Latest posts

የጥበብ - መንገድ
21 Sept, 05:45
forwarded from @geraworqtilayee
ግጥሚያው፦ ሥነ ግጥምኳስ፦ የቃል ሊቀ መኳስእስታዲየሙ፦ ወመዘክርደጋፊው፦ ታዳሚውአሰላለፍ፦ በሰልፍአሰልጣኝ፦ ኪነት(ለነገ ማክሰኞ ሁላችሁም በነፃ ተጋብዛችኋል)


የጥበብ - መንገድ
20 Sept, 17:17
አያ ሙሌ ቁጭ ካለበት ሱቅ የተጋበዛትን ኮካ ኮላ ለባለሱቁ ትቀመጥልኝ ብሎ ይሰጠዋል። ባለሱቁም ኮካኮላዋን ወደ ሳጥኑ ሳይሆን መደርደሪያ ላይ ያስቀምጣታል።አያ ሙሌ ከአንድ ወር በላይ ቆይቶ ወደዚህች ሱቅ ሲመለስ ባለሱቁ "አያ ሙሌ አስቀምጥልኝ ያልካት ኮካ ኮላ አለች በማለት ከመደርደሪያው ላይ አንስቶ ይሰጠዋል።አያ ሙሌ ተገርሞ ብቻ ዝም አላለም። እንዲህ ሲል ነበር የልቡን ምኞት ጭምር የተናገረው:—" ለአንተ ነበር ሃገርን አደራ መስጠት! "


የጥበብ - መንገድ
20 Sept, 15:44
forwarded from @sebleworkbooks
እናማ ሰንበት ን እንዲህ ብናሳልፍስ ! ሙዚቃ ... መጽሐፍ... ድርሰት...




የጥበብ - መንገድ
20 Sept, 05:45edited
እንደ ማስታወቂያ 🙏📖 @sebleold inbox 📥 0946523397
የጥበብ - መንገድ
19 Sept, 15:36
forwarded from @sebleworkbooks
እንደ ማስታወቂያ 🙏📖@sebleold inbox 📥0946523397


የጥበብ - መንገድ
18 Sept, 17:49
''አቅፈሽ - ስትስሚኝ '' ኩሬ ልቤ ደፈረሰ ሰማይ ገጹ ተላወሰ ፣ የብርሃን አረፋ ከአይንሽ ምንጭ ሲቀዳ .. እንደ ጠበል ፡ እንደ ቅዱሱ ስባረክበት ፡ ለወጉ ለ'ምሱ ፡ «አቅፈሽ - ስትዳብሽኝ ! »ሁሉም ሆነ... ጎደሎ ዓለሜ ሞላልኝ የአዝማናት ስለቴ ሰመረልኝ ስብርባሪ ክንፎቸ - በልጅነት ያጣኋቸው ለቃቅሜ፡ ጠገንኳቸው ፡፡© የአባ ልጅ !


የጥበብ - መንገድ
17 Sept, 18:25
ያመሻሽ ስንኞች (በእውቀቱ ስዩም)በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤ ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤“”””” እሳቴን አንድጄ ጭራሮ ማግጄ ሰታቴየን ጥጄ ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤
የጥበብ - መንገድ
17 Sept, 12:40
የጠፈር ባይተዋር (መንገድ ስጡኝ ሰፊ) [ዛሬ የሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ የልደት ቀን ነው!🥰 ...ገብሬ ከሳለው ስዕል በስተግርጌ "GK" በማለት ፊርማውን ያኖር ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ልጅ ለወለዱ ወዳጆቹ እንደስጦታ እነርሱ ዘንድ ይዞ የሚሄደው ትልቁ ስጦታ ስዕል ነበር። በረቂቅ አሳሳል ዘይቤ የተዋቡ የገብረክርስቶስ ስዕሎች በበርካታ ሰዎች ዘንድ የመገኘቱ ምስጢር ይህ ነው። ለአብነት


የጥበብ - መንገድ
15 Sept, 17:45
እንደ ሃሳብ ባይሻገሩ 🙌


የጥበብ - መንገድ
14 Sept, 17:28
እነሆ ክረምት አለፈ፡፡ ወቀትም ተለወጠ፡፡ በእውኑ የወቅቶችን መለወጥ ያህል ምናብን የሚያጥበረብር ሌላ ምን ነገር ይኖራል?እናም የወቅቱ መለወጥ ባነቃቃው ምናብ እንደገና የጉዞን ነገር በተረክ እናወጋለን። . . .ሰውዬው ጨርቁ ላዩ ላይ ያለቀ መናኝ ነው። ከሀገር ሀገር ብዙ ዓመታት መንከራተት በኋላ የአመሻሿ ፀሐይ ከደመና ጋር እየተጫወተች አካባቢውን በለጋስ ብርሃን ያጥለቀለቀችበት አንድ የመጸው አመሻሽ፣ ወደ አንድ ገበሬ የጤፍ ማሳ ደረሰ። የጤፉ ማሳ በነፉስ ስውር እስትፋንስ ሲደባበስ የሚያሳውን እንደ ማዕበል የሚደንስ፣ የሚያስደንቅ ንቅናቄ ተመልክቶ በውበቱ ፈዞ ቀረ።በዚህ ዓይነት የሚያባብል ድንገቴ የመወሰድ ስሜት ውስጥ እያለ ገበሬው ከዕለት ውሎው ሲመለስ ተመለከተ። ተጠግቶም እየተሽቆጠቆጠ ምስጋናውን ገለጠ፡፡ገበሬውን በመደነጋገር ‹‹እንደምታዬው ምንም ልሰጥህ የማልችል ከዕለት ውሎዬ የምመለሰ አፈር ገፊ ነኝ። ምን እሰጥህ ዘንድ ትሻለህና ታመሰግነኛለህ?›› ‹‹በፍጹም። ከሰጠኸኝ በላይ ሌላ ምንም አልሻም። የጤፍ ማሳህ ከነፋስ ጋር የሚያደርገውን ረቂቅ ድሪያ ተመለከትሁ። ነፍሴም ፈጽማ ሀሴትን አደረገች። እናም ይሄን ውበት በንጽህና፣ በላብና በድካም የገለጡ እጆችን ለማመስገን ከፊትህ ቆሜያለሁ፡፡›› ገበሬውም በመገረም ‹‹ዘንድሮ መቸም ካበደው ለማበድ የተዘጋጀው ይበልጣል፡፡›› እያለ ለራሱ እያልጎመጎመ መንገዱን ቀጠለ።. . .ይህ ተረክ ዓለማቀፍ ተረክ ነው። ተረኮች እጅ እግር ሳይኖራቸው በነጋሪዎቻቸው ምናብ ላይ እንደጉም እየተሳቡ ተሰዳጅ ናቸውና ይህ ተረክ በሌላ ቦታ፣ በሌላ ቋንቋ ትንሽ
የጥበብ - መንገድ
14 Sept, 17:10
ነስሩዲን ለፀጉር ቆራጩ እንደገባ ጉርሻ ገንዘብ ይሰጠዋል ። ሰውዬም በጣም ገርሞት ጌታዬ ከመቁረጤ በፊት ጉርሻ የሰጡኝ የመጀመሪያው ሰው ነዎት » አለ በደስታ ! « ጉርሻ አይደለም » አለ ነስሩዲን ጆሮዬ ላይ እንዳትጮህ አፍ ማስያዣ ነው ።“የሙላ ነስሩዲን ዘመን አይሽሬ ቀልዶች !”


የጥበብ - መንገድ
14 Sept, 06:08
( 'ያወቁ ፡ እየመሰላቸው ፡ ስለማያውቁ ፡ ያወቁ ፡ ይመስላቸዋል ፡፡' ) : ዘርኣያዕቆብ


የጥበብ - መንገድ
13 Sept, 15:34
በ18ኛው መቶ ክ/ዘመን የአባይን ምንጭ ለመፈለግ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ስኮትላንዳዊው ቀላዋጭ ጀምስ ብሩስ የኢትዮጵያውያንን የጥሬ ስጋ አበላል ሲገልፅ " በመጀመሪያ ሰፊ ዳስ ይዘጋጃል። ከዚያ እድምተኛው በዳሱ ከተሰበሰበ በኋላ እንዳያመልጥ በጥብቅ የታሰረ በሬ እየተነዳ ወደ ዳሱ ይገባል" ከዛ ኢትዮጵያንን መሳደብ ይጀምራል "በዳሱ ውስጥ የተሰበሰበው ሰው ተራ በተራ እየተነሳ ታስሮ ከቆመው በሬ ስጋ ቆርጠው ያወጣሉ" ይላል።"የሚፈልጉትን ያህል ከበሉ በኋላ በሬው ከዳሱ ይወጣና ሳር ይግጣል"😁ይህንን ሁሉ የሚለው ጠጁን፣ጮማውን፣ ካቲካላውን እንደልቡ እያፈሰ ስለኖረባት ሀገር ነበር።ታዲያ ብዙ አውሮፖውያን ፀሀፊዎች በድንቁርናው በመሳለቅ "እኛ ግማሽ አካሉ ተበልቶ ግማሹን ለማኖር ሳር የሚግጥ እንስሳ የሚኖርበት ሀገር አልኖርንም" ብለው አፌዙበት። ያሳተመው መፅሀፍም ተሰብስቦ ተቃጠለ።


የጥበብ - መንገድ
11 Sept, 08:28edited
እ ን ቁ ጣ ጣ ሽ - እንኳን አደረሰን 💛 🌻🌼


የጥበብ - መንገድ
4 Sept, 16:57edited
ዘጠና በመቶ ባህሪዬን እና ነገረ ስራዬን የወረስኩት ከናቴ ነው:: ይህ ማለት ውበቷንና ትህትናዋን ወይ ሆደ ሰፊነቷን ወረስኩ ማለት አይደለም፡፡አንዴ 20 አመት የሆንኩ ግዜ ለራስህና ለህዝቡ ሲባል ከገዳማቱ ክአንዱ ገብተህ መነኩሴ ብትሆን ይበልጥኑ ይበጅ ነበር ብላ ያለችኝ ትዝ ይለኛል ፡፡እርግጥ ነው ወደዚች አለም ከመምጣቴ በፊት አንቺ እንደናቴ ከመሆንሽ በስቀር፡፡“ባትወለድ ኖሮማ መላእክ ሆነህ ትቀር ነበር” ብላ መለሰችልኝ “አሁንም እኮ መላእክ ነኝ አልኳት፡፡”“ታዲያ ክንፎችህሳ የታሉ? ብላ ፈገግ ብላ ጠየቀችኝ ”“እጆቿን በትካሻዬ ለይ አኖርኳቸውና ‘ ክንፎቼ እኘሁልሽ’፡፡ አልኳት“ግና ተሰብረዋላ! አለች፡፡”"The Broken Wings" ለሚለው ስራው ርእሱን እንዴት እንደሰጠው ለተወዳጆ ሜይ ዚያዳ ከጻፈው ደብዳቤ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ (ጂብራን እና ሜይ ዚያዳ ጋር ገራሚ ፍቅር ነበራቸው) ጂብራን በደብዳቤው ላይ ሲያጠቃልል እናቴ ከአድማሱ ወዲያ ማዶ ወደ አለው እውነተኛው አለም ብትሄድም ነገር ግን የተሰበሩ ክንፎች የሚሉት ቃሎቿ በውስጤ ቀሩ ፡፡ እኔም ለ ድርሰት ተጠቀምኩባቸው፡፡


የጥበብ - መንገድ
3 Sept, 16:43
forwarded from @sebleworkbooks
የተለያዩ የልቦለድ ፡ የታሪክ ፡ የስነልቦና እንዲሁም የፍልስፍና መጽሐፍ እኛ ጋር ያገኛሉ ። እንዲሁም በተጨማሪ የ Delivery አገልግሎት እንሰጣለን - ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን !#አድራሻችን አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በገንዘብ ሚኒስቴር ጀርባ ገባ ብሎ እንገኛለን ።ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፦ 0946523397 ይደውሉልን ።እንዲሁ ም Telegram ቢፈልጉ @sebleold inbox 📖https://t.me/sebleworkbooks ያገኙናል ።


የጥበብ - መንገድ
2 Sept, 14:00
ስህተቶችን መቀበልጀርመናዊዉ ፈላስፋ ፊሪደርክ ኒቼ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር ፦" ስለሁሉም ነገር በመነታረክ መኖር ምንም ጥቅም የለዉም ። አልፎ አልፎ ስህተቶችን መስራት ሰዋዊ ተፈጥሮ ነዉ ።"አየርላንዳዊዉ ደራሲ ጀምስ ጆይስም ይህንን አስተያየት ይጋራል ። እርሱ ደግሞ እንዲህ ይላል ፦" ለአንድ ሰዉ ስህተቶቹ ወደ ግኝት የሚያደርሱት መጓጓዣዎች ናቸዉ ።"እንደዚህም ሆኖ ግን ሁልጊዜም ስለ ጥቃቅኗ ዝርዝር ጉዳይ ሳይቀር ትክክል መሆናቸዉን ሽንጣቸዉን ገትረዉ መከራከርን ስራዬ ብለዉ የያዙ በርካቶች እንዳሉ እናዉቃለን ። እኛ ራሳችንም ብንሆን በዚሁ ምድብ መካተት አይቀርልንም ። ለራሳችን ስህተት መስራትን እንፈቅድለትማ ።ይህ አይነቱን ዝንባሌ ይዘን ታዲያ የምናተርፈዉ ነገር ቢኖር ወደፊት ለመራመድ መቸገርን ብቻ ነዉ ። ምክንያቱም ወደፊት ለመራመድ መወሰድ ያለባቸዉ አዳዲስ ዉሳኔዎች ይኖራሉ ። ዉጤታቸዉን አስቀድመን ማወቅ ስለማንችል ስህተት መስራትን በመፍራት ባለንበት ተገትረን እንቀራለን ።ስህተት የመስራት ፍርሃት ነዉ የተልካሻነት ጓዳችንን ለቀን ወደ ልሂቅነት አደባባይ እንዳንወጣ በር ቆልፎ የሚያስቀረን ። በልዩ መልኩ ድንቅ እና እጅግ ምርጥ ከመሆን አቅቦን የተራነታችንን ብልኮ እንድንከናነብ ጨርሶም እንዳናወልቀዉ አስሮ የሚያስቀረን ።ይህንን ፍርሃት መቋቋም ከቻልን ወደ ነፃነት የሚያቀርበን ወሳኝ እርምጃ ለመዉሰድ ብርታቱን እናገኛለን ።
የጥበብ - መንገድ
1 Sept, 16:35edited
ቅድም ድንገት ከሐብት ማማ ደረሼ መቅፅበት በሞላ የእድሜ ጎዳና እንደ ዥረት ተጅመልሙሎ ተከሰከሰ የስኬቴ ነገር ( ወገኖቼ ሃብት የጥዋት ጤዛ ነው ! )“ አብሽር ”ራሴን “ በርታ ”ምናምን ብዬ ፣ ጥበብ በተሞላበት ምክር ደለልኩት !እንዲያውም “ የምን ቁዘማ ፡ ትካዜ አልኩ ና ለራሴ እንደ ንጉስ ሰለሞን ወይን ጠጅ ባታገኝም ፣ አንድ ሺህ እቁባት ባይቀርቡልህም ፣ አረቂ እየጣጣህ ኮማሪዋን ማሽኮርመም አለብህ አለኩት (ይህ ነፃ ፍቃድ ይሉት ጅል አማካሪ ) !መልካም ! “ ይሄም ትንሽ ስጋን የሚያፋፋ ነገር ነው ”የሐብቴን ነገር ረስቼ ፣ የድርሰት ግባአት የሚሆን ነገር ልቃርም አይኖቼን ለውበት ስዬ ፡ አዕምሮ ዬን ለፍልስፍና አውድማ አጥርቼ ፣ ሸራ ወደተጎናነበችው ግድግዳዋ መወላለቅ ወደ ያዘው የአረቂ ቤት ገባሁ ፤ ዳሩ ግን ከዛ አካባቢ እነማን ይውላሉ የሚል ስጋት አደረብኝ ፡ ነገር አዋቂ ሽማግሌዎች ፡ በ ፍቅረኛቼው የተከዱ ምስኪን አፍቃሪዎች ፡ ኑሮን እሹሩሩ ለማለት ሚስት ልጃቸውን ትተው የመጡ በጉልበት የሚያድሩ የቀን ሰራተኞች ፡ ወይስ የዎትሮዊ ጠጭ ዎች አሊያ ! ኮማሪዋ ጋር የአይን ፍቅር ይዞት የሚመላለስ ብቻ ሌላም ሌላ ...፡ ምሃራ እንደ አየ ቆሎ ተማሪ ሽቁርር ብዬ ስገባ ፣ ሁሉም አይኖች አረፉብኝ ገላዬ ሳሳ ፡ ከጥንስሱ ብርክ ብርክ አለኝ ፣ ኑር ማለት ለካ ቀርቷል ።ከዛ ይሄን ባህል ለምን ቀረ እያልኩ ሳንሰላስል (የማይረባ ነገር ላይ መቆየት ምን ጥቅም )ከንፈሮቿ የጎመሩ ወደ ብስል እንኮይ ፍሬ የምታደላ ሴት አረቂውን አምጥታ ልትቀዳልኝ ስትል አይኔ ተወርውሮ መንታ ጡቶቿ
የጥበብ - መንገድ
1 Sept, 16:35



የጥበብ - መንገድ
31 Aug, 08:32
ታሪክ ፦ በ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ከነበሩ አብዬ ጦርነቶች መካከል የአፄ ልብነ ድንግል እና ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም ኤልጋዚ ጦርነት ይጠቀሳል ታዲያ ይሄን ጦርነት እየተከተለ ሲዘግብ የነበረዉ ሽሃቡዲን አህመድ ዐብዱልቃድር ( ዐረብ ፈቂህ ) ነዉ ።ዐረብ ፈቂህ ፦ ኢማም አህመድ ኢብራሂም ከዐፄ ልብነ ድንግል ያደረጉትን ረጅምና መራራ ጦርነት የተተረከበት ዋናዉ መጽሐፍ በዐረቢኛ ስሙ " ፈቱሕ አል ሐበሻ " ( ሐበሻን የማቅናት ዘመቻ ) ይባላል ።የጦርነቱ ዋና የመረጃ ምንጭ በማዕረግ ስሙ ዐረብ ፈቂህ ተብሎ የሚታወቀዉ ታዋቂዉ የየመኑ የሕግ ባለሙያ ሽሃቡዲን አህመድ ቢን ዐብዱልቃድረ የተባለዉ የኢማም አህመድ ዜና መዋዕል ጸሐፊ በ1535 በጦርነቱ መካከል በዐረቢኛ ቋንቋ የጻፈው ታላቅ መጽሐፍ ነዉ ።የዐረብ ፊቂህ መጽሐፍ በተለይ የሚገልፀዉ የጦርነቱን አመታቶች ከ1524 _ 1535 ድረስ የተፈፀመዉን የዘጠኝ ዓመታት ታሪክ ብቻ ነዉ ። የመጽሐፉ ደራሲ ዐረብ ፈቂህ አለቃዉ ኢማም አህመድ በአዳሉ የወላስማ መሳፍንታዊ የገዥ መደብና በሀገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት አመራር ላይ በአካባቢዉ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ታላቅ ጦርነት አካሂዶ በሰሜን ምዕራብ በጣና ሀይቅ አጠገብ በደንቢያ ማለትም በፈላሻ ምድር የመንግስቱን ማዕከል ከመሰረተዉ በኋላ የጦርነቱን ታሪክ በድንገት ያቆማል ። ይህ በኢማም አህመድ ዐመፅ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ አጠቃላይ የመካከለኛዉ ክፍለ ዘመን ታሪክ ቁልፍ የመረጃ ምንጭ የሆነዉ ታላቅ መጽሐፍ ለትዉልድ እና ለታሪክ የተላለፈዉ በአዳል መንግስት ተወላጆችና ወራሾች እጅ በታላቋ የሐረር ከተማ ሲጠበቅ
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
