gram news
قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل ) channel avatar

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

@abu_hibetillah_asselfiy

ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፈታዋወች ሙሐደራዎች የሚለቀቅበት የሰለፉነ አስሷሊህ ዕምነት የሚብራራበት ቻናል ነው። ይ ቀ ላ ቀ ሉ https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy አስተያየትና እርማት ካላችሁ 👇 @Abu_Hibetillah_bot

ProjectsENReligion

17,500subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    25 Sept, 14:00

    ጥያቄ ? 📮📮ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ።ነቢዩሏህ ኢብራሂም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰይፍ የተዋጉ ነቢይ ናቸው ፡፡
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    25 Sept, 13:41

    ታላቅ የሙሓደራ ፕሮግም🖱የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን፦💡🇸🇦. ኡስታዝ አቡል ሁበይብ🌟⬅️ርዕስ🔴 አጠቃይ ምክር ለጧሊበል ዒልሞች➡️🇸🇦. ወንድም አቡ ኢምራን🌟👈 ርዕስ🔴 ሞት➡️🇸🇦. ወንድም አቡ ሹራ አህመድ🌟⬅️ርዕስ🔴 በሰአቱ➡️ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️🔘 ፕሮግራሙ አቡ ሹራ ይመራል🕰 የፕሮግራም ሰዓት ፡😴 ጅሙዓ ምሽት √🔻2:00 ~ በኢትዮ 🔺8:00 ~ በሳዑዲ 🔻9:00 ~ በዱባይ🛜 ፕሮግራሙ የሚካሄደው 🔽📥📥📥📥📥📥📥📥▶️https://t.me/sobabilelmesjide
    Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    24 Sept, 16:43

    🌿 የነብዩሏህ ዩሱፍን ባህሪ የተሸከመ ወጣት 🌿ሑሰይን ቢን ዐብዱረህማን እንዲህ ይላል፦ከመዲና ሰዎች መካከል አንድ ወጣት ነበር። ከዑመር ቢን አል-ኸጣብ رضي الله عنه ጋር ሁሉንም ሶላቶች በጀመዓ ይሰግድ ነበር። ዑመርም በጀመዓ ካልታየ ይፈልገውና ሁኔታውን ይጠይቅ ነበር።ይህ ወጣት በአንዲት የመዲና ሴት ዘንድ የፍቅር ፍላጎት ተፈጠረባት። ለአንዲት የምታውቃት ሴትም ጉዳዩን ነገረቻት።እሷም፦ “እኔ እንዴት ወደ ቤቴ እንደምታስገባው እረዳሻለሁ” አለቻት።ከዚያም ወጣቱ በሚያልፍበት መንገድ ተቀመጠችና፦ “እኔ እድሜዬ የገፋ ሴት ነኝ፤ አንዲት በግ አለችኝ፣ እኔ ግን ማለብ አልችልም። እባክህ ወደ ቤቴ ገብተህ ታልብልኝ?” አለችው።ወጣቱም በመልካም ልብ ገባ። ነገር ግን ቤት ውስጥ ሲገባ ምንም በግ አላገኘም። ሴቲቱም፦“እዚህ ተቀመጥ፤ ልጠራት ሄጄ እመጣለሁ” አለችው። ከዚያም የታሰበውን አደረገች። ወጣቱን ለማሳሳት ሞከረች። ወጣቱ ግን ወዲያውኑ ወደ ቤቱ ውስጥ ያለ የሶላት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ። እሷም ወደ እርሷ እንዲቀርብ ጠየቀችው።እሱ ግን፦ “አንቺ ሴት ሆይ! አላህን ፍሪ!” አላት። እሷ ግን አልተመለሰችም። ወጣቱ እምቢ ሲላት ጩኸት አሰማች። ሰዎችም መጡ። እሷ ግን እውነቱን ከመናገር ይልቅ ወጣቱን በመክሰስ፦ “ይህ ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር!” አለች።ሰዎቹም ወጣቱን ያዙት፣ ደበደቡትና አሰሩት።♦️ በማግስቱ ጠዋት ዑመር رضي الله عنه ሶላት ከጨረሱ በኋላ ይህ ወጣት ታስሮ ወደ እርሳቸው ቀረበ። ዑመርም ሲያዩት ወደ አላህ ዱዓ አደረጉና፦ «اللَّهُمَّ لَا تُخَلِّفْ ظَنِّي فِيهِ» “አላህ ሆይ! በእሱ ላይ ያለኝን መልካም ግምት አታሳስተኝ!” አሉ።ከዚያም ምን እንደተፈጠረ ጠየቁ። ሰዎቹም የተከሰተውን በራሳቸው መንገድ ነገሯቸው። ዑመር رضي الله عنه ግን ወጣቱን በመመልከት፦ “እውነቱን ንገረኝ” አሉት። ወጣቱም የተፈጠረውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በእውነት ነገራቸው። ዑመርም፦ “ያቺን አሮጊት ታውቃታለህ?” አሉት። “አዎን፣ እንደገና ባያት አውቃታለሁ” አለ። ዑመር رضي الله عنه የሴቲቱን ጎረቤቶችና አሮጊቶች አስጠሩ። እያንዳንዳቸው እያለፉ ሳለ፣ ያቺ ሴት በመጣች ጊዜ ወጣቱ፦ “እሷ ናት፣ የአማኞች መሪ ሆይ!” አለ። ዑመር رضي الله عنهም ወደ እሷ ተመልሰው፦ “እውነቱን ንገሪኝ!” አሏት። በመጨረሻም ሴቲቱ የወጣቱን ንግግር ሁሉ አረጋገጠች።ያን ጊዜ ዑመር رضي الله عنه እንዲህ አሉ፦ 🌿 «الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي جَعَلَ فِينَا شَبِيهَ يُوسُفَ عَلَيْهِ السَّلَامُ» “አላህ ምስጋና ይገባው! በመካከላችን ከዩሱፍ አለይሂሰላም ጋር የሚመሳሰል ሰው ያደረገልን አላህ ምስጋና ይገባው!”
    721153Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    24 Sept, 11:49edited

    🌹 የፍቅር እውነተኛ ቋንቋ አንዳንድ ጊዜ ቃል አያስፈልገውም… 🌹በሻር ቢን በርድ እንዲህ ይላል፦ وَإِذَا الْتَقَيْنَا وَالْعُيُونُ رَوَامِقٌصَمَتَ اللِّسَانُ وَطَرْفُهَا يَتَكَلَّمُتَشْكُو فَأَفْهَمُ مَا تَقُولُ بِطَرْفِهَاوَيَرُدُّ طَرْفِي مِثْلَ ذَاكَ فَتَفْهَمُ “ስንገናኝና ዓይኖቻችን እርስ በርሳቸው ሲመለከቱ፣ አንደበታችን ዝም ይላል፤ የዓይኖቻችን እይታ ግን ይናገራል። እሷ በዓይኗ ትናገራለች፤ እኔም የምትለውን ያለ ቃል እረዳለሁ። ዓይኔም በተመሳሳይ ሲመልስላት፣ እሷም የምለውን ትረዳለች።”🌿 ይህ ነው ፍቅር ሲያጠራ…● እውነተኛ ፍቅር ሲኖር፣ ሁሉንም ነገር በቃላት መግለጽ አያስፈልግም። ● አንድ እይታ ብቻ ብዙ ነገር ይናገራል። ● አንድ ፈገግታ የልብን ምስጢር ያሳያል። ● አንድ የዓይን እንባ ያለ አንድም ቃል ህመምን ያስረዳል። ● አንድ ዝምታም ከሺህ ቃላት የበለጠ ሊናገር ይችላል። 🫀ለምትወደው ሰው ዓይን ልዩ መልእክት አለው።◆ ሰዎች በአንተ ፊት ላይ ፈገግታ ብቻ ሊያዩ ይችላሉ፤ ◆ የሚወድህ ግን ከፈገግታህ ጀርባ ያለውን ድካም ሊያይ ይችላል። ◆ ሌሎች ሰዎች “ደህና ነኝ” የሚለውን ቃልህን ሊያምኑ ይችላሉ፤ ◆ የሚወድህ ግን ዓይኖችህን ያያልና፣ “አይ፣ ዛሬ ደህና አይደለህም” ሊልህ ይችላል።🌹 ከዚህ ሀሳብ ጋር የሚያስደንቅ ነገር በነቢዩ ﷺ ሐዲስ ውስጥም እናገኛለን።አቡ ሁረይራ رضي الله عنه አንድ ጊዜ በጣም ተርበው ነበር። እንዲህ ይላሉ፦ «ثُمَّ مَرَّ بِي أَبُو الْقَاسِمِ ﷺ فَتَبَسَّمَ حِينَ رَآنِي، وَعَرَفَ مَا فِي نَفْسِي وَمَا فِي وَجْهِي» “ከዚያም አቡል-ቃሲም ﷺ አለፉብኝ፤ እኔን ሲያዩኝ ፈገግ አሉ፤ በነፍሴ ውስጥ ያለውንና በፊቴ ላይ የሚታየውን ሁኔታ አወቁ።”ይህ የሚያሳየን ነገር በጣም ውብ ነው። 🌿 ነቢዩ ﷺ አቡ ሁረይራ رضي الله عنه ምንም ሳይናገሩ የነፍሳቸውን ሁኔታ ከፊታቸው ላይ ተረዱ።
    888111Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    24 Sept, 05:43

    forwarded from @sefinetunuh

    በቃሪዕ ሙስጠፋ ኢብኑ ሙሐመድ🎤🧡
    803voice message142Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    24 Sept, 04:19

    የኢትዮጵያ ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የጦርነት ታሪክ ነው። ዘፈኑም፣ ቀረርቶውም፣ ተረትና ምሳሌውም እንዳለ ከመG ደል ጋር በተያያዙ መልእክቶች የታጨቀ ነው። ህዝቡም ሰርቶ ከመለወጥ፣ ኑሮን ከማሸነፍ በላይ ጦረኝነትን እና ገዳ ^ ይነትን እንደ ጀግንነት የሚቆጥር ነው።አባትሽ አይገ^ ድል ወንድምሽ አይገ^ ድል አርሶ ያብላሽ እንጂ ሆድሽ እንዳይጎድል።አገራቸው ወዲያ ዳርቻ ቀበሌ ተበድሮ ገ^ ዳይ ጥይት እንደ ጥሬወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንዳባቱ፣ ስጡት አመልማሎ ይፍተል እንደናቱበሀገራችን ከህግና ስርዓት፣ ከመልካም መኗኗር በላይ ጉልበተኝነት ነው የሚያስከብረው። ጉልበተኛ ወገን የሌለው ሰው አንገቱን ደፍቶ ነው የሚኖረው።ሁሉም ለጦርኝነቱ ምክንያት ቢደረድርም እውነታው ግን የህዝቡ ባህልና ስሪት ከጦረኝነት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ይሄ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ያለ የነበረ ያልተቀየረ እውነታ ነው። ከየትኛው ጉዳይ በላይ በጦርነት ላይ ይረባረባል። ከየትኛውም ጉዳይ በላይ የጦርነት ዜና ይመስጠዋል፣ ያነፈንፋል።በርግጥ ጦረኝነት የዓለም ታሪክ ነው። ግን ዛሬ ላይ ሃገራት የህዝባቸውን አመለካከት እየቀየሩ ውስጣዊ ሰላም በማስፈን ተረጋግተው እየኖሩ ነው። እኛ ግን እዚያው ነን። የጦርነት አዙሪት ውስጥ ስንማቅቅ እንኖራለን። አንዱ መዓት ጠባሳ ጥሎ ሲያልፍ ደግሞ ሌላው ይጀምራል። አሳማሚ እውነት። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
    90541Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    23 Sept, 18:07

    🌹«ፍቅር ሁልጊዜ ለትዳር የሚበቃ መሠረት አይደለም…»አንድ ወንድ የሚወዳትን ሴት ሲያገባ፣ ከጋብቻ በኋላ የሴትነቷ ምስጢር ቀስ በቀስ ይገለጥለታል፤ እሷም ቀድሞ በምናቡ ውስጥ ከነበረችው ሴት የተለየች ትሆናለች፤ እሱም በእሷ ምናብ ውስጥ ከነበረው ወንድ የተለየ ይሆናል።ምክንያቱም ከጋብቻ በፊት ፍቅር ብዙ ጊዜ በምናብ፣ በመናፈቅና በማይታወቀው ምስጢር ይገነባል። ከጋብቻ በኋላ ግን እውነተኛው ሕይወት ይጀምራል፤ የተደበቀው ይገለጣል፣ ምናቡም ከእውነታው ጋር ይገናኛል።ስለዚህ ፍቅር ብቻውን የትዳር ደስታ መሠረት አይደለም። በተለይም ፍቅሩ ከፍተኛ መናፈቅና የልብ መቃጠል ላይ ብቻ የተመሠረተ ከሆነ፣ ከጋብቻ በኋላ የብስጭት ምክንያት ሊሆን ይችላል። እውነተኛ ትዳር ግን ፍቅር ብቻ ሳይሆን ብስለት፣ ትዕግሥት፣ ኃላፊነት፣ መከባበርና በአላህ ላይ የተመሠረተ ፍርሃት ይፈልጋል።አንድ ወንድ ከጋብቻ በኋላ የቀድሞውን የምናብ ምስል በሚስቱ ውስጥ ማግኘት ካልቻለ፣ ይህንን በብስለት ከመቀበል ይልቅ ያጣውን ነገር በሌላ ሴት ውስጥ መፈለግ ከጀመረ፣ መከራው በእሱ ብቻ አይቆምም፤ ሚስቱን፣ ቤተሰቡንና ልጆቹንም ይጎዳል።ምክንያቱም ሴት በትዳር ውስጥ የምታገኘው የባሏ ታማኝነትና አክብሮት በስሜቷ ላይ ጥልቅ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው።ትዳር የምናብ ቦታ አይደለም፤ የእውነት ሕይወት ነው።ፍቅር ያስጀምረዋል፤ ታማኝነትና ኃላፊነት ግን ያስቀጥሉታል።t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asself
    1,050164Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    23 Sept, 14:10edited

    ሰዋ ካርድ የምፈልጉ ከኛጋ ታገኛላችሁ በዚህ አናግሩን@umureyan_33 @Riiche1
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    22 Sept, 18:09edited

    ​🌹 "የሴት ልጅ የዓይን ማረፊያ (ደስታዋ) ደግ/መልካም ባል ነው።…" 🌹 قُرَّةُ عَيْنِ الْمَرْأَةِ زَوْجٌ صَالِحٌ…የሴት ልጅ የዓይን ብሌን፣ የልብ ረፍትና የነፍስ ሰላም የሚሆነው ባል ያለው ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ የሚያስተዳድርበት ጥበብ፣ የሚያከብርበት ልብ፣ የሚጠብቅበት ወንድነት እና የሚራራበት ርህራሄ ነው።እሷን ከእርሱ ጋር የሚያሳርፋት ባል፣ እሷን እንደ ተጠቂ ሳይሆን እንደ አማና የሚመለከት ነው።▶እሷ ስታዝን የሚያቅፋት፣ ▶ስትደክም የሚያበረታታት፣ ▶ስትጨነቅ የሚያረጋጋት፣ ▶ስትደናገር የሚመክራት፣ ▶ስትናገር የሚያዳምጣት፣ ▶ስትሳሳት የሚሸፍናት፣ ▶ስታደርግ የሚያመሰግናት ባል ነው የሴት ዓይን ብሌን።🌷እውነተኛ ባል ሚስቱን ለመግዛት ሳይሆን ለመጠበቅ ይፈልጋል። ለማስፈራራት ሳይሆን ለማረጋጋት ይፈልጋል። ሁልጊዜ “እኔ ነኝ የምወስነው” ከማለት ይልቅ፣ “እንዴት ብንወስን ይሻላል?” ብሎ ያማክራታል።🌿 እሷን የሚወዳት ብቻ ሳይሆን፣ ክብሯን የሚጠብቅ ባል ያስፈልጋታል።
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    22 Sept, 13:47

    🫀 ልብ ልክ ሁሉም ነገር በአላህ ቁጥጥር ስር መሆኑን ስትረዳ ትረጋጋለች።አንተ የምትችለውን አድርግ፤ የተቀረውን ለአላህ ተወው።ምክንያቱም የምትፈራው ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም፤ የምትጠብቀውም ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም።የዛሬ ጭንቀትህ የነገ መጨረሻህን አይወስንም። የዛሬ መዘግየት የአላህ ውሳኔ እንደተረሳህ አያሳይም። አንድ በር ሲዘጋ ሁሉም በሮች ተዘግተዋል ማለት አይደለም።🌿 ኢብኑ አባስ رضي الله عنهما እንዲህ ይላሉ፦ «وَاعْلَمْ أَنَّ مَا أَخْطَأَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُصِيبَكَ، وَمَا أَصَابَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُخْطِئَكَ.» “ያመለጠህ ነገር ሊደርስብህ አልተፃፈም፤ የደረሰብህም ነገር ሊያመልጥህ አልተፃፈም።”ይህን በልብህ በጥልቀት ስትረዳ፣ ሰዎች ከአንተ ሲርቁ አትፈራም፤ አንድ ነገር ሲዘገይ አትፈርስም፤ የፈለግኸው ነገር ሳይሆን ሲቀርም አላህ እንደሚያውቅ ታምናለህ።⚠️ ኡመር ኢብኑል-ኸጧብ رضي الله عنه እንዲህ ብለዋል፦ «لَوْ كُشِفَ الْغِطَاءُ مَا ازْدَدْتُ يَقِينًا.» “መጋረጃው ቢነሳ እንኳ ያለኝ እርግጠኝነት አይጨምርም።
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    22 Sept, 06:50edited

    ለሚስትህ መልካም ውለታ ዋልላት (በዋጋ ሊተመን የማይችል መልካም አያያዝን ያዛትታላቁ ሊቅ አል-ዓላማ ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡«ከዚህ በመቀጠል እወቅ፤ ለሚስትህ ያለህ አያያዝ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ ስትገመግም፣ ለአዳጊ ሴት ልጅህ የሚሆን ባል ልታጭላት አስብና—እንዴት እንዲይዛት ትፈልጋለህ? በደረቅነትና በግፍ እንዲይዛት ትፈቅዳለህ ወይ? መልሱ፦ አይደለም የሚል ነው። ታዲያ የሌላውን ሰው ልጅ በከባድና ጨካኝ ሁኔታ መያዝ ካልወደድክ፣ የራስህ ሴት ልጅ በሌሎች ሰዎች እንድትያዝ የማትፈልገውን ነገር ይዘህ የሌላውን ሰው ልጅ ልትይዛት አይገባም። ይህ ደግሞ እያንዳንዱ ሰው ሊያውቀው የሚገባ መሠረታዊ ሕግ ነው።»(አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ ዓላ ዛዲል ሙስተቅኒዕ፣ ጥራዝ 12፣ ገጽ 381)https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
    Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
    1,14012Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    22 Sept, 06:20

    ✍ከልባቸው ፍቅር የሚሰጡ ውቦችከነፍሷ በላይ የምትወድህ እና በአንተ ዓለም ውስጥ ልዩ ቦታ ያላት አንዲት እንስት አለች። ይህቺ ሴት በነጻነት የምትተነፍሰው እና የልቧን ምስጢር ሁሉ ያለምንም ፍርሃት የምታዋይህ አንተ ፊት ብቻ ነው። ለአንተ የምታሳይህ የፍቅር ዓይን እና የምትሰጥህ እንክብካቤ ከሌላው ዓለም ፈጽሞ የተለየ ነው።ከአንተ ጋር ስትሆን ቀልዱንም ቁምነገሩንም ቀላቅላ የምታብድልህ ልዩ እብድ ትሆናለች። እንዲህ እንዳሻት የምትሆነው በአንተ ስለምትሰክንና ፍጹም ስለምትተማመንብህ ነው። በአንተ እቅፍ ውስጥ የትኛውም ምድር ላይ የማይገኝ ሰላምና እረፍት ይሰማታል። ከሌሎች ሰዎች ጋር ስትሆን ግን የንግግሯን ጥንካሬ እና ክብሯን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ተጋድሎ ታያለህ። ከአንተ ውጭ ባለው ዓለም ውስጥ አንተ ዘንድ እንደምታያት ዓይነት ለስላሳ አትሆንም።ይህቺ ልዕልት በሕይወትህ ውስጥ ልትመጣ የምትችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከእርሷ ጋር አብሮ የሚመጣው ንጹሕ ፍቅርና መታደል ድጋሚ አይገኝም። ወይ ጠብቀህ አብረሃት ትዘልቃለህ አሊያም እርሷን በማጣትህ ትከስራለህ። በኋላ ላይ የእርሷን ዓይነት ስሜት አንድ ፐርሰንት እንኳ ያላትን ሴት ፍለጋ ብትንከራተትም አታገኛትም።ስለዚህ በዚህ ልክ የሚወዷችሁን እመቤቶች አክብራችሁ ጠብቁ።
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    22 Sept, 06:09

    📢ታላቅ የነፍስ አድን ጥሪ ለወንድማችን መስዑድ አወልይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት ለጋ ወጣት ወንድማችን መስዑድ አወል ይባላል። የ16 አመት ልጅ ሲሆን ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሴ ከተማ ሲሆን እንደማንኛውም ሰው ህይወቱን ለመለወጥ በማሰብ ከቤት ከወጣ ወር ከአስራ አምስት ቀን ሆኖታል እሱም ወደ ሳዑዲ ለመሄድ በበረሃ ጉዞ የጀመረ ቢሆንም አሏህን በማይፈሩ እና አጭበርባሪ ደላሎች አማካኝነት ወደ ሊቢያ የወሰዱት ሲሆን፣አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ታስሮ እና ተዘቅዝቆ እየተደበደበ ህይወት ውጭ ህይወት ግቢ ላይ ይገኛል።ለዚህ ወንድማችን አጋቾች የጠየኩት ገንዘብ ሶስት ሚሊየን(3,000 000) ብር ቢሆንም ቤተሰብ ያለውን በሙሉ አሟጦ 500 000 ሺ ብር አጊንተዋል።ነገር ግን አጋቾቹ ሙሉው ገንዘብ የማይገባላቸው ከሆነ ወንድማችንን እንደሚገሉት እየነገሩን ይገኛሉ። እና የተከበራቹህ የሱና ወንድም እህቶቸ የተቻላችሁን በማድረግ ወንድማችንን ከሞት ቤተሰቡን ደግሞ ከጭንቀት ትገላግሉን ዘንድ በአሏህ ስም ሁላችሁም በቻላችሁ አቅም እንድትረዱን እንጠይቃቹሀለን።ባረከሏሁ ፊኩም!🔹ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት👇 1000365388184 ስም፡Saliha Hassen Endris🔹ደውለው ስለልጁ ሁኔታ ለመጠየቅና ለመርዳት የቤተሰብ ስልክ 📞 0945697003 📞 0943725521
    Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    21 Sept, 21:16

    forwarded from @asselefiyah_channel

    እንዴት አያችኋቸው ?🌸ماشاء الله🌸
    Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
    950248Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    21 Sept, 12:31

    አድስ የገባ ንፁህ የጫካ ማርባሉበት እንልካለን ማዘዝ ለምትፈልጉ በ 09 30 32 05 04 09 42 81 99 70 አቡ ሒበቲላህ ብለው ይደውሉ ። ወይም በቴሌግራም አድራሻየ ያናግሩኝ 👇👇👇 @Abu_Hibetilah_bot @Abu_Hibetilah_bot @Abu_Hibetilah_bot @Abu_Hibetilah_botአድራሻየ ደሴ መናፈሻአድስ ነገር ለማገኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
    Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )Image from a post by قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
    1,450video7Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    21 Sept, 04:28edited

    🌹ሴቶች ሊረዱት የሚገባ የወንድ ልጅ ስሜት…ትዳር በአንድ ቤት ውስጥ ሁለት ሰዎች መኖር ብቻ አይደለም፤ ሁለት ልቦች እርስ በርሳቸው መረዳዳት፣ መተሳሰብና መረጋጋት ነው።አንዳንድ ጊዜ ወንድ ስሜቱን በብዙ ቃላት አይገልጽም። የሚወደውንም ሰው ለማሳየት ሁሌ ረጅም የፍቅር ንግግር አያደርግም። አንዳንዴ ግን በአንድ እይታ፣ በአንድ ንክኪ፣ በአንድ ቃል ውስጥ የተደበቀ ብዙ ስሜት አለው።🌹ስለዚህ ባልሽ ወደ አንቺ ሲቀርብ፣ ሲያናግርሽ፣ በፍቅር ጊዜ ሲፈልግሽ፣ ይህን እንደ ቀላል ጉዳይ ብቻ አትመልከቺው። አንዳንዴ ከአንቺ የሚፈልገው ነገር አካላዊ ቅርበት ብቻ ሳይሆን፣ “አንቺ ትወጂኛለሽ፣ አንቺ ትፈልጊኛለሽ፣ አሁንም በልብሽ ውስጥ ቦታ አለኝ” የሚል የልብ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ፍቅር አንዱ የሌላውን ፈቃድ መናቅ አይደለም። በትዳር ውስጥም ሁለቱም ሰዎች ስሜታቸው፣ ድካማቸውና ሁኔታቸው እንዲከበርላቸው ያስፈልጋል። እውነተኛ ፍቅር ግፍ አይደለም፤ ርህራሄ ነው። 🌷 ባልሽ ሲደክም አሳርፊው። 🌷 ሲያዝን አዳምጪው። 🌷 ሲፈልግሽ ስሜቱን አትናቂ። 🌷 አንቺ ስትደክሚ ደግሞ ሁኔታሽን በፍቅር ንገሪው። “ዛሬ ደክሞኛል” ማለት እምቢታ አይደለም። “አሁን አልችልም፣ ግን እወድሃለሁ” ማለትም ፍቅርን መግፋት አይደለም። የሚያምረው ትዳር የሁለቱም ሰዎች ልብ የሚሰማበት ትዳር ነው።🥀 ባልሽን እንደ ባል ብቻ አትዪው… እንደ የልብሽ ሰው እዪው። ከስራ ሲመለስ ፈገግ ብለሽ ተቀበይው።
    1,3202710Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    21 Sept, 03:28

    1,120file92Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    20 Sept, 15:26edited

    🌷ሴት ልጅ ከወንድ ምን ትፈልጋለች?ሴት ከወንድ የምትፈልገው ብዙ ነገር የሚመስል ቢሆንም፣ የልቧን ሰላም የሚገነባው በአብዛኛው ከወንድ ልጅ የምትፈልገው እውነተኛ ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ክብር ነው።🌹 ① ሴትነቷን የሚወድላት ፍቅር የሚሰጣት ወንድ ትፈልጋለች፦ሴት ባሏ ሴትነቷን እንዲወድ፣ እንደ ሚስቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ተወደደች ሴት እንዲያሳያት ትፈልጋለች።እንደሚወዳት እንዲነግራት፣ በቃሉ እንዲያረጋጋት፣ በአመለካከቱም “አንቺ ለእኔ ልዩ ነሽ” የሚል ስሜት እንዲሰጣት ትፈልጋለች። እሷ ፍቅርን ስታገኝ የባሏን ወንድነት ታረጋግጣለች፤ እሷም በራሷ ሴትነት ውስጥ በሰላም ትኖራለች ስለዚ ወንድሜ በደንብ ፍቅር ስጣት።🌿 ② እዝነት እርህራሄና እንክብካቤ ትፈልጋለች፦ሴት ባሏ የምትወጣውን ድካም እንዲያይላት ትፈልጋለች። ቤትን መጠበቅ፣ ልጆችን ማሳደግ፣ ባሏን መንከባከብ ብዙ ጊዜ ሳይታይ የሚከናወን ትልቅ ሥራ ነው። አንዳንድ ጊዜ “ደክሞሻል?” ብሎ መጠየቅና፣ ●“እኔ አለሁልሽ”አብሽሪ ማለት፣ ●በርህራሄ መመልከት፣ ●እና በችግሯ ጊዜ ከጎኗ መቆም… እነዚህ ትንንሽ የሚመስሉ ነገሮች በሴት ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ይይዛሉ። ርህራሄውን ስታገኝ የመልካም ባህሪውን ውበት ትሰማለች፤ እሷም በተቻላት መጠን ባሏን፣ ልጆቿንና ቤቷን በፍቅር ትንከባከባለች።👑 ③ አንተን እንዲታከብርህ እንደምትፈልገው እሷም ካንተ ክብር ትፈልጋለች፦
    1,610108Open in Telegram
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    20 Sept, 14:28

    "ኢሬቻ በ10ደቂቃ""Irreecha daqiiqaa 10 kessatti "በፉኣድ ሙሐመድ በኦሮምኛ ቋንቋ የቀረበ ትምህርት ትምህርቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፦ https://t.me/fuadorodurus/1981
    TelegramFuad Mohammed" إريتشا في عشر دقائق " "Irreecha daqiiqaa 10 kessatti " https://youtu.be/zceQq7gaSy8?feature=shared Fuad mohammed https://t.me/fuadorodurus
  • قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

    19 Sept, 16:37edited

    🌿 አንዳንድ ሰዎች…🌿 በመጨረሻም አንዳንድ ሰዎች የተፃፉልን ዕድል ሳይሆኑ፣ የተማርንባቸው ትምህርቶች እንደነበሩ እንረዳለን።🌿 አንዳንዶች ወደ ሕይወታችን የመጡት ለዘላለም ሊቆዩ አይደለም፤ አንድ ነገር አስተምረውን ከዚያ ሊሄዱ ነው።🌿 አንዳንዶች ደስታን ያመጣሉ፣ አንዳንዶች ሕመምን፤ አንዳንዶች ፍቅርን ያስተምሩናል፣ ሌሎች ደግሞ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ያሳዩናል።🌿 አንድ ቀን ወደኋላ ተመልሰን ስናይ፣ በእነሱ ላይ ያፈሰስነው እንባ ሁሉ ምክንያት እንዳልነበረው እንረዳለን። የተሰበረው ልብ ምናልባት የተሻለ ሰው ለመሆን የከፈልነው ዋጋ ነበር። አንዳንድ መለያየቶች ቅጣት አይደሉም፤ ጥበቃ ናቸው። አንዳንድ የተዘጉ በሮች ኪሳራ አይደሉም፤ አላህ ከማናውቀው ነገር የሚጠብቀን መንገድ ናቸው።🌿አንዳንድ የተሰበሩ ተስፋዎችም ልባችንን ወደ እውነተኛው ተስፋ እንድናዞር ያደርጉናል። ስለዚህ የሄዱትን ሁሉ በእንባ አንያዛቸው፤ የተማርነውን ትምህርት እንያዝ። የሰጡንን ትዝታ እናመስግን፣ የወሰዱብንንም ልባችን እንልቀቅ።🌿እና በመጨረሻ… የተፃፈልን ሰው ከሆነ ርቆ ቢሄድም መንገዱ እንደገና ያገናኘዋል፤ ያልተፃፈልን ከሆነ ግን ምንም ያህል ብንይዘው የሚቆይ አይሆንም።🌿 ሰዎች አንዳንዴ የሕይወታችን መድረሻ አይደሉም፤ መንገዱን ያስተማሩን ምዕራፎች ናቸው። እና አንድ ቀን ያንን ምዕራፍ በእንባ ሳይሆን በምስጋና እንዘጋዋለን። 🌿
    1,530128Open in Telegram