Latest posts

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
22 Sept, 03:34
የዕለቱ ስንቅእንዳያስፈራችሁ... አቅም የለውም!ስለ ፈተና ስናስብ ብዙ ጊዜ ዲያብሎስን አግዝፈን እናየዋለን። ሐዋርያው ጴጥሮስ "እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራል" ቢለንም (1ጴጥ 5፥8)፤ ነቢዩ ዳዊት ግን "የኃጢአተኞችን ጥርስ ሰብረሃል" ብሎናል (መዝ 3፥7)።ይህን አስመልክቶ ታላቁ አባ እንጦንስ ሲናገር፦ "የዲያብሎስን ሐሳብ አትፍሩ፤ እርሱ ኃይል የሌለው ደካማ ነው፤ ጌታችን ጥርሱን ሰብሮታልና" ይላል።ዲያብሎስ ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው! ትልቁ መሣሪያው ማጓራትና በድምፁ ማስደንገጥ ብቻ ነው። በክርስቶስ ለሚያምንና በጸሎት ለሚተጋ ሰው ግን ዲያብሎስ ምንም ማድረግ የማይችል ደካማ ፍጡር ነው።ዛሬ የሚያስፈራራችሁን ማንኛውንም የጠላት ድምፅ በክርስቶስ ስም እለፉት። ድምፁ እንጂ አቅሙ አይጎዳችሁምና! 🙏🏽✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Akka isin hin sodachifne... Humna hin qabu!
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
21 Sept, 03:32
የዕለቱ ስንቅሰው ሆይ እናስተውል!!ሰው እግዚአብሔርን እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አይተውምም !✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Yaa namaa, haa hubannu!!Namatu Waaqayyoon dhisa malee, Waaqayyo nama hin dhiisu!"✨✨✨ Guyyaa Gaarii ✨✨✨
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
20 Sept, 18:48
📚 ውድ አንባብያን!እንሆ፣ የእረፍት ጊዜያችን አልፎ ወደ ግቢ የምንመለስበት ጊዜ ደርሷል።❤️ በእረፍት ጊዜ ከቤተመጽሐፍት ክፍል የተዋሳችሁትን መጽሐፍት በጥንቃቄ እንዳነበባችሁ ተስፋ እናደርጋለን። ስለሆነም ወደ ግቢ ስትመጡ ያዋሳችሁትን መጽሐፍት ሁሉ በጥንቃቄ ይዛችሁ እንድትመጡ በአደራ እንጠይቃለን። 🙏📖⚠️ ማሳሰቢያ-> መጽሐፉ ላይ ጉዳት ካለ የተቀደደ፣ የተበላሸ ወይም ሌላ ጉዳት የደረሰበት መጽሐፍ ካለ አስጠግናችሁ እንድታመጡ እንጠይቃለን። -> መጽሐፍ የጠፋባችሁ ካላችሁ የጠፋ መጽሐፍ ካለ በገንዘብ ክፍያ እንደማንቀበል፣ የጠፋውን መጽሐፍ በመግዛት እንድታስረክቡ እናሳስባለን። -> ወደ ግቢ ከመጣችሁ በኋላ የቤተመጽሐፍት አባላት በስልክ እየደወሉ መጽሐፎቹን ስለሚቀበሉ፣ ስልክ ሲደወልላችሁ በመተባበር መጽሐፎቹን እንድታስረክቡ እንጠይቃለን። -> Withdraw ያደረጋችሁ ወይም በሌላ ምክንያት ግቢ የማትመጡ ተማሪዎች በዚህ ምክንያት ወደ ግቢ መምጣት የማትችሉ ከሆነ፣ ከታች በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር ደውላችሁ መጽሐፎቹን እንዴት ማስረከብ እንደምትችሉ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን።📞 ለተጨማሪ መረጃ፣ ሀሳብ ወይም አስተያየት:+251900045135 ማዕዶት 0941239090 ፀዲ


የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
20 Sept, 08:50
ሰላም ውድ ተማሪዎች 👋 እንደሚታወቀው የኢንተርን ሪፖርት የሚቀጥለው ሳምንት እናስገባለን 📅 ስለሆነም ፕሪንት ማስደረግ ለምትፈልጉ ሁሉ ሐሞና ኮፒ ቤት አለው 🖨️ ይላችኋል።ታዲያ ፕሪንት ለማስድረግ ከቤት ሁላ መውጣት አይጠበቅባችሁም 🏠 ሪፖርት file፣ በከለር ፕሪንት መደረግ የለባቸውን ገጾች፣ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥራችሁን አንድ ላይ በማድረግ ከታች በተቀመጠው username በመላክ 📩 ፕሪንት ማስደረግ ትችላላችሁ። ሐሞናም ሁሉን ዝግጁ አድርጎ ይጠብቃችኋል።በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይለዋል ይሄ ነው ያለምንም ድካም(መቼስ የአዳማን ጸሀይ ታውቁታላችሁ ☀️ 😴) ፣ በተቀላጠፈ አገልግሎት ⚡፣ ጥርት ካለ ፕሪንት ጋ ሐሞና ኮፒ ቤት 👉ታዲያ ቀደም ብሎ መላክ እንዳይረሳusername: @LILAD2 📞0916893233 📞0931460438📍ቦሌ በር ፊትለፊት


የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
20 Sept, 03:33
የዕለቱ ስንቅ"እግዚአብሔር ይቅርታን እንጂ፣ 'ነገን' ቃል አልገባልህም።""ዘመኑን ዋጁ ቀናቱ ክፉዎች ናቸውና፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።" —ኤፌሶን 5፥16-17✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Waaqayyo dhiifama malee, 'bor' siif waadaa hin galle.""Guyyoonni ammaa kun hamoolii waan ta'aniif yeroo fayyadamaa; kanaafuu fedhiin Waaqayyoo maal akka ta'e hubadhaa malee wallaaltota hin ta'inaa." — Efesoon 5:16-17✨✨✨ Guyyaa Gaarii ✨✨✨
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
19 Sept, 03:33
የዕለቱ ስንቅዓለም ስትጠራን፣ ማራኪ ገጽታዋን አሳይታ ስታስነሳን እኛም አብረን እንሮጣለን። ነገር ግን ቀኑ ሲመሽ፣ የደስታዋ ፍጻሜ የባዶነት ስሜት ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን። የሚያልፈውንና ጠወልጎ የሚቀረውን የዚህን ዓለም ከንቱ ክብር ብንከተል የምንሰበስበው ትርፍ ድካም እንጂ ሌላ አይደለም።ወዳጄ፣ የሰው ልጅ ልብ በፈጣሪው ምስል የተፈጠረ ስለሆነ ማረፊያው ከፈጣሪው ውጪ ሌላ ሊኖር አይችልም። ጊዜያዊ መዝናኛዎች ለአፍታ ሊያሳስቱን ይችላሉ፤ ነገር ግን እውነተኛውና የማይናወጠው ሰላም የሚገኘው የማይለወጠውን አምላካችንን አጥብቆ በመያዝ ብቻ ነው። ዛሬ ልብህን ከዚህ ዓለም አላፊ ሩጫ መልስ፤ ደስታህም በእግዚአብሔር ብቻ ይሁን!" ልብህ በእግዚአብሔር ደስ ይበለው፤ የሚያልፈውን ዓለም ተከትለህ አትጥፋ፤ የማይለወጠውን ፈጣሪህን አጥብቀህ ያዝ። " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa GuyyaaAdunyaan yommuu nu waamtu, bifa ishee isa miidhagaa agarsiiste nu kakaastutti nuyis ishee waliin fiigna. Garuu galgalli yoo ga'u, xumurri gammachuu ishee duumessa qullaa (muraa fi waa maleeyyii) ta'ee arganna. Kabaja faayidaa hin qabne kan adunyaa kanaa isa darbuu fi baqqa'u yoo hordofne, bu'aan nuyi walitti qabannu dadhabbiidhaan ala waa biraa miti.Hiriyaa
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
18 Sept, 03:30
የዕለቱ ስንቅ" ዓመቱ ሲለወጥ ቁጥር ብቻ ሳይሆን የሚለወጠው፤ ሕሊናችን ከክፉ ሥራ ታጥቦ ለአዲስ መንፈሳዊ ሕይወት መዘጋጀት አለበት። "ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Barri yeroo jijjiiramu lakkoofsa qofa miti kan jijjiiramu; sammuu keenya hojii badaa irraa dhiqamee jireenya hafuuraa haaraaf qophaa'uu qaba."Qulqulluu Yohaannis Afaan Warqee✨✨✨ Guyyaa Gaarii ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬ ®የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
17 Sept, 03:31
የዕለቱ ስንቅብዕር ምንም ያህል ውድ ቢሆን ወረቀት ከሌለው አይጽፍም፤ ቀለምም በራሱ ምንም ቢደምቅ ጸሐፊ ከሌለው ትርጉም አይሰጥም።ወዳጄ ሆይ፤ እኛም ያለ ፈጣሪያችን ሕይወታችን ባዶና ትርጉም የለሽ ነው። ብዙ ጊዜ የተመሰቃቀለውን ሕይወታችንን በራሳችን አቅምና እውቀት ለማስተካከል ስንሞክር፣ ልክ መሪ እንደሳተ መኪና ይበልጥ እንጎዳለን እንጂ አንስተካከልም። የእኛ የሕይወት ንድፍ አውጪና የጥበብ ሥራው ስለሆንን፣ በትክክል ሊያስተካክለን የሚችለው ሠሪያችን እግዚአብሔር ብቻ ነው።ስለዚህ ዛሬ በከንቱ ሩጫና በጭንቀት የደከመውን ልብህን ወደ ፈጣሪህ መልሰው። እርሱ የጠፋውን ፈልጎ የሚያገኝ፣ የተሰበረውን የሚጠግን፣ የደከመውንም የሚያጸና ርኅሩኅ አምላክ ነውና።"መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።" (መዝ. 37÷5)የሕይወቱን መሪ ለፈጣሪው ያስረከበ ሰው ምንኛ የታደለ ነው!✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa GuyyaaQalamni meeqas qaalii yoo ta'e, waraqaa malee hin barreessu, qalamni kophaa isaatti meeqas yoo miidhage, barreessaan yoo hin jiraanne hiika hin qabu.
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
16 Sept, 03:30
የዕለቱ ስንቅ" ክፉ ልማድን መተው ለአዲስ ዓመት የሚደረግ ከሁሉ በላይ ውብ የሆነ ስጦታ ነው። "ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅአዲስ ዓመት ሲባል አዲስ ልብስ፣ አዲስ የቤት ዕቃ ወይም ውጫዊ ለውጥ ብቻ አይደለም የሚጠበቅብን። እውነተኛው መታደስ የሚጀምረው ከውስጣችን በዓመታት ለምደን ባፈራናቸው ክፉ ልማዶችና ኃጢአቶች ላይ ድል በመንሳት ነው።ባለፈው ዓመት በእኛነታችን ተጣብቆ የነበረውን የቁጣ፣ የሐሜት፣ የጥላቻ ወይም የቸልተኝነት መጥፎ ልማድ ዛሬ በአዲስ መንፈስ እንተወው። ፈጣሪያችን ከእኛ የሚጠበቀው ውድ ስጦታ የንስሐና የተሰበረ ልብ ንጽሕና ነውና።ወዳጄ፣ አዲሱን ዓመት ስንጀምር ካለፈው ርኩሰት ራሳችንን አጽድተን፣ በፍቅር፣ በትዕግሥትና በንጹሕ ሕሊና እንሻገር!✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Amala badaa dhiisuun Bara Haaraaf kennaa hundumaa caalaa bareeda ta'eedha."
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
15 Sept, 03:31
የዕለቱ ስንቅለአዲስ ሕይወት የሚሆን አዲስ ዘመንበእግዚአብሔር ዘንድ ካለ ከበዛው ከምሕረቱ የተነሣ ያለፈውን ዘመን አሳልፎ አዲስ ጅማሮን ሰጥቶናል። አዲሱን ዘመን በአዲስ ተስፋና ምኞት ብቻ ሳይሆን በአዲስ ልቡና [በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ በሚሆን] እንቀበለው። ከኀጢአት እንሽሽ፥ ወደ ክርስቶስም እንቅረብ፥ በፊቱም በብርሃን እንመላለስ።አዲሱ ዘመን የእግዚአብሔርን መልካምነት የምናይበት፣ በእርሱም ታምነን የምንመላለስበት ይሁንልን። በዘመኑም መጨረሻ "እነሆ በእግዚአብሔር ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ ለዚህ ደረስን" የምንልበት ይሁንልን። አሜን። "በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።" — መዝሙር 65:11✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa GuyyaaJireenya Haaraaf Bara HaaraaWaaqayyo bira kan jiru araara isa baay'ee irraa kan ka'e, bara darbe dabarsee eegumsa haaraa nuuf kenneera. Bara haaraa kana abdii fi hawwii haaraa qofaan osoo hin taane, garaa haaraadhaan (Hafuura Qulqulluudhaan haaromuu ta'uun) haa fudhannu. Cubbuu irraa haa baqannu, gara Kiristoositti haa dhihaannu, fuula isaa durattis ifaan haa deddeebinu.Bari haaraa kun bara gaarummaa Waaqayyoo itti arginu, Isattis amanamnee
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
14 Sept, 03:33
የዕለቱ ስንቅ“እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ። አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ” መኃልይ 2፥11 በተከፈተው የዘመን ዐውድማ ላይ ቆሞ፣ አምላካችን በእናትነት ርኅራኄና በአባትነት ጥበቃው በፍቅር ወደ እቅፉ ይጠራናል :-“ወዳጆቼና ልጆቼ ሆይ! አያችሁት አይደል... ያ የጭንቀት ክረምት፣ ያ ያስለቀሳችሁ የመከራ ዝናብ፣ ያ ጉልበታችሁን ያብረከረከው የበሽታና የኀዘን ጎርፍ አልፎ ሄደ።" እነሆ አዲስ ዘመንን፣ አዲስ ዕድልን አድርጌላችኋለሁና፤ ኑ ከእኔ ጋር ተሰብሰቡ፤ በኃጢአት የበተናችሁን አሮጌ ሕይወት ትታችሁ ወደ እኔ እቅፍ ኑ።ኑ ከእኔ ጋር በፍቅር ኑሩ፤ እኔ ግን አዲስ ሕይወትና አዲስ ተስፋ ልሰጣችሁ፣ ትናንትን በአሳለፍኩበት ፍቅሬ ዛሬም ላስደስታችሁ እሻለሁና ኑ!ኑ ወዳጆቼ ለእናንተ አዲስ ሕይወትና አዲስ ተስፋ ልሰጣችሁ ትናንትን እንዳሳለፍኳችሁ ለዚህም እንዳደረስኳችሁ እንደገና ልባርካችሁና ላስደስታችሁLive stream finished (57 minutes)
13 Sept, 18:55
Live stream scheduled for Sep 13 at 18:00
13 Sept, 18:00
Live stream started
13 Sept, 17:58

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
13 Sept, 13:19
" የምሕረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለህ ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ። " መዝሙረ ዳዊት 64÷11🌼 እንኳን ለአዲሱ ዘመን ዘመነ ሉቃስ አደረሳቹ!🌼🌼የአዲስ ዓመት መርሐግብር🗓 ዛሬ ⏱ ማታ 3:00 ላይ 📌 በዚው channel ( https://t.me/gibigubaye ) ባላችሁበት ቦታ ሆናቹ መርሐግብሩን እንድትሳተፉ ጋበዝናችሁ።🌼🌼 መልካም በዓል! 🌼🌼

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
13 Sept, 08:17

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
13 Sept, 05:30
የዕለቱ ስንቅ«እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።» ኢዮ 2፥23 ይህ አምላካዊ ቃል እግዚአብሔር በደረቀው ሕይወታችን ላይ በረከቱንና ምሕረቱን አዝንቦ ፍጹም እንደሚያረካን የሚናገር የታመነ የተስፋ ቃል ነው።አምላካችን የፈተናውንና የሕመሙን ዘመን አሳልፎ በጸጋውና በፍቅሩ ሊጎበኘን ደጃችን ላይ ቆሟል.......ስለዚህ አሮጌውን የፍርሃት ልብስ ጥለን ልባችንን በደስታና በእልልታ ለእግዚአብሔር በማቅናት አዲሱን ዘመን ከሕያው አምላካችን ጋር በምስጋና እና በቅዱስ ቁርባን አንድ በመሆን እንጀምር።መልካም የተቀደሰና የተባረከ አዲስ ዓመት ይሁንልን 🌻💛✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬Galaa Guyyaa"Isin ijoollee Tsiyoon, Waaqayyo Waaqni keessan rooba isa jalqabaa qajeelummaan isiniif kennee jiraatii, akkuma isa duraas rooba jalqabaafi rooba boodaa isiniif roobseeraatii Isatti gammadaa, Isaafllee ilillee jedhaa!" Eeyob 2:23 Dubbiin Waaqayyoo kun, Waaqni jireenya keenya gogaa irratti eebbaafi araara isaa roobsee guutummaatti akka nu quubsusu kan dubbatu dubbii abdii amanamaadhaa.
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
12 Sept, 13:05
" የምሕረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለህ ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ። " መዝሙረ ዳዊት 64÷11🌼 እንኳን ለአዲሱ ዘመን ዘመነ ሉቃስ አደረሳቹ!🌼🌼የአዲስ ዓመት መርሐግብር🗓 እሁድ መስረከም 3 ⏱ ማታ 3:00 ላይ 📌 በዚው channel ( https://t.me/gibigubaye ) ባላችሁበት ቦታ ሆናቹ መርሐግብሩን እንድትሳተፉ ጋበዝናችሁ።🌼🌼 መልካም በዓል! 🌼🌼


የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
12 Sept, 07:39
🗓 Yohaannis Cuuphaa QulqulluuSinksaara Ji'a Maskaramaa Waaqayyo tokko kan ta'e Abbaa, Ilmaa fi Afuura Qulqulluu maqaan isaanii haa eebbifamu. Maskarama lama (2) gaafa kana ijoollee lubichaa Zakaariyaas kan ta'e Yohaannis Cuuphaan kabajamaan seera kan diige Mooticha Herodis harkaatti wareegama ta'e. Kunis kan ta'e, haadha manaa Filphos kan taate Heroodiyaadaaf jecha Raajichi Yohaannis yeroo isa goyyootti (ceeraatti) ture; Filphos obboleessa isaatiin "Haadha manaa obboleessa keessaa fudhachuun siif maaliif eeyyamama?" isaaniin jedha tureef. Qulqulluu Yohaannis Herodis haadha manaa obboleessa isaanii Heroodiyaada fudhachuusaa fi waan hamaa inni raawwatu hundaaf isa ceepha'a ture. Akkasumas ceephoo irratti ceephoo itti dabale. Kanaafis Yohaannis irratti haaloo qabatee gara mana hidhaatti isa galche. Herodis Yohaannis widee (sodaa) ture; nama qajeelaa fi qulqulluu ta'uusaa waan beekuuf
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
12 Sept, 07:32
🗓 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስስንክሳር ዘወርኀ መስከረም አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሁለት በዚች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ። ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና ። ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር ። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው ። ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር ።ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ ።የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት። ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው ። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
