gram news
Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን} channel avatar

Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

@abureyanmustefa

👉የዚህ ቻናል አላማ በአላህ ፍቃድ ሰዎች ተውሂድ እና ሱናን እንድያውቁ ከሽርክ እና ከቢድዓ እንዲሪቁ ለማድራግ ነው ❗️❗️ በሰለፎች (በደጋጎች) መንገድ !! ↪️📚የሱና ዑለማዎችና ኡስታዞች የኪታብ ቂርኣትና ሙሓደራዎች ፈታዋዎች ሌሎቹም ጠቀሚ ፅዑፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው 👌 https://t.me/ABUREYANMUSTEFA https://t.me/ABUREYANMUSTEFA

ProjectsENReligion

5,100subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    22 Sept, 19:14

    🌊✨ ጥያቄ ! ✨🌊📖❓ በሸሪዓችን «ቢድዓቱል ሐሰና» (ጥሩ ቢድዓ) የሚባል ነገር አለንዴ?👇 ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላችሁን የሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ! 📲🌊
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    22 Sept, 03:52

    አላህ ብዙ ውለታ ውሎልን እኛ ግን ሚገባውን ምስጋና አናመሰግነውም። ስናመሰግነው እንደሚጨምር ቃል የገባልንን ረስተን የጎደለንን እያየን እናማርራለን።አላህ ሆይ ካመስጋኝ ባሮችህ አድርገን🤲
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    21 Sept, 04:35

    ኧረ ክፋት… ኧረ ትቢት…………አንዱ የሁዲ ብዙ የሰው ዕዳ ተሸክሞ ይሞታል። ነገሩን የሚያውቁ የሰፈሩ ዑለማዎች ወደ ሟች ልጅ በመምጣት;"እንደው ቤቷን ሽጠህም ቢሆን አባትህ ተሸክሞት ከሞተው ዕዳው ብትቀንስለት" አሉት።"አባቴ ላይ የነበረውን ዕዳ ጨርሼ ብከፍልለት ጀነት ይገባልን?" አላቸው"ኣይ ጀነት እንኳ አይገባም" አሉት።እንግዲያውስ "እሱም በእሳቱ እኔም በቤቱ እንኑርበት ተዉኝ!!" አላቸው።
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    20 Sept, 15:36

    ውዴታቸው ካለህ ለሰው ልጅ አለቃ መንዙማህን ትተህ በሐዲስ ተብቃቃ።ብትወዳቸውማ ሰይዱል አንቢያ ሱናቸው ለያዘ ባላልክ ወሀቢያ።አፍህ ይሞግታል የረሱል ውዴታ ስራህ ተቃራኒ የሚያስቆጣ ጌታ።ወንድና ሴት አብሮ ሆኖ በአንድ ቤት መውሊዳቸው ብሎ ይላል ሰለዋት።ምን ዓይነት ሰለዋት ምን ዓይነት ውዴታ ረሱል በጀነት አንተ ሌላ ቦታ??ወዳጅ ለወደደው ይታዘዛል እንጅ ክልከላው ተላልፎ አያነሳም ፈንጅ።በልብህ ውስጥ ካለ የነብዩ ፍቅር ልደታቸው ሳይሆን ትዕዛዛቸው አክብር።
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    19 Sept, 02:57

    በዝንብ ምክንያት አንዱ እሳት ሌላው ጀነት ገቡ!!ኢማሙ አሕመድ በዘገቡት ወደ ረሱልﷺ በተጠጋ ሐዲስ እንዲህ ይላሉ፦የሆኑ ህዝቦች የሚያመልኩት ጣዖት ነበራቸው። በዝያ አካባቢ የሚያልፍ ማንኛውም ሰው ለዝያ ጣዖት ቁርባን እንዲያቀርብ ያስግድዱታል።አንድ መንገደኛ ሲያልፍ "ለአምላካችን ቁርባን አቅርብ" አሉት። "ምንም የማቀርበው ነገር የለኝም" አላቸው። "ዝንብም ቢሆን አቅርብ" አሉት። እሱም ዝንብ አቀረበለት፧ በዚህ ሰበብ እሳት ገባ።ሌላም ሰው መጣና ለእሱም "ለአማላካችን ቁርባን አቅርብ" አሉት። እሱ ግን "ከአላህ በስተቀር ለማንም ምንም ዓይነት ቁርባን አላቀርብም" አላቸው። አንገቱን ብለው ገደሉት፧ ጀነት ገባ።
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    17 Sept, 16:44

    ምክር ለወዳጅ🚩🚩📖መርህህ ቁርኣን እና ሐዲስ ይሁን!! አረዳድህ ቀደምቶችህ በተረዱት ልክ ይሁን; የትኛውም ንግግር ስትናገርም ይሁን የትኛውም አቋም ስቲዝ በዚህ አካሄድ ላይ የቀደመህ መኖሩን እርግጠኛ ሁን።📊ሐቅን ዕወቅ የሐቅ ባልተቤቶች ታውቃቸዋለህ; ከሐቅ ውጪ ያለው ባጢል ነው፤ ከሐቀኞች ውጪ ያሉት ባጢል ላይ ናቸው‼️🔥በሚጠፉ ሰዎች መጥፋት አትገረም፤ የፀኑ ሰዎች "እንዴት ፀኑ?" ብለህ ጠይቅ ያፀናቸው ነገር አጥብቀህ ያዝ‼️🚩የማንም ወቀሳ እንዳይጎዳህ እና የማንም ሙገሳ እንዳያስጨንቅህ ከፈለክ ስራህን ለ☝️አላህ ብቻ ብለህ ስራ‼️📈የኸይር በር ለመክፈት ታገል፤ የሸር በር ለመዝጋት ልፋ፤ "ልጠንቀቅ" በሚል መረብ ታስረህ በዳዕዋ ላይ ከሚደረግ እንቅስቃሴ ራስህን እንዳትቆጥብ❗️🚫ላለ መሳሳት ሞክር፤ ስህተትን ፈርተህ ግን ከስራ እንዳትርቅ‼️⛔️ሐቅን ይዘህ በምታደርገው ጉዞ ብቸኝነትህ ጭርታ እንዳይፈጥርብህ፤ በባጢል ላይ የሚጎርፉት ብዛታቸው እንዳይሸነግልህ‼️
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    17 Sept, 05:19edited

    ከደጋጎች አንዱ ለይል ተነስቶ ይሰግድና…………አላህ ሆይ! እኔ ማለት፦ ያ…… ሰዎች የሚያውቁኝ ሷሊሕ ሳልሆን; አንተ የምታውቀኝ ወንጀለኛው ባሪያህ ነኝ፤ አደራህ ግርዶሽህ እንደትገልጥብኝ!! ብሎ ያለቅስ ነበር።ቦታ ከማንሰጣቸው ትላልቅ የአላህ ፀጋዎች አንዱ; ድክመታችን, ዓይባችን, ወንጀላችን እንዳይታይ የሰተረበት ግርዶሹ ነው።አንደኛችን ሲትሩ ተገልጦ ሙሉ ማንነታችን ሰዎች ቢመለከቱት; ይቅርና ሌላው ሰላምታ እንኳ የሚያቀርብልን እስከማይኖር ሁሉም ይጠየፈን ነበር።
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
    73852Open in Telegram
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    16 Sept, 07:18

    አዲስ ንጋት...…… ከአላህ ጋ የሚደረግ ግንኙነት የሚታደስበት…… ልቦች ጌታቸው ላይ የነበራቸው ተስፋ የሚሞሉበት…የዕለቱ ትልቁ ስኬት ማለት; 💫ቀንህን ለጌታህ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ስትጀምረው ነው!!💫የዕለቱ የመጀመሪያ ጉዞህ ወደ አላህ ቤት የምታደርገው ጉዞ ሲሆን ነው!!💫የዕለቱ የመጀመሪያው ንግግርህ ከጌታህ ጋ የምታደርገው ንግግር ሲሆን ነው!!ለልቡ ብርኃን፧ ለቀልቡ ሰኪና አጎናፅፎ, የሌሊትና የቀን መላኢካዎች በተጣዱበት, ውሎውን በሰላት የጀመረ ሰው ምንኛ የታደለ ነው??!!🤲አላህ ይወፍቀን🤲
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    16 Sept, 05:48edited

    ለሚስትህና ለልጆችህ የምታወጣው ፧ የቤት ውስጥ ፍጆታዎች እና የመሣሠሉ ወጪዎች; ያላገባህ ቢሆን ኖሮ ይጠራቀምልህ የነበረ ሀብትህ ነው የሚመስልህ??? ወይስ ኖርማል ነህ???እውነታው ይህ ነው; ገቢህ የሚሰፋልህ በሚሰጥህ ሀላፍትና ልክ ነው!!የሁሉም ሪዝቅ በአላህ እጅ ነው፧ አንተ ግን የቤተሰቦችህን ሪዝቅ ለማዳረስ የተገራህ መስመር ብቻ ነህ።በአንተም ይሁን በሌላ በኩል አላህ ለእነርሱ የወሰነላቸው ሪዝቃቸው ይመጣላቸዋል። ከመሆኑም ጋ አላህ የእነርሱ ሀላፍትና ላይ የመቆም ክብር አጎናፅፎሃል።የምታደርገው ወጪ ከገቢህ የሚቀነስ ብዝበዛ አድርገህ ማሰብ ሳይሆን => አላህ ለዚህ ክብር ስለመረጠህ አመስግነው
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    15 Sept, 16:37

    forwarded from @hussinassilty

    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    15 Sept, 16:36

    "مَنْ تتبع رخص العلماء فقد تزندق"የዑለማዎች ማግራራት የተከተለ ሰው ዝንዲቅ ይሆናልአንድ ሱንይ ሰለፍይ ዓሊም በሁለት መልኩ ወይም ከሁለት በአንዱ ሊሳሳት ይችላል።1ኛው, ምንም ያህል ዕውቀቱ ጥግ የደረሰ ቢሆንም ሰው ነውና እንደማንኛውም ሰው ሊሳሳት ይችላል። 2ኛው, ኢጅቲሃድ አድርጎ; ባወቀውና በደረሰበት ዕውቀት ልክ ጥናትና ምርምር አድርጎ የሆነ አቋም ሊይዝ ወይም ፈትዋ ሊሰጥ ይችላል። ያንን አቋሙ ግን ሌላ እሱጋ ባልደረሰ ዕውቀት ሲመዘን ስህተት ይሆናል። ይህንኑ በማስመልከት ነው ረሱልﷺ እንዲህ ያሉት፦«አንድ ዓሊም የራሱን ጥረት አድርጎ ትክክል ከሆነ ሁለት ምንዳ ይኖሩታል፤ የራሱን ጥረት አድርጎ ከተሳሳተ (ለጥረቱ) አንድ ምንዳ ይኖረዋል: ስህተቱ ይማራል።»ዓሊም ይሳሳታል ማለት ነው። ችግሩ የእሱ መሳሳት ላይ ሳይሆን አንዳንድ ልበ ደካሞች ዘንድ ያለው ልፍስፍስነት ላይ ነው።ዑለማዎች ናቸው ሱንዮች ናቸው በሚል ሽፋን ሁሌም ዑለማዎች የሚያግራሩትን ብቻ አነፍንፈው የሚከተሉ አሉ። የዚህ ዓይነቱ ነው "ከእስልምና የወጣ ዝንዲቅ መሆኑ አይቀርም" የተባለው።የሆነ ዓሊም ፎቶ ሊያግራራ ይችላል፤ ሌላኛው ዓሊም ኒቃብ ሊያግራራ ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ፂም ማሳጠር ሊያግራራ ይችላል፤ አንዱ መውሊድ ሲያግራራ፤ ሌላው ልብስ መጎተት ሊያግራራ ይችላል። ሰው እንደመሆናቸው ተሳስተው ወይም ዓሊም እንደመሆናቸው ኢጅቲሃድ አድርገው ተሳስተው ሊያግራሩ ይችላሉ;ሁሉንም ጋ እየዞረ ያግራሩትን ብቻ የሚለቃቅም ሰው መዘንደቁ አይቀሬ ነገር ሆኗል።
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    14 Sept, 10:20

    የኛ ነብይ ይህ ናቸው!! አውነተኛ!! በንግግራቸው፣ በቃላቸውና በድርጊታቸው ሁሌም እውነተኛ ነበሩ። በፍጹም ውሸት ተናግረው አያውቁም። ከመልዕክተኝነታቸው በፊት እንኳ "ታማኙ ሙሐመድ ሙሐመድ አል_አሚን" ይባሉ ነበር። [ቡኻሪ:3559] አደራ ጠባቂ!! በገንዘብና በክብር ረገድ በጣም የታመኑ ነበሩ። አደራን ለባለቤቱ ያደርሱ ነበር፤ ማንንም አታለው አያውቁም።
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    14 Sept, 10:20

    የኛ ነብይ ይህ ናቸው!!አውነተኛ!! በንግግራቸው፣ በቃላቸውና በድርጊታቸው ሁሌም እውነተኛ ነበሩ። በፍጹም ውሸት ተናግረው አያውቁም። ከመልዕክተኝነታቸው በፊት እንኳ "ታማኙ ሙሐመድ ሙሐመድ አል_አሚን" ይባሉ ነበር። [ቡኻሪ:3559]አደራ ጠባቂ!! በገንዘብና በክብር ረገድ በጣም የታመኑ ነበሩ። አደራን ለባለቤቱ ያደርሱ ነበር፤ ማንንም አታለው አያውቁም። [ቡኻሪ:3534]አዛኝ!! ለሰዎች፣ ለእንስሳትና ለአእዋፍት ሳይቀር በጣም አዛኝ ነበሩ። በጣም ሩህሩህ ነበሩ፤ ማንንም አይጎዱም ነበር። [ሙስሊም: 2316]ትሁት!! ከሰዎች ጋር በጣም ትሁት ነበሩ። ከድሆች ጋር ይቀማመጣሉ፤ ራሳቸውን ይኻድማሉ፤ ከማንም ሰው ዕርዳታ አይጠይቁም ነበር። [ሙስሊም:2865]ፍትሓዊ!! በፍርዳቸው እና ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ፍጹም ፍትሓዊ ነበሩ። እውነትን ያስፈጽሙ ነበር፤ ፍርዱ በራሳቸው ወይም በቤተሰባቸው ላይ ቢሆን እንኳ።
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    13 Sept, 03:26

    ዘከሪያﷺ……………📖{رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا} {ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ} ብሎ ከለመነ በኋላ;{وَأَنتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ} {አንተ ከወራሾች ሁሉ የተሻልክ ነህ} ብሎ አስከተለ።ቆም ብለህ ስታየው እንዲህ የሚል ይመስላል፦ "ጌታዬ ሆይ! በጠየኩህ መሠረት የሚወርሰኝ ልጅ ባትሰጠኝ እንኳ: አንተ ከወራሾቹ ሁሉ የተሻልክ ወራሽ ነህ"ይህ አገላለፅ በማማር ደረጃ እጅግ ድካ የደረሰ ውብ ገለፃና ከረቡል ዓለሚን ጋ የተደረገ ያማረ ኣደብ ያለው አነጋገር ነው።ሁሉም ሙእሚን ይህንን መገንዘብ አለበት፦ አላህን ለምነኸው: የለመንከው ነገር ቀጥታ ባይሰጥህ እንኳ እሱ ዘንድ የሚደረግልህ የዱዐህ ምትክ 👇 👉አንተ ፈልገህ ከለመንከው ነገር የተሻለና በላጭ ነው!!
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    12 Sept, 04:15

    ወንጀልህ ምንም ያህል ቢበዛ እንኳ ወደ አላህ ከመመለስ አታመንታ!!በወንጀል ጥላ ስር በሆንክ ጊዜ የሰተረህ ጌታህ: በተውበት ክንፍ ስትንሳፈፍ አያዋርድህም!!
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    10 Sept, 07:20

    ሰለፊያ ዱሮም የነበረች አሁንም ያለች ወደ ፊትም የምትኖር መንገድ ናት ኢንሻ አሏህ።
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    10 Sept, 03:06

    እጅ እግር እንስጥ ለአሏህ ትዕዛዞች ሁሉ እና ለመልክተኛ ትዕዛዝ
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    8 Sept, 15:33

    ኩራት ትዕቢቱ ዘረኝነት ክፋቱ ብሽሽቅና ውሸቱ ሁሉም እዚጋ ያበቃል ።https://t.me/ABUREYANMUSTEFA
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    8 Sept, 13:34edited

    ረሱልﷺ…………📚«إنَّ أوَّلَ ما يُحاسَبُ به العبدُ يومَ القيامةِ من عملِه صلاتُه، አንድ ባሪያ የቀቂያማ ዕለት ከስራዎቹ ሁሉ መጀመሪያ የሚጠየቀው ስለ ሰላቱ ነው:فإن صلحت فقد أفلح وأنجح، እሷ ከተስተካከለችለት በእርግጥም ድኗል ተሳክቶለታል፤وإن فسدت فقد خاب وخسر እሷ ከተባለሸት ከስሯል ጠፍቷል።»አሉ።
    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}
  • Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}

    8 Sept, 03:45

    Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}Image from a post by Mustefa kedir➣ሙስጠፋ ኸድር {Abu reyan አቡ ረያን}