gram news
በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB ) channel avatar

በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

@ethiobookclub2

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው 1ጴጥሮስ 1:23-ፍጻሜ

ProjectsENReligion

4,400subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    22 Sept, 17:08

    13/01/2019 ሉቃስ 11:5-14እንዲህም አላቸው ከእናንተ ማናቸውም ወዳጅ ያለው፥ በእኩል ሌሊትስ ወደ እርሱ ሄዶ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ሦስት እንጀራ አበድረኝ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን? ያም ከውስጥ መልሶ አታድክመኝ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን? እላችኋለሁ፥ ወዳጅ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ንዝነዛው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፍትላችሁማል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?.......1 ቆሮንጦስ 7:12-18 ያዕቆብ 5:14-17 ሐዋ.ሥራ 19:17-22👉ቅዳሴ ዘባስልዮስ (እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ)ምስባክ መዝሙር 31:1-2ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢአቶሙወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኵሎ ጌጋዮሙብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ
    18471Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    22 Sept, 13:48

    መልካም ዜና ለወላጆች ብርሃን የጥናት ማዕከል እንደተለመደው በ2019 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የሚሆን የኢንተራንስ ማዘጋጃ ቲቶር በመደበኛ መርሐ ግብር ከሰኞ እስከ አርብ እና በቅዳሜና በእሑድ መርሐግብር አዘጋጅቷል ። ያለን ቦታ የተወሰነ በመሆኑ አስቀድመው ልጆችዎን ያስመዝግቡ ። አድራሻ ፦ ከአጠና ተራ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ሕንጻችንለበለጠ መረጃ ፦ 0986777407 0937329987 ይደውሉ የቴሌግራም አድራሻ ፦ @MWYSMGK ፦ @mogeswy
    Image from a post by በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )Image from a post by በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    21 Sept, 16:30

    12/01/2019 ማቴዎስ 18:15-19“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል....ቆሮንጦስ 5:3-11 ይሁዳ 1:9-20 ሐዋ፡ሥራ 20:28-31👉 ቅዳሴ ዘቄርሎስምስባክ መዝሙር ፴፫ : ፯ – ፰ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    20 Sept, 18:05

    11/01/2019 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ሉቃስ 21:12-21ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤ ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል። ሰለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤ ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና። ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤ በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ። ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ.....ዕብራውያን 12:1-12 ያዕቆብ 3:1-13 ሐዋ.ሥራ 10:1-9ምስባክ መዝሙር 78:10-11ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነበቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወይባዕ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሐንትርጉም
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    19 Sept, 16:02

    ዘሰንበተ ክርስቲያን ማርቆስ 4:24-39እንዲህም አላቸው፥ “የምትሰሙትን አስተውሉ፤ በሰፈራችሁበት በዚያ መስፈሪያ ይሰፍሩላችኋል፤ ይጨምሩላችኋልም። "ላለው ይሰጡታል፤ ይጨምሩለታልም፤ የሌለውን ግን፤ ያን ያለውን እንኳ ይወስዱበታል።”እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔር መንግሥት፤ መልካም ዘርን በምድሩ ላይ እንደሚዘራ ሰው እንደዚሁ ናት። እርሱም በሌሊት ይተኛል፤ በመዐልትም ይነሣል፤ እርሱም ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል፤ ያድጋልማል ምድሪቱም ከእርስዋ ፍሬ ትሰጣለች፤ መጀመሪያ ቡቃያን፥ ከዚህም በኋላ ዛላን፥ ቀጥሎም በዛላው ላይ ፍጹም ሰብልን ትሰጣለች። ፍሬንም ፈጽሞ ባፈራ ጊዜ ያንጊዜ መከር ደርሶአልና፤ ማጭድ ይላካል።”"እንዲህም አለ፥ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እመስላታለሁ? ምንስ ትመስላለች? "እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፤ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካሉ አዝርዕት ሁሉ ታንሳለች። "በተዘራችም ጊዜ ትበቅላለች፤ ከአትክልትም ሁሉ ትበልጣለች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ በታች ሊጠለሉ እስከሚችሉ ድረስ ታላላቅ ቅርንጫፎችን ታወጣለች።”መስማትን በሚችሉበት መጠን እንዲህ ባለ ብዙ ምሳሌ ቃሉን ነገራቸው። ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም። ለብቻቸውም ሲሆኑ ለደቀ መዝሙርቱ ሁሉን ነገር ይተረጒምላቸው ነበር። ያንጊዜም ሲመሽ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ወደ ማዶ እንሻገር” አላቸው። ሕዝቡንም አሰናበተና በታንኳ ወሰዱት፤ ከእነርሱም ጋር ሌሎች ታንኳዎች ነበሩ። ጽኑ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፤ ከሞገዱም የተነሣ ውኃው ታንኳውን እስኪሞላው ድረስ ማዕበሉ ወደ ታንኳው ይገባ ነበር። “እርሱ ግን በታንኳው በስተኋላ
    602115Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    19 Sept, 06:55

    "ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጥል አይደለም፡፡የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በእናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ"ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
    6091941Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    18 Sept, 16:04

    09/1/2019 ማቴዎስ 7:24-ፍጻሜስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ። ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና..........ሮሜ 8:35-ፍጻሜ ያዕቆብ 1:2-13 ሐዋ.ሥራ20:16-22👉ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ)ምስባክ መዝሙር 45:3-4ደምፁ ወተሐምጉ ማያቲሆሙወአድለቅለቁ አድባር እምኃይሉፈለግ ዘይውኅዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር
    6631321Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    17 Sept, 16:40edited

    08/01/2019 ማቴዎስ 23:29-ፍጻሜእናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ። እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ። እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል። ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም.....ዕብራውያን 11:23-29 ይሁዳ 1:9-12 ሐዋ.ሥራ 7:30-39👉ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ (ዓቢይ)ምስባክ መዝሙር 131:9-10ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑበእንተ ዳዊት ገብርከ
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    16 Sept, 15:22

    07/01/2019 ማርቆስ 1:23-29በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ፡ እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ። ሁሉም ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው? ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ። ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ...ዕብራውያን 13:13-22 1 ጴጥሮስ 3:14-18 ሐዋ.ሥራ 16:16-22👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም (ጐሥዐ)ምስባክ መዝሙር 83:6እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይልወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን
    806122Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    16 Sept, 14:36

    በቤተክርስቲያናችን ዲያቆን ተደርገው መሾም ያለባቸው ያገቡ ምዕመናን ብቻ መሆን እንዳለባቸው አሁን ያለንበት ጊዜ ከምንም በላይ ማሳያ ነው። እንደሚታወቀው አገልጋይ ሲሆን አንድ ሰው ልታይ ልታይ በሚል የተርእዮ ፈተና መፈተኑ አይቀርም ስለዚህም አገልግሎቱ ለእግዚአብሔር መሆኑን ይረሳና እርሱ ጎልቶ የሚታይበት ወደ ማድረግ ሊሔድ ይችላል። ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ በተለይ የአዲስ አበባ አድባራት ላይ
    Telegramኪዳን ዘኢየሱስበዚህ ኹሉም ነገር አላፊ በኾነው ዓለም ውስጥ እየኖርን ፣ ለማያልፈው ዘለዓለማዊ ለኾነው ለክርስቶስ እንኑር "እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና" (1ኛ ጢሞ 6፡16)
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    16 Sept, 11:58

    forwarded from @kidanzeiyesus

    በቤተክርስቲያናችን ዲያቆን ተደርገው መሾም ያለባቸው ያገቡ ምዕመናን ብቻ መሆን እንዳለባቸው አሁን ያለንበት ጊዜ ከምንም በላይ ማሳያ ነው። እንደሚታወቀው አገልጋይ ሲሆን አንድ ሰው ልታይ ልታይ በሚል የተርእዮ ፈተና መፈተኑ አይቀርም ስለዚህም አገልግሎቱ ለእግዚአብሔር መሆኑን ይረሳና እርሱ ጎልቶ የሚታይበት ወደ ማድረግ ሊሔድ ይችላል። ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ በተለይ የአዲስ አበባ አድባራት ላይ ቅዳሴ ሲቀደስ ዜማው በምልክቱ መሆኑ ቀርቶ "ቀሸረው" ለመባል ዜማውን ለማሳመር የሚሽረቀረቁት ፤ በተለይ የክብረ በዓል ቀን ቅዳሴ ከሆነማ አይጣል ነው ዲያቆናቱ እኔ ልቀድስ ፣ እኔ ልቀድስ በሚለው ይጣላሉ እንዲሁም በሰው ፊት ድምጹ ያምራል እንዲባሉ አላግባብ ዜማውን ማስረዘም እና ማሽቀርቀር ውስጥ ይገባሉ ፤ እንዲሁም ሶሻል ሚዲያ ላይ በልብሰ ተክህኖ "ጎምለል ጎምለል" እያሉ መውጣትን ተያይዘውታል። መቼስ የእኛ ምዕመን ምስኪን ነው አገልጋዮችን "ቅዱሳን" አድርጎ እስከ መሳል በተለየ ዓይን ስለሚያይ ገና ጉርምስናውን ያልጨረሰ አንድ teenagerን የተለየ አድርጎ በማየት በትዕቢት ያሳብጡታል።እንዲሁም ሴቶች ብዙህ ጊዜ በእውቅና እና በዝና እንደ ሚፈተኑ ግልጽ ነው። በማኅበረሰብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ለሚሰጠው ወንድ ልባቸው ይሳሳል ምክንያቱም status ይማርካቸዋል pre-approved መሆኑን ያሳያልና። በዚህ ምክንያት ብዙህ ሴቶች እነዚህን ጎረምሳ ዲያቆናት idolize ወደ ማድረግ ይሔዳሉ ፤ Social media ላይ እያየን ያለነው trend አሰቃቂ ነው ሴቶች ዲያቆን ካልሆነ አላገባም ፣ ዲያቆኔ ሲቀድስ
    77796Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    15 Sept, 16:43

    06/01/2019 ዮሐንስ 12:36-ፍጻሜየብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ፡” አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው። ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ በእርሱ አላመኑም። ኢሳይያስ ደግሞ በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው። ክብሩን ስለ አየ ኢሳይያስ ይህን አለ፥ ስለ እርሱም ተናገረ። ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል። በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል። እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ። ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    14 Sept, 15:08

    05/01/2019 ማቴዎስ 13:31-44ሌላም ምሳሌ እንዲህ ብሎ መሰለላቸው፤ “መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው ላይ የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች። እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን ከአታክልት ሁሉ ትበልጣለች፤ የሰማይ ወፎችም መጥተው ከቅርንጫፎችዋ በታች እስኪያርፉ ድረስ ታላቅ ዛፍ ትሆናለች።”ሌላ ምሳሌንም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “መንግሥተ ሰማያት ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የለወሰችውን፥ ሁሉንም እንዲቦካ ያደረገውን እርሾ ትመስላለች።” ኢየሱስም ይህን ሁሉ ለሕዝቡ በምሳሌ ነገራቸው፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም። በነቢይ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከጥንት የተነገረውንም ምሳሌ እናገራለሁ” የተባለው ይፈጸም ዘንድ።ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጒምልን” አሉት። እርሱም መልሶ አላቸው፤ “መልካም ዘርን የዘራ የሰው ልጅ ነው። እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው። "የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም ፍጻሜ ነው፤ አጫጆቹም መላእክት ናቸው። እንግዲህ አስቀድሞ እንክርዳዱን እንደሚለቅሙት፥ በእሳትም እንደሚያቃጥሉት በዚህ ዓለም ፍጻሜም እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅም መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም ዐላውያንንና በደልን የሚያደርጉትን ሁሉ ይሰበስባሉ። ወደ እሳት ጒድጓድም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። "ያንጊዜም ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፤ ጆሮ ያለው መስማትን
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    13 Sept, 15:04

    4/1/2019 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ዮሐንስ 10:1-22እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም። ኢየሱስም ደግሞ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም። በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል። መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    12 Sept, 16:02

    ዘሰንበተ ክርስቲያን ዮሐንስ 1:15-38ምስክሩ ዮሐንስ ስለ እርሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፥ “እኔ ስለ እርሱ ከእኔ በፊት የነበረ ከእኔ በኋላ ይመጣል ያልኋችሁ ሰው ይህ ነው፥ እርሱ ከእኔ አስቀድሞ ነበረና።” "እኛም ሁላችን ከሙላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀበልን። "ኦሪት በሙሴ ተሰጥታን ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነልን። በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ገለጠልን እንጂ እግዚአብሔርንስ ከቶ ያየው የለም።"አይሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠይቁት ዘንድ ካህናትንና ሌዋውያንን ከኢየሩሳሌም በላኩ ጊዜ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው። እርሱም፥ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ አመነ እንጂ አልካደም። “እንኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት፤ “አይደለሁም” አለ፤ “እንኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይደለሁም” አለ። “እንኪያስ አንተ ማነህ? ለላኩንም መልስ እንድንሰጥ ስለ ራስህ ማን ትላለህ?” አሉት። “እርሱም፥ “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተናገረ የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ እያለ በምድረ በዳ የሚሰብክ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ። የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩ። “እንኪያስ ክርስቶስን ካልሆንህ፥ ኤልያስንም ካልሆንህ፥ ነቢይንም ካልሆንህ ለምን ታጠምቃለህ?” ብለው ጠየቁት። “ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ በውኃ አጠምቃችኋ ለሁ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል። ከእኔ በኋላ የሚመጣው፥ ከእኔ በፊት የነበረው፥ የጫማውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማይገባኝ ነው።” ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ
    1,010171Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    12 Sept, 10:05

    "ማንንም አትወንጅል ማንንም አትዳኝ ስህተታቸውን አትዘርዝር ድካማቸውን አታጉላ ራስህን ብቻ ውቀስ ለራስህም 'እኔ ነኝ መጥፎ ኃጢአተኛ' በለው ይህ ነው የመንፈሳዊ ሕይወት ጅማሮ አንዱ መንገድ ነው።" (አባ ሴራፊም)
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    11 Sept, 17:31

    2/1/2019 ማርቆስ 6:14-30ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ። ሌሎችም ኤልያስ ነው አሉ፤ ሌሎችም ከነቢያት እንደ አንዱ ነቢይ ነው አሉ። ሄሮድስ ግን ሰምቶ እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል አለ። ሄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን አግብቶ ነበርና በእርስዋ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን አስይዞ በወኅኒ አሳስሮት ነበር፤ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና። ሄሮድያዳ ግን ተቃውማው ልትገድለው ትፈልግ ነበር አልቻለችም፤ ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር። ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ ስትዘፍን ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የተቀመጡትን ደስ አሰኘቻቸው። ንጉሡም ብላቴናይቱን የምትወጂውን ሁሉ ለምኚኝ እሰጥሽማለሁ አላት፤ የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ፡ ብሎ ማለላት። ወጥታም ለእናትዋ ምን ልለምነው? አለች። እርስዋም የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ አለች ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም። ወዲያውም ንጉሡ ባለ ወግ ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው። ሄዶም
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    11 Sept, 16:29edited

    “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ 65፥11ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22መልካም አዲስ ዓመት
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    11 Sept, 16:25

    forwarded from @amin7_27

    ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
    969file3Open in Telegram
  • በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )

    10 Sept, 17:52

    forwarded from @stphk

    ተገኝታለችየሰንበት ትምህርት ቤታችን የህፃናት 2 ተማሪ የሆነችው ህፃን ሳምራዊት ተገኝታለች። እርሷን በመፈለግ ላገዛችሁን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን እግዚአብሔር ይስጥልን።
    Image from a post by በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )Image from a post by በእንተ ቅዱሳን መጻሕፍት ( BOOK CLUB )
    1,1402214Open in Telegram