Latest posts

Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
22 Sept, 09:49
የምንወደው እና የምንናፍቀው እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ተመልሷል።እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫመስከረም 30 እንገናኝ!#GreatEthiopianRun #EntotoCBERun


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
11 Sept, 07:43edited
🌼እንኳን ለ2019ዓ.ም. አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቸሁ 🌼ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ዓመቱ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ይመኛል።#GreatEthiopianRun #NewYear


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
25 Aug, 06:00
እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ.) መውሊድ በሰላም አደረሳችሁ።ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ይመኛል።#GreatEthiopianRun #Mewlid


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
17 Aug, 10:17
የአትሌቶች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል! 🏆ለ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ውድድር የአትሌቶች ምዝገባ ላምበረት በሚገኘው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ እየተካሄደ ይገኛል።🪪 ለምዝገባ ሲመጡ፦ መታወቂያ ፣ ፋይዳ ወይም ፓስፖርት ይዘው መምጣትዎን አይዘንጉ።#GreatEthiopianRun #Registration #Athletes


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
13 Aug, 05:50
🔥እየደረሰ ነው⏳ 100 ቀናት ብቻ ቀርተዋል! 🔥በ100 ቀናት ውስጥ የአፍሪካ ትልቁ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ይከሔዳል 🇪🇹እርስዎም ሌላ የማይረሳ የሩጫ ቀን ለማሳለፍ ይዘጋጁ! 🏃🏾♀️🏃🏾♂️2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ 💫#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #100DaysToGo #Ethiopia


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
7 Aug, 15:15





Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
7 Aug, 15:14edited
የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. የመደበኛ ምዝገባ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ60,000 ሯጮችን የሚያስተናግደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት በግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚደረገው የምዝገባ ጊዜ እያጠረ መጥቷል።በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ካለው ከፍተኛ ምላሽ የተነሳ በባንክ ኦፍ አሜሪካ የስያሜ አጋርነት የሚቀርበው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. መደበኛ ምዝገባ ተጠናቋል።ከማክሰኞ እስከ ማክሰኞ የዘለቀው የሰባት ቀናት የምዝገባ ጊዜ ውድድሩ ከተጀመረበት 1994ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት የ26 ዓመታት ታሪክ ውስጥ አጭሩ የምዝገባ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።የዘንድሮው ምዝገባ ይበልጥ የቀለለው ግለሰቦች በቴሌብር (telebirr) መተግበሪያ በኩል በመጠቀም እና ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነ የምዝገባ ሂደት ነው። ነፃ የውድድር ምዝገባ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች ገቢ ማሰባሰብ እና የሰዓት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር በተደረገው አጋርነት የመጡ አዳዲስ ስኬቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል።ለዘንድሮው ውድድር ከተዘጋጁት ጠቅላላ 60,000 ቦታዎች ውስጥ 3000 የሚሆኑት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለሚወስዱ ተማሪዎች በነፃ የሚሰጡ ሲሆን፣ ይህም አጋርነቱ ሰፊ የኅብረተሰብ ክፍል በውድድሩ ላይ እንዲሳተፍ ለማድረግ ያለውን ዓላማ የሚያሳይ ነው።በተጨማሪም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመረጡ ሦስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ለማሰባሰብ የታለመውን ‘ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ’ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በጥቅምት ወር
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
3 Aug, 17:17
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል።ምዝገባው በቴሌብር በኩል ብቻ እየተከናወነ ሲሆን ያሉን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ሳይሞሉ በፊት ይመዝገቡ።✨ሩጫዬ ቀለሜ ✨✨ 2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor #Telebirr


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
2 Aug, 05:24edited
ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ - በቴሌብር ይመዝገቡ!ከ60ሺህ ተሳታፊዎች መሐከል አንዱ ይሁኑ!የምዝገባ ዋጋ - ከመስቀል አደባባይ ለሚጀምረው ቀይ መነሻ 790 ብር - ከግዮን ሆቴል ፊት ለፊት ለሚጀምረው እና የመሮጫ ቁጥር ለሚኖረው አረንጓዴ መነሻ 950 ብርየ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበ ✨ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ✨#GreatEthiopianRun #MyRunMyColor


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
19 Jul, 07:25edited
አትሌት ሴና ገመቹ እና ራሔል እምቢበል የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር አሸናፊዎች ሆኑመነሻ እና መድረሻውን ሐረር በር ላይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶችእና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10ኪ.ሜ. ውድድር የተደረገ ሲሆን በወንዶች አትሌት ሴና ገመቹ በ32:04:77 በመግባት የአንደኛነት ደረጃን ሲይዝ ምህረት አወቀ ሁለተኛ እና ኢብራሒም መሐመድ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።በሴት አትሌቶች ውድድር ራሔል እምቢበል በ41:43:23 በመግባት ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ አምራን ሸምሱ ሁለተኛ እና አዚዛ ሙክታር ሶስተኛ ደረጃ ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ ርቀት ውድድራቸውን ያደረጉት የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተጓዥ ተሳታፊዎች መሐከል በተካሔደው ውድድር በወንዶች ዮሐንስ አየልኝ እንዲሁም በሴቶች ርብቃ ግርማ አሸናፊዎች ሆነዋል።ዛሬ በድምቀት በተከናወነው ውድድር ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሀመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በክብር እንግድነት ታድመዋል።ከ16 አመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ.ውድድር እና ከ11 አመት በታች ልጆች የተሳተፉበት የ1 ኪ.ሜ.ውድድር ሌላው የዕለቱ ድምቀት ነበር፡፡ሐረር የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ስድስተኛ እና የመጨረሻዋ መዳረሻ ከተማ ስትሆን ዛሬ ከተካሔደው የሩጫ ውድድር ባሻገር ትናንት የጀጎል ግቢ የተጎበኘበት የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
19 Jul, 07:25





Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
18 Jul, 08:51edited
ጋዜጣዊ መግለጫየ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ነገ በሐረር ፍፃሜውን ያገኛል፡፡የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር የመጨረሻ መዳረሻ የሆነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐረር ከተማ የሚደረገው የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በሐረር ነገ ጠዋት ይካሔዳል።ዛሬ ረፋድ በሐረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተነገረው ውድድሩ ነገ ማለዳ ከ1:00 ሰዓት ጀምሮ መነሻ እና መድረሻውን በዱቅ በር / ሐረር በር ፊት በማድረግ ይከናወናል።ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሐረር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያዘጋጀው ውድድር ከመደበኛው የሩጫ ውድድር ባሻገር ዛሬ ማምሻውን የእግር ጉዞ እና የጀጎል ግንብን ውስጥ የመጎብኘት እንዲሁም በአጠቃላይ የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ጉዞ ላይ አብረውት ለነበሩ ተሳታፊዎች እና አጋሮች ዕውቅና የሚሰጥባቸው መርኃ-ግብሮችንም ያካተተ መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡በመግለጫው የሐረር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሚ አብዱልዋሲ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው “ይህ ታላቅ ስፖርታዊ ክንውን ሀገራችንን እና ውብቷን ሐረርን በስፖርት ቱሪዝም (Sports Tourism) ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ አለው። በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የመጣችሁ ሁሉ ፤ በሐረር ቆይታችሁ የማይረሳ ውብ ጊዜን እንደምታሳልፉ ሙሉ እምነት አለኝ” የሐረርን ዝግጁነት አመላክተዋል።በነገው የሩጫ ውድድር ፕሮፌሽናል አትሌቶችን ጨምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር የመጡ 110 ተሳታፊዎች በ10ኪ.ሜ. ርቀት ይወዳደራሉ፡፡በተጨማሪም 2500 የሐረር እና አካባቢው ነዋሪዎች በ5ኪ.ሜ.
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
18 Jul, 08:51





Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
1 Jul, 08:39
ጋዜጣዊ መግለጫየአዲስ አበባ ሯጮች በአፍሪካ እምብርት ላይ በሚካሄድ ማራቶን ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ቀረበበኢትዮዽያ ሩጫ ከስፖርት በላይ ነው ፤ ሩጫ የሀገር ኩራት፣ የጋራ በዓል፣ የጤና ፣ የህብረተሰብ ትስስር እና የነፍስ ደስታ ነው።በአፍሪካ ዕምብርቷ ኡጋንዳም ተመሳሳይነት ያለውን ስሜት ለመጋራት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ከተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን ጋር በመተባበር ለሩጫ ወዳጆች ጥሪን አቅርቧል።ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን የሩጫ ውድድር ወደ ታላቅ በዓል የመቀየር ተመሳሳይ ባህል አላቸው። ከአዲስ አበባ ለሚሄዱ ሯጮች በካሴሴ የሚስተዋለው የባህል ድባብ፣ ሙዚቃ እና የህዝብ አቀባበል እንደ ቤት እንዲሰማ የሚያደርግ የቅርብነት ስሜት አለው።በሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ በእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ እና ሌሎችም የሩጫ አፍቃሪያን፣ ያንኑ የሩጫ መንፈስ በመያዝ ከሀገር ውጪ በመጓዝ ውድድሩን እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን።ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በኡጋንዳ፣ ካሴሴ ከተማ የሚካሄደው ተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን፣ ከአዲስ አበባ የባህር ዛፍ ጠረን ካለው ቀዝቃዛ አየር ወደ ሳቫናው ግርማ ሞገስ እና ወደ ሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ የሚያደርጉት ልዩ የሩጫ ጉዞ ነው። በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ ሲጠነከር፣ በዩጋንዳ ካሴሴ ደግሞ ሞቅ ያለ ፀሐይና የኢኩዌተር መስመር ላይ የሚደረግ ውድድር ይጠብቅዎታል።የተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሌብል (World Athletics Label RoadRwenzorimarathonRegister for the marathonRun the Tusker Lite Rwenzori Marathon in Kasese, Uganda. Register now!
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
1 Jul, 08:39



2,900Open in Telegram
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
29 Jun, 04:56edited
📌 ምዝገባ ተጀምሯል!በቀላሉ በሲቢኢ ብር ፕላስ በነፃ አሁኑኑ ይመዝገቡ 📲🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን ሰኔ 27 ይካሔዳልእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨ቅዳሜ - ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. እንገናኝ!#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun #EntotoCBERun


Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
28 Jun, 09:23edited
አትሌት እስራኤል አባተ ለተከታታይ ዓመት የሳፉሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባ ምንጭ አሸናፊ ሆነ2018 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባ ምንጭ በአርንጓዴዋ አርባ ምንጭ ስፖርት፣ ቱሪዝምን እና አካባቢ ጥበቃን በአንድ ላይ በማጣመር በድምቀት ተከናውኗል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር እንደገና አበበ፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ መስፍን መንዛ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።ውድድሩ መነሻውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲቀላ አደባባይ በማድረግ ፕሮፌሽናል አትሌቶች እና ከአዲስ አባባ ተጓዥ ተሳታፊዎችን ያካተተ ልዩ የ10 ኪ.ሜ ውድድር የተደረገ ሲሆን የ2017 ውድድር አሸናፊ የነበረው አትሌት እስራኤል አባተ የአንደኛ ደረጃነቱን ሲይዝ ሙሉቀን ታደለ ሁለተኛ እና ሙሉነህ ፍቃዱ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።በሴት አትሌቶች ውድድር ምንትዋብ ወልዴ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ጠንካራ ፉክክር በተደረገበት የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ፉክክር ሜሮን አበበ እና ሰላም አበበ ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ ርቀት ውድድራቸውን ያደረጉት የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተጓዥ ተሳታፊዎች መሐከል በተካሔደው ውድድር በወንዶች የቦቆጂ አሸናፊው ዮሐንስ አየልኝ ሲያሸንፍ አማን ኃ/ማርያም እና አብዮት ሞገስ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው ጨርሰዋል። በሴቶች ውድድር ሩት ሙሉጌታ ቀዳሚ ስትሆን የግሌ እሸቱ እና ኬቲ ዱትኮ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።ከ16 አመት በታች ታዳጊ አትሌቶች የተሳተፉበት የ1.5 ኪ.ሜ. ውድድር እና ከ112,820Open in Telegram
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
28 Jun, 09:23



2,300Open in Telegram
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
23 Jun, 13:37edited
የሶስተኛው አመት የሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባ ምንጭ የአካባቢ ጥበቃ መልዕክትን በመያዝ የፊታችን እሁድ ይካሔዳልበጉጉት የሚጠበቀው የ2018 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባ ምንጭ ለሶስተኛ ተከታታይ አመት በመጪው እሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ከተማ ይካሄዳል። እስካሁን 4 ከተማዎች ላይ ውድድር የተደረገበት የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ (Discover Ethiopia Classics) የስድስት ከተሞች ውድድር አካል የሆነው ይህ የአርባ ምንጭ ውድድር ፤ ዘንድሮም ከስፖርታዊ ይዘቱ ባለፈ የአካባቢ ጥበቃ መልዕክት ላይ ትኩረቱን አድርጓል።ዘንድሮ ውድድሩ ከፍተኛ ሀገራዊ እና ክልላዊ ትኩረትን የሳበ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የሚጓዙ የተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 120 የሚጠጋ ሲሆን፣ ከአርባ ምንጭና አካባቢዋ ደግሞ ቁጥራቸው 2,500 አዋቂዎች እና 500 ህፃናት እና ታዳጊዎች በዚህ ደማቅ የሩጫ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።የ2018 ሳፋሪኮም ታላቁ ሩጫ በአርባ ምንጭ ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር (GIZ) ጋር በመተባበር “ጤናማ መልክዓ ምድር፣ ለጤናማ ህይወት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ አላማውም የመሬት መራቆት የሚያስከትለውን ጉዳት በማስገንዘብ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ ማህበረሰብ ለመገንባት መሟገት ነው። ይህ መሪ ቃል የመሬት ጤንነት ከህዝብ ጤና እና ደህንነት ጋር በቅርብ የተቆራኘ መሆኑን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ነው።በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ የተፈጥሮ አካባቢያችንን መንከባከብ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን የሚያስታውስ የቅርብ
Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
23 Jun, 13:37



3,000Open in Telegram
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
