gram news
Federal Ethics And Anti- Corruption Commission channel avatar

Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

@feacc

Use This Link For More Information https://twitter.com/EthiopiaFeacc https://www.youtube.com/channel/UCO_WiCAiDIkMMwqsZGK47nw/?guided_help_flow=5/ https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ProjectsENPolitics

11,100subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    22 Sept, 13:45

    የአቢሲንያ ባንክ አመራሮች “የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ሚና!’’ በሚል መሪ ቃል ስልጠናዊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 12/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን “የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ሚና!” በሚል መሪ ቃል ለአቢሲንያ ባንክ አመራሮች ዘርፍ ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።ስልጠናዊ ውይይቱ በባንኩ የሚስተዋሉ ዋና ዋና የሙስና ሥጋቶችና ተጋላጭነቶች፣ ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር ዙሪያ ለአመራሩ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።ስልጠናዊ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአቢሲንያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ የባንክ አሠራርና ቴክኖሎጂ በፍጥነት በሚለዋወጥበት ወቅት ስልጠናዎችም ከለውጡ ጋር መራመድ እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ሥነምግባር ግን ከሰው ባህሪ ጋር የተያያዘና በማንኛውም ጊዜ ትኩረት የሚሻ መሠረታዊ እሴት መሆኑንም አስረድተዋል።ባንኩ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር በሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራዎች፣ በተለይም በሥነምግባር ግንባታ ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ በቃሉ፣ አመራሮች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል የተገኙ እውቀቶችን በሥራ ላይ እንዲተገብሩ አሳስበዋል።የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር ሥራም ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር በቀጣይነት እንደሚጠናከር ጠቁመዋል።በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ኪዳነ ምህረት በበኩላቸው፣ ዘርፍ ተኮር ስልጠናው
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    22 Sept, 13:45

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    22 Sept, 05:17

    ሥነምግባራዊ አመራርና ሠራተኛ ማፍራት ዘላቂ የፀረ-ሙስና ትግል መሠረት ይሆናል!ሙስና የሕግ የበላይነትን፣ የተቋማትን ተዓማኒነትና የሕዝብን እምነት የሚጎዳ አደገኛ ወንጀል ነው። ስለሆነም ሙስናን በቁጥጥርና በሕግ አፈጻጸም ብቻ ለመከላከል ከመሞከር ባለፈ፣ ሙስናን የማይታገስ የሥነምግባር ባህል መገንባት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ በሥራ ቦታ ታማኝነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ፍትሐዊነትንና የሕዝብን ጥቅም የሚያስቀድም ሥነምግባራዊ አመራርና ሠራተኛ በማፍራት ይጀምራል።ሥነምግባራዊ አመራርነት በቃል ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ በዕለታዊ ውሳኔና ተግባር የሚረጋገጥ ነው። አመራር ሕግንና የሥነምግባር መርሆችን በራሱ በመተግበር፣ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን እንዲሁም ለሠራተኞች አርአያ በመሆን የተቋሙን የሥነምግባር ባህል ይቀርጻል።በተመሳሳይ፣ ሠራተኞችም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በሙያዊ ብቃት ሲወጡ፣ ለሕዝብ የሚሰጠው አገልግሎት ይሻሻላል፤ ለሙስና የሚፈጠሩ ዕድሎችም ይቀንሳሉ። ስለዚህ የአመራር አርአያነትና የሠራተኛ ታማኝነት የተቋማዊ ሥነምግባር ባህል መሠረቶች ናቸው።የሥነምግባር ግንባታም በሥልጠና ብቻ የሚጠናቀቅ ሥራ ሳይሆን፣ በተቋማት ውስጥ በቀጣይነት የሚተገበር ሂደት ነው። በዚህም ግልጽ የሥነምግባር መርሆች፣ ፍትሐዊ አሠራሮች፣ የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ሥርዓቶችና የሚያጋጥሙ የሥነምግባር ጥሰቶችን በአግባቡ የሚያስተናግዱ ሥርዓቶች መዘርጋት ይገባል።ይህም አመራርና ሠራተኞች በሙያዊ ኃላፊነት እንዲሠሩ ከማገዙም በላይ፣ ሙስናን ለመከላከል፣ የተቋማትን ብቃት ለማሳደግና የሕዝብን እምነት ለማጠናከር
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    22 Sept, 05:16

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    21 Sept, 13:21

    ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ከሲቪል ማኅበራት ጋር ያለው ስትራቴጂካዊ ቅንጅት ተጠናክሮ ይቀጥላል(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 10/2019 ዓ.ም) የሲዳማ ክልል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ማኅበራት ጋር ባለፉት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል።በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ዮሳ፣ መንግሥት ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን ከሥር መሠረታቸው ለማስወገድ የጸና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ይዞ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።እንደ አቶ ዮሴፍ ገለጻ፣ ሙስናን እንደ አገራዊ ስጋት በመንግሥት ጥረት ብቻ በዘላቂነት ማስወገድ አዳጋች በመሆኑ፣ ቤተሰብና የሃይማኖት ተቋማት በጎ የሥነምግባር እሴቶችን የተላበሰ ትውልድ በመቅረጽ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።ሕዝባዊ መሠረት ያላቸው ተቋማትም ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በማውገዝና በመታገል ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበኩላቸው፣ ሙስናን መከላከል የጋራ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር የሕዝብን ሰላም የሚያደፈርሱ፣ ልማትን የሚያስተጓጉሉና ግጭትን የሚያፋፍሙ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።ችግሩ ከሥነምግባር ዝቅጠት ጋር በተያያዘ በመሆኑ፣ ሲቪክ ማኅበራት ነገን የሚረከበውን ትውልድ በበጎ ምግባር የመቅረጽ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።ኮሚሽኑም ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ከሲቪክ ማኅበራት ጋር
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    21 Sept, 13:21

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    21 Sept, 05:07edited

    በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ ስለመርዳትሙስና የሕግ የበላይነትን፣ የመልካም አስተዳደርንና የተቋማትን ተዓማኒነት የሚያዳክም፣ የሕዝብን እምነት የሚጎዳ እና የሀገርን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያደናቅፍ ከባድ ወንጀል ነው።በሙስና የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትም የወንጀሉ ውጤት በመሆኑ፣ ምንጩ እንዳይታወቅ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የወንጀሉን ውጤት ለመደበቅ የሚፈጸም ተጨማሪ የሕግ ጥሰት ነው።በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 33 በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና በወንጀሉ ስለመርዳት ይደነግጋል።የወንጀሉን ምንጭ ለመደበቅ ሀብቱን በሌላ ሰው ስም ማስመዝገብ፣ ከሕጋዊ ገቢ የተገኘ አስመስሎ ማቅረብ ወይም በሕጋዊ ግብይት የተገኘ ለማስመሰል መሞከር የዚህ ተግባር መገለጫዎች ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም የሀብቱን ምንጭ ለመደበቅ በማወቅ የሚረዳ ወይም የሚተባበር ሰው በተፈጸመው ድርጊት መሠረት ለሕግ ተጠያቂ ይሆናል።በሙስና ወንጀል ፈጻሚ ባለመሆን ብቻ ከተጠያቂነት መዳን አይቻልም፤ የወንጀሉን ውጤት ለመደበቅ፣ ምንጩን ለማስመሰል ወይም ይህንን ተግባር ለማስፈጸም በማወቅ የሚሳተፍ ማንኛውም ሰው በሕግ ሊጠየቅ ይችላል። ይህም የሙስና ውጤትን ማስቀጠልና ለወንጀሉ ሽፋን መስጠት ራሱ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ተግባር መሆኑን ያሳያል።የፀረ-ሙስና ትግልም የመንግሥት ተቋማት ብቻ ኃላፊነት አይደለም። በሙስና የተገኘ ሀብት ምንጩ ተደብቆ ሕጋዊ እንደሆነ ሲቀርብ ወይም ይህንን ለመደበቅ የሚደረግ ተግባር ሲታወቅ፣ በሕግ
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    21 Sept, 05:07

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    19 Sept, 12:58

    የቀድሞ የቪቶል ነዳጅ ነጋዴ በሙስና ወንጀል የአራት ዓመት እስራት ተፈረደበት(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 9/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) በቪቶል የነዳጅ ንግድ ኩባንያ ይሠራ የነበረው ጃቪየር አጊላር በኢኳዶርና በሜክሲኮ ባለሥልጣናትን በመደለል የንግድ ውሎችን ለማግኘት በፈጸመው የሙስና ድርጊት በዩናይትድ ስቴትስ የአራት ዓመት እስራት ተፈረደበት።አጊላር ከ2015 እስከ 2020 ድረስ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጉቦ በማውጣት፣ ለቪቶል ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የነዳጅና የጋዝ ንግድ ውሎች ለማስገኘት መሥራቱን የዩኤስ የፍትሕ መምሪያ ገልጿል።ይህም ጉቦ በመክፈል የመንግሥት የንግድ ውሳኔዎችን በመጠምዘዝ ትርፍ ለማግኘት የተፈጸመ የሙስና ድርጊት እንደነበር ተገልጿል።አጊላር በባለሥልጣናት ላይ የጉቦ መስጠት ድርጊትን ለመፈጸም መመሳጠር እና ያለአግባብ ገንዘብን ለመደበቅና ለማስተላለፍ መመሳጠር በሚሉ ክሶች በብሩክሊን ፌዴራል ፍርድ ቤት ጥፋተኝነቱ ተላልፎበታል።የአሜሪካ አቃቤ ሕጎች የ12 ዓመት እስራት እንዲጣልበት ቢጠይቁም፣ ፍርድ ቤቱ የአራት ዓመት እስራት፣ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የሙስና ወንጀል የገንዘብ ውርስ እና 100 ሺህ ዶላር ቅጣት ወስኗል ተብሏል።በተያያዘ ጉዳይ ቪቶል በ2020 በብራዚል፣ በሜክሲኮና በኢኳዶር ላሉ ባለሥልጣናት ጉቦ መስጠቱን አምኖ፣ በአሜሪካና በብራዚል የተካሄዱትን ምርመራዎች ለመፍታት 164 ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል።የአጊላር ጉዳይ በላቲን አሜሪካ ከመንግሥት ኩባንያዎች የንግድ ውሎችን ለማግኘት ባለሥልጣናትን በጉቦ መደለልን በተመለከተ በዩኤስ
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    19 Sept, 12:58

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    18 Sept, 15:30

    ካቢኔው በሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አደረጃጀት ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 8/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።1ኛ, ካቢኔው በቀዳሚነት ለልማት ለሚለቀቅ መሬት ለሚነሳ ቅሬታ የአቤቱታና ይግባኝ ሰሚ አካል ማቋቋም ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።ይህ አሰራር በልማት ምክንያት መሬታቸውን በሚለቁ ነዋሪዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በግልጽነትና በፍጥነት ለመፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።2ኛ, ካቢኔው በመቀጠልም የቋሚ ንብረት ታክስ /property tax/ አፈጻጸም ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት በመወያየት ለውሳኔ ወደ አስተዳደሩ ምክር ቤት ልኳል።ረቂቁ የአስተዳደሩን የውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ራሱን የቻለ ጠንካራ የፋይናንስ ምንጭ ይፈጥራል።3ኛ:- የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተቀናጀ የዘላቂነት አስተዳደርና የአገልግሎት ማሻሻያ ፓይለት ትግበራ ፕሮጀክት ላይ በመወያየት ውሳኔ አስተላልፏል።ማዕከላቱ ጥራታቸውን ጠብቀው በዘላቂነት እንዲሰሩ በማድረግ ወጣቶች በክህሎትና በእውቀት የሚበለጽጉበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በተጨማሪም ወጣቱ ትውልድ በበጎ ሥነ-ምግባር ታንጾ፣ ከአልባሌ ሱሶች የራቀና ለሀገር የሚጠቅም አምራች ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ ያግዛል።4ኛ, የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አደረጃጀት ላይ በመወያየት ውሳኔ አስተላልፏል።የሌብነትና የብልሹ አሰራር ምንጮችን ከስራቸው በማድረቅ የመንግስትንና የህዝብን
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    18 Sept, 15:30

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    17 Sept, 05:20

    በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ የሙስና ወንጀልሙስና የሕግ የበላይነትንና መልካም አስተዳደርን የሚያዳክም፣ የሕዝብን እምነት የሚጎዳ እና የአገርን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያደናቅፍ ወንጀል ነው። ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠርም ኢትዮጵያ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007ን አውጥታለች።አዋጁ ከደነገጋቸው የሙስና ወንጀሎች መካከል “በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ” በአንቀጽ 16 የተደነገገ ወንጀል ነው።በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ የሙስና ወንጀል ምንድነው?በሥራ ወይም በኃላፊነት የተገኘን ሥልጣን፣ ተፅዕኖ ወይም ተሰሚነት በመጠቀም ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማስገኘት ጥቅም መጠየቅ፣ መቀበል ወይም መስጠት የዚህ ወንጀል አካል ነው።ይህም ከሥራ ደረጃ፣ ሹመት፣ ሽልማት፣ የአገልግሎት ዋጋ፣ ውል፣ ጨረታ ወይም ሌላ የሕዝብ ጥቅም ጋር በተያያዘ ውሳኔ እንዲሰጥ ወይም እንዲለወጥ ተፅዕኖ ለማሳደር ሕገ-ወጥ ጥቅም መጠየቅን ወይም መቀበልን ያካትታል።በተጨማሪም አንድ ሰው ተፅዕኖ የማሳደር አቅም እንዳለው በመግለጽ ወይም ሌሎችን በማሳመን ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መጠየቅ፣ መቀበል፣ መስጠት ወይም ቃል መግባትም በሕግ የተከለከለ ነው።በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ የሙስና ወንጀል የሚያስከትለው ተጠያቂነትበአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 16 መሠረት፣ በዚህ ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው እንደወንጀሉ ሁኔታ ከ1 ዓመት እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራትና ከ3,000 እስከ 60,000 ብር መቀጮ ሊቀጣ ይችላል።የወንጀሉ ዓላማ፣ የተገኘው ጥቅም መጠን፣
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    17 Sept, 05:19

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    16 Sept, 13:27

    የኤጀንሲው የቀድሞ ኃላፊ በ8.49 ሚሊዮን ዶላር የሙስና ወንጀል 14 ዓመት ተፈረደባቸው(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 6/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቻይና ፍርድ ቤት በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ የተቋረጠውን የቻይና የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር (CFDA) የቀድሞ ኃላፊ ቢ ጂንግኳን በሙስና ወንጀል የ14 ዓመታት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።በምስራቃዊቷ ሻንዶንግ ግዛት የሚገኘው ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ቢ ጂንግኳን ከ1995 እስከ 2025 ባለው ጊዜ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ላይ በነበሩበት ወቅት፣ ከ57 ሚሊዮን ዩዋን (8.49 ሚሊዮን ዶላር) በላይ የሚገመት ገንዘብና ንብረት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀበላቸውን ገልጿል።ፍርድ ቤቱ በውሳኔው እንዳስታወቀው፣ ቢ ጂንግኳን ለተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በንግድ ሥራ፣ በአስተዳደራዊ ፈቃድና በፕሮጀክት አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ድጋፍ በማድረግ ጉቦ ተቀብለዋል ብሏል።ቢ ጂንግኳን በ2015 መጀመሪያ ላይ የCFDA ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ ይህም መንግሥት የአገሪቱን የመድኃኒት ግምገማ ሥርዓት ለማሻሻል ሰፊ ለውጥ ከጀመረበት ጊዜ ጥቂት ወራት በፊት እንደነበር አመላክቷል።ቢ እ.ኤ.አ. በ2018 ከባድ የክትባት ቅሌት ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ከኃላፊነታቸው የለቀቁ ሲሆን፤ በኋላም በፍርድ ቤት ፊት ጥፋታቸውን አምነው መጸጸታቸውን መግለጻቸውን ፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ገልጾ ሮይተርስ ዘግቧል።ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾#NCRS ሞባይል መተግበሪያ#ለAn
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    16 Sept, 13:27

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    16 Sept, 06:41

    በመልካም ሥነምግባር የታነጸ ትውልድ በጋራ እንገንባ!ትምህርት እውቀትና ክህሎትን ከማስጨበጥ ባለፈ፣ ብቁ፣ ታማኝ፣ ኃላፊነት የሚሰማውና ለሀገሩ የሚተጋ ትውልድ የሚገነባበት የሀገር ግንባታ መሠረት ነው። በመሆኑም የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በእውቀት እንዲበለጽጉ ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ሥነምግባርና በሀገራዊ እሴቶች የሚታነጹበት ዘመን እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ልንወጣ ይገባል።የዛሬ ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች ናቸው። ስለሆነም በትምህርት ዘመኑ በትጋት በመማር፣ እውቀትና ክህሎታቸውን በማዳበር፣ ታማኝነትን፣ ኃላፊነትን፣ ሕግ አክባሪነትንና ሌሎች መልካም እሴቶችን በተግባር በማዳበር ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው የተሻለ ነገ መገንባት ይገባቸዋል። የነገ ሀገራችን አቅጣጫና እድገት በዛሬው ትውልድ የእውቀት፣ የክህሎትና የሥነምግባር ግንባታ ላይ ይመሠረታል።ይህን የትውልድ ግንባታ ለማሳካት የቤተሰብ ሚና ወሳኝ ነው። ልጆች መልካም ሥነምግባርን ከሚነገራቸው ቃል ብቻ ሳይሆን፣ በየዕለቱ ከሚመለከቱት ተግባር ይማራሉ። ወላጆችና ቤተሰብ ታማኝነትን፣ ሀላፊነትን፣ ሌሎችን ማክበርንና በአግባቡ መኖርን በተግባር በማሳየት ለልጆቻቸው ጥሩ አርአያ መሆን ይገባቸዋል።መምህራን ደግሞ እውቀትን ከማስተላለፍ ባለፈ የተማሪዎችን አመለካከትና ሥነምግባር በመቅረጽ የነገን ትውልድ የሚያንጹ የትውልድ መሪዎች ናቸው። በሙያዊ ብቃት፣ በፍትሐዊነት፣ በታማኝነትና በኃላፊነት በመምራት ለተማሪዎቻቸው ተጨባጭ አርአያ መሆን፣ እንዲሁም በትምህርትና በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ
    Google PlayNCRS - Apps on Google PlayReport corruption in Ethiopia securely. Track progress & fight injustice.
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    16 Sept, 06:41edited

    Image from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption CommissionImage from a post by Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
  • Federal Ethics And Anti- Corruption Commission

    12 Sept, 10:46

    100 ሺህ ተከታዮች፤ የጋራ ተሳትፎ ድል!የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የፌስቡክ ገጽ ተከታዮች ቁጥር 100 ሺህ ተሻግሯል፤ የጉዞአችን አካል ሥለሆናችሁ እናመሰግናለን!!ይህ ቁጥር የተከታዮች ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ፣ በፀረ-ሙስና ትግል፣ በህግ ማስከበር ዙሪያ የሚደረገውን የጋራ ጥረት የሚያመላክት አንድ ትልቅ ምዕራፍ ነው።በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩትዩብ፣ በኤክስ እና በቲክቶክ የምናጋራቸው መረጃዎችና መልዕክቶች የኮሚሽኑን ሥራ ለህብረተሰቡ በቀላሉና በተከታታይ ለማድረስ ብቻ ሳይሆን፣ ህብረተሰቡ የሥነምግባር ግንባታንና የፀረ-ሙስና ትግሉን የራሱ አድርጎ እንዲሳተፍ የሚያስችሉ የግንኙነት መድረኮች ናቸው።ሙስናን መታገል የአንድ ተቋም ብቻ ኃላፊነት አይደለም፤ የሁላችንም የጋራ ተልዕኮ ነው። ስለዚህ በዲጂታል ሚዲያ የምንፈጥረው ግንዛቤ፣ የምንለዋወጠው መረጃ፣ የምንሰጠው ሀሳብ እና የምናደርገው ተሳትፎ ሁሉ የበለጠ ታማኝ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂ ማህበረሰብ ለመገንባት የራሱ አስተዋፅዖ አለው።100 ሺህ ተከታዮች መድረሳችን የጉዞው መጨረሻ ሳይሆን፣ የበለጠ ለመሥራት፣ የበለጠ ለመድረስና የበለጠ ለማሳተፍ አዲስ መነሻ ነው።በቀጣይም የዲጂታል መድረኮቻችንን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም፣ ግልፅ፣ ተደራሽና ተዓማኒ መረጃን በማቅረብ፤ የህብረተሰቡን ድምፅ፣ ሀሳብና ተሳትፎ በማጠናከር የትውልድ ሥነምግባር ግንባታንና የፀረ-ሙስና ትግሉን አብረን እናጠናክራለን።100 ሺህ ተከታዮች፣ 100 ሺህ ድምፆች፤ አንድ የጋራ አላማ!!የዚህ ጉዞ አካል ለሆናችሁ፣ መልዕክቶቻችንን