gram news
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ channel avatar

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

@amstkilogg

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማዕከል የ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ዋና የቴሌግራም ገጽ፤ መርሐ ግብራት ፥ #የቅዱሳን_ታሪክ #መጽሐፍ_ትረካ #መጽሐፍ_ጥቆማ #ብሒላተ_አበው https://t.me/amstkilogbigubae በዩትዩብ ቤተሰብ እንሁን ☟☟☟https://www.youtube.com/@5kilogbigubae የፎቶ ማህደር ☟☟☟ https://t.me/+9PbLapMJu91hZThk

ProjectsENReligion

4,060subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    20 Sept, 16:38

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
    78073Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    20 Sept, 08:24

    " ጼዴንያ ማርያም " “ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዓላ በእዱ፡፡ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ፡፡ አመ ተቀብዑ ማርያም እምሐፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ፡፡ በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውሕዱ፡፡ ፅዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ፡፡” በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::ለእመብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮጵያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ በጐዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከማያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ፡፡ ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው፡፡ አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም፡፡ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: ይህቺ ክብርት ስዕለ አድኅኖ የአሁን መገኛ 4 መረጃዎች አሉ:-1.ያለችው ኢትዮዽያ ውስጥ (ደብረ ዘመዳ በሚባል ገዳም) ነው::
    579751Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    20 Sept, 08:23

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    17 Sept, 07:01

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    17 Sept, 06:03

    https://forms.gle/LjqeA2Zn7pinsCJm8
    Google Docsየ6ወራት የዜማ መሳሪያዎች ስልጠናበማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሰሜን ማስተባበሪያ ለ6 ወራት የሚቆይ የዜማ መሳሪያዎች ስልጠና
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    17 Sept, 06:03

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    16 Sept, 10:29

    መማርመማር በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚጀምር ቢሆንም፣ መቼም ቢሆን አያበቃም...​ ይህ የመማር ጉዞ እንደ ሕይወታችን የእድገት ደረጃዎች የተለያየ መልክ ይይዛል። ሕፃንነት ሁሉንም ነገር የምናምንበትና የምንቀበልበት ወቅት ነው። በዚህ እድሜ ትምህርት ያስፈልገናል፤ ብዙ እንጠይቃለን፤ እውነትን እንፈልጋለን። ነገሮችን ያለ ክርክር እንቀበላለን፤ ሌሎችን በማየትም ብዙ ነገሮችን እንቀስማለን።በመጀመሪያና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ ነገሮችን በጥልቀት ተረድተን ወደ ውስጥ የምናስርጽበት ሌላ ዓይነት ትምህርት ይጀምራል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መማር በውይይትና በክርክር ላይ የተመሰረተ ይሆናል፤ መረጃዎችንም መርምረንና አበጥረን በአእምሯችን እናከማቻለን። በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን ደግሞ መረጃዎችን በራሳችን መርምረን ወደ ማዘጋጀት እንሸጋገራለን፤ በተወሰነ መልኩም በራሳችን መተማመን እንጀምራለን። ከዩኒቨርሲቲ በኋላ ግን ወደ ተግባራዊው ዓለም ስንገባ ሌላ ዓይነት የመማር ሂደት ይጀምራል።ይህ የሕይወት ትምህርት የተወሰነ ፕሮግራም ወይም የፈተና ቀን የለውም። በማንኛውም ሰዓት፣ በማንኛውም ነገር፣ ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት በተግባር እንፈተናለን። ስለዚህ እኛም ለሕይወት ፈተናዎች ራሳችንን ማዘጋጀት ይኖርብናል። ከአረጋውያን፣ ከመምህራንና ከመንፈሳዊ አባቶች በተጨማሪ ከሌሎች ሰዎች ተሞክሮ መማር እንችላለን። መጽሐፍትም ሌላኛው ትልቅ የመማሪያ ምንጫችን ናቸው። ከእውቀት ምንጮች ሁሉ ስንቀዳ በጥበብና በጥንቃቄ መሆን አለበት፤ መረጃዎችንም በደንብ መርምረንና ለይተን መውሰድ ይኖርብናል።ሕይወትን
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    16 Sept, 10:29

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    12 Sept, 07:55

    ሰላም ለበድነ ሥጋከበንጹህ ግንዘተ ሥጋ ለተገነዘ ለቅዱስ በድነ ሥጋህ ዳግመኛም የሰማይ የብርሃን ክዋክብት ጌጥን ለተሸከመ መቃብርህ ሰላምታ ይገባል። ጣፋጭ ፍሬን ያፈራህ የገነት ተክል መልካም ዛፍ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ይህን ያንተን የመልክህን ስም የሚንቅና የሚያቃልል ፍጡር በሰውና በመላእክት አፍ ተለይቶ የተወገዘ ይሁን። የቅድስና ፍሬ መዓዛን ያፈራህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የንጽሕናን ሰላማዊ ፍሬ እመገብ ዘንድ ደስ እንዲያሰኝ የምለምንውም ኹሉ እንዲፈጸምልኝ የሥራዬም ትርፍ እጥፍ ይሆንልኝ ዘንድ ቅዱሳን መላእክትም አብረውኝ እንዲቆሙ እኔ ያንተ ወዳጅ የአማላጅነትህን ጸጋ እማፀንሃለሁ"አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ ዘዕለተ ልደቱ፤ መጽአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት ሎቱ፤ አሥመረቶ ወትቤሎ ሀበኒ በጻሕል ርእሰ ዮሐንስ ወንጌላዊ።" ዚቅ ዘመስከረም ፪የቅዱሱን ታሪክ ለማንበብእንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን!
    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
    1,020152Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    11 Sept, 14:42

    🌼🌼ዘመነ ሉቃስ🌼🌼✍️ይትባረክ ጉልላትየአ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባዔ የ2019 ዓ.ም ሰብሳቢ🌻ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች፤ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ!😊✨️በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።✨️ መዝ 65 ፥ 11​🌻የዕድሜያችንን ርዝመት በምሕረቱ ጽፎ፣ የዘመናት ባለቤትነቱን በሥራው ገልጦ፣ ያለፈውን ዓመት በደካማነታችን ላይ በይቅርታ አልፎ ለዚህ ለተባረከ አዲስ ዓመት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን።❣️ነቢዩ "በምድረ በዳ መንገድን፥ በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ" እንዳለ፤ የገባንበት አዲሱ ዘመን በሕይወታችን በረሃ ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ የሚፈስበት የተቀደሰ ዓመት ይሁንልን።😊በኃጢአት የዛለ ማንነታችን በመንፈሳዊ ተጋድሎና በዕንባ ንስሐ የሚታደስበት፣በፍቅረ ቢጽ እጦት ለቀዘቀዘው ልባችን ሰማያዊው የክርስቶስ ፍቅር የሚሰፍንበት፣የወንጌል ብርሃን በኑሮአችን፣ በንግግራችንና በግብራችን ሁሉ ተገልጦ ለዓለም ሁሉ ማረፊያ የሚሆንበት፣በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እናታዊ አማላጅነት ጥላ ሥር ሆነን ፈተናን የምናሸንፍበት የተስፋ ዘመን ይሁንልን። እኛ ተማሪዎች ሰሎሞን የለመናትን ጥበብ ገንዘብ አድርገን በትምህርታችን በዕውቀትና በምግባር የላቀ ፍሬ የምናፈራበት፤በፍቅርና በአንድነት ጸንተን የግቢ ጉባኤያችንን የወንጌል ዓላማ ወደ ላቀ ደረጃ የምናሸጋግርበት የሰላምና የዕድገት ዘመን ያድርግልን።🌻🎉ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
    1,04081Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    11 Sept, 08:17

    881file11Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    11 Sept, 07:11

    2018 እንደ ቀልድ አለቀና 2019 ገባ ። አይገርምም?የፈረንጆቹ 2019 ራሱ እንደ ትናንት ቅርብ መስሎ ይሰማኛል። ጊዜው በጣም ይነጉዳል፤ ብዙዎቻችሁም ይህንን ስሜት የምትጋሩኝ ይመስለኛል።ይህ ዓመት ፈጣን፣ ያኛው ደግሞ ቀስ ያለ ነበር እንላለን። ሆኖም ይህ የእኛ ስሜት እንጂ፣ የጊዜ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ዘመኖችን እኩል አድርጎ ሰጥቶናል። ትልቁ ጥያቄ ግን፦ ከዘመን ዘመን ስንሸጋገር፣ አዲስ ዘመንን አዲስ የሚያደርገው ምንድነው? ብዙ ቅዱሳን ክርስቶስን ያላወቁበት፣ ከእርሱ ጋር አንድ ሳይሆኑ የኖሩበትን ዘመን እንደ ኖሩት አይቆጥሩትም። ከክርስቶስ ተለይተን ምን ሕይወት አለና? ጌታን አግኝተው፣ በእርሱ እና ለእርሱ የኖሩበትን ዘመን ነው በእውነት ኖረናል ብለው የሚቆጥሩት። እኛስ? ምን ያህሉን ዘመናችንን ከክርስቶስ ጋር ኖረናል? የተሸራረፉትን ሰዓታት ሁሉ ብንሰበስባቸው፣ ከክርስቶስ ጋር የነበርንባቸው ጊዜያት በጠቅላላ የዓመታችንን ስንት ፐርሰንት ይይዙ ይሆን?ወደ ቀደመው ጥያቄያችን ስንመለስ፣ ዓመቱ ሳናስበው የሚያልቅብን ከእግዚአብሔር ተለይተን በዓለም እየባዘንን ስላሳለፍነው ይሆን? ከጊዜ ባለቤቱ ጊዜን ሰርቀን ይሆን? ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ስላልበላንና ስላልጠጣን ይሆን?ሊቁ አውጉስጢን እንዳለው፦ “አቤቱ፥ አንተ ለእራስህ ፈጥረኸናልና፥ ልባችንም በአንተ ውስጥ እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም።” እኛም ከእርሱ ጋር አንድነት ከሌለን፣ ሁሌ እንደባከንን እንኖራለን።
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    11 Sept, 07:10

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    10 Sept, 11:56

    ክፍል 2 ከትናንት የቀጠለ...ጌታዬ ሆይ፣ ትእዛዛትህ በልቤ ውስጥ የተወደዱ ይሁኑ። እነርሱን በመጠበቅም ውስጥ ሀሴትን ላግኝ፣ ነፍሴም የተወደደ ጣዕማቸውን እያጣጣመች ትርካ። ይህ መንፈሳዊ ሕይወትህን ልትገነባበት የሚገባ ጠንካራ መሠረት ነው። ሕይወትን በማያቋርጥ ትግል መቀጠል በእጅጉ ያማል፣ መውጣት እና መውረድ፣ መነሳት እና መውደቅ፣ አንዴ ከእግዚአብሔር ጋር፣ እንደገናም ከዓለም ጋር እየዋሹ መኖርም በእውነት እጅግ ያማል፣ ያደክማልም። ስለዚህ፣ ቀና በል እና እግዚአብሔርን እንዲህ በለው፦ “አቤቱ! ጌታዬ ሆይ፣ ይህን ከንቱነቴን ከእኔ አስወግድ፤ ዓለም እና ምኞቶቿም በጸጋህ፣ ቅዱስ በሆነው መንፈስህ እና በመለኮታዊ ኃይልህም ከእኔ ይራቁ።” “የዓለምን ፍቅር ከልቤ ውስጥ አውጣልኝ። ይህንን ድንጋይ ልቤንም ከእኔ አስወግድልኝ።” እኔ በጣም ደካማ ነኝ፤ ፈተናንም ልቋቋም አልችልም። ይህንንም ድካሜን ትንሽ በምትባል ፈተና እንኳ ደጋግሜ ወድቄ አይቼዋለሁ። የራሴ የምለው ኃይልም የለኝም፣ በራሴ ላይም መታመን አልችልም። ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ወደ ሕይወቴ ግባና አድነኝ። ለሞት እንደተቃረበ ሰው እጅግ ፈርቼአለሁ፤ ሳይመጣብኝ እንዲህ የፈራሁት ሞት በእውነትም ቢመጣብኝስ ምን ይውጠኝ ይሆን? ጌታዬ ሆይ፣ ምን ላድርግ? ሕይወትን አገኝ ዘንድ ወደ መቅደስህ ከተማ ተጠግቼ የመሠዊያውን ቀንድ ይዣለሁ። አንተን የሚወድህ፣ ደግሞም አብልጦ ይወድህ ዘንድ የሚጓጓው ይህ ልቤ፣ አሁንም የኃጢአትን ፍቅር እንደያዘ ነውና የመሠዊያውን ቀንድ ብለቅ ምንም ኃይል አይኖረኝም፤ ሞትም ይጠብቀኛል። አዎ! ጌታ ሆይ፣ አሁንም በዚያው ምኞቴ እና
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    9 Sept, 11:43

    አዲሱን ዓመት እንዴት እንጀምር?ክፍል 1ለውጥ የሚመጣው እንዴት ነው? በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚመጣው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ዙፋን ላይ እስካልነገሠ ድረስ፣ እውነተኛ ለውጥ ልናመጣ አንችልም። እስቲ ራሳችንን በውል እንጠይቅ፤ በሕይወታችን ውስጥ ለሚታየው አለመረጋጋት እና ሰላም ማጣት ምክንያቱ ምንድን ነው? ለመውጣት እና ለመውረዳችን ምክንያቱ ምንድን ነው? ለምን እንነሳለን? ለምንስ ፈጥነን እንወድቃለን? በመንፈሳዊ ሕይወታችን የሰደደው ችግርስ ምንድን ነው?በግልጽ ለመናገር ትልቁ ችግራችን ይህ ነው፦ እግዚአብሔርን መውደድ እንፈልጋለን፤ ልባችን ግን አሁንም ዓለምንና የዓለምን ምኞት እንደያዘ እና እንደወደደ ነው። አዎ! ዓለምን መውደድ ብቻ ሳይሆን፣ ከዓለምም ውስጥ የምንመኘው፣ ልባችን የሚፈልገው፣ የሆነ ነገር አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ብለን እነዚህን ምኞቶች ለመታገልና ለመቃወም እየሞከርን ኃጢአት ላለመስራት ብንጥርም፣ በልባችን ግን አሁንም ከዓለም ጋር ያለንን ፍቅራችንን አልተውንም። ልባችን አንድ ሆኖ አልጸናም፤ ሁለት ልብ ሆነናል። አንድ ጸሐፊ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “በዚያን ወቅት ከራሴ ጋር እታገልና እዋጋ ነበር ፤ በአንድ አካል ውስጥ ያሉ ሁለት ሰዎች እንደሆንኩ እስኪሰማኝ ድረስ፣ አንዱ ልቤ ወደፊት እንድራመድ ሲገፋኝ ሌላኛው ማንነቴ ደግሞ እንዳልራመድ ወደኋላ ይጎትተኝ ነበር።” ስለዚህ መላው ችግራችን ከዚህ ለሁለት ከተከፈለ ማንነታችን የሚመነጭ ነው። ይህም መከፋፈል በውስጣችን የሚካሄድ ትልቅ ጦርነት ነው፤ የዓለም ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    9 Sept, 11:43

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    8 Sept, 10:43edited

    ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር- እግዚአብሔር የሰራት ቀን ይህች ናት (መዝ 117(118)፡24)ይህች ዕለት በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆች ቁስል ላይም የተሾመ ፈታሄ ማህጸን ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት የሆነ የቅዱስ ሩፋኤል በአለ ሢመቱ፣ የቅዳሴ ቤቱም የሚከበርባት ዕለት ናት። (ጦቢት ፲፪፥፲፭)ዳግመኛም በዚህች ዕለት አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫፥፰-፲፯)፡፡ የጦቢትን ዓይንም አብርቶ ለልጁ ለጦቢያም መልካም ትዳርን ያበጀለት በዚህች ዕለት ነው።ይህች ዕለት ከዕለታት ተለይታ የተመረጠች ናት። የሰማይ ደጆች የሚከፈቱባት መላእክት የሚወጡባት የሚወርዱባት ጸሎት ልመናችንንም የሚያሳርጉባት የእግዚአብሔር አምላካችንን ቸርነት ምህረትን የሚያወርዱባት ዕለት ናት። ቀላያተ ማያትም የሚባረኩበት ለእያንዳንዱ ለሚያምንም ሁሉ የስጋም የነፍስም ድኅነት የሚያገኝባት ዕለት ናት።የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ ቅዱስ ሩፋኤል(ጦቢት ፲፪፥፲፭) ለሀገራችን ለምድራችን ቸርነት ምህረትን ያድርግልን። በአዲሱንም ዓመት ባርኮ ይስጠን።ወስብሐት ለእግዚአብሔር፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ሥነ-ጽሑፍ ንዑስ ክፍል
    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
    93983Open in Telegram
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    7 Sept, 13:47edited

    «በረከትን ሁሉ የተሸከምሽ አንቺን የማይወድ ማን ነው? አንድ ጊዜ ቀምቶ የወረሳቸውን ንብረቶች ሁሉ መልሰሽ ከወሰድሽበትና ባዶውን ካስቀረሽው ከሰይጣን በቀር አንቺን ማን ይጠላል? አንቺን ተስፋ አድርጎ ወደ ሲኦል የወረደ ማንም የለም፤ ያለ አንቺም ወደ ሰማይ የወጣ የለም። ያለ ንስሐ እግዚአብሔርን ማየት የሚችል ማን ነው? በአንቺስ ተስፋውን አድርጎ በሰይጣን እጅ የወደቀ ማን ነው? በአንቺ ሳይታጠብ ንጹሕ የሆነ አለን? በአንቺ ውኃነት ተክሉን አጠጥቶ የደስታን ፍሬ ያልቀጠፈ ማን ነው? በንስሐ እንባስ ፊቱን አጥቦ በልቡ እግዚአብሔርን ያላየ ማን ነው? ለበደለኞች አማላጅ ትሆኚ ዘንድ የተሰጠሻቸው የይቅርታ እናቱ ንስሐ ሆይ፤ አንቺ ብፅዕት ነሽ፤ የመንግሥቱን ቁልፍ ሰጥቶሻልና አንቺ ጠይቀሽ እግዚአብሔር የሚዘጋው በር የለም» አረጋዊ መንፈሳዊ"... ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ዘጸዋዕኮ ለጳውሎስ ጸውዐነ ውስተ ከብካብከ ዘበሰማያት...""... ጳውሎስን የጠራኸው ስምህ የጣፈጠ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኛንም ወደ ሰማያዊት ሠርግህ ጥራን ..." ሰአታት ዘሌሊትእኛም ይህን ሰምተን ልንመለስ ይገባል። ንስሓ ዕለት ዕለት የምንድንባት ብትሆንም በተለይ ይህች የጳጉሜን ወር ዳግም ምጽአት የሚታሰብባት ናትና ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን።
    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    6 Sept, 14:33

    forwarded from @mkaddisababacentermedia

    ቀጥታ ሥርጭት ተጀምሯል በማኅበረ ቅዱሳን የዩቱብ ቻናል ይከታተሉ ከሥር ባለው ሊንክ ይጠቀሙhttps://www.youtube.com/live/aYUh8Flon_E?si=H6_-DAPgzKXvhRyR
    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
  • ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

    31 Aug, 10:17

    Image from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤImage from a post by ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ