Latest posts

Hilina Belete
6 Aug, 21:17
ምን ባደርግ እክስ ይሆን? ኆኅተ ብርሃንን እንዴት ብወዳት ብድር እመልስ ይሆን? ቤተ ክርስቲያናችንን እንዴት ባገለግላት ያሸከማችሁኝን ዕዳ አቀል ይሆን? እግዚኦ... ምንድን ነው ያደረጋችሁት? ግርግርን ስሸሽ እንደ ኖርሁ የሚያውቀኝ ሁሉ ይመሰክራል፤ ከዚህ ቀደም ሚዜ ያደረጋችሁኝ ኹሉ ሚዜነቱ ሰማዕትነት እንደ ሆነብኝ ታውቁታላችሁ። ሚዜ ሆኜአችሁ እንኳን ከሁነቱ ጋር ባለ መጣጣሜ "በማያውቀው ሰው ሰርግ የተገኘ ይመስላል" እያላችሁኝም አልነበር!? ... እኔና አጋሬ ዕቅዳችን ባሕር ዳርን አልፎ በሚገኝ አንድ የደቡብ ጎንደር ክፍል ውስጥ፣ ዘወትር በሕይወታችን ወስጥ ያሉ አባታችን በሚኖሩበት ቦታ ሥርዓተ ተክሊላችንን ፈጽመን ወደ ሱባኤ መግባት ነበር። በተለያየ ምክንያት አልሆነም። እዚያ ካልሆነ በኆኅተ ብርሃን መፈጸሙ ግድ ነበር። እናም ሰርግ ሳይኖር፣ ጥሪ ሳይኖር፣ ሚዜ ሳይኖር፣ አጀብ ሳይኖር፣... ሥርዓታችንን ፈጽመን እንመለሳለን ብለን ከቀናት በፊት ወሰንን። ከሳምንት በፊት ሙሽሪት አመለጣትና (ሆን ብላ ብዬ አዲሱን ትዳር ከምበጠብጥ ብዬ መሆኑ ይመዝገብልኝ😂) ...ብቻ "አመለጣትና" ለኆኅተ ብርሃን ወንድሞቼ ቀኑን ነገረቻቸው። ከዚያ በኋላ መጠነኛ መረጃ እንጂ የዛሬው ዝግጅት መኖሩን አልገመትሁም ነበር። የእኔ አሳብ ሰውን ሳናስቸግር የሌሊት ሥርዓቱን ፈጽመን፣ ቁርሳችንን ፍትፍት በልተን መለያየትና ለወዳጅ ዘመድ ማሳወቅ ነበር። ሚዜ ሆነው ከጎኔ የቆሙትን ወንድሞች እንኳን ሚዜነታቸውን ያወቅሁት ትናንት ማታ ለተክሊሉ ሥርዐት ስንዘጋጅ ነበር። ለካስ ከሙሽሪት ጋር ተናበው በሳምንት ውስጥ ራሳቸውን ሚዜዎቼ2,160Open in Telegram
Hilina Belete
6 Aug, 21:17

1,800Open in Telegram
Hilina Belete
22 Jul, 13:26

3,820Open in Telegram
Hilina Belete
22 Jul, 13:26

3,290Open in Telegram
Hilina Belete
10 Jul, 19:58

3,530Open in Telegram
Hilina Belete
4 Jul, 09:45
ታቦትን በተመለከተ ከቤተ ያሬድ ሚዲያ ጋር ይህን ቆይታ አድርገናል። ተጋበዙልኝ!https://youtu.be/OBIgPGnEgCsYouTubeይህ የዩቲዩብ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት እና ክርስቲያናዊ ትውፊት የጠበቁ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ነው። የቤተያሬድ የዩቲዩብ ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ Facebook https://www.facebook.com/share/1Bx57PEqcf/ Tiktok tiktok.com/@beteyaredmedia Telegram https://t.me/+M5WlMxUV5jE1YmU5…4,040Open in Telegram
Hilina Belete
20 Oct 2025, 19:01edited
ባለ ቅኔው እንዲህ አለ:-ጉይ አብ መንገለ ራማ ወኢታጎንዲ ህዳጠ፣ እስመ ከማሁ ለወልድ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ተሴጠ።ስተረጉመው:-ልክ ወልድ እንደ ተሸጠው - ተቸረቸረ ተሸጠ - የመንፈስ ቅዱስ ጸጋም። አብ ሆይ! ወደ ራማ ሽሽ - ጥቂትም ቢሆን አትዘግይ - ይሸጡሃል አንተንም።መቼስ ቅኔ ድንበር የለበት፤ የማይገልጸው የለ! ብሎ ብሎ ሽሽ አለው።Sometimes retreat is better than surrender ይላሉ መሰል ነጮቹም።8,560Open in Telegram
Hilina Belete
13 Oct 2025, 21:19
ፍቁረ እግዚእ- (ከድንግል ጋር) ከሁሉ ይልቅ ከጌታ ጋር በፍቅር እስከ መጨረሻ የጸና እርሱ ነው። - ከሁሉ ይልቅ ከእመቤታችን ጋር በፍቅር እስከ መጨረሻ የጸና እርሱ ነው። - ከሁሉ መጻሕፍት ይልቅ ክቡር የሆነው የእርሱ ወንጌል ነው። - ብርሃን፣ ፍቅር፣ እውነት፣ ሕይወት እና ሃይማኖት ከየትኛውም ወንጌል ይልቅ በእርሱ ወንጌል ተደጋግመው ተጠቅሰዋል። - ከሐዋርያት ሁሉ በዕድሜ ትንሹ እንደ ነበር ይታመናል። በብስለቱ ግን "አባ አረጋዊ" ነው። - በሰማዕትነት ከከበሩት ከወንድሞቹ ከሐዋርያት ይልቅ የምድር ሕይወቱ ፍጻሜ የተለየ ነው። - የነጎድጓድ ልጅ ሆኖ እያተኮሰ መጥቶ ፍቁረ እግዚእ እስኪሆን ቀዝቅዞ የፍቅር ሐዋርያ ተብሏል። - የአገልግሎቱም የጽሑፎቹም ዋነኛ ጭብጥ ፍቅር ነው። - በዕድሜ ሸምግሎ መራመድ እንኳን ተስኖት ሳለ የራሱ ደቀ መዛሙርት ተሸክመውት ይሰብክ ዘንድ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበበት ይወስዱት ነበር። የመጨረሻ ዘመን ስብከቱ ግን ዘወትር አንድ ዓይነት ነበር - ፍቅር።"ልጆች ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ!"- 'ለምን ሁሌ ይህን ትሰብካለህ?' ሲሉትም መልሱ ዘወትር ተመሳሳይ ነበር:- "ምክንያቱም የጌታ ትእዛዝ ነውና፤ ይህ ብቻውን ቢደረግ እንኳን በቂ ነው" ይል ነበር።ፍቁረ እግዚእ! በረከቱ ይደርብን!ዲያቆን ሕሊና በለጠ
8,180Open in Telegram
Hilina Belete
5 Oct 2025, 05:05
የበአታ ሰንበት ተማሪዎች የዕለቱን (የመስከረም 25ን) መዝሙር "ትብሎ መርዓት"ን እንዴት እንዳዜሙት መጨረሻ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትላችሁ ስሙልኝማ!ያሬዳዊስ ማለት እንዲህ ነው!!!ትብሎ መርዓት ለመርዓዊሃ ወልድ እኁየ ነዓ ኀቤየ ወሪደ ኢታጎንዲ ዬ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ ምስለ ጴጥሮስ አዋዲ ወጳውሎስ ሰዳዲ /ዬ/ ማርያም መስቀሎ ለበዓል ኀበ ትወዲ /ዬ/ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ /ዬ/ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ። ... ሙሽሪት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ሙሽራዋን ውዴ ሆይ ከሰባኪው ከጴጥሮስ ከአሳዳጁ ጳውሎስ ጋር ማርያም መስቀሉን ከኪሩቤል ጋር አመሳስላ /አንድ አድርጋ/ በምታከብርበት /ቀራንዮ/ ወደ እኔ ና አትዘግይ ትለዋለች። የጋዲ እንጨት መስቀል እሰይ አበበ።(መስከረም 25 - የዘመነ መስቀል የመጨረሻዋ ቀን ስትሆን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሰቡባታል)https://youtu.be/Xk9xLF-8rP8?si=8yQ8ICaA2sSTEYBt
5,480Open in Telegram
Hilina Belete
3 Oct 2025, 12:56edited
የዛሬ ስደስት ዓመት ስለ ኢሬቻ የተጻፈ!https://www.facebook.com/share/p/1AzFC3Jceg/FacebookLog in or sign up to viewSee posts, photos and more on Facebook.3,720Open in Telegram
Hilina Belete
25 Sept 2025, 08:02edited
የጌታ ደም መፍሰስ ትርጉሙ ድኀነት ነው፡፡ ስለዚህ ደሙ በማንኛውም ጊዜ፣ ቦታና ቁስ ላይ የሚፈስ አልነበረም፡፡ ደሙ የሚፈስበት ጊዜ፣ ቦታና የሚፈስበት ቁስ ልዩና በመለኮታዊ ጥበብ የተመረጡ ናቸው፡፡ ብቻ ደሙ ዝም ብሎ የሚፈስ አልነበረም፤ አይደለምም፡፡ በተወለደ በ8ኛው ቀን ይገዘር ዘንድ ግዝረት ወደሚፈጸምበት ቤት ወሰዱት፤ ደሙ የሚፈስበት ጊዜም ሆነ ቦታ ገና ነበርና ቁሱም የስለት መሣሪያ አልነበረምና ያሃ ሳያርፍበት እንዲሁ በመንፈስ ቅዱስ ተገዝሮ ተገኘ፡፡ አይሁድ በተደጋጋሚ ሊወግሩት ቢነሡ፡ ለኃጢአት ይቅርታ ደሙ ይፈስበት ዘንድ የተመረጠው ነገር ድንጋይ አልነበረምና ይሠወርባቸው ነበር፡፡ የደሙ ምሳሌ፣ ኋላም በምሥጢረ ቁርባን ደሙ ይሆን ዘንድ የተመረጠው ወይን ነው፡፡ እመቤታቸን ውኃውን ወደ ወይን ይለውጥ ዘንድ ስትማጸነው "ጊዜዬ አልደረሰም" ያላት በመስቀሉ ላይ ደሙ የሚፈስበት ጊዜ ገና እንደ ሆነ ሲገልጽ ነው፡፡ ደሙ በጋን ውስጥ ሳይሆን በመስቀል ላይ፣ በቃና ዘገሊላ ሳይሆን በቀራንዮ የሚፈስ ስለ ነበር ነው፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ለአማናዊው ሙሽራ፡ ሰርጉ ለሚባል ለስቅለቱ የቃናው ሰርግ፣ ከእመቤታችን ከነሣው ሥጋው በመስቀሉ ላይ ለሚፈስ ደሙም፡ በእመቤታችን ምልጃ ከውኃነት የተለወጠው ወይኑ ምሳሌ ነው፡፡ እንግዲህ ደሙ የትም ቦታ ላይ በምንም ዓይነት መንገድ ከመፍሰስ ተጠብቆ ቆይቶ የፈሰሰው በመስቀሉ ላይ ነው፡፡ ታዲያ ደሙ አዳነኝ ብሎ የሚያምን ሰው ደሙ የፈሰሰበትን መስቀሉን እንዴት ሊቃወም ይቻለዋል? ጌታ 33 ዓመት ከ3 ወር በምድር ላይ ሲኖር ደሙን ምንም ነገር ላይ ሳያፈስ ቆይቶ በመስቀሉ ላይYouTubeይህ የዩቲዩብ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት እና ክርስቲያናዊ ትውፊት የጠበቁ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ነው። የቤተያሬድ የዩቲዩብ ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ Facebook https://www.facebook.com/share/1Bx57PEqcf/ Tiktok @kesisyaredgebremedhin Telegram https://t.me/+M5WlMxUV5jE1YmU5…4,910Open in Telegram
Hilina Belete
11 Sept 2025, 10:16edited
ኹላችንም የተወለድንበት የየራሳችን የልደት ቀን አለን። የአዲስ ዓመት ዕለት ግን የጋራ የልደት ቀናችን ይመስላል። አዲስ ዓመት ብሔራዊ የልደት ቀን ነው። በአዲስ ዓመት ያሳለፍነውን መከራም ሆነ ስኬት ለአሮጌው ዘመን ትተንለት÷ በመከራው መቆዘሙን በስኬቱም መፈንጠዙን ገትተን÷ እንደ አዲስ እንደ ተወለደ ሰው በተስፋ መነሣት ይገባል። አዲሱን ዓመት በግልም ሆነ በጋራ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በኋላችን ያለውን እየረሳን በፊታችን ያለውን ለመያዝ የምንዘረጋበት" (ፊል.3÷13) የስኬትና የጽድቅ ዘመን ያድርግልን።መልካም አዲስ ዓመት!ደ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን!4,440Open in Telegram
Hilina Belete
27 Aug 2025, 12:09

5,150Open in Telegram
Hilina Belete
26 Aug 2025, 12:09
ዝም ብዬ አይሻለሁ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ)ያ'ይን ማረፊያዬ! ዝም ብዬ አይሻለሁ።ፊደል ነሽ ለቃሉ - ሰብእናሽ ትርጓሜ - ሃይማኖትሽ ፍቅር የተዋሕዶ ቅኔ - ትሕትናሽ ዜማ ነው - ውበትሽም ምሥጢር ቅኔ ዜማ ምሥጢር - እምነትና ምግባር - ፊደል ከትርጓሜ እንዲዋሐዱልኝ - ዝም ብዬ አይሻለሁ - ደግሜ ደግሜ።ድንግል የንታዬ ያይን ማረፍያዬከድምጻዊው በላይ - ትሕትናሽ ዜማ ነው - ጆሮን ይማርካል ከዘራፊው በላይ - ውበትሽ ቅኔ ነው - ወርቁ ይራቀቃል ከገጽሽ ላይ ምሥጢር - ከመልክሽ ትርጓሜ - ዝም ብሎ ይፈልቃል።ድንግል የኔታዬ5,510Open in Telegram
Hilina Belete
26 Aug 2025, 12:08

3,130Open in Telegram
Hilina Belete
21 Aug 2025, 17:32
ዐረገችከሰማዮች ይልቅ ውብ ሰማይ ነበረች፣ የጨለማውን ሊቅ ድቅድቅ የሰበረች፣ እውነተኛ ፀሐይ ከርሷ ቢፈነጥቅ ብርሃን ያበሰረች። እርሷ ያወጣችው አማናዊ ፀሐይ፣ እንዳገዘፈችው ኑሮ በምድር ላይ፣ ሞቶ ተነሣና ከፍ ብሎ ቢያርግ ቢሔድ ወደ ሰማይ፣ እርሷም ሞተችና ፀሐዩአን ልትፈልግ ተነሣች ወደ ላይ፣ ዐረገች ወደ ላይ ብርሃን ልጇን ልታይ። ©ዘሕሊና
4,810Open in Telegram
Hilina Belete
19 Aug 2025, 18:10
እዚህ ላይ አንድ የጽሑፍ ዑደት በመጠኑ ግቡን ሳይመታ አይቀርም። (ፎቶውን ይመልከቱ!)።- ኦርቶዶክሳዊነት ምንድን ነው የሚሉ ሁሉ ይህን መጽሐፍ ቢያዩ መልካም ነው። የቅዱስ ኤፍሬምን ሕይወትና ግጥማዊ ሥራዎችን መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በጥልቀት ተቃኝቶበታል።- ይህ መጽሐፍ የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን ዶግማዊና ነገረ ሰብአዊ መሠረትን ይዳስሳል። በጉዳዩ ላይ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ አስተምህሮ ያላቸውን የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያንን ምልከታ በጥልቀት ያሳያል።- ይህ መጽሐፍ የአከራካሪውን ሊቅ የአውግስጢኖስ ሕይወትና አስተምህሮን መሠረት በማድረግ የምዕራቡን ዓለም ክርስትና: በተለይም የካቶሊካውያንን የእምነት መነሻዎችን ያሳያል፤ ኦርቶዶክሳዊ አተያዮችንና ምላሾችንም በየትምህርቶቹ ያቀርባል።አውግስጢኖስ መጽሐፍ እንደ ገና መታተሙንና ገበያ ላይ መዋሉን ቅዳሜ ዕለት ባኮስ መጻሕፍት መደብር ካበሰረን በኋላ አሁን ሦስቱም በገበያ ላይ ይገኛሉ።መልካም ንባብ!!!ዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን
3,360Open in Telegram
Hilina Belete
19 Aug 2025, 06:09
Assumption - Dormition - ፍልሠታ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ)#Assumption የሚለው ቃል ወደ ላይ መነጠቅ፣ መወሰድ፣ መፍለስ ወይም ማረግ እንደ ማለት ሲሆን ይህን ቃል አጉልተው የሚጠቀሙት ካቶሊካውያን እመቤታችን በምድር ሕይወቷ ፍጻሜ ላይ ወደ ገነት እንደ ተወሰደች በግርድፉ ያስረዳሉ። (በግርድፉ ያልኩት በምክንያት ነው)።ዋናው ትኩረታቸው የእመቤታችን ወደ ሰማይ ማረጓና መክበሯ ላይ ነው። ሞቷ ላይ ግልጽ ሆኖ የሚነገር ነገር የለም። በዓሉንም "Assumption of the Blessed Virgin Mary" በማለት August 15 ያከብሩታል እንጂ ሞቷን አጉልተው አይናገሩም። በዓሉ ግን ደማቅ ነው። ካቶሊካውያን በበዙባቸው ሀገራትም ብሔራዊ በዓል ነው።አሁን ለሥራ ተልእኮ በምገኝባትና አብዛኛው ሕዝቧ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ በሆኑባት በካሜሩን ውስጥ ዓርብ August 15 ብሔራዊ በዓል ነበር - Assumption of Mary. ምዕራባውያኑ ይህን በዓል ከምሥራቁ ዓለም በመቀበል ማክበር የጀመሩት በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቢሆንም፣ በእመቤታችን ዕረፍት ላይ ግን ግልጽ አስተምህሮ የላቸውም። ከፊሉ መሞቷን ሲያምኑ ሌሎቹ ግን "አልሞተችም እንዲሁ ነው ያረገችው" ይላሉ።ፖፕ ፒየስም በኖቬምበር 1፣ 1950 (እ.ኤ.አ.) አስተምህሮውን Munificentissimus Deus በተባለው ዶግማውን ባብራሩበት ሥራ ላይ ሲያብራሩት "The immaculate mother of God, the ever virgin Mary, having completed the course of her earthly life, was4,330Open in Telegram
Hilina Belete
19 Aug 2025, 06:09


2,720Open in Telegram
Hilina Belete
16 Aug 2025, 17:21
የዲያቆን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን ሦስቱ መጻሕፍት በባኮስ መጻሕፍት መደብር አሳታሚነት ለገበያ ቀርበዋል።#የአውግስጢኖስ መጽሐፍ ከብያኔ ነፃ በኾነ መንገድ የአውግስጢኖስን ማንነትና የሥራዎቹን ይዘት በዚያውም የምዕራቡን ዓለም ክርስትና የሚያስቃኝ መጽሐፍ ሲኾን፥#ኦርቶዶክሳዊ_መንፈሳዊነት መጽሐፍ ደግሞ የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን ትምህርተ ክርስትና ምን እንደሚመስል ያስቃኛል።#ብርህት_ዓይን መጽሐፍ ግን በኦሬንታል ኦርቶዶክስ ክርስትና (ነገረ መለኮትን በግጥም የሚያቀርበው) በተለይም በሱርስት ትውፊት ያለውን የነገረ መለኮት አቀራረብ፣ አተያይና ጭብጥ በጥልቀት የሚመረምር የጥናት መጽሐፍ ነው።እነዚህን ሦስት ወሳኝ የነገረ መለኮት መጻሕፍት በማንበብ ትጠቀሙ ዘንድ እንጋብዛችኋለን።©ባኮስ መጻሕፍት መደብር
4,920Open in Telegram
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
