Latest posts

Prosperity Party A.A - ብልፅግና
22 Sept, 05:16





Prosperity Party A.A - ብልፅግና
22 Sept, 05:16





Prosperity Party A.A - ብልፅግና
22 Sept, 05:15
የአደባባይ በዓላት ለቱሪዝም ዘርፍ ማንሰራራት እና ለዘላቂ ዕድገታችን መረጋገጥ!ብዝሀ ዘርፍ የልማት አቅጣጫን እየተከተለች የምትገኘው ኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት ብዙም አስታዋሽ ያልነበረውን የቱሪዝም ዘርፍም አንዱ የእድገቷ ምሶሶ በማድረግ አንፀባራቂ ድሎችን ማስመዝገብ ችላለች፡፡በማንሰራራት ላይ ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ማህበራዊ መስተጋብርን በማጠናከርና የሀገራችንን መልካም ገፅታ በማጉላት ከሚያበረክተው ትልቅ አስተዋፅዖ ባሻገር ከዘላቂ ልማት ግቦቻችን ጋርም የተናበበ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መስህቦችን በአግባቡ በማልማት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እንደ ሀገርም ሆነ በመዲናችን ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ልማቶቻችን አንዱ ለአንዱ ተመጋጋቢ መሆናቸውም ሁሉን አቀፍ ዕድገታችን እንዲፋጠን ምቹ መደላድል ፈጥሯል፡፡ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባሻገር ለአደባባይ በዓላት ደማቅ አከባበር ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል፡፡የአደባባይ በዓላት ከባህላዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ እሴቶቻቸው ባሻገር ኢኮኖሚያዊ አበርክቷቸውም ቀላል አይደለም፡፡የአለባበስ፣ የአመጋገብ እንዲሁም የውበት አጠባበቅ ስርዓቶች ልዩ ልዩ ባህሎች ጎላ ብለው የሚታዩባቸው የሀገራዊ እሴቶች ነፀብራቅ ሲሆኑ፣ የህዝብ ለህዝብ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብርንም ያሳድጋሉ፡፡በበዓላት ወቅት ገበያው ይሞቃል፣ ኢኮኖሚው ይነቃቃል። ከበዓላት ቀደም ብሎም በተለይም የባህላዊ አልባሳት ግብይት ጎልቶ ይታያል። ባህላዊ ምግቦችን ለማዘጋጀት
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
21 Sept, 07:07



Prosperity Party A.A - ብልፅግና
21 Sept, 07:06
የአደባባይ በዓላት እና ታሪካዊ ቅርሶቻችን ትውልድ ተሻጋሪ የወል ፀጋዎቻችን ናቸው!ኢትዮጵያ ህብር መልክዓ ምድር፣ ተስማሚ የአየር ንብረት፣ ውብ የተፈጥሮ ፀጋዎች እንዲሁም ጥልቅ የሆኑ እሴቶች ያሏት ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ብዝሀ መልክ ያላት ሀገራችን ታይተው የማይጠገቡ የቱሪስት መዳረሻዎች አሏት፡፡ በዩኔስኮ (UNESCO) የተመዘገቡና ወደ ፊት የሚመዘገቡ የሚዳሰሱ ቅርሶች አስታዋሽ አጥተው የነበሩ ሲሆን ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ለሀገራዊ ቅርሶች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ዘመን ተሻጋሪ እድሳት ተደርጎላቸዋል፡፡ዓለም በሚደመምበት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተከናወነው የእድሳት ተግባር ተጋርጦበት የነበረውን ችግር በማስወገድ ዘመን ተሻጋሪ ማድረግ ተችሏል፡፡በታሪካዊቷ ጂማ ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የጅማ አባ ጅፋር ቤተመንግስትም ደረጃውን የጠበቀ እድሳት ተደርጎለት የስዕበት ማዕከል ሆኗል፡፡ለአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት የተደረገው እድሳት ደግሞ ለጎንደር ከተማም አዲስ ውበት በማላበስ የከፍታ ጉዞዋን አብሳሪ ሆኗል፡፡ሌላው ሀገራዊ ሀብታችን የጥንታዊቷ የሀረር ከተማ ምልክት የጀጎል ግንብም በተቀናጁ የልማት ስራዎች ማራኪ ግርማ ሞገስ ሊላበስ ችሏል፡፡በመዲናችንም ብሔራዊ ቤተ መንግስትን ጨምሮ በርካታ ሀገራዊ ቅርሶች በተደረገላቸው ደረጃውን የጠበቀ እድሳት ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻዎች ሆነዋል፡፡ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ጊዜያቶች በዩኔስኮ (UNESCO) ካስመዘገበቻቸው ቅርሶች ባሻገር በቅርብ ዓመታት ውስጥም የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ መልካ ቁንጡሬ እና ባልጪት መካነ
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
17 Sept, 14:53



1,560Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
17 Sept, 14:53
ለዓለም ከተሞች ምሳሌ የሆነች ከተማ - አዲስ አበባአዲስ አበባ ዝቅተኛ የአደጋ ተጋላጭ የሆነች፥ ደህንነቷ የተጠበቀና የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም ከተማ በሚል ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ሁለተኛ ከተማ ሆና ተቀምጣለች።የጂኦስፓሻል ኩባንያ አልፋ ጂኦ በዋነኝነት በሶስት መመዘኛዎች የአዲስ አበባ ከተማን የመዘነ ሲሆን አካላዊ የአየር ንብረት ለውጥ፥ አደጋ ተጋላጭነት፤ሊገጥሙ ለሚችሉ አደጋዎች አስተዳደር እና ፖሊሲ ምላሽ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የማላመድ እርምጃዎች ላይ በማተኮር ነው ምዘናው የተካሄደው።በእነዚህ መመዘኛዎች አዲስ አበባ ከተማ ከ72 ከተሞች ጋር ተወዳድራ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለዓለም ከተሞች ምሳሌ ሆናለች፡፡በዓለም የስልጣኔ ቁንጮ የተባሉትን እንደነ ፓሪስ እና ለንደን የመሳሰሉት ከተሞች አስከትላ በዓለም ላይ የአየር ንብረት ተጋላጭነት የምትቋቋም ከተማ በሚል ከአሜሪካዋ ቺካጎ ቀጥሎ በቁንጮ ላይ የተቀመጠችው አዲስ አበባ በኮሪደር እና የመንዝ ዳርቻ ልማት ያከናወነችው ስራዎች እና የዘረጋቻቸው ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች በዚህ ደረጃ እንድትቀመጥ አስችሏታል፡፡አዲስ አበባ የዓለም ቀልብ የምትስብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ብቻ አይደለችም ከምቹነት ባለፈ የአደጋ ተጋላጭነቷ ዝቅተኛ የሆነች፥ ደህንነቷ የተጠበቀ የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም ከተማ ናት ፡፡በዓለምአቀፉ ጂኦስፓሻል ኩባንያ አልፋ ጂኦ (Alpha Geo) ለአዲስ አበባ የተሰጠው ማረጋገጫ ለፖሊሲ አውጪዎች፤ ኢንቬስተሮች እና የመሰረተ ልማት ባለቤቶች አዲስ አበባ ከተማ በተመለከተ የውሳኔ ሀሳቦች ለመስጠት እጅጉን ጠቃሚ1,430Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
16 Sept, 09:17



1,590Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
16 Sept, 09:17
ትምህርትን ለትውልድ ብልጽግናን ለሀገር!ትምህርት የአንድ ትውልድ የእውቀት ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ሀገር የነገ ዕድል መሠረት ነው። ዘላቂ ልማት፣ ሁለንተናዊ ብልጽግናና የተሻለ የወደፊት ሀገራዊ አቅም ያለ ጥራት ያለው ትምህርት ሊገነባ አይችልም። በተለይም ዓለም በፍጥነት ወደ ዲጂታል እውቀትና ቴክኖሎጂ በምትሸጋገርበት በዚህ ዘመን፣ የትምህርት ሥርዓታችን የተማሪዎችን እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባለፈ ለሀገር ልማት የሚያስፈልጉ ብቁ፣ ፈጣሪና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎችን ማፍራት ይጠበቃል።ትምህርት የጋራ እውቀትንና እሴቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሸጋግር፣ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይን የሚገነባ ድልድይ ነው። ስለሆነም ትምህርትን በሀገራዊ ልማት ሂደት ውስጥ እንደ ቁልፍ መሣሪያ በመውሰድ፣ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በሥነ-ምግባርና በሀገር ፍቅር የታነጹ ዜጎችን ማፍራት የዛሬ ትውልድ ዋነኛ ኃላፊነት ነው።የሀገራችን የትምህርት ሥርዓት በተለይም ከጥራትና ከአግባብነት አንጻር ለረጅም ጊዜ የተለያዩ ስብራቶችና ውስብስብ ተግዳሮቶች ሲገጥሙት ቆይቷል። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግሥትም እነዚህን ተግዳሮቶች በመለየት፣ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታን ከማዘጋጀት ጀምሮ በዘርፉ የተጀመሩ ለውጦችን በማጠናከር ላይ ይገኛል።በቀጣይ አምስት ዓመታትም የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በማጠናከር፣ በትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራት፣ አግባብነትና ፍትሐዊነት የላቀ ውጤት ለማምጣት ትኩረት ይደረጋል። የቅድመ አንደኛ ትምህርት ተሳትፎን በቁርጠኝነት በማስቀጠል ወደ 100 በመቶ ማድረስ፣1,450Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
16 Sept, 06:25

1,060Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
16 Sept, 06:25
በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ። ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው። ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው። በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #aa_prosperity1,120Open in Telegram
Prosperity Party A.A - ብልፅግና
15 Sept, 12:47



1,090Open in Telegram
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
