Latest posts

ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
21 Sept, 13:42
በጋምቤላ የቱሪስቶች መረጃ ማዕከል እና የወጣቶች መዝናኛ ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ርክክብ ተደረገ፤መስከረም 11/2019 ዓ.ም. ጋምቤላ፤የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግና የመሰረተ ልማት ክፍተቶችን ለመፍታት ታሳቢ ያደረገ የቱሪስቶች መረጃ ማዕከል እና የወጣቶች መዝናኛ ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ርክክብ አደረገ። የጋምቤላ ክልል መንግሥት ፕሬዚዳንት ክብርት ዓለሚቱ ዑመድ እና የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ በተገኙበት፤ በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በክልላሉ ቱሪዝም ቢሮ እና በተቋራጭ ድርጅቱ መካከል የሥራ ርክክብ ተከናውኗል ።የክልሉ ፕሬዚዳንት ክብርት ዓለሚቱ ዑመድ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ በቀረበው የፕሮጀክት ዲዛይን መሠረት ግንባታው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር፣ ለረጅም ጊዜ ህልም ሆኖ የቆየውን የልማት ጥያቄ ወደ ሥራ የሚያስገባ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡንና ጎብኚዎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመው፣ በቀጣይ ለስኬታማነቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ ለጎብኚዎችና ለአካባቢው ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲሁም በስፍራው ያሉ (ነባር) ግንባታዎችን ከአዲሱ ማዕከልና ፓርክ ጋር አጣጥሞ ለመስራት ታስቦ የተቀረጸ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ይህ ፕሮጀክት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ከያዛቸው በርካታ የልማት ሥራዎች መካከል አንዱና ዋነኛው




ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
19 Sept, 18:09
እንኳን ለወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ‘ጊፋታ’ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!‘ጊፋታ’ በወላይታ ቋንቋ “መሻገር”— ከአሮጌው ወደ አዲሱ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያመላክት፣ የወደፊቱን በተስፋና በደስታ የሚቀበሉበት ታላቅ የህዝቦች ባህላዊና ታሪካዊ በዓል ነው። ጊፋታ የእርቅ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የደስታ እንዲሁም የመረዳዳትና የመከባበር እሴቶች በጉልህ የሚንጸባረቁበት ደማቅ ኩራታችን ነው።ባለፈው ዓመት በ2018 ዓ.ም (2025 G.C.) በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ (Intangible Cultural Heritage) ሆኖ የተመዘገበው ይህ ድንቅ በዓል፣ ትውልድን ከትውልድ ጋር የሚያስተስር ጥልቅ የህዝቦች መስተጋብር በመሆኑ የመላው ዓለም የጋራ ሀብት ለመሆን በቅቷል።የቱሪዝም ሚኒስቴር ይህን የዓለም ሀብት ኢትዮጵያውያን እና የመላው ዓለም ጎብኚዎች ወደ ውቢቷ ወላይታ በማመራት የጊፋታን በዓል ከነሙሉ ባህላዊ ውበቱ ከደማቁ የ‘ጨዋታ’ እና የውዝዋዜ ትርኢቶች፣ ከባህላዊ አልባሳትና ጣፋጭ ባህላዊ ዜማዎች ጋር አብረው እንዲያከብሩና እንዲጎበኙ ጥሪውን ያቀርባል።በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ እና የብልጽግና ይሁንልን! መልካም የጊፋታ በዓል!#Gifata #UNESCO #EthiopianHeritage #VisitEthiopia #TourismEthiopia #WolaitaGifata #LandOfOrigins #UNESCOWorldHeritage




ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
19 Sept, 13:39
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ህዳሴ፣ አዳዲስ የለሙ መስህቦች እና እድሎች!በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ እውን የሆኑትና ሥራ የጀመሩት አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦች፣ የሀገሪቱን የቱሪዝም ምህዳር ከመሠረቱ በመቀየር እና በዓለም አቀፉ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ውስጥ ተወዳዳሪ፣ ማራኪና ዘመናዊ መድረክ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ የስትራቴጂክ እና የሁለንተናዊ ፋይዳ አላቸው።ለአብነት በታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሶቿ ብቻ ትታወቅ የነበረበትን ባህላዊ አሰራር በመቀየር፣ አዳዲሶቹ መስህቦች እንደ አንድነት ፓርክ፣ ወንጪና ጨበራ ጩርጩራ (ኮይሻ)፣ እንጦጦ ፓርክ፣ ቤኑና፣ ኒኢንሌ ፓልም ሎጅ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት፣ አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከላትና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ የከተማ፣ የጂኦ-ቱሪዝም፣ የጉባኤ እና የኮንፈረንስ (MICE Tourism) አማራጮችን አስፍተውታል። ይህም ሀገሪቱ ለተለያዩ የዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ፍላጎቶች (ከመዝናናት እስከ See more https://www.facebook.com/share/1GAUNmPwQ1/www.visitethiopia.et ወቅታዊ መረጃ ለማግኘትhttp://mot.gov.et https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins https://web.facebook.com/ECB.Official https://t.me/tourismethiopia t.me/ethiopialandoforigins https://x.com/pr_mot_ET?t=G498j4uRQeaui3oL1NvXmQ&s=35 https://x.com/ECBethiopia https://www.




ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
18 Sept, 18:09
የመዳረሻዎች ልማት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ!መስከረም የዘመን መለወጫ፣ የምድር መታደስና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት ልዩ ወር ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ በሚከበረው የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን፣ ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ፣ የባህልና የታሪክ ሀብቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰፊው የምታ አስተዋውቅበትና በዘርፉ የተመዘገቡ ታላላቅ ስኬቶችን የምታበስርበት ወቅት ነው።በተለይም በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አቅጣጫ ጠቋሚነትና ሀሳብ አመንጭነት የተከናወኑ የመዳረሻ ልማት ስራዎች የሀገራችንን የቱሪዝም ገፅታ በጽኑ መሰረት ላይ የገነቡና ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ከተከናወኑት የኮሪደር ልማቶችና ፓርኮች ጀምሮ በክልሎች የተገነቡት የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ሙሉ በሙሉ በመቀየር አዲስ See more https://www.facebook.com/share/1GAUNmPwQ1/www.visitethiopia.et ወቅታዊ መረጃ ለማግኘትhttp://mot.gov.et https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins https://web.facebook.com/ECB.Official https://t.me/tourismethiopia t.me/ethiopialandoforigins https://x.com/pr_mot_ET?t=G498j4uRQeaui3oL1NvXmQ&s=35 https://x.com/ECBethiopia https://www.linkedi




ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
18 Sept, 05:26
ዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት - የቱሪዝም አዲስ ቅኝት!በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ በመስከረም ወር በልዩ ልዩ ኩነቶች የሚከበረው የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በደመቀ ሁኔታ ሊከበር ዝግጅቱ ተጠናቋል። የዘንድሮው የቱሪዝም ቀን "Digital Agenda and Artificial Intelligence to Redesign Tourism" ወይም "ዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት - የቱሪዝም አዲስ ቅኝት" በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን፣ ይህም የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።See more https://www.facebook.com/share/1GAUNmPwQ1/www.visitethiopia.et ወቅታዊ መረጃ ለማግኘትhttp://mot.gov.et https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins https://web.facebook.com/ECB.Official https://t.me/tourismethiopia t.me/ethiopialandoforigins https://x.com/pr_mot_ET?t=G498j4uRQeaui3oL1NvXmQ&s=35 https://x.com/ECBethiopia https://www.linkedin.com/company/ethiopiaconventionbureau#EthiopiaLandofOriginstouris የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia


ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
16 Sept, 16:26
የውድድር ማስታወቂያ!የአለም የቱሪዝም ቀን እየተቃረበ ነው!ታዲያ ውቧን ሃገራችንን ለማስተዋወቅ የምንጠቀምበትን "ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ" (Land of Origins Ethiopia) መለያ በተለያየ የፈጠራ ስራ (በስዕል፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ፣ በጽሁፍ፣ በቅርፃ ቅርፅ ወዘተ) መግለፅ እችላለሁ ብለው ያስባሉ?አዎ ካሉ... የቱሪዝም ሚኒስቴር የፈጠራ ስራዎችን አወዳድሮ መሸለም እና ማስተዋወቅ ይፈልጋል!የስራ ማስገቢያ ጊዜ፡ እስከ መስከረም 13/2019 ዓ.ም ብቻ!የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት እና መለያውን በፈጠራ የሚገልፅ ስራዎን፦ በኢሜይል፡ info@mot.gov.et ወይም በአካል ቦሌ አካባቢ በሚገኘው የቱሪዝም ሚኒስቴር ቢሯችን ድረስ በመምጣት ማቅረብ ይችላሉ።መልካም እድል!#LandOfOrigins #Ethiopia 🇪🇹 #WorldTourismDay


ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
16 Sept, 06:43
የኢትዮጵያ ወጣት ልዑካን በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል (#WorldYouthFestival) ላይ በመገኘት የሀገራቸውን ውብ የባህል ሀብት፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ማረፊያ የቱሪዝም መስህቦች እና ልዩ ሀገራዊ መታወቂያዎችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በብቃት አስተዋውቀዋል።ወጣቶቹ በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የመስህብ ስፍራዎችን በሚገባ በማስገንዘብ ውጤታማ የህዝብ ለህዝብ የዲፕሎማሲ ስራ አከናውነዋል።#Ethiopia #LandOfOrigins #WorldYouthFestival #YouthDiplomacy #TourismPromotion




ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
10 Sept, 19:36
“ከምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ፣ አዲሱ አመት የሰላም፣ የብልፅግና እንዲሁም የማይረሱ ጉዞዎች ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። መልካም አዲስ ዓመት!”ክብርት ሰላማዊት ካሳ የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር


ቱሪዝም ሚኒስቴር - Ministry of Tourism
10 Sept, 14:35
የቱሪዝም ሚኒስቴር በመቄዶንያ ማዕከል ለሚገኙ አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሄደ::ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባየቱሪዝም ሚኒስቴር መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በማስመልከት በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መደገፊያ ማዕከል በመገኘት ከአረጋውያን ጋር የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሄደ።በጋራ የምሳ መርሃ-ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን፣ የሚኒስቴሩ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ንጉሴ ክብሩ በማዕከሉ ለሚገኙ አረጋውያን፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች እና ለመላው የመቄዶንያ ማኅበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።አቶ ንጉሴ አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት ለማዕከሉ ያደረጋቸውን የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች በማስታወስ፣ የዛሬው የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር የዚሁ አጋርነት ቀጣይ አካል መሆኑን እና ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።በተጨማሪም የማኔጅመንት አባላት በማዕከሉ የሚሰጡ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት አገልግሎቶችን በመዘዋወር ጎብኝተዋል።



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
