Latest posts

The Christian News
21 Sept, 10:18
‹‹የሰብዕና ኃይል ከመለኮት ዕይታ›› በሚል ርዕስ በዶ/ር ተፈራ በላቸው የተዘጋጀ መጽሐፍ በኢገስት አዳራሽ ተመረቀ፡፡በጤናው ዘርፍ ከ34 በላይ በሳይንሳዊ መንገድ የተገመገሙ የምርምር ጽሑፎችን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያበረከቱትና በደቡብና በምስራቅ አፍሪካ ማዕከል አድርጎ ለሚሠራው ተቋም የቀጠና ዳይሬክተር በመሆን እየሠሩ የሚገኙት መጋቢ ዶ/ር ተፈራ በላቸው ሁለተኛ መጽሐፋቸውን እነሆ ብለዋል፡፡የእንኳን ደኅና መጣችሁ ንግግር በማድረግና የመክፈቻ ጸሎት በማድረግ ፕሮግራሙን መጋቢ ሳምሶን ስምዖን ጀምረዋል፡፡በአገር ውስጥ የሌሉት የጸሐፊው ባለቤትና ልጆቹ የእንኳን ደስ አለህ መልእክታቸውን በተቀረጸ ድምፅ ያሰሙ ሲሆን የጸሐፊው የቅርብ ቤተሰቦችም ደስታቸውን እንዲሁ ገልጸዋል፡፡መጽሐፉ ከቤተሰብ፣ ከቤተ ክርስቲያን፣ ከመሪነትና ከትዳር አንጻር ዳሰሳ የተደረገ በአቶ ሹምዬ፣ በወ/ሮ ብርክታዊት፣ በወ/ሮ ዮዲትና በዶ/ር መስፍን በስፋት ቀርቧል፡፡‹‹የሰብዕና ኃይል ከመለኮት ዕይታ›› ደራሲ ዶ/ር ተፈራ በላቸው መጽሐፉ ችግር የወለደው ለመፍትሔ አጋዥ ነው በማለት መጽሐፉ በተለያዩ ቦታዎች በስልጠና መልክ የተሰጠ የነበረና በብዙዎች ጥያቄ ወደ መጽሐፍ እንደተቀየረ አክለዋል፡፡መጽሐፉ በስምንት ምዕራፎች የተቀነበበና ስለ ሰብዕና ምንነት ስለ ሰብዕና ግንዛቤና ስለ ሰብዕና ዐይነቶችና ስብዕናን ከክርስቶስ ልብ ስለ ማስማማት በሚሉና በሌሎች ተጓዳኝ ርዕሶች ዙርያ ሰፊ ማብራሪያን ሳይንሱንና መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሳይበርዝ የቀረበ ነው፡፡ መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዘኛ በአንድ መድብል ሆኖ መቅረቡ ደግሞ ለየት


The Christian News
12 Sept, 20:12
🔴#ቀጥታ ስርጭት l ከአዲስ አበባ እስታድየም l ልዩ የአዲስ አመት ፕሮግራም l ተከስተ ጌትነት እና ዳንኤል አምደሚካኤልhttps://www.youtube.com/watch?v=lkvUTtdatCkYouTubeWelcome to Our channel This is The Christian News from Ethiopia if you subscribe Our channel you get more benefits. news, blogging , information, vine ... all Entertainment are available in Our channel subscribe now Thanks For Watching. LIKE, SHARE &…
The Christian News
11 Sept, 14:49
"አዲስ ዓመት ራሳችንን የምንመለከትበት ነዉ" ቄስ ዮናስ ይገዙየ2018 ዓመተ ምሕረትን በሰላም አሳልፈን ዛሬ ወደ 2019 ዓመተ ምሕረት መድረሳችን የራሳችን ብርታትና ጥበብ ውጤት አይደለም።በዓመቱ ውስጥ ደስታና ሐዘን፣ ስኬትና ፈተና፣ ትርፍና ኪሳራ፣ ተስፋና ተስፋ መቁረጥ እና ይህን የሚመስሉ የተለያዩ ገጽታዎችን አሳልፈናል።አንዳንዶቻችን የምንወዳቸውን ሰዎች አጥተናል፤ ሌሎች ደግሞ በአዳዲስ ዕድሎች ተባርከናል። በእነዚህ ሁሉ መካከል ግን እግዚአብሔር ጠብቆናል፣ መርቶናል፣ አጽንቶናል፡፡በመሆኑም፣ እስከ ዛሬ ድረስ በነገር ሁሉ የረዳንና የጠበቀንን አምላካችን እግዚአብሔርን እያመሰገንን፣ እንኳን ለአዲሱ ዓመት ለ2019 ዓመተ ምሕረት በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ:: በዚህም አጋጣሚ፣ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና በራሴ ስም ለሁላችሁም ያለኝን መልካም ምኞት ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።አዲስ ዓመት ማለት የቀን መቀየር ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ ዓመት ራሳችንን የምንመለከትበት፣ ያለፈውን የምንገመግምበት፣ የተሳሳትነውን የምናርምበት፣ ያለንን ጥንካሬ የምናስቀጥልበትና ለሚመጣው ዘመን አዲስ ራዕይና አቅጣጫ የምንይዝበት ጊዜ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው፣ “ያለፈው ዓመት እንዴት ነበር? ምን አደረግሁ? ምን ተማርኩ? ምን ተሳካልኝ? የቱጋ ወደቅሁ? ምን ማስተካከል አለብኝ?'' ብሎ ራሱን ሊጠይቅ ይገባል፡፡ሙሉ መልዕክቱን ለመስማት ሊንኩን ይጠቀሙ https://youtu.be/4e8VrXLyN98


The Christian News
11 Sept, 09:31
ቀጥታ ከአዲስ አበባ እስታድየም የአዲስ አመት ልዩ ፕሮግራም https://www.youtube.com/live/dfzAUaxbxHQ?si=NAuELDS5lTE7JTXtYouTube#gospel #billy #thechristiannews #singer #jesus #jesuschrist #መልካም በዓል #marsiltvworldwide #yonatanaklilu #abiye #ebc #fana_tv #ebs #reels #saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopia #ethiopiantvshow #saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopianews #ethiopiantvshow…
The Christian News
11 Sept, 05:49
https://www.youtube.com/watch?v=3iYbN95mR4gYouTube🔴 #ቀጥታ ስርጭት / 🔴 #ቀጥታ ስርጭት / 🔴 #ቀጥታ ስርጭት / ከአዲስ አበባ እስታድየም / ልዩ የአዲስ አመት ፕሮግራም Welcome to Our channel This is The Christian News from Ethiopia if you subscribe Our channel you get more benefits. news, blogging , information, vine ... all Entertainment…
The Christian News
10 Sept, 15:07
ካውንስሉ መግለጫ ሰጥቷል። ሙሉ ዝርዝሩን ይመልከቱ https://youtu.be/Eqxb2um_v0wYouTubeካውንስሉ መግለጫ ሰጥቷል። ሙሉ ዝርዝሩን ይመልከቱወዳችሁ እና ፈቅዳችሁ ስለምትመለከቱን ከልብ እናመሰግናለን!!! Like, Share ማድረጎን አይርሱ!! #በ0930699543_ማንኛውንም_አይነት_የክርስቲያን_መረጃዎችን_በቴሌግራም_ለክርስቲያን_ዜና_ሚዲያ_መጠቆም_ይችላሉ #The_Christian_News Welcome to Our channel This is The Christian News from Ethiopia if you subscribe Our channel you…
The Christian News
9 Sept, 17:35
በአዲስ አበባ እስታድየም ልዩ የአዲስ አመት መረሃ ግብር መስከረም 1/2019ዓ.ም#እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። እነሆ አዲስ ነገር አደርጋለሁ እርሱም አሁን ይበቅላል። ኢሳ 43፤19የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ አርብ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የምሥጋና የአምልኮና የጸሎት መርሐግብር አዘጋጅቷል።ከማለዳው 12፡00 እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰአት በሚቆየው በዚህ መርሐግብር ላይ ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና ፓስተር ስለሺ ክንፉ ዘማሪ ፓስተር ዳንኤል አምደሚካኤል እና የተለያዩ አገልግዮች አብረውን ይኖራሉ።እግዚአብሔርን ከፍ በማድረግ ወደምንዘልቅበት ወደዚህ የአዲስ አመት መቀበያ መርሐግብር ላይ ወዳጆቻችንን በመጋበዝ ትገኙ ዘንድ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጥሪውን ያቀርባል።በከከተማ እና ከሀገር ዉጪ ላላችሁ በእለቱ የቀጥታ ስርጭቱን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። You tube;- https://www.youtube.com/@ECFEMedia-et


The Christian News
8 Sept, 19:13edited
#በጎ አድራጎት ሰዎችን በፍቅር የሚያስተሳስር ተግባር መሆኑ ተገለጸ።የሆሳዕና ከተማ ካባ ጨፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን #አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ65 አቅመ ደካሞች ከ785 ሺህ 830 ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስና የምግብ ድጋፍ አድርጋለች።የቤተ ክርስቲያኗ የፍቅርና ርኅራኄ አገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪ ወንጌላዊ ዘውዴ ተመስገን እንደገለጹት፤ ዘርፉ ለአቅመ ደካሞች የምግብ፣ የአልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁስና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።አገልግሎቱ ከተጀመረበት ከሁለት ዓመት በፊት አንስቶ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆሙት አስተባባሪው፣ ለአብነትም ለ16 ሰዎች መነሻ ገንዘብ በመስጠት የራሳቸውን ንግድ እንዲጀምሩ ማስቻሉን አብራርተዋል።አገልግሎቱ በቋሚነት 65 ሰዎችን እንደሚደግፍ የጠቆሙት ወንጌላዊ ዘውዴ፤ በዘንድሮው የአዲስ ዓመት ድጋፍም ዘይት፣ አልባሳት፣ ዱቄት፣ ጋቢ፣ ብርድ ልብስና የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች መካተታቸውንና አጠቃላይ ወጪውም 785 ሺህ 830 ብር መሆኑን ገልጸዋል።የሆሳዕና ካባ ጨፌ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ሰብሳቢ አቶ መለሰ ሚሽቆ በበኩላቸው፤ የድጋፉ ዋና ዓላማ አቅመ ደካሞች በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ ማስቻል እንደሆነ ተናግረዋል።ድጋፉ በበዓላት ብቻ የተገደበ አለመሆኑን የጠቆሙት ሰብሳቢው፤ የትምህርት ቤት ወርሃዊ ክፍያ፣ የቤት ኪራይ፣ እንዲሁም ቤት የማስገንባት ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው በቀጣይም የድጋፉን መጠንና የተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ ታቅዷል ብለዋል።ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ Facebook


The Christian News
7 Sept, 18:55
የ6ኪሎ ጉባኤ #እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የማረሚያ ቤት አገልግሎት በዝዋይ (ባቱ) ለሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤት የወንጌል ስርጭት አካሄደ።በአመት ሶስት ጊዜ በመደበኛነት የወንጌል ስርጭቶችን የሚያካሂደው የ6 ኪሎ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የማረሚያ ቤት አገልግሎት ከሌሎች አብያተክርስቲያናት ከተወጣጡ አገልጋዮች ጋር በመሆን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ በዝዋይ የክልሉ ማረሚያ ቤት ባዘጋጀው የወንጌል ስርጭት ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወንጌልን ሰምተው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተቀላቅለዋል።በዕለቱም የአምልኮ፣ የቃል እና የስጦታ እንዲሁም የማረሚያ ቤት ጉብኝት የተካሄደም ሲሆን በማረሚያ ቤቱ ለምትገኘው ቤተክርስቲያን የወንበር፣ የምንጣፍ፣ የመብራት አንፖል፣ የአልባሳት፣ የሴፍቲ ታንከር እንዲሁም ልዩ ልዩ ድጋፎች ተበርክቶላቸዋል።በዝዋይ ባቱ ለሚገኘው ማረሚያ ቤት ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ድጋፍ መደረጉን የገለፁት የማረሚያ ቤቱ አዛዥ ኮማንደር ኡርጌ ፋዬ የቤተክርስቲያኒቱ የማረሚያ ቤት አገልግሎት በተደጋጋሚ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በቀጣይም የማረሚያ ቤቱ አገልግሎት አስተባባሪ የሆነው ወንድም አዲስ በቀለ የማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጿል ሲል Gmm tv Ethiopia ዘግቧል።


The Christian News
5 Sept, 17:52
እንኳን አደረሳችሁ አዲስ አበባ እስታድየም እንገናኝ https://www.youtube.com/watch?v=ZgSge2OoyHM&t=218sYouTubeአዲስ አበባ እስታድየም "ልዩ የአዲስ አመት" መረሃ ግብር l ECFE MEDIAአዲስ አበባ እስታድየም "ልዩ የአዲስ አመት" መረሃ ግብር l ECFE MEDIA #ይህ #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የሚዲያ ገጽ ነው። Thanks For Watching Follow us on Facebook ;- Telegeram ;- Tiktok;- LIKE, SHARE & SUBSCRIBE For More Videos!
The Christian News
5 Sept, 17:44
"ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ የሚለውን ሃሳብ በተግባር ያሳየ ስራ ነው" ፓስተር ጻዲቁ አብዶየቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት እና የሰርክል ተቋም ሃላፊ የሆኑት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ይህንን ያሉት "ቶሎ ና" የተሰኘው የዝማሬ የአልበም ምርቃትና ለ365 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት መዝጊያ መረሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።ቦሌ በሚገኘው በዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን እየተከናወነ በሚገኘው መረሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ፓስተር ጻዲቁ ዘመኑን በዋጀው ዲጅታል ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ለመዋጀት እህት ትዕግስት እጅጉ የሰራችውን ስራ አድንቀዋል።ዘመኑ ክፉ ሆኖ ፍጻሜው በቀረበበት በዚህ ሰዓት የክርስቶስን ምጽዓት እንድንናፍቅ የሚያደርግ እና እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎን እንዳንተኛ ክርስቶስ መምጫው በደጅ ነውና "ቶሎ ና" የተሰኘውን ዝማሬ በማዘጋጀቷ አመስግነዋል።


The Christian News
5 Sept, 14:29
አራተኛው የሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት በመካኼድ ላይ ይገኛል።በአራተኛው የሕንጸት የመጻሕፍት ዕውቅና ሥነ ሥርዐት በፓስተር ጻዲቁ አብዶ ተጽፎ የቀረበው "በቀል በቀለኛን ያጠፋል" የተሰኘው መጽሀፍ በነገረ መለኮት ዘርፍ፥ በስልታዊ ነገረ መለኮት ንዑስ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም ተሸላሚ ሆኗል።በመንፈሳዊ እድገት ዘርፍ የ2018 ዓ.ም. ተሸላሚ መጽሐፍ በበርናባስ ዘመነ የተዘጋጀው "ወንጌል ይዘቱና አቀራረቡ" የተሰኘው መጽሀፍ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን በታሪክ ዘርፍ በዮናስ ጎርፌ ተጽፎ የቀረበው "ፕሮቴስታንታዊያን በኢትዮጵያ ፖለቲካ" የተሰኘው መጽሐፍ የ2018 ዓ.ም. ተሸላሚ መጽሐፍ ሆኗል።በአራተኛው የሕንጸት የመጻሕፍት ዕውቅና ሥነ ሥርዐት በፈጠራ ሥራ ዘርፍ፥ በኢ-ልብ ወለዳዊ ዘውግ በግለ ታሪክ ንዑስ ዘርፍ ደግሞ በዶ/ር ንጉሴ ተፈራ የተጻፈው "ዞር ብዬ ሳየው" የሚል ርዕስ ያለው ግለ ታሪክ መጽሀፍ የ2018 ዓ.ም. ተሸላሚ መጽሐፍ ሆኗል።በፈጠራ ሥራ ዘርፍ፥ በልብ ወለድ ንዑስ ዘርፍ "በታችም በምድር" በሌሎሳ ግርማ ተሸልሟል። በወጣት ሀንኤል ኩረማ የተዘጋጀው "የእብራውያን መልዕክት ማብራርያ" በነገረ መለኮት ዘርፍ፥ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት ንዑስ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም. ተሸላሚ መጽሀፍ ነው።በነገረ መለኮት ዘርፍ፥ በተግባራዊ ነገረ መለኮት ንዑስ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም. ተሸላሚ መጽሐፍ ደግሞ በመጋቢ ሰለሞን አበበ የተጻፈው "ድፍርስ ጅረቶች" ደሃም ስም አለው የተሰኘው እና በቅርብ ጊዜ ለንባብ የበቃው መጽሀፍ ነው።አራተኛው የሕንጸት የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት አሁንም በETC


The Christian News
4 Sept, 17:39
#አዲስ #ዜና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከአለምአቀፍ ሜኖናይት ኮንፍረንስ (MWC) መውጣቷን አሳወቀች።የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እያካሄደች በምትገኘው 95ኛው ጠቅላላ መሪዎች ጉባኤ ከአለምአቀፍ ሜኖናይት ኮንፍረንስ (Mennonite World Conference /MWC) ለመውጣት ውሳኔ አሳልፋለች።በጉባኤው ቤተክርስቲያኒቱ ላለፉት 59 አመታት በዚህ ተቋም ውስጥ የነበራት ተሳትፎና ግንኙነት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ከዚህ ጥናት ጋር የቤተ ክርስቲያኒቱ ስነመለኮት ኮምሽን ያዘጋጀው ምክረሃሳብም ተካቷል።በዚህ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤው በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ (መአመጉ) የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በመቀበል ቤተክርስቲያኒቱ አባል ሆና ለ59 አመታት ከቆየችበት የሜኖናይት አለምአቀፍ ኮንፍረንስ (MWC) እንድትወጣ አጽድቋል።የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከተቋሙ ጋር ምንም እንኳን የገንዘብና የሥራ ግንኙነት ባይኖራትም በዚህ ግብረሰዶማዊነትን በአካታችነት በተቀበለ ተቋም ውስጥ አባል በመሆኗ ምክንያት ላለፉት ወራት ስሟ በተለያየ መንገድ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተገናኘ የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር በቀጣይ ማብራሪያ የሚሰጥ እንደሆነም አሳውቀዋል።በቤተክርስቲያኒቱ 95ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ጨምሮ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት ፕሬዝዳንቶች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።በተጨማሪም የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን


The Christian News
4 Sept, 08:56edited
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የ2018 ዓ.ም የልጆች በዓል ሳምንት በተለያዩ ማኅበረ ምዕመናን በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።የዘንድሮው የልጆች በዓል ሳምንት፣ በምሳሌ 22፥6፣ “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሪ ጥቅስ በመያዝ፣“ ጠንካራ ቤተሰብ፦ ስኬታማ ትውልድ” በሚል መሪ ርዕስ ተከብሯል።በአንድ ሳምንት የተከበረው ይህ በዓል፣ ልጆች በጸሎት፣ በአካባቢ ጽዳት፣ በስፖርታዊ ጨዋታዎችና ውድድሮች፣ እንዲሁም በተለያዩ የሥነ-ጽሑፍ አገልግሎቶች እንዲሳተፉ በማድረግ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የልጆችና ወላጆች የጋራ ቀን ተካሂዶ፣ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ልጆች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመጨረሻም ሁሉን አቀፍ ኮንፈረንስ በማካሄድ የበዓሉ ሳምንት ተጠናቋል።ተጨማሪ ዜናዎችን ከFacebook ያንብቡ በቪዲዮ ዜናዎችን መከታተል ከፈለጉ በ youtube ይመልከቱ


The Christian News
4 Sept, 05:52
የባለ ትዳሮች ሴሚናር እና የቃል ኪዳን ማጽኛ መረሃ ግብር በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ ተካሄደ።በደቡብ አፍሪካ በጆሃንስበርግ የምትገኘው ወንጌል አብሳሪዎች አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በባላ ትዳሮች ላይ ያተኮረ የሶስት ቀናት ሴሚናር ተካሄደ።ከAugest 28-30/2026 በተካሄደው የባለ ትዳሮች ፕሮግራም ሰልጠናውን የሰጡት በጋብቻ ረጅም ዘመን ያሰቆጠሩት እና በተለያየ ጊዜ የጋብቻ ሴሚናር በመሰጠት የሚታወቁት ወንጌላዊት ሊዲያ ዮናሰ እና የወንጌል አብሳሪዎች ዋና መጋቢ እና የሳውዝ አፍሪካ አብያተ ክርሰትያናት ካውንሰል ፕሬዝዳንት ፖሰተር ብርሃኑ ታምሬ (ዶክተር) ናቸው።በመጀመሪያ ቀን የእግዚአብሔር ዓላማ በጋብቻ ውስጥ ከሚል ሀሳብ ተነስተው የባል እና የሚስት ሚና በመረዳት መተግበር፤ በውጤቱ ደስተኛ ቤተሰብ መሆን በሚል ርዕስ ሰልጠና ተሰጥቷል።ሁለተኛ ቀን ከሁለቱም ወገን ከባሎችና ሚስቶች ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶ፡ በተተኪ ትውልድ ባለድርሻነት፤ በሚል አምስት ባለ ድርሻ አካላት ተጠቅሶ ማብራሪያ በጥልቀት የተሰጠ ሲሆን ባለድርሻ አካላት በቅድሚያ ቤተሰብ፤ ሲቀጥል ቤተክርስቲያን፤ ትምህርት ቤት፤ መንግስት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በሚለው ቅደም ተከተል ተጠቅሰዋል።እነዚህ ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን ካልተወጡ ከቤተሰብ አንስቶ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው በሴሚናሪው አስገንዘበዋል።ሴሚናሩ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ባደረገ መነሻ ሁሉን የሰው ልጅ መስተጋብር የዳሰሰ ሲሆን ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊና ዘመናዊ የሥልጣኔ


The Christian News
2 Sept, 14:20
#ድንቅ የአምልኮ ምሽት 🔥🔥3ቀን ብቻ ቀረ! 🔥መዝሙር 150:6 6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።"ሃሌሉያ! ሃሌሉያ! ሃሌሉያ!" እያልን በጋራ ጌታን የምናመልከበት ልዩ የአምልኮ ምሽት ተዘጋጅቷል።🗓 ቅዳሜ ነሐሴ 30📍 አያት መካነኢየሱስየአያት መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምእመናን Ayat Mekane Yesus Churchhttps://maps.app.goo.gl/GYStjnDUYLPN5Ln88ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመሆን የዚህ ድንቅ ምሽት ተካፋይ ይሁኑ


The Christian News
2 Sept, 13:56
በሚዛን መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ኮምፓሽን ፕሮጀክት ለደሀ ደሀ ተማሪዎችና ወላጆች የአዲስ አመት መዋያ ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ፕሮጀክቱ ለ216 የደሀ ደሀ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ2ሺ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል።በሚዛን መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኢቲ - 3002 የህጻናትና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ዘገየ እንደገለጹት ቤተክርስቲያኗ ከኮምፓሽን ፕሮጀክት በምታገኘው የገንዘብ ድጋፍ በመደበኛ ተግባር 216 የደሀ ደሀ ቤተሰብ ተማሪዎችን የምግብ፣ የአልባሳትና የትምህርት ቁሳቁስ ወጪን በመሸፈን እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።የዛሬው ድጋፍ አዲስ አመትን ከክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ 1 ሚሊየን 813ሺ ብር ወጪ በማድረግ ጤፍ ፣ ዘይት ፣ አልባሳት ፣ ደብተር ፣ እስክሪብቶ ፣ እርሳስና ሳሙና ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።ቤተክርስቲያኗ ከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር የእምነት ፣ የብሔርና የቀለም ልዩነት ሳታደርግ የደሀ ደሀ ቤተሰብ ተማሪዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ እየሰራች መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተሾመ በቀጣይ ሳምንት የዚሁ ድጋፍ አካል የሆነው የአልባሳት ስርጭት እንደሚደረግም ገልጸዋል።አሁን ላይ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ2ሺ በላይ የተማሪ ቤተሰቦችን አቅፎ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ባለሙያ ወይዘሮ ደብሪቱ ሀይሉ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ 216 ህጻናትና


The Christian News
2 Sept, 11:31
#ቶሎ ና 🔥🔥🔥 ደረሰ ደረሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ግማሽ አልበም 🔥🔥የእህታችን አገልጋይ ትዕግሥት እጅጉ ቶሎ ና የተሰኘው የክርስቶስን ምፅአት እንድንናፍቅ የሚያስታውሰን ኢየሱስን የሚሰብከን ቶሎ ና የተሰኘ ኢፒ (ግማሽ አልበም) የፊታችን ነሀሴ 30 ቅዳሜ ቀን ከ8:30 ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።በእለቱ የእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም ዝማሬ ይቀርባል።ሁላችሁም ተጋብዛችኋል 🔥🙏🔥🙏


The Christian News
2 Sept, 10:38
"15 ዓመታትን ስለሰላም እየሰራን ተጉዘናል" የሃይማኖት ተቋማትየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የምስረታ 15ኛ ዓመት እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናውኗል።በእስካይ ላይት ሆቴል በነበረው በመረሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ አመራሮችና የክልል ጉባኤ አመራሮች ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።"15 ዓመታት እምነትን በቀጣይነት፣ ሰላምን ህብረብሔራዊ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ባለው መረሃ ግብር በክብር እንግዳነት የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለ15 ዓመታት ያካሄደው የጋራ ጉዞ በእምነት ተቋማት ትብብርን በማጠናከር፣ ሰላምንና ማህበራዊ ውህደትን በማሳደግ ለሀገራዊ እድገትና ልማት ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው የጋራ ሀብታችን የሆነው ሰላም መጠበቅ እና ማበልጸግ የሚቻለው ሁላችንም ኃላፊነታችንን መወጣት ስንችል ነው ያሉ ሲሆን ሁላችንም ባለንበት አካባቢ እና ተቋም ውስጥ ለሰላም ግንባታ አስተዋጽኦ በማበርከት የሰላም ምሳሌ በመሆን ሰላምን ልናጸና ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የሃይማኖት ተቋማት የሀገራችንን ሰላምና አብሮነት ላይ ላለፉት አስራ አምስት አመታት በመስራት ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡን የተናገሩት ደግሞ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር


The Christian News
30 Aug, 06:18
ሟች እራት ላይ ተገኘ።🍔 🍔 🍔ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜበZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ በወንድም ተመስገን ነጋሽ በZadok Perth Youtube የሚቀርብ ተከታታይ የመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርትሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
