Latest posts

Space Science and Geospatial Institute
22 Sept, 09:53
https://vm.tiktok.com/ZN8Mkgmun/
Space Science and Geospatial Institute
21 Sept, 16:17
አዲሷ ፔጋሱስ 1 (PEGA-SUS1) ሳተላይት በአጠቃላይ ዘጠኝ ሳተላይቶችን እንደሚያካትት በተገለጸው ስብስብ ውስጥ የመጀመሪያዋ ፈር ቀዳጅ ናት።በቀጣይም ለ6G ቴክኖሎጂ እና ለቻይና የሳተላይት ኢንተርኔት ፈጠራ ትልቅ መሠረት በመጣል ከመሬት እስከ ህዋ የሚዘልቅ የተቀናጀ የመገናኛ መረብ ለመገንባት መንገድ ትከፍታለች ተብሎ ተስፋ ተይዟል።#SSGI EBC #ChinaSpace #PEGASUS1 #SatelliteTechnology #GalaxySpace #SpaceInnovation
Space Science and Geospatial Institute
21 Sept, 16:17
ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ አዲስ ባለብዙ ተግባር ሳተላይት ይፋ አደረገችየቻይና ተመራማሪዎች የህዋ ቴክኖሎጂን ወደ አዲስ ደረጃ የሚያሸጋግር ትልቅ ስኬት አስመዝግበዋል። ቀደም ሲል ሳተላይቶች የሚሰሩት አንድ የተወሰነ አገልግሎት ብቻ ቢሆንም (ለምሳሌ ምስል ማንሳት ብቻ ወይም የቴሌኮም መረጃ ማስተላለፍ)፣ አሁን ግን መገናኛን፣ ዳሰሳን፣ ማስላትን እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሂደትን በአንድ ላይ የሚያጣጥም ባለብዙ ተግባር ሥርዓት እውን አድርገዋል።ለዚህ አዲስ ስኬት ማሳያ የሆነችው ፔጋሱስ 1 (PEGA-SUS1) የተሰኘችው 150 ኪሎ ግራም የምትመዝን ሳተላይት ናት።ሳተላይቷ በሼንዘን የሚገኘው ፔንግቼንግ ላብራቶሪ፣ በቤጂንግ የሚገኘው ጋላክሲ ስፔስ የግል ኩባንያ እና ሌሎች የምርምር ተቋማት በጋራ የበለጸገች ሲሆን በቻይና የንግድ ሮኬት አማካኝነት ከሌሎች 8 ሳተላይቶች ጋር ወደ ህዋ ተልካለች።የዚች ሳተላይት ዋና ልዩነቷ መረጃን ከህዋ ወደ መሬት ካወረደ በኋላ መተንተን ሳይሆን መረጃውን እዚያው ህዋ ላይ እያለች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ራሷ ማቀናበር መቻሏ ነው።እንደ ጋላክሲ ስፔስ ከፍተኛ ቴክኒክ ባለሙያ ሬን ጂያዶንግ ገለጻ ለምሳሌ የደን ቃጠሎ ቢከሰት ሳተላይቷ የቃጠሎውን መኖር እና የጉዳቱን መጠን እዚያው ህዋ ላይ አጠናቅራ ዋናውን ውጤት ብቻ በፍጥነት ወደ መሬት ትልካለች።ይህም ጥሬ ምስሎችን ሙሉ በሙሉ መላክ ስላይስፈልግ የማስተላለፊያ ጊዜን እና የመረጃ መጠንን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።




Space Science and Geospatial Institute
21 Sept, 16:15
https://www.facebook.com/share/1GLNqFagUR/FacebookLog in or sign up to viewSee posts, photos and more on Facebook.
Space Science and Geospatial Institute
19 Sept, 07:53
https://youtu.be/eHhQhrnKX90?si=_AgGQjGBfRapv9EiYouTubeየኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰለጠነ፦ በ25 ማዕከላት የተካሄደ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ስልጠና |ETV | EBCየኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (Space Science and Geospatial Institute - SSGI) በቴክኖሎጂ የተካኑና ለአገር የሚጠቅሙ አዳዲስ ፈጠራዎችን ማምጣት የሚችሉ ትውልዶችን በማፍራት ረገድ የራሱን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ ይገኛል ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ በሚገኙ 25 ማዕከላት ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ፣ በስፔስ ሳይንስ፣ በጂኦስፓሻል እና በፈጠራ ዘርፎች…
Space Science and Geospatial Institute
18 Sept, 16:45
https://vm.tiktok.com/ZN86xoUhe/
Space Science and Geospatial Institute
18 Sept, 03:56
https://youtu.be/cFomw6rUTKU?si=VeCNVwE_qUJ7GdNfYouTubeየባሌ ሮቤ የተማሪዎች ፈጠራ 🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨
Space Science and Geospatial Institute
17 Sept, 18:07

Space Science and Geospatial Institute
11 Sept, 05:27
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲሳ ይልማ አዲሱን የ2019 ዓመት በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት፥
Space Science and Geospatial Institute
11 Sept, 04:37
ለመላው የኢንስቲትዩቱ የስራ ባልደረቦች፣ የተቋማችን አጋር አካላት እና ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!መጪው 2019 ዓ.ም በሁሉም መስኮች የላቀ ስኬት የምናስመዘግብበት፧ በሥራችን ልቀን የምንገኝበት፣ የሠላም፣ የጤና፣ የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።መልካም አዲስ ዓመት!ለተጨማሪ መረጃ:- የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022 Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute Telegram: https://t.me/spacegeospatial ከምድር እስከ ህዋ … SSGI
1,080Open in Telegram
Space Science and Geospatial Institute
11 Sept, 04:29
https://vm.tiktok.com/ZN82wRYqT/
Space Science and Geospatial Institute
11 Sept, 03:05

Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 18:34
https://vm.tiktok.com/ZN82crXPf/
Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 17:59
https://www.facebook.com/share/r/1MByNyARxq/Facebook812 views | Reel by Ethiopian News Agency1,230Open in Telegram
Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 17:01
ኢንስቲትዩቱ የ2019 አዲስ ዓመትን በማስመልከት ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ማዕድ ማጋራት አከናወነ። ======= SSGI ======= (ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም SSGI) ኢንስቲትዩቱ ከምርምርና ልማት ስራዎቹ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለመቄዶንያ ሐረጋዊያን መርጃ ማዕከል፣ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል እና በዋናው መስሪያ ቤት በጥበቃ ስራ ላይ ለተሰማሩ የፌዴራል ፖሊሶች አንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ስራ ባልደረቦች ሆነው በተለያዩ ጊዚያት እክል ለደረሰባቸው ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃግብር አካሂዷል።በዚህ መርሃ ግብር ላይ ድጋፉን ያስረከቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ ሲሆኑ ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም የአዲስ ዓመት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።ኢንስቲትዩቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈቱ የስፔስና ጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ ምርምሮችን ከማካሄድ ባለፈ፤ ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።ለተጨማሪ መረጃ:- የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022 Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute Telegra




Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 11:45
በተለይም ተማሪዎቹ ያሳዩት የትምህርት ዘርፎች ቅንጅት (Interdisciplinary integrity) እጅግ አስደናቂ መሆኑን ጠቁመው፤ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ እስከ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ቴክኖሎጂ፣ ከዘመናዊ ግብርና (Smart-Farming) እስከ ባለብዙ አገልግሎት ሰው አልባ አውሮፕላን (UAV) ልማት ድረስ የሰሯቸው ስራዎች ኢንስቲትዩቱ እና ሀገር ትልቅ ተስፋ የሚጥልባቸው የነገ ተስፋዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።ከዚህ መደበኛ የክረምት ስልጠና ጎን ለጎን፣ በኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ስር የተመረጡ ተማሪዎች በመጪው ኖቬምበር 2026 በሩሲያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ አስትሮኖሚ ኦሎምፒያድ(OWAO 2026) ላይ ሀገራቸውን በብቃት ለመወከል ተጠናክረው በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።ለዚሁ ውድድር ተማሪዎቹን ብቁ ለማድረግ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እና የክለቡ አስተባባሪዎች ከተማሪዎቹ ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ይገኛሉ።የማጠናቀቂያ ዝግጅቱ ተማሪዎች ያበለፀጓቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በክብር እንግዶች ከተጎበኙ በኋላ በታላቅ ድምቀት ተጠናቅቋል#SSGI #ESKS
Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 11:45
ጳጉሜ 5 የነገ ቀን «ነገን ዛሬ መገንባት» የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና አጠናቀቀ። ======= SSGI ======= (ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ SSGI) በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) አዘጋጅነት ከክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮ ስፔስ እና ጂኦስፓሻል ታዳጊዎች ክለብ (ESKC) የ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠና በታላቅ ስኬት ተጠናቋል።በዘንድሮው ስልጠና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተጨማሪ በ10 ክልሎች በሚገኙ 25 ማዕከላት አማካኝነት ከ4,000 በላይ ታዳጊዎች ተሳትፈዋል።ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በክልል ደረጃ ከፍተኛ የተሳታፊዎች ቁጥር እድገት የታየበት እና የፕሮግራሙን ተዳራሽነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ሆኗል።ስልጠናው ከዚህ ቀደም ሲሰጡ በነበሩት እንደ ሳተላይት ቴክኖሎጂ፣ ስፔስ እና ፕላኔታሪ ሳይንስ፣ አስትሮኖሚ እና አስትሮፊዚክስ፣ ጂ.አይ.ኤስ (GIS)፣ ድሮን (UAV)፣ ሮኬት ሳይንስ፣ ሮቦቲክስ እና ፓይተን ፕሮግራሚንግ ባሉ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በዘንድሮው ዓመት አዲስ ተጨማሪ ዋና የትምህርት ዘርፍ በመሆን "የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ (AI & Machine Learning)" መሰረታዊ እና የተጠናከረ ስልጠና በስፋት ተካቶ ተሰጥቷል።በማጠናቀቂያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ (ኢ/ር) ለታዳጊዎች ጥልቅ መልዕክት እና የማበረታቻ መልዕክት




Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 08:40

Space Science and Geospatial Institute
10 Sept, 05:56edited
ጳጉሜ 5 ቀን የነገው ቀን ======= SSGI ======= ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል።በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል!የክቡር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክትለተጨማሪ መረጃ:- የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022 Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute Telegram: https://t.me/spacegeospatial ከምድር እስከ ህዋ … SSGI


Space Science and Geospatial Institute
9 Sept, 18:22




Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
