Latest posts

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
10 Sept, 14:46
ተፈጥሮ ራሱን አድሷል ተራሮች አረንጓዴ ለብሰዋል! አበቦች በሜዳ ፈክተዋል! አዲስ ዓመት አዲስ ዘመን መጥቷልበስራ የምንበረታበት በውጤት የምንታጀብበት የስኬት ዓመት ይሁንልንመልካም አዲስ ዓመት

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
9 Sept, 18:27
የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰቦች የአየር ንብረት እና የምግብ ደህንነት ጉባዔ ተጠናቀቀ።ከ30 በላይ ከሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ማህበራት እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶች ንቅናቄዎች በአዲስ አበባ ላለፉት ሶስት ቀናት ያካሄዱትን ውይይት በማጠናቀቅ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።ተሳታፊዎቹ በአህጉሪቱ እየተባባሰ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቋቋም የአፍሪካ የምግብ ደህንነት እና የአየር ንብረት ፍትህ ተነጣጥለው ሊታዩ እንደማይችሉ በማስመር፣ የመፍትሔዎቹ ባለቤትም እራሳቸው አፍሪካውያን መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል።በተሰናዳው መግለጫ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ በንድፈ-ሀሳብ በሚገቡ ቃል ኪዳኖች እና በተጎጂ ማህበረሰቦች ዕለታዊ ህይወት መካከል ሰፊ ክፍተት እንዳለ ተመላክቷል።ይህንን ችግር ለመቅረፍም በመጪዎቹ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የጉባኤ መድረኮች ላይ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጥሪ የቀረበ ሲሆን እነዚህም ለግብርና እና ምርታማነት ማዕከላዊ ቦታ መስጠት፣ ቀጥተኛ እና ተደራሽ የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሀገር ውስጥ እና ተፈጥሯዊ መፍትሔዎችን ማጠናከር እንዲሁም ፍትሃዊ ሽግግር እና መብትን ማስጠበቅ ላይ ያተኮሩ ናቸዉ።በማጠቃለያቸው አፍሪካ የምግብ እና የአየር ንብረት እጣ ፈንታዋ በሌሎች ሀገራት እንዲወሰንላት መጠበቅ እንደሌለባት ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
9 Sept, 13:28
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የበዐል ስጦታየህብር ቀንበዐላት ላይ የሚታየው የመረዳዳት ባህል የአብሮነትእና የመተሳሰብ እንዲሁም የአንድነታችን ማሳያዎች ነው።ዐዲሱን ዓመት በደስታ ለመቀበልና በጋራ ለማክበር ሁሉም በዙርያው ያሉትን ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ሊያስብ ይገባል።የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዐዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሰራተኞቹ የበዐል ስጦታ አበርክቷልባህል ወደ መሆን የተሸጋገረውን የመደጋገፍ ባህል ይበልጥ በማጠናከር አንድነታችንን ማፅናት እንደሚገባ በስጦታ መርሀግብሩ ላይ ተገልጿልመልካም ዐዲስ ዓመት

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
9 Sept, 05:32

1,020Open in Telegram
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
9 Sept, 05:32
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክትየኅብር ቀንበትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል።ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል።እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን።በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን።አንድ ህዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
8 Sept, 12:15

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
8 Sept, 12:14
የአፍሪካ አህጉራዊ የመካከለኛ ዘመን ግምገማ (Mid-TermReview) በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሄደ።አዲስ አበባ ጷጉሜን 3/2018 ዓ.ም (የፕ.ል.ሚ)በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UN-ECA) በተካሄደው የአፍሪካ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አህጉራዊ የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ጉባኤ ላይ ሚኒስቴሮች፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች ተገኝተዋል።የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በጉባዔዉ የመክፈቻ ንግግር ኢትዮጵያ ያስመዘገበችውን አበረታች የኢኮኖሚ ስኬቶች አንስተው አብራርተዋል።ኢትዮጵያ የህዝብ አገልግሎቶችንና ኢኮኖሚዋን ለማዘመን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አማካይነት በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቷን አንስተዋል።ሚኒስትር ዴኤታዋ አያይዘዉም ኢትዮጵያ ድህነትን በሁሉም መንገድ ለመቀነስ እና ሁሉንም የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራች መሆኗንና አበረታች ውጤት እያስመዘገበች እንደሆነ አንስተዋል።በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ ኢኒሸቲቭ እና በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ የተደረጉት ኢንቨስትመንቶች አካባቢን ከመጠበቅ ባሻገር ለምግብ ዋስትና እና ዘላቂ ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።ወ/ሮ ጥሩማር አክለውም ኢትዮጵያ የምታደርገው ሽግግር ዘላቂ፣ አካታች፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ያረጋገጠ እና ወደኋላ የማይመለስ እንዲሆን ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።እ.ኤ.አ እስከ 2031 ባሉት ዓመታትም በገጠር
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
8 Sept, 06:07

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
8 Sept, 06:06
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት"የጽናት ቀንኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡ ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡ ይህ በራስ የመቆም አቅም፣ የሕዝባችን ሰላምና የሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሀገራዊ ጽናታችንን በተጨባጭ ልማትና በጠንካራ የመጠበቅና የመከላከል አቅም እያረጋገጥን የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልጽግና እናጸናለን!"
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
7 Sept, 14:05

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
7 Sept, 14:05

1,090Open in Telegram
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
7 Sept, 14:04
የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአየር ንብረት እርምጃዎችን በምግብ ስርዓቶች እና በግብርና ላይ ለማጠናከር ያለመ አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።አዲስ አበባ ጳጉሜን 2 / 2018 ዓ.ም (የፕ.ል.ሚ)በአፍሪካ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ አህጉራዊ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።በአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ትብብር (Alliance for Food Sovereignty in Africa) እና በተባባሪ ድርጅቶች አዘጋጅነት ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ ታላቅ ጉባኤ በምግብ ስርዓቶችና በግብርና ላይ የአፍሪካን አቅም ለማጠናከር እና የተናበበ አህጉራዊ አቋም ለመገንባት ያለመ ነው።በጉባኤው ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ 100 የሚጠጉ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ አርሶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እና የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የያደም (YADAM) ፋዉንዴሽን መስራች እና የአፍሪካ የስነ-ምግብ አምባሳደር አቶ ደመቀ መኮንን በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ስነ-ምግብ የአንድ ግለሰብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለአህጉር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት እንዲሁም ለተሻለ አእምሯዊና አካላዊ ልማት ወሳኝ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ስነ-ምግብ፣ ጤና እና የአየር ንብረት ለውጥ ተነጣጥለው የማይታዩና ለአጠቃላይ ስነ-ምህዳር ጤናማነት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆናቸውን አብራርተዋል።የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
7 Sept, 12:55
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia
3 Sept, 17:54

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.