Latest posts

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
11 Aug, 09:48
https://youtu.be/WUpN3lCNHiw?si=q35CF0fRHhq8R_0aYouTube#ዘሰኑይ ውዳሴ ማርያም#አንድምታ #ትርጓሜEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
11 Aug, 09:47
https://youtu.be/WUpN3lCNHiw
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
10 Aug, 09:58
https://youtu.be/5fwxp9FqXmsYouTube#ዘሰኑይ ውዳሴ ማርያም#አንድምታ #ትርጓሜEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
18 Jun, 16:11



2,050Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
18 Jun, 16:06
ከዚህ በኋላ ባለ ጠጋው ከሄደበት በተመለሰ ጊዜ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ‹‹ይህ የምሰማው ምንድነው›› ብሎ ጠየቀ፡፡ እነርሱም ‹‹ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት፡፡ እነሆ ዓርባ ቀናት በሰርግ ላይ ነው፡፡ ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝህ ሰጥተውታል›› አሉት፡፡ ይህንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ፡፡ ባሕራንም ከዚህ በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር በሚገባ እየዘከረና ለቤተ ክርስቲያኑም እየታዘዘ የሚያገለግል ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዓሉን በሚገባ አክብረን በረከት እንድንቀበል ይርዳን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኀይል በሀገራችን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከተሠውት የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይሁን፤ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ምንጭ፡– ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል፣ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ1,620Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
18 Jun, 16:06
ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ፣ካ-ከመ፣ኤል-አምላክ መኑ ከማከ አምላክ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው? ማለት ነው።(ኪ.ወ.ክ)። ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስ በትዕቢቱ ፈጣሪነትን ሽቶ በዓለመ መላእክት ሁከት ባስነሣ ጊዜ የቅዱሳን መላእክት ፊታውራሪ ሆኖ ዲያብሎስን የተዋጋ ጽኑዕ መልአክ ነው። "በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት፣ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም። ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም።"(ራእይ ፳፪:፯) ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ነው። ይሁዳ በመልእክቱ "የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በማለት ሊቀ መላእክትነቱን ገልጾአል። (ይሁዳ ፱) ይህችውም ቅሩበ መንበር ተደርጎ የተፈጠረው ዲያብሎስ የተዋት ክብሩ ናት። ቅዱስ ሚካኤል ይቅር የሚል ከመዓት የራቀ ነው።(ሄኖ፥፲፥፩፪) ለሰው ባደረገው በጎነት ለሕዝቡ ሁሉ ታዛዥ ነው። የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይ ጭምር ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳ ጻድቃንና ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው፤ በሕይወታቸውና በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል፡፡ ይህንንም በቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፈ ስንክሳር እና በድርሳነ ሚካኤል ሰኔ ፲፪ ቀን ተጽፎ እናገኘዋለን። ይህም ቀን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተከብሮ የሚውልበት ታላቅ ዕለት ነው፡፡ በእስክንድርያ ከተማ ክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የበጥሊሙስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበር፤ ሕዝቡም ሰኔ በገባ በዐሥራ ሁለት የዚህን ጣዖት1,210Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
18 Jun, 16:06
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ‘’ከመላእክት አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።’’ (ት.ዳን. ፲ ፥፱) እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ‼️ በዓል “አብዐለ” አከበረ÷ አበለጠ÷ ዕለትን በዓል አደረገ ከሚለው ግስ የወጣ ስም ነው። ይህም የደስታ፥የዕረፍት ቀን ፥በዓመት በወርና በሳምንት የሚከበር፥ ያለፈ ድርጊት የሚታወስበትና ምእመናን የበዓሉን ምሥጢር እያሰቡ ሐሴት የሚያደርጉበት ማለት ነው:: ዕለቱም ምእመናን መደበኛ ሥራቸውን ትተው ለበዓሉ ይገባዋል የሚሉትን ተግባር የሚፈጽሙበት የበዓሉን ባለቤት እግዚአብሔርንና የበዓሉን ምክንያት እያሰቡና እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ነው። ቅዱስ ዳዊት “….በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ:: ”(መዝ ፵፩፥፬፡፡) እንዳለው። በዓላት የዕረፍት ቀናት ናቸው ማለት ከሥጋዊ ወይም ምድራዊ (ዓለማዊ) ሥራዎች የሚያርፉባቸው ናቸው ለማለት ነው። በአንጻሩ ግን መንፈሳዊ ሥራዎች ሁሉ እንደየችሎታ የሚከናወንባቸው መሆናቸው መረሳት የለበትም፡፡ እነዚህ ዕለታት እግዚአብሔር በራሱ ወይም በቅዱሳኑ አድሮ ለሠራቸው ድንቅ ሥራዎች (ተአምራት) መታሰቢያዎች ናቸው። (መዝ፻፲፥፬)፡፡ ፻፲፩፥፮፡፡ ሉቃ፳፪፥፲፱፡፡) በበዓሉ ዋዜማ ለዕለቱ የተሠራውን የምስጋና ቃል እየመሩ፣ እየተመሩ፣ እያነሡ፣ እየዘመሙ፣ መስተብቁዕ እየደገሙ፣ እያመረገዱ፣ እያመለጠኑ፣ እየጸፉ ሊቃውንቱ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ። በዚህ መልኩ ከሚከበሩ ዐበይት በዓላትም አንዱ በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
1,080Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
6 May, 09:46



2,280Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
6 May, 09:46
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክበስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ አምላክ አሜን!ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦ ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችሁ! “እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)። የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤ ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት2,020Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
9 Mar, 17:57
#ዜና_ዕረፍት ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት #መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐረፉ። #ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ ገብርከ #ወልደ_ሰማዕት ሀገረ ሕይወት መንግስተ ሰማያት ያውርስልን፤ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኦርቶዶክሳውያን2,390Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
#ዜና_ዕረፍት ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት #መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐረፉ።#ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ ገብርከ #ወልደ_ሰማዕት ሀገረ ሕይወት መንግስተ ሰማያት ያውርስልን፤ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
1,680Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
#መዝሙር_ዘሰንበት_መጻጕዕ
1,440Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
#ምስባክ_ምኵራብ_እምሐሙስ_እስከ_ቀዳሚት_ሰንበት
1,410Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
፨ ቅዱስነትዎ እንኳን አደረስዎ ፨/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።
1,220Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
#ምስባክ_ዘምኵራብ_እምሰኑይ_እስከ_ረቡዕ
1,090Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24

1,020Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24
#በጣሊያን_ወረራ_ወቅት_አስተዋጽዖ_ካደረጉት_መካከል_ዐበይቶቹ_ገዳማትና_አድባራት፤ #ከካህናት፡፡ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል፤ ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤ 300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤ 2,000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡ ፠ይህንን እኩይ ተግሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤ ፠ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕታት #ብፁዕ_አቡነ_ጴጥሮስ_(ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም. መሐል አ.አ ላይ በስምንት ጥይት ያረፉት)ና #ብፁዕ_አቡነ_ሚካኤል_ (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት) ፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው #ታላቁ_ሊቅ_አቡነ_ክፍሌ፡፡ ፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም. ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ #የደብረ_ሊባኖስ_መነኰሳት፡፡ ፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ_መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 #የዝቋላ_መነኰሳት፡፡ ፠ በጥቅምት1,260Open in Telegram
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:24





መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:23
አገር ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤በደረሰው አደጋ ዙሪያ
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
8 Mar, 04:23
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት›› (ማቴ 5÷51 ፤ ቅዱስ ያሬድ)ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
