Latest posts

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
22 Sept, 10:30edited
ሊንኩን ከስር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/Yo40At75hII?si=YQKSZMAzi-37imnz https://youtu.be/Yo40At75hII?si=YQKSZMAzi-37imnz https://youtu.be/Yo40At75hII?si=YQKSZMAzi-37imnz https://youtu.be/Yo40At75hII?si=YQKSZMAzi-37imnz

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
21 Sept, 06:31edited
ሶስት መቶ ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ለ252 ተማሪዎች የትምህርት መማርያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ። በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ምዕራብ ሸዋ አካባቢው ክልል በእጀርሳ ላፎ ወረዳ የኦላንኮሚ ከተማ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ለተማሪዎች የመማርያ መሳርያዎችን ድጋፍ አደረገች።እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን እጀርሳ ላፎ ወረዳ፣ የኦላንኮሚ ከተማ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ የአቅም ውስንነት ላለባቸው 252 ተማሪዎች ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትምህርት መሣሪያዎችን በመግዛት ድጋፍ አድርጋለች። የኦላንኮሚ ከተማ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ፓስተር ዋቅጅራ ቡሊታ እንደተናገሩት፣ ቤተክርስቲያን የወንጌልን ትምህርት በማስተማርና መንፈሳዊ ስራን ከመሥራት በተጨማሪ፣ እግዚአብሔር ከሰጣት ተልዕኮዎች አንዱ ድሆችን ማሰብና መርዳት እንደሆነ በመግለጽ እንዲሁም በሚያስፈልግበት ጊዜ አቅም ከሌላቸው፣ ከታመሙና ከታሰሩ ሰዎች ጎን በመቆም የሐሳብ፣ የገንዘብና የጸሎት ድጋፍ በማድረግ የእግዚአብሔርን ፍቅር ልናሳያቸው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።የኦላንኮሚ ከተማ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ የመሪዎች ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አበራ ጢዬ እንደገለጹት፣ ወንጌል በችግር ላይ ያሉና ድሆችን በመርዳት ረገድ ጠንካራ ትምህርት አለው። ደካሞችን፣ ድሆችንና በችግር ላይ ያሉትን መርዳት የእግዚአብሔርን ፍቅር መግለጽ እንደሆነ ገልጸው፣ ድሆችንና በችግር ላይ ያሉትን መርዳት የልግስና ሥራ ብቻ ሳይሆን፣ ከፍቅር ትዕዛዝና ከክርስቲያናዊ እምነት እሴት አንዱ መሠረታዊ ክፍል መሆኑን ተናግረዋል። አያይዘውም በዚህ ድጋፍ ላይ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
21 Sept, 06:29

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
21 Sept, 06:10edited
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የተማሪዎች የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ፕሮግራም ተካሄደ።ቅዳሜ መስከረም 9/2019 ዓ.ም በጉለሌ ጳውሎስ አጥቢያ የተማሪዎች የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ፕሮግራም ተካሂዶዋል።በዕለቱ የክልሉ የልጆች እና የወጣቶች ክፍል ሃላፊ የሆኑት መጋቢ ሽመልስ ጠጂ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የፕሮግራሙ ዓላማ ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የመንፈስ ቅዱስን ሙላት ተቀብለው ስኬታማ እንዲሆኑ እና የእግዚአብሔር አብሮነት ከፊታቸው እንዲቀድም መሆኑን ገልጸዋል። በመቀጠልም ዘማሪ ታማኝ ሙልነህ በዝማሬ አገልግሏል። አገልጋይ አቤል "የመፍትሔ ትውልድ መሆን" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል ለተማሪዎች ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጸልየዋል። በርካታ ልጆች በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተሞልተው ከአጋንንት እስራት ተፈተዋል።መጋቢ ሽመልስ ጠጂ ሁልጊዜ ክልሉ በሚያዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በንቃት የሚሳተፉትን አጥቢያዎች አመስግነዋል። ተሳታፊዎች ጌታ መልካም ጊዜ እንደሰጣቸውና መንፈሳዊ መነቃቃትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። ለበለጠ_መረጃ 👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc 👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/ 👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
21 Sept, 06:10

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
21 Sept, 06:10

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
20 Sept, 16:26edited
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የአጥቢያ መሪዎች፣የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣የወጣት ተወካዮች ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ።መስከረም አርብ 8 እና ቅዳሜ 9 /2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የተካሄደው የመሪዎች ፣የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣የወጣቶች አገልግሎት መሪ ተወካዮች ስልጠና ተጠናቋል። የመጨረሻው ከሰዓት ስልጠና ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሴሚናሪየም ኮሌጅ ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት መምህር አዛርያ ሹሚ "ትምህተ እግዚአብሔር እና ቤተክርስቲያንና መላዕክት በሚሉ ነጥቦች ላይ ስልጠናውን ሰጥተዋል።በመቀጠል የቤተ እምነቱ የስነ መለኮትና ደቀ መዝሙርነት ዋና ክፍል ሀላፊ መጋቢ ታምራት አውሎ መሰረታዊ የክርስትና ማስተማርያ መጽሐፍ ፣የመምህሩ መመርያ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰጥተዋል። በመቀጠል የቤተ እምነቱ ማህበራዊ ዋስትና ክፍል ሀላፊ የሆኑት መጋቢ ምንዋብ ተካ " በቤተ እምነቱ የተዘጋጀውን የአምስት አመት ስልታዊ እቅድ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።በመጨረሻም የክልሉ ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ፋሲል ተክሉ በሁለቱ ቀናት ስልጠና ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነው በስልጠናው መሰረት ያገኛችሁትን እውቀትና መረዳት በየአጥቢያችሁ በመሄድ በመንፈስ ቅዱስ ላይ በመደገፍ መንፈሳዊ ሃላፊነታችሁን ተወጡ ሲሉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ያገለገሉትን አገልጋዮች በጸሎት ባርከው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።ለበለጠ_መረጃ 👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc 👉ፌስቡክ፡ https://www.faceb
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
20 Sept, 16:26

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
20 Sept, 16:25

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
20 Sept, 16:25

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
19 Sept, 09:18edited
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የአጥቢያ መሪዎች፣የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣የወጣት ተወካዮች ስልጠና በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።ቅዳሜ መስከረም 9 /2019 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ እየተካሄደ የሚገኘው የመሪዎች ስልጠና ላይ ከ500 በላይ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣የወጣቶች አገልግሎት መሪ ተወካዮች በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ። ፕሮግራሙ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን በመጋቢ ኤርሚያስ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል። በመቀጠል የክልሉ ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ፋሲል ተክሉ ለሰልጣኞች መንፈሳዊ ሰላምታ በመስጠት ስልጠናው በመልካም ሁኔታ ሁለተኛ ቀኑን እየተሰጠ እንደሚገኝ በመግለጽ ሰልጠኞችን አበረታተዋል። ዶ/ር ዘለለው አርጋው "የጥንታዊ ጴንጤቆስጤዊነት ክርስትና አስተምሮ እና መጽሃፍ ቅዱሳዊ ልምምዱ በሚል ርዕስ ስልጠናውን ሰጥተዋል። ትላንትና አርብ ከሰዓት የነበረው ስልጠና የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ሴሚናሪ ኮሌጅ አስተማሪ በሆኑት በመምህር ሀብታሙ ሰለሞን እና በመምህር መንግስቱ ወልደማርያም የተሰጠ ሲሆን የነጻ ጸጋ እና የጸጋ ሉዕለዊነት መጽሐፍ ቅዱሳዊና ስነ መለኮት ዳሰሳ እንደ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከምታምንበት አንጻር እንዴት ይታያሉ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጥናታዊ ጹሁፍ በማቅረብ ስልጠናውን ሰጥተዋል። ይህ የመሪዎች፣የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እና የወጣት ተወካዮች ስልጠና ዛሬ ከሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ መሆኑን የታወቀ ሲሆን መስከረም 26 እና 27/2019 "ዓ.ም በአዋሬ ሙሉ ወንጌል
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
19 Sept, 09:18

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
5 Sept, 18:59
#የኢትዮጵያ_ሙሉ_ወንጌል_ስነ_መለኮ_ሴሚናሪየም_ተማሪዎችን_በደመቀ_ሁኔታ_አስመረቀ። ቅዳሜ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሴሚናሪየም ተማሪዎችን በደመቀ ሁኔታ ሲያስመርቅ የቤተ እምነቱ ፕሬዚዳንት ፣ የሴሚናሪው ፕሬዚዳንት ፣ከደቡብ አፍሪካ የመጡ እንግዶች፣ ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል። የመክፈቻ ጸሎት ተደርጎ ዘማሪ ፓስተር ያሬድ ማሩ በዝማሬ በማገልገል ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል። በመቀጠል
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church
5 Sept, 17:15
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የአገልጋይ ሹመት ተካሄደ። እሁድ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም በጀቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል በአለም ገና አጥቢያ የአገልጋይ ሹመት ፕሮግራም ሲካሄድ የክልሉ ፕሬዚዳንት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የጸሎት እና የዝማሬ አምልኮ ጊዜ ተካሄዶአል። የክልሉ ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ አእምሮ መልካሙ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉ ሲሆን እንዲሁም የወንድም ጉዲሳ
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.