዳ) ያገኛል። እነሱ መልስ ካልሰጡት ግን፣ ከእነሱ የተሻለና ይበልጥ የጠራው የሆነ አካል (መላኢካ) መልስ ይመልስለታል።”(📚 ሶሂህ አልጃሚ 3697)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    18 Sept, 03:03

    ጁሙዓ ሰለዋት ዱዓረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁሙዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለእኔ ይቀርብልኛልና።(📚አቡ ዳውድ ሰሂህ ብለውታል: 1531)ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾በጁሙዓ ቀንና ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በእኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።(📚ሰሂህ አልጃሚ: 1209)ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    17 Sept, 02:53

    ሽበት በኢስላምረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿لا تَنتِفُوا الشَّيْبَ، ما مِنْ مُسْلِمٍ يَشيبُ شَيْبَةً في الإسلامِ، إلّا كانَتْ لَهُ نورًا يومَ القيامَةِ﴾“ሽበታችሁን አትንቀሉ። አንድ ሙስሊም በኢስላም ውስጥ ሆኖ አይሸብትም በቂያማ ቀን ለእሱ ብርሃን የሚሆንለት ቢሆን እንጂ።”(📚ሶሂህ አልጃሚዕ 7463)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    16 Sept, 02:57

    ቢያውቁ ኖሮረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي النِّدَاءِ وَالصَّفِّ الْأَوَّلِ ثُمَّ لَمْ يَجِدُوا إِلَّا أَنْ يَسْتَهِمُوا عَلَيْهِ لَاسْتَهَمُوا﴾“በአዛንና በመጀመሪያ ሶፍ የሚገኘውን (ምንዳ) ሰዎች ቢያውቁ ከዚያም ዕጣ ካልተጣጣሉ የማይገኝ መሆኑን ቢረዱት ኖሮ ዕጣ ይጣጣሉበት ነበር፡፡”(📚ቡኻሪ 615 ሙስሊም 437 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    56184Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    15 Sept, 03:43

    ሰዎችን የምታሰግድ ከሆነረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿إِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِلنَّاسِ فَلْيُخَفِّفْ ؛ فَإِنَّ مِنْهُمُ الضَّعِيفَ، وَالسَّقِيمَ، وَالْكَبِيرَ، وَإِذَا صَلَّى أَحَدُكُمْ لِنَفْسِهِ﴾“አንዳችሁ ሰዎችን የሚያሰግድ ከሆነ ቀለል ያድርግ (አያስረዝም)። በእነሱ ውስጥ ደካማ፣ በሽተኛና ባለ ጉዳይ ይኖራልና። አንዳችሁ ለብቻው ከሰገደ ግን የፈለገውን ያህል ያስረዝም።”(📚ቡኻሪ 703 ሙስሊም 467 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    14 Sept, 02:50

    ሰባት አይነት ሰዎችረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾“ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከእሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣ ምፅዋትን (ሰደቃ) የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።"(📚ቡኻሪ 1423 ሙስሊም 1031 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    13 Sept, 01:21

    ሐዲሰል ቁድሲረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿قالَ اللَّهُ عزَّ وجلَّ: إذا تَحَدَّثَ عَبْدِي بأَنْ يَعْمَلَ حَسَنَةً، فأنا أكْتُبُها له حَسَنَةً ما لَمْ يَعْمَلْ، فإذا عَمِلَها، فأنا أكْتُبُها بعَشْرِ أمْثالِها، وإذا تَحَدَّثَ بأَنْ يَعْمَلَ سَيِّئَةً، فأنا أغْفِرُها له ما لَمْ يَعْمَلْها، فإذا عَمِلَها، فأنا أكْتُبُها له بمِثْلِها﴾“የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ ‘ባሪያዬ መልካም ስራን ለመስራት አስቦ (በሆነ ምክንያት ሳይሰራው ቢቀር) እንደ አንዲት መልካም ስራ አድርጌ እጽፍለታለሁ። ከሰራው ደግሞ በአስር እጥፍ አድርጌ እጽፍለታለሁ። መጥፎ ስራን ለመስራት አስቦ እስካልሰራው ድረስ እምርለታለሁ፤ ከሰራው ግን ልክ እንደ እርሷ አንዲትን መጥፎ ሥራ ብቻ አድርጌ እጽፍለታለሁ።’”(📚ቡኻሪ 42 ሙስሊም 129 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    12 Sept, 02:57

    ድንቅ ነቢያዊ ምክርረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿ومَن يَسْتَعْفِفْ يُعِفَّهُ اللَّهُ، ومَن يَسْتَغْنِ يُغْنِهِ اللَّهُ، ومَن يَتَصَبَّرْ يُصَبِّرْهُ اللَّهُ، وما أُعْطِيَ أحَدٌ عَطاءً خَيْرًا وأَوْسَعَ مِنَ الصَّبْرِ.﴾“እራሱን ከሐራም የቆጠበ አላህ ከሐራም ይጠብቀዋል። በራሱ ለመብቃቃት ጥረት ያደረገ አላህ የሚብቃቃበትን ነገር ይሰጠዋል። ትዕግስት ለማድረግ የጣረ ትዕግስትን ይለግሰዋል። ለአንድ ሰው ከትዕግስት የተሻለና እጅግ ሰፊ የሆነ ነገር እንደተሰጠው አይነት ለማንም አልተሰጠም።”(📚ቡኻሪ 1469 ሙስሊም 1053 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    11 Sept, 14:24

    ስለ ቂያማ ዕለት የተነገሩ ሐዲሶች!ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿ثَلَاثَةٌ لَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ: شَيْخٌ زَانٍ، وَمَلِكٌ كَذَّابٌ، وَعَائِلٌ مُسْتَكْبِرٌ﴾“ሶስት አይነት ሰዎች በቂያማ እለት አላህ አያናግራቸውም፣ ከወንጀላቸው አያፀዳቸውም፣ ወደነሱም አይመለከትም፣ አሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። እነሱም፦ የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ የመሪ ውሸታምና የድሃ ኩራተኛ ናቸው።”(📚ሙስሊም ዘግበውታል፡ 107)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    4 Sept, 13:17

    እውነተኛ መመካትን በአላህ ላይ ብትመኩ ኖሮረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿لو أنَّكم توَكَّلتم على اللهِ حقَّ توَكُّلِهِ، لرزقَكم كما يرزقُ الطَّيرَ، تغدو خماصًا، وتروحُ بطانًا.﴾“እናንተ በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነ መመካትን ብትመኩ ኖሮ ወፎችን እንደሚመግበው ይመግባችሁ ነበር። ሆዷ ባዶ ሆኖ ጠዋት ትወጣና ከሰዓት በኋላ ሆዷን ሞልታ ትመለሳለች።”(📚ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል 2344)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    2,24012Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    28 Aug, 12:53

    ሰባት አይነት ሰዎችረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ في ظِلِّهِ، يَومَ لا ظِلَّ إلّا ظِلُّهُ: الإمامُ العادِلُ، وشابٌّ نَشَأَ في عِبادَةِ رَبِّهِ، ورَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ في المَساجِدِ، ورَجُلانِ تَحابّا في اللَّهِ اجْتَمعا عليه وتَفَرَّقا عليه، ورَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذاتُ مَنْصِبٍ وجَمالٍ، فَقالَ: إنِّي أخافُ اللَّهَ، ورَجُلٌ تَصَدَّقَ، أخْفى حتّى لا تَعْلَمَ شِمالُهُ ما تُنْفِقُ يَمِينُهُ، ورَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خالِيًا فَفاضَتْ عَيْناهُ.﴾“ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከእሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣ ምፅዋትን (ሰደቃ) የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።"(📚ቡኻሪ 1423 ሙስሊም 1031 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    1,62016Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    21 Aug, 14:28

    አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ...ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿لا تَزُولُ قَدَما ابنِ آدمَ يومَ القيامةِ مِن عندِ ربِّه، حتى يُسْأَلَ عن خَمْسٍ: عن عُمُرِه فِيمَ أَفْناه؟ وعن شبابِه فِيمَ أَبْلاه؟ وعن مالِه مِن أين اكتسبه وفِيمَ أنفقه؟ وماذا عَمِل فيما عَلِم؟﴾“የአደም ልጅ በቂያማ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንዳጠናቀቀው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።”(📚ሶሂህ አልጃሚ፡ 7299)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    14 Aug, 13:33

    ወንጀል ከሰሩ በኋላረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿ما من عبدٍ يُذنِبُ ذنبًا فيُحسِنُ الطَّهورَ ثمَّ يقومُ فيُصلِّي ثمَّ يستغفرُ اللهَ إلّا غفر اللهُ له.﴾“አንድ ባሪያ ወንጀል በሚፈፅምበት ወቅት ውዱእ በትክክል ያድርግ፡፡ ከዚያም ሁለት ረከዓዎችን ይስገድና አላህን ምህረት ይማፀን፡፡ አላህ ምህረትን ይለግሰዋል፡፡”(📚አቡ ዳውድ 1521 ቲርሚዚ 406 ዘግበውታል)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    2,04014Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    7 Aug, 13:08

    ከኩራት ተጠንቀቁረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿لا يَدْخُلُ الجَنَّةَ مَن كانَ في قَلْبِهِ مِثْقالُ ذَرَّةٍ مِن كِبْرٍ قالَ رَجُلٌ: إنّ الرَّجُلَ يُحِبُّ أنْ يَكونَ ثَوْبُهُ حَسَنًا ونَعْلُهُ حَسَنَةً، قالَ: إنّ اللهَ جَمِيلٌ يُحِبُّ الجَمالَ، الكِبْرُ بَطَرُ الحَقِّ، وغَمْطُ النّاسِ﴾“በልቡ ውስጥ የሰናፍጭ ፍሬ እንኳን ኩራት ያለበት ጀነት አይገባም። አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ ሰውዬው ልብሱ ቆንጆ ጫማውም ቆንጆ እንዲሆን ይወዳል’ ይህ ከኩራት ነውን? እሳቸውም እንዲህ አሉት፦ አላህ ቆንጆ ነው ቆንጆን ነገር ይወዳል። ኩራት የሚባለው ሐቅን አለመቀበልና ሰዎችን አሳንሶ መመልከት ነው።”(📚ሙስሊም ዘግበውታል 91)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    2,290181Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    24 Jul, 12:46

    የሙዓዚንነት ምንዳረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿المؤذِّنُ يُغفَرُ لهُ مدى صوتِه، ويُصدِّقُه كلُّ رَطبٍ ويابِسٍ ولهُ مثلُ أجرِ مَن صلّى معَه﴾“ሙአዚን ድምፁ በሚደርስበት ልክ (ወንጀሉ) ይማርለታል። እርጥብም ሆነ ደረቅ ነገር ሁሉ እውነትነቱን (በቂያማ ለት) ይመሰክርለታል። ከእርሱ ጋር የሰገደም ¹ ሰው አጅር (ምንዳ) ተመሳሳዩን ያህል ያገኛል።”(📚ሶሂህ አተርጊብ፡ 234)¹ የሰጋጆች ምንዳ እኩልነት፡ ሙአዚኑ ሰዎችን ወደ ሶላት በመጥራቱ ምክንያት መጥተው ከእርሱ ጋር የሰገዱትን ሰዎች ያህል አላህ ተመሳሳይ አጅር ይሰጠዋል። ይህ የሚሆነው የሰጋጆቹ አጅር ምንም ሳይቀነስ አላህ ከራሱ ችሮታ ለሙአዚኑ ተጨማሪ እኩል አጅር ይሰጠዋል። ምክንያቱም “ወደ በጎ ነገር ያመለከተ ሰው የሰሪውን ያህል ምንዳ ያገኛል” የሚል የኢስላም መርህ ስላለ ነው።የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    2,36012Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    30 May, 02:48

    ዋናው ነገር ጤናረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦﴿اسْأَلُوا اللَّهَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ ؛ فَإِنَّ أَحَدًا لَمْ يُعْطَ بَعْدَ الْيَقِينِ خَيْرًا مِنَ الْعَافِيَةِ﴾“አላህን ይቅርታንና ጤንነትን ጠይቁት። ማንም በአላህ በእርግጠኝነት ከማመን ቀጥሎ እንደ ጤንነት መልካም ነገር አልተሰጠውም።”(📚ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል 3558)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    3,1401031Open in Telegram
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    29 May, 03:15edited

    የዚክር ትሩፋትከአቡ ሁረይራ (رَضِيَ ٱللَّٰهُ عَنْهُ) ተይዞ እንዲህ ይላል፦﴿جاءَ الفُقَراءُ إلى النبيِّ ﷺ، فقالوا: ذَهَبَ أهْلُ الدُّثُورِ مِنَ الأمْوالِ بالدَّرَجاتِ العُلا، والنَّعِيمِ المُقِيمِ يُصَلُّونَ كما نُصَلِّي، ويَصُومُونَ كما نَصُومُ، ولَهُمْ فَضْلٌ مِن أمْوالٍ يَحُجُّونَ بها، ويَعْتَمِرُونَ، ويُجاهِدُونَ، ويَتَصَدَّقُونَ، قالَ: ألا أُحَدِّثُكُمْ إنْ أخَذْتُمْ أدْرَكْتُمْ مَن سَبَقَكُمْ ولَمْ يُدْرِكْكُمْ أحَدٌ بَعْدَكُمْ، وكُنْتُمْ خَيْرَ مَن أنتُمْ بيْنَ ظَهْرانَيْهِ إلّا مَن عَمِلَ مِثْلَهُ تُسَبِّحُونَ وتَحْمَدُونَ وتُكَبِّرُونَ خَلْفَ كُلِّ صَلاةٍ ثَلاثًا وثَلاثِينَ﴾“ድሆች (ምስኪኖች) ወደ ነቢዩ (ﷺ) ዘንድ በመምጣት ሀብታሞችና የገንዘብ ባልተቤቶች በገንዘባቸውና በሀብታቸው ትልቁን ደረጃና ማይቋረጥ የሆነውን ፀጋ (ጀነትን) ይዘውብን ሄዱ (በለጡን)፤ እኛ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ። እንደምንፆመው ይፆማሉ። ነገር ግን እነሱ የገንዘብ ትሩፋት አላቸው፤ በእሱ ሐጅ ያደርጉበታል፣ ዑምራ ያደርጉበታል፣ ጂሃድ ያደርጉበታል፣ ሰደቃ ያወጡበታል አሉ። የዚህን ጊዜ ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉ፦ ታዲያ አንድን ጉዳይ አልነግራችሁምን? ያን ነገር ከያዛችሁት እናንተን የቀደማችሁ የሆነን
  • የነብዩ ﷺ ሶሂህ ሐዲሶች በአማርኛ

    28 May, 02:41

    አያመ ተሽሪቅከበሺር ኢብኑ ሰሂም ተይዞ፦ ነቢዩ (ﷺ) ስለ አያመ ተሽሪቅ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦﴿لا يدخلُ الجنَّةَ إلاَّ نفسٌ مسلمةٌ، وإنّ هذِهِ الأيّامَ أيّامُ أكلٍ وشربٍ..﴾“ነፍሱ ሙስሊም የሆነች ቢሆን እንጂ ጀነትን አይገባም። እነዚህ ቀናቶች ደግሞ የመብያና የመጠጫ ቀናቶች ናቸው።”(📚ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል 1407)የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Amharic_Hadith
    2,10016Open in Telegram