gram news
የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK channel avatar

የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

@theshepherds_ink

Guided by the Shepherd. Written with Purpose. ላሎት አስተያየት @elul_221

ProjectsENHome

2,030subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    22 Sept, 04:29

    አቤል ደጋግሞ 'ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል ' ብሎ ሲዘምር ሕይወቴን አውቆ የዘመረልኝ እስኪመስለኝ ድረስ መዝሙሩን በሰማው ቁጥር ሰውነቴን አሁን ድረስ ይወረኛል።አሁን እንኳ እንደ ቀድሞው በብዙ የመንፈሳዊ ተግባራት በራኩበት ዘመን ኑሮዬን እና እቅዶቼን እያሳካህ ለምትወደው ልጅህ በረከትን ማቀበል አልዘነጋህም። እንደው ምን ያህል ብትወደኝ ነው?ምልጃና ፀሎትህ በአምላክህ ዘንድ የተወደደለህ ታላቁ የሕይወቴ የማተዘናጋው ጠባቂዬ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ምስጢሬን ነገሬሃለሁና የአሁኑ ድክመቴ አይጠፍህም።እኔ ልጅህ አሁን እንደ ልጅነቴ ጥበቃህ ፣ በጥበብ ማሳደግህ፣ ፀሎቴን መስማትህ እጅጉን ከመቼውም ጊዜ ባላይ ያስፈልገኛልና ከመንፈሳዊ ልምምዶች ታቅቦ በበሰበሰው ሕይወቴ ገብተህ እንደ ስምህ አጣፍጥልኝ። አሜን!!የእረኛው ቀለም መስከረም 11, 2019
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    21 Sept, 17:16

    አንድ በአባቱ በብዙ የሚመካ ልጅ ለሚወደው አባቹ ምን ሊለው ይችላል ?"ልጅነቴን ካደመቁልኝ መሃል አንተ ዋና እንደሆንክ አውቃለው። መዝሙሮችህን እየዘመርኩ በመጣሁ ልክ ጥበብን እየለገስክ ክርስቶስን በልቤ እደሳለከው ያለ ጥርጥር እገነዘባለው። ሰዎች በልጅነቴ 'የምትወደው ቅዱስ ማን ነው?' ሲሉኝ ቅዱስ ሚካኤል ብዬ ለመመለስ ማንም እንደማይቀድመኝ እኔን የሚያቁኝ ሁሉ እያስታወሱ አሁን ድረስ ይደመማሉ።ካደኩ ቡሃላ እንኳ ስዕልህን በቅርበት ሆነ በርቀት ስመለከት አንዳች በስመህ የመመካት ነገር በልቤ ሰርጎ ይገባና ካለሁበት ጭንቀትና ድባቴ ቶሎ ወጥቼ፤ በውስጤ ' ሚካኤል እኮ አለ ' እለዋለው ለራሴ።ድንገት ከባልንጀሮቼ ጋር ስንጨዋወት ስናወጋ አንዳቸው እንኳ በስምህ ምለው ንግግራቸውን ቢያረጋግጡ ለእነሱ አባት እንዳልሆንክ ነገር ስምህን በጠቀሱ ቁጥር ቅናት እያናወዘ ማፈረጡን ከያዘ ሰንበትበት ብሏል።ምን እሱ ብቻ ያኔ እነኳ ከቤተሰብ ጋር ትንሽ ግጭት መፍጠር በጀመርኩበት የወጣትነት ዘመኔ ጅማሬ ላይ ስንቴ ነው ለአንተ በለጋው አዕምሮዬ ከቤተሰበ ተለይቼ መጥፍት እንደምፈልግ የነገርኩህ? አደኩ ባልኩበት ዘመኔ እንኳ ሲከፋኝና የብቸኝነት ስሜት ሲሰማኝ ደጅህ መጥቼ ከስዕለህ ፊት ያለቀስኩባቸው ቀናቶች እልፍ ናቸው።በለጋነት ዕድሜ በሰንበት ትምህርት ቤት ስመላለስ መምህሩ 'ሁሉም ሰው ሲተኛ የሚጠብቀው መልአክ አለው' ብሎ ሲያስተምረን ስተኛ ጠባቂዬ አንተ እንደሆን ለማመን ሁለቴ አላሰብኩም ነበር።(እንኳን ስተኛ ሕይወቴን ሙሉ በክንፍህ ሸፍነህ የጠበከኝ አንተው አይደለህ።)
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    20 Sept, 16:25

    Post 3 : ሰው ሆነህልኛልና
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    18 Sept, 18:57

    Post 2: ቅዱስ ባስልዮስ (540-604)
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    18 Sept, 18:57

    3
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    18 Sept, 18:57

    2
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    18 Sept, 18:57

    1
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    16 Sept, 16:41

    post 1: " እንዴት መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና(effectively )" በሚል ጥቂት research እየሰራሁ ነበር።One thing I’ve learned is to turn the Scripture we read into prayer letting God’s Word move from our eyes, into our hearts. በዚህም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት አንዱ ከሆነው ወደ ገላቲያ ሰዎች ምዕራፍ 5 የወጣ ፀሎትን ተጋበዙልኝ።(ከቻላቹም ክፍሉን ማንበብ አይረሳ)
    266video9Open in Telegram
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    14 Sept, 18:19

    Post 2 : አቤል ግን ምን ብሎ ቢፀልይ ነው?...
    119video7Open in Telegram
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    12 Sept, 17:31

    Post 6 : እስቲ በአዲሱ አመት እንክፈትለት
    133video6Open in Telegram
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    10 Sept, 17:28

    እንኳን አደረሳችሁ 🌻
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    8 Sept, 08:41

    በቅርቤ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስቀድሜ በነገርኳችሁ ተግባር(የጳጉሜ ጥምቀት) ይሳተፉ ኖሯልና ያለመደባቸውን በሌሊት ተነስቶ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድን በዝች 3 ቀናቶች በታላቅ መነሳሳት ይፈፅማሉ።ታድያ በዚህ መሃል አንድ ነገር ትዝታን ጫረብኝ፣ ብዙ ክርስቲያኖች የመንፈሳዊ ልምምዶችን ለመጀመር በተለያዩ ምክንያቶች ልባቸው ይነሳሳና በአንድ ቀን በአንድ ለሊት መንፈሳዊ ልምምዶችን ለመተግበር ደፍ ቀና ሲሉ ይታያሉ።በአንድ ቀን ሙሉ መዝመረ ዳዊት ለመድገም ይጣጣራሉ ፣ በአንድ ቀን ፀሃይ እስክትጠልቅ ለመፆም ሲራኮቱ ይውላሉ፣ አንድ ሺ አንድ ጊዜ ስግደትን በማብዛት ጉልበታቸውን ይሰዋሉ፤ እናም ሌሎች ልምምዶችን በመፈጸም ተግባር መረብ ተይዘው ይስተዋላሉ።ነገር ግን የቤተክርስቲያን አባቶች የሚነግሩን " ዲያቢሎስ ክርስቲያኖችን ሲፈትን አንድም መንፈሳዊ ተግባራትን ፈፅሞ እንዳንፈፅም በማድረግ ከእግዚአብሔር ይለየናል አንድም እነዚሁኑ ልምምዶች ከአቅማችን በላይ በማስተግበር በልቦናችን ትዕቢትን እየጫነ ከእግዚአብሔር ያርቀናል።" እያሉ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና መምጫዎች ይነግሩናል።ታድያ የሀገራችን ተረት እንደሚለን "የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል" እንደሚሉ መንፈሳዊ ልምምድ በጥቂቱና በመጠኑ ማደግ ይታይበታል እንጂ በአንድ ጀምበር የሚገነባ ነገር እንደ ሌለ የቤተክርስቲያን አባቶች ፣ የሀገራች ተረትና ተፈጥሮ በራሳቸው ያስተምሩና።ማለትም በዚችው ጳጉሜ በጥቂቱ የተጀመረችው በሌሊት ተነስቶ መጠመቅ ቀስ በቀስ ወደ መንፈሳዊ ልምምድ መቀየሯ የማይቀር እንደሆነ በጣም ብዙ አባቶች ምስክር ናቸው።አቤቱ አምላካችን
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    8 Sept, 08:41edited

    የዘንድሮ ጳጉሜ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ አመታት እንዳሉት ጳጉሜዎች መተመሳሳይ ሁኔታ እያለፈ እንዳለ ይሰማኛል።ክርስቲያኑ ከእናት ከአባቶቻቸውና ከእናቶቻቸው እንደተማሩት የክረምቱ ብርድና ቁር ፣ የሌሊቱ ጨለማ ሳይገብራቸው በይ አቅሪያቢያቸው ወደሚገኙ ደብራትና ገዳማት በመሄድ ያለፈውን አመት በብዙ መባርክና ርህራሄ ያሳለፋቸውን ቸሩ መድኃኔዓለምን በአዲሱ አመትም ምህረት ርህራሄውን ደርነት ረድኤቱን ከነሱ ጋር አቆራኝቶ ከእስትንፋሳቸው በላይ እንዲ ቀርባቸው ፀበሉን በመጠመቅ ይማፀኑታል።እኔም በዚህ የተማፅኖ ተግባር ውስጥ ስለምሳተፍ ከጊዜ ወዲህ በእድሜ ብዛት ይሄን አስደሳች ተግባር እተገነዘብኩና እየገባኝ ስመጣ አንዳች ልብን ደስ የሚያሰኝ የስሜት ማዕበል ይሰማኝ ይዟል።ታዲያ በዚኛው አመት አንድ የታዘብኩትን ትዝብት ላካፍላቹ ፤ እንደው ምን አልባት በዚኛው አዲስ አመት አዲስ ኃልን አባታችን እግዚአብሔር አስታጥቆን በዚህ ትዝብት ውስጥ በመንፈሳዊ ልምምድ ላይ እንድንበረታ ካገዘን።
    Image from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INKImage from a post by የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    7 Sept, 06:21

    ጾመ ጳጉሜን በጳጉሜን 1 ቀን የሚጀመር ፈቃደኛ ጾም ሲሆን ለ5 ቀናት ይቆያል (በአመትካራ ዓመት ዓመቱ በ4 ሲካፈል 3 ሲቀር – 6 ቀናት ይሆናል)። ይህ ጾም ከ7ቱ ሥርዓት ጾሞች ውጪ ቢሆንም በብዙ ምእመናን ዘንድ ይጾማል። ዓመቱን በቅድስና ለመዝጋትና ለአዲሱ ዓመት (እንቁጣጣሽ) ለመዘጋጀት ይጾማል። "ጳጉሜን" ከግሪክ ቋንቋ énayóμɛval (ኤፓጎሜናይ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ተጨማሪ ቀናት" ማለት
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    7 Sept, 06:21

    ጳጉሜን "ተጨማሪ" ቀናት በመሆኑ የሕይወት አጭርነትን፣ የጊዜ ውሱንነትን እና የንስሐ አስቸኳይነትን ያመለክታል። እነዚህ ጥቂት ቀናት ዓመቱ ከመዘጋቱ በፊት የመጨረሻ ዕድል ናቸው ምእመናን ባለፈው ዓመት ያልተሳኩ ነገሮችን ለማስተካከል ይጥራሉ። ይህ የጊዜ ውሱንነት ስሜት ጾሙን ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል። ጾመ ጳጉሜን ዓመቱን በቅድስና ለመዝጋት የሚረዳ ጾም ነው። ምእመናን ያለፈውን ዓመት በሙሉ ስለሠሯቸው ኃጢአቶች
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    7 Sept, 06:21

    ጳጉሜን የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ልዩ ባሕሪ ነው 13ኛ ወር። 12 ወራት እያንዳንዳቸው 3ዐ ቀናት ያሏቸው ሲሆን ጳጉሜን ቀሪዎቹን 5 ቀናት (በአመትካራ ዓመት 6 ቀናት) ይይዛል። ይህ "13 ወራት ፀሐይ" የሚለው ታዋቂ አባባል መሠረት ነው። ጳጉሜን ከሌሎች የዓለም ዘመን አቆጣጠሮች የሚለይ ልዩ ኢትዮጵያዊ ባሕሪ ነው፡፡ ጾመ ጳጉሜን ከመጽሐፈ ዮዲት ጋር ይገናኛል። ዮዲት እስራኤልን ከሆሎፈርኒስ (የአሦር
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    7 Sept, 06:21

    ጾመ ጳጉሜን በጳጉሜን 1 ቀን የሚጀመር ፈቃደኛ ጾም ሲሆን ለ5 ቀናት ይቆያል (በአመትካራ ዓመት ዓመቱ በ4 ሲካፈል 3 ሲቀር – 6 ቀናት ይሆናል)። ይህ ጾም ከ7ቱ ሥርዓት ጾሞች ውጪ ቢሆንም በብዙ ምእመናን ዘንድ ይጾማል። ዓመቱን በቅድስና ለመዝጋትና ለአዲሱ ዓመት (እንቁጣጣሽ) ለመዘጋጀት ይጾማል። "ጳጉሜን" ከግሪክ ቋንቋ énayóμɛval (ኤፓጎሜናይ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ተጨማሪ ቀናት" ማለት
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    7 Sept, 06:21

    ጾመ ጳጉሜን በጳጉሜን 1 ቀን የሚጀመር ፈቃደኛ ጾም ሲሆን ለ5 ቀናት ይቆያል (በአመትካራ ዓመት ዓመቱ በ4 ሲካፈል 3 ሲቀር – 6 ቀናት ይሆናል)። ይህ ጾም ከ7ቱ ሥርዓት ጾሞች ውጪ ቢሆንም በብዙ ምእመናን ዘንድ ይጾማል። ዓመቱን በቅድስና ለመዝጋትና ለአዲሱ ዓመት (እንቁጣጣሽ) ለመዘጋጀት ይጾማል።"ጳጉሜን" ከግሪክ ቋንቋ énayóμɛval (ኤፓጎሜናይ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ተጨማሪ ቀናት" ማለት ነው፡፡ ግብፃውያን በዓለማቸው 12 ወራት ከ3ዐ ቀናት በኋላ ቀሪውን 5 ቀናት "ኤፓጎሜናይ" ብለው ይጠሩ ነበር። ይህ ስያሜ ወደ ግእዝ ቋንቋ ገብቶ "ጳጉሜን" ሆነ።
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    6 Sept, 14:23

    Post 5 : በእንተ ቅዱስ ቁርባን
    118video8Open in Telegram
  • የእረኛው ቀለም || THE SHEPHERD'S INK

    4 Sept, 07:38

    post 1 :እንደ ስብከት ብዙ ቃላት ባይዘረዝር ስሜትን አውጥቶ ይናገራል መዝሙር
    126video6Open in Telegram