Latest posts

ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 18:21
"65% የሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ አማራ ያላነሳውን ጥያቄ፣ 11% የሚሆነው የከተማ ነዋሪ ኦሮሞ እንዴት ያነሳል”ኮሚሽነሩበአሶሳ ከተማ የኢሬቻ በዓል ማከበሪያ ቦታን በተመለከተ በፀጥታ አመራሮች መካከል ውጥረት መንገሱ ተሰምቷል፡፡በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ ከተማ፡ የኢሬቻ በዓል አከባበር ቦታን እና የከተማዋን ባለቤትነት ጉዳይ አስመልክቶ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ተገለጸ።በወጣው መረጃ መሠረት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እስከዛሬ በዓሉን ያከብሩበት የነበረውን "ቤጊ ሰፈር" የሚባለውን ስፍራ በመተው፣ በከተማዋ እምብርት ላይ የሚገኘውንና የኮሪደር ልማት ያረፈበትን "ሼህ ሆጀሌ አደባባይ" ለበዓሉ ማከበሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።በተጨማሪም "አሶሳ የኦሮሚያ ናት" የሚሉ ጥያቄዎች በስብሰባው ላይ ተነስተዋል። ይሁን እንጂ ጥያቄው ውድቅ የተደረገ ሲሆን፣ የክልሉ ፀጥታ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብዱልሃብ የከተማዋን የሕዝብ ስብጥር በመጥቀስ ጠንካራ ምላሽ ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ በምላሻቸው፡ "65% የሚሆነው የከተማዋ የአማራ ሕዝብ ያላነሳውን ጥያቄ፣ 11% የሚሆነው የኦሮሞ ሕዝብ እንዴት ያነሳል? እኔ ከዚህ በኋላ ከአማራ ሕዝብ ጎን ነኝ" በማለት ተናግረው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ በአሶሳ ከተማ በመክፈት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የፀጥታ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያደርግ የነበረው ሙከራ በጥቅሉ በከተማዋና በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የፖለቲካና የፀጥታ ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ይነገራል።
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 18:21



ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 17:47
አሁን ያለአባላት ተሳትፎ እና ውሳኔ ተቋቁሟል የተባለው "ጽምዶ/ትብብር" በአሽዋ ላይ እንደቆመ ቤት ወጀብን መቋቋም የማይችል ነው።ይህ በአማራ የህልውና ትግል ላይ የተፈፀመ ታላቅ በደል ነው። በዚህ ልክ ነገሮችን ማመዛዘን የሚችል መሪ የሌለን በመሆኑ ከልብ ባዝንም፣ በእግዚአብሔር እመካለኹና በትግሉ ተስፋ አልቆርጥም። ፈጣሪ በዚህ ትግል ውስጥ ብዙ ተዓምራትን አሳይቶናል። ወደፊትም ያሳየናል።አፋብን የህግ በላይነት የተከበረበት ቤት እንዲሆን የተጀመረው ህጋዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ፈጥኖም ሆኖ ረፍዶ፣ በጽምዶ/ትብብሩ ዙሪያ የአባላት ድምፅ ወሳኝ ይሆናል። በዚህ ሂደት እስር እና ግድያ ያጠናክረናል እንጂ አይበግረንም።እስክንድር ነጋ፣ የአፋብን አባል።መስከረም 12፣ 2019 ዓ.ም --- ግልባጭ :---- ለአፋብን አባላት እና ደጋፊዎች --- ለመገናኛ ብዙሃን (ለህዝብ) --- ለማህበራዊ ሚዲያ (ለህዝብ) #ኢትዮጵያ #followerመስከረም 12/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን!
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 17:47
---ለአፋብን ፖሊት ቢሮ።--- ከእስክንድር ነጋ።---ጉዳዩ---ያለ አፋብን አባላት ተሳትፎ እና ውሳኔ ስለተቋቋመው "ትብብር"።--- መስከረም 12፣ 2019።አፋብን ከተመሠረተበት ጥር 9፣ 2018 አንስቶ እስካለንበት መስከረም 2019 ድረስ የአማራ ህልውና ትግል ትላልቅ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድሎች ያስመዘግባል ተብሎ በህዝብ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት እንደነበር ይታወሳል። ይህ ተስፋ ሁለቱ የፋኖ አደረጃጀቶች አንድ ከመሆናቸው በፊት በአፋህድ ላይ እንደ ድርጅት፣ በእኔ ላይ እንደግለሰብ የተፈፀሙ በደሎችን እንደ ፀጋ እንድቆጥራቸው እስከማድረግ የደረሰ ነበር። መስዋዕትነት እና ጨዋነት ለአፋህድ ድርጅታዊ ባህል፣ ለአባላቱ ደግሞ ግለሰባዊ ሱስ እንዲሆን በመጠኑም ቢሆን ስንጥር የቆየን በመሆናችን፣ የአፋህድ ድርጅታዊ ህልውና በዚያ መንፈስ መቋጨቱ ከፍተኛ የህሊና እርካታ ሰጥቶኛል።ሆኖም፣ እንደ አፋብን ለመሰለ አዲስ ድርጅት የተስፋ፣ የብዙ ስራዎች እና የብዙ ውጤቶች ማስመዝገቢያ ግዜ በሆነው እና በተለምዶ "የጫጉላ ሽርሽር ወቅት" ተብሎ በሚታወቀው የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናቶች፣ ለትግሉም ሆነ ለድርጅቱ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ወይም የለውጥ ተስፋ ሳይመዘገብ ቀርቷል።በመላው ዓለም እንደሚታወቀው፣ "የ100 ቀናቶቹ የጫጉላ ሽርሽር ወቅት" የመንግሥት ወይም የድርጅት መሪ ብቃት ምን ያህል እንደሆነ የሚመዘንበት ወሳኝ ወቅት ነው። በጫጉላ ዘመኑ ውጤታማ ያልሆነ መሪ በቀጣይነት ውጤታማ የመሆን ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው።የአፋብን መሪ ወደሥልጣን የወጣበት ሂደት ብቃትን፣ ቅቡልነትን እና
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 17:47



ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
22 Sept, 07:50edited
#ኦህዴድ ቤተክርስቲያን ገብቶ ሰንደቅአላማውን ሲገፍፍ አደረ‼️#ኦህዴድ ከዚህ በፊት ጭፍጨፋ የፈፀመበት ሻሸመኔ ከዚህ በፊት ጭፍጨፋ በፈፀመበት ሻሸመኔ አጥር ደፍሮ በመግባት ቤተ ክርስቲያን የተዋበችበት ሰንደቅ አላማ ሲገፍፍ፣ ሲያስወግድ አድሯል።👉በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየተመረቀ ባለው ሕንጻ ላይ ለምርቃቱ ማድመቂያ ትናንት የተሰቀለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሎጎ ያለበት ባንዲራ ጉልበተኞቹ ኦህዴዶች ቄሮን አሰማርተው ሌሊቱን አውርደውት ማደራቸውን መረጃ አካፍለናችሁ ነበር። ይሁንናT በሊቀጳጳሱ መመሪያ ሰጪነት ድጋሚ የተሰቀለ ቢሆንም ጉልበተኞቹ ኦህዴዶች ድጋሚ ጣሪያው ላይ በመውጣት አስገድደው አውርደውታል።#ፎቶው ላይ በቀይ የተከበቡትን በትኩረት ይመልከቱ። ዘቤተ ሚካኤል 12/01/2019መስከረም 12/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh




ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
21 Sept, 10:30edited
ትግራይ ቴሌቪዥን ታገደ‼️የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥን መታገዱን አስታወቀትላንት መስከረም 10/2019 ዓ.ም የትብብር ኃይሎችን የጋራ መግለጫ ማሰራጨቱን ተከትሎ የትግራይ TV በኦህህዴድ አፋኝ ፋሽስታዊ አገዛዝ ከስርጭት ታግዷል። በመቀጠልም ከዚህ ጣቢያ መረጃ በተቀበሉ እና ባሰራጩ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መመሪያ ተላልፏል።መስከረም 11/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 21:38
https://youtube.com/live/fNZRj0I0RhY?feature=shareYouTubeየኦነጋዊ ርእዮት ልሂቃን ወንድሞቻችን ስለ ዘር ማጥፋት ዝግጅት ምን ልብ ያላልነው አደጋ እየነገሩን ነው?እንዚህን ኦነጋውያን ልሂቃን ልናመሰግናቸው ይገባል። ኦነጋዊው የገዳና የጽንፈኛ ዉሃብያ ጋብቻ በኦሮሞ ሕዝብ የብሔር ፖለቲካ ስር ተደብቆ ምን እንደደገሰልን፣ አሁን የሚሆነው እልቂት ለምን እንደሚካሄድ በግልጽ ንግርውናል። ልብ ያለው ልብ ይበል!! #Ethiopia #Genocide #Abiy #OLF #TPLF Fano #Amara, #Oromo #Orthodox #Fantahun #Tedy #Zemde 🎙️ New…
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 21:37

1,110Open in Telegram
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 16:04edited
ኦህዴድ ከጫካው ክንፍ ኢ መደበኛ ታጣቂው OLA ጋር ጥምር ጦር አሰማርቶ ከክልሉ ተሻጋሪ ፀረ አምሓራ ዘመቻ አድርጓል። ይህ፣ በአምሓራ ነዋሪዎች ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተፈፀመ ዘግናኝ በደል ነው።መስከረም 10/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 11:22edited
#በ24 ሰዓታት 2000 ድሮኖች ተጨናገፉ‼️የሩሲያ የአየር መከላከያ በ24 ሰዓታት ውስጥ 2 ሺህ የሚጠጉ የዩክሬን ድሮኖችን እንዳጨናገፉ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀየአየር መከላከያ ሥርዓቶች በአንድ ቀን ውስጥ መትተው የጣሏቸው መሣሪያዎች፦🔸1,951 ባለ ወጥ ክንፍ የዩክሬን ድሮኖች፣ 🔸ስምንት የፍላሚንጎ ክሩዝ ሚሳዔሎች፣ 🔸ስምንት ተንሸራታች የአየር ቦምቦች፣ 🔸አራት የሂማርስ ሮኬቶች።ተጨማሪ ዝርዝሮች፦▪️የዩክሬን ኃይሎች በአንድ የውጊያ ቀጣና እስከ 455 የሚደርስ የሰው ኃይል ጉዳት አስተናግደዋል።▪️በሌሎች ቀጣናዎች ደግሞ በአንድ አካባቢ ከ280 በላይ፣ በሌላ አካባቢ እስከ 230 እንዲሁም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እስከ 195 እና 40 ጉዳቶች ሪፖርት ተደርጓል።▪️ዩክሬን በካርኪቭ ክልል ከባባ ውስጥ በገባ ቀጣና ከ30 በላይ ወታደሮቿን፣ አንድ ብረት ለበስ የውጊያ ተሽከርካሪ፣ አንድ መደበኛ ተሽከርካሪ እና አንድ የምድር ሮቦት ሥርዓት አጥታለች።መስከረም 10/2019 ዓ.ም


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 11:17
#የአገዛዙ ድሮን ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️በዛሬው ዕለት መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከሰዐታት በፊት 4:20 አካባቢ በትግራይ ክልል ዓዲነብርኢድ በሚባል ቦታ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ቦታ ላይ የኤርትራ ሰራዊት እንዳለ ሲጠረጠር ትናንት መስከረም 9 ምሽት የኤርትራ_ሰራዊት ጨለማን ተገን በማድረግ በአስገደ ፅንብላ አድርገው ወደ ትግራይ ክልል ዓዲ ዳዕሮ፣ ዓዲነብርኢድ፣ ዓዲሃገራይ፣ በሽራሮ ከተማ ና ታሕታይ አድያቦ ወረዳ እንደገቡ እየተዘገበ ይገኛል። የኤርትራ መንግስትም ሆነ ህወሓት ይሔን ጉዳይ ያስተባብላሉ።መስከረም 10/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 10:55
#የጭቁን አምሓሮች ድምፅ! ===============((())))================== ዳንግላ ቻግኒ አዲስ ቅዳም ጃዊ …70% በላይ የአምሓሮች መኖሪያ የጎጃም አስትዳድር አካል ሆነው ሳለ በግፍ አምሓራን ገፊ እና ጨቋኝ በሆነው አዊ ዞን አስተዳድር ስር የተካተቱ አምሓራ ከየመዋቅሩ ሲሳደድባቸው፣ ሲገፋባቸው የቆዩ፣ የወያኔ ፀረ አምሓራ ጥላቻ በጥቂት የአገው የወያኔ ካድሬዎች በዞናቸው አምሓራ ላይ ቀንበር ጭነው ሲጨቆንባቸው የኖሩ የጎጃም አምሓራ የውስጥ አምሳለ ወልቃይት፣ አምሳለ ራያ፣ አምሳለ ወለጋ አስተዳድሮች ናቸው። ከነዚህ አካባቢዎች አምሓራ እየተገፋ ሲፈልስ፣ ሲማረር ኖሯል። በነዚህ ወረዳዎች ብዙሓኑ አምሓራ በቢሮክራሲ ውስጥ፣ በፀፅታ ዘርፉ ውስጥ በተጠና ሁኔታ ተገላይ ነው። የክልሉ አስተዳድርም ሆነ አምሓራ ፋኖ፣ የውስጥ ወለጋዎቹን መስመር ሳያስይዝ ከክልሉ ውጭ ላሉ ሊደርስ ቤዛም ሊሆን አይችልም! በነገራችን ላይ፣ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና መምህርት #መስከረም አበራ ከዳንግላ የወጣች ፈርጥ የአምሓራ ትግል ኮከብ ነች። ሌሎች፣ ከነዚህ አካባቢ የወጣችሁ የአምሓራ ልሒቃን እና ንቁዓን በጎጃም በአዊ ዞን አስተዳድር ስር አምሓራ በመሆናችሁ የደረሱባችሁን በደሎች አጋልጡ! አምሓራ ከክልሉ ውጭ በላቀ በክልሉ ውስጥ ወያኔ ኢፍትሓዊ በሆነ መልክዓ ምድር ላይ ባዋቀራቸው ልዩ አስተዳድር • አዊ ዞን/የአገው ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን • ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳር ዞን • በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን • በአርጎባ ልዩ ወረዳ አስተዳድር ወዘተ ውስጥ ያለ አምሓራ ክፉኛ ተበድሏል። በስመ ክልሉ ውስጥ
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 10:55



ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 00:29edited
#ድርቁ እየተስፋፋ፣ ርሓብ እየተባባሰ ነው‼️በእርስበርስ ግጭት በምትታመሰው ሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የድርቅ ቀውስ እየተባባሰ ነው‼️በተጠናቀቀው አመት የክረምት ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታየው የዝናብ መዘግየትና እጥረት በሰው፣ በእንስሳት እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያሰከተለ ይገኛል። አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ በርካታ ዞኖችና ወረዳዎች ድርቁ አስከፊ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እና ተጓዳኝ ችግሮች መዳረጉን ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት ተረድታለች።ድርቁ ከተባባሰባቸው ክልሎች መካከል አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና አፋር የሚገኙበት ሲሆን፤ የዋዜማ ባልደረቦችም ከእነዚሁ ክልሎች ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የተመለከተ መረጃ አሰባስበዋል፡፡መስከረም 09/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
20 Sept, 00:25
ፅናት እና የሞራል ከፍታ ጋሽ ታዲዮስን መስሎ እስከመጨረሻው ላመኑበት ለፀኑት የአላማ ልጆቻቸው ድንቅ ምሳሌ ሆነዋል!



ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
19 Sept, 22:25edited
በጋምቤላ ክልል በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉበጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ።ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም መነሻቸውን ከጋምቤላ ከተማ አድርገው ወደ ኢታንግ ፣ ላረ እና ጅካዎ ወረዳዎች በመጓዝ ላይ ነበሩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን የአይን ምስክሮች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።በወታደራዊ አጀብ ይጓዙ እንደነበር የተገለጸው ስድስት ተሽከርካሪዎች አቦል ወረዳ ሲደርሱ ጥቃቱ መፈጸሙ ተሰምቷል።በደረሰው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 16 ሊደርስ እንደሚችል የአይን ምስክሮች ተናግረዋል።የተጎጂዎችን ቁጥር ደግሞ 60 ያህል ሊሆኑ እንደሚችሉ የተናገሩም አሉ።ለበርካቶች ህይወት ህልፈት እና መቁሰል ምክንያት ለሆነው የትናንትናው የታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት አረጋግጧል።በጋምቤላ ክልል የላረ ወረዳ በተደጋጋሚ የታጣቂዎች ጥቃት መጋለጧን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የትናንቱ ጥቃት ግን ማንነትን መሠረተ ያደረገ ከተጓዦች መካከል ተመርጠው እየተገደሉ ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጸዋል።መስከረም 09/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
19 Sept, 22:19
#አላማ ቢስ ሟቹን እንቀንሰው፣ በንቃት ፈጣሪ ጥሪ በጅምላ እንማርካቸው!በአፈሳ ወደጦርነት የሚማገዱ ወጣቶች አላማ ቢስ ሟች ናቸው። በጫካ የሚንቀሳቀሱ የህልውና ትግል ሰልፈኞች ጠንካራ የፕሮፖጋንዳ መስኮት እና ንቃት/ግንዛቤ ፈጥሮ ጥሪ አቅራቢ ሆነው ቢገኙ ሳይተኩሱ እጅ የሚሰጡ የፋሽስቱ ጭፍራዎች እጅ ከማይሰጡት የሚልቁ ናቸው። ቅሉ! ታጣቂው ኃይል፣ በቂ ግንዛቤን አሳዳጊ፣ ሀገራዊ ርዕይን ጠቋሚ በስነ ልቦና እና ሞራል ከፍታ እርሱ ተገኝቶ መገኘቱን አታች፣ ለፋፊ የራሱ ሚዲያ የለውም። የታላቁ ህዝብ የህልውና ዘብ የሆነው "#ፋኖ" እስካሁን በቀጥታ ኃላፊነት የሚወስድበት ቋሚ • የራዲዮ • የቴሌቪዥን • የማህበራዊ ሚዲያ ወዘተ…ለተጋድሎ ያወጣውን ምክንያታዊ በደል እና ከነፃነቱ ለጥቆ ለህዝበ ወኪሉ እና ኢትዮጵያውያን ያለውን ፖለቲካዊ ርዕዮት የሚያስደምጥበት የራሱ የሐሳብ መሸጫ ምኩራበ መድረክ ሚዲያ የለውም። ትልቅ፣ ነገር ግን፣ የተተወ ወይም ችላ የተባለ ችግር! በየግለሰቡ እና ራስ ተነሽ የጎፈንድሚ ጡረተኞች የሚያቆሙት ሰንብቶ ፈራሽ ድንኳን ሚዲያዎች ለአምሓራ የህልውና ትግል ዋስትና ሰጭ ሀቅም አይሆኑሞ!
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
19 Sept, 21:35edited
የሆነው እንዲህ ነው!ትግራይ ውስጥ ትህነግ ከተናቀ ሰንበትበት ብሏል። ራሱ ያዋቀረው መንበረ ሰላማ የሚባል ቡድን ሳይቀር "ሕዝቡ ከእናንተ እኛን ነው የሚሰማው" ማለት ጀምሯል። በዚህ ምክንያት ከፖለቲከኞቹ ጋር ልዩነቶች አሉ። የአንዱ የመንበረ ሰላማ አባል ቤት ባለፈው በጥይት ተመትቶበታል።ራሱ ትህነግ ቤተ ክርስቲያንን ሊመታ ያዋቀረው ቡድን ራሱን እንደ አስታራቂ ቆጥሮም ወደነ ደብረፅዮን ይመላለሳል። ለታደሰ ወረደም ለሌላውም እነ ደብረፅዮን ጋር ሽምግልና ከርሟል። ትህነግ ደግሞ ይህን እየፈለገ አይደለም።በቅርቡ ደግሞ ሌላ ችግር ተፈጠረ። ትህነግ የቆሎ ተማሪዎችን ሳይቀር ለግዳጅ ውትድርና ማፈስ ጀመረ። ከታች በየደብሩ ያሉ እውነተኛዎቹ አባቶች ትህነግ ከላይ ያዋቀረውን የመንበረ ሰላማ አመራር አስጨነቁት። ከታች በየደብሩ ያሉትን ካልያዘ የማንም አመራር መሆን አይችልምና እየመረረውም ቢሆን የቆሎ ተማሪዎች በትህነግ እየታፈሱ መሆኑን መግለጫ ሰጠ። ይህኔ ትህነግ ራሱ ያደራጀውን ቡድን ያውቀዋልና ተበቀለው። ራሴ አቋቁሜ እኔን በሕዝብ ሊያስጠላ አይችልም ብሎ ሴት ላከበት። የቡድኑን ሁኔታና ጉድ ያውቃልና "እኛ ከእናንተ የተሻለ ተሰሚነት አለን" የሚለውን መንበረ ሰላማ ጉድ ራሱ ትህነግ አስወጣው። ያቋቋምኩህ ለራሴ ፖለቲካ ሆኖ እያለ ዘነፍ ካልክ አሳይሃለሁ ነው ያለው። ለሌሎቹም ማስጠንቀቂያ ነው። ትህነግን ተዳክሟል በህዝብ ተጠልቷል ብሎ መናቅ፣ መቃረን ከጀመረ ሌላው የቡድኑ አባልም ተመሳሳይ የቅሌት መረጃ አይቀርለትም ። መረጃ ያልተያዘበት የለም! መስከረም 08/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #


ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…
19 Sept, 21:28edited
ታድዮስ ታንቱ ከእስር ተፈቱ፡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋልየኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣ የታሪክ አዋቂ እና የፖለቲካ ተቺ/ተንታኝ የሆኑት አቶ ታድዮስ ታንቱ ዛሬ ከእስር መፈታታቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል። አቶ ታድዮስ ታንቱ በተለያዩ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ በሀገራዊ የታሪክ ትረካዎች እና በማህበራዊ ምህዳሩ ላይ ባላቸው ጠንካራ እና ግልጽ አቋም የሚታወቁ አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ ናቸው። በተለይም በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ብሔራዊ አንድነት እና የፖለቲካ ሂደቶች ላይ በሚሰጧቸው ስለታም ትችቶችና ትንታኔዎቻቸው በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትና ተደራሽነት አላቸው። ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ የቆዩት አቶ ታድዮስ፣ በዛሬው ዕለት ነጻ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ተከተሎ የቅርብ ወዳጆቻቸው፣ የደጋፊዎቻቸው እና በማህበራዊ ሚዲያ የሚከታተሏቸው በርካታ ዜጎች ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። የአቶ ታድዮስ ከእስር መፈታት በፖለቲካው እና በማህበራዊው ምህዳር ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።መስከረም 08/2019 ዓ.ም ሞዐ ሚዲያ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ #ታማኞች ነን! #we are trustworthly! https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418 https://t.me/Moamediamoresh

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
