Latest posts

Addis Admass
22 Sept, 19:58
"ከ10 ዓመታት በኋላ ወንድሜን ዶክተር ቴድሮስን በኒው ዮርክ ድንገት በማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ።" - አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት
Addis Admass
22 Sept, 19:46
ከአስር ሺህ በላይ የብራና መጻሕፍት ወደ ዲጂታል ተቀየሩከአስር ሺህ በላይ የብራና መጻሕፍት በዲጂታል ቅጂ ተዘጋጅተው ለጥናትና ምርምር ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ታሪክና የብራና ጽሑፎች ተመራማሪው አቤሜሌክ ኤርሚያስ ገለጹ። ተመራማሪው እንደገለጹት፤ እስካሁን በተከናወኑት በዲጂታል የማዘጋጀት ጥቂት ሥራዎች እንኳን፣ ቀደም ሲል ማንም ሊደርስባቸው ያልቻላቸው አዳዲስ የንግድ መስመሮች እንደነበሩ ማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም የብራና ጽሑፎችን ለሰዎችና ለተመራማሪዎች በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።በዲጂታላይዜሽን ሥራው አማካኝነት የብራና መጻሕፍቱ ባለቤትነትና የት እንደሚገቡ በግልጽ ማወቅ በመቻሉ፣ ቀደም ሲል ተሰርቀው የነበሩ በርካታ የብራና ጽሑፎችን ማስመለስ እንደተቻለም ተመራማሪው አቤሜሌክ ገልጸዋል። ይህ አዲስ ስኬት የአገሪቱን ጥንታዊ የታሪክና የባህል ቅርስ ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው መድረክ ላይ ተመልክቷል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 19:36
«ኢትዮጵያ ለአንድ ሰው ልትሰጥ የሚገባትን የመጨረሻ ክብር ሰጥታኛለች!»የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው "ድል ቁርሱ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ። በ8 ምዕራፎችና በ355 ገጾች የተቀነበበው ይህ መጽሐፍ፤ የፊልድ ማርሻሉን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያሳለፉትን ውጣ ውረድ፣ ለሀገር ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እና የሰጡትን ቁርጠኛ አመራር በስነ-ጽሑፋዊ ለዛ ይተርካል።በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በራሳቸው ሕይወት ላይ መጽሐፍ ለማሳተም ፍላጎት አልነበራቸውም፤ ነገር ግን ታሪካቸው ለቀጣዩ ትውልድ አርአያ ሊሆን ይችላል በሚል በብዙዎች ጉትጎታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። "በበላይ ዘለቀ፣ በአብዲሳ አጋ ሀገር ይገነባል፣ በፊልድ ማርሻል ብርሃኑም ይገነባል፤ ነገር ግን የሆነን ሰው ለማግነንና ለመካብ መሆን የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።አክለውም "ኢትዮጵያ ለአንድ ሰው ልትሰጥ የሚገባትን የመጨረሻ ክብር ሰጥታኛለች፤ እኔም ለኢትዮጵያ የሰሰትኩት አንዳች ነገር የለም" በማለት የላቀ ምስጋናቸውንና ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ይህ መጽሐፍ የነገን መከላከያ ለመገንባትና ትውልድን ወደፊት ለማሸጋገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አፅንኦት ሰጥተውበታል።ENA-የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 19:28
የመተሃራ ከተማ ከንቲባና አሽከርካሪያቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈበኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መተሃራ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ አዲሱ ዋቆ እና አሽከርካሪያቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ አደጋው የደረሰው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከመተሃራ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር በማይሞላ «ኢላላ» በተባለ ቦታ ላይ ሲሆን፣ የነበሩበት ተሽከርካሪ ከቦቴ መኪና ጋር በመጋጨቱ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ታውቋል።እንደ አካባቢው ነዋሪዎች እና የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገለጻ፣ አሽከርካሪው አደጋው በደረሰበት ዕለት ወዲያውኑ ሕይወቱ አልፏል። ከንቲባ አቶ አዲሱ ዋቆ ግን አደጋው ቢደርስባቸውም በወቅቱ ተርፈው በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ የቆዩ ቢሆንም፣ ሕይወታቸውን ማዳን ሳይቻል ቀርቶ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 19:18
የኖርዲክ የምግብ ሳምንት በማርከስ አዲስ ተጀመረበአዲስ አበባ የሚገኘው የፊንላንድ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፣ በታዋቂው ኢትዮጵያዊ-ስዊደናዊ ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን የሚመራው «ማርከስ አዲስ» ሬስቶራንት የኖርዲክ የምግብ ሳምንትን ማስተናገድ ጀምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት 47ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው ይህ ሬስቶራንት፣ የከተማዋን ማራኪ እይታ እያሳየ ልዩ የምግብ ተሞክሮ ያቀርባል። ኤምባሲው እንደገለጸው፤ የምግብ ባህል ሰዎችን የሚያቀራርብና ባህልን የሚያስተዋውቅ ትልቅ ድልድይ ነው።በቀጣዮቹ ሳምንታት የኖርዲክ ሀገራት የምግብ ባህላቸውን የሚያስተዋውቁ ሲሆን፣ የፊንላንድ ሳምንት ደግሞ ጥቅምት 7 ይጀምራል። ኤምባሲው የፊንላንድን ባህላዊ ጣዕሞች በአዲስ አበባ ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ተገኝተው ይህንን ልዩ ተሞክሮ እንዲካፈሉ ጥሪ አቅርቧል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 19:07
የክቡር አቶ ይልማ ደሬሣ የአሜሪካ የሚሲዮን ግብ ምንና ምን መሆኑ እንደተገለጸው፤ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዋና መልዕክተኛ ዋሽንግተን እንደደረሱ፤ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የተላከውን ልዩ መልዕክት ለአሜሪካው መሪ ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ለማቅረብ ቀጠሮ ጠየቁ፡፡ የስቴት ዴፓርትመንት፤ (ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) እና የዋይት ሐውስ ቤተመንግሥት ኃላፊዎች ከተወያዩበት በኋላ፤ የተሻለው መንገድ ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት እ.ኤ.አ ሐምሌ 7 ቀን 1943 ዓ.ም የዓለም የእርሻና የምግብ ጉባኤ የመልዕክተኞች መሪዎች የሆኑትን የሬሴፕሽን ግብዣ በማድረግ ስለሚቀበሉ! በዕለቱ ክቡር አቶ ይልማ ደሬሣን የንጉሠ ነገሥቱን ልዩ መልዕክት ለማቅረብ እንዲችሉ ተወሰነ፡፡በመሠረቱ አቶ ይልማ ዴሬሣ የያዙት ዋናው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በእንግሊዞች ወታደራዊ አስተዳደር የደረሰባትን ችግር በተቻለ ያህል ለአሜሪካው መሪ በቃል ለማስረዳትና በሜሞራንደም (ማስታወሻ) ያዘጋጁትንም ጽሑፍ አያይዞ በእጅ - ለመስጠት ነው።በተጨማሪም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለወዳጃቸው ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ፈርመው የላኩትን የመታሰቢያ ፎቶግራፍ ለማቅረብ አቶ ይልማ ተዘጋጅተዋል፡፡ ነገር ግን የዋይት ሐውስ ፕሮቶኮል ሹም አቶ ይልማ ዴሬሣ ፕሬዚዳንቱን እንዲያነጋግሩ የፈቀደላቸው ጊዜ፤ ከሰባት ደቂቃዎች የማይበልጥ ስለሆነ በዚች ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ዋና ዋና ችግሮች አሟልቶ ለማስረዳት ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መልዕክተኛ እጅግ የከበደ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ( School Of Economics ) የተመረቁትና ጣዕም ያለው እንግሊዝኛ ተናጋሪ የሆኑትTelegramAddis Admassየአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ
Addis Admass
22 Sept, 19:07
"እናንተ ኢትዮጵያውያኖች አገራችሁ ያላትን የተከበረ ጥንታዊ ታሪክና ባሕል የማንፀባረቅ ተሰጥዎ ያላችሁ ናችሁ."-ፕሬዚዳንት ሩዝቬልትክቡር አቶ ይልማ ደሬሣ.......ታላላቆቼ ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስና ክቡር አቶ መኮንን ሀብተወልድ የገለጻችሁልኝ አስተያየት በአዕምሮዬ ስለተቀረጸ፤ ለሥራዬ መልካም ድጋፍ ሆኖ እንደሚረዳኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እዚህ ላላችሁት ለታላላቆቼና ለጓደኞቼ በአጭሩ ለማረጋገጥ የምፈልገው፤" .........ለእኔ ለይልማ ደሬሣ በዚህ ዓለም ከኢትዮጵያ የሚበልጥብኝ ነገር የለም......."፡፡ ስለዚህ ለተላኩበት ለአሜሪካ ለሚያዳምጡኝ የአገሬን ችግር በተቻለኝ ዘርዝሬ አስረዳለሁ፡፡ ለሚከራከሩኝም በተቻለኝ ጠንክሬ እሟገታለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዘ አስተያየት ሲሰጡ፤ ሥራ ሳይጀመር ብዙ የሚናገር ብዙ አይሠራም" ብለዋል፡፡ ስለዚህ እኔም ጥቂት የምናገርና ብዙ የምሠራ ሆኜ ለመገመት እንድችል፤ ንግግሬን ማሳጠር እወዳለሁ፡፡ ለሰጣችሁኝ ጥልቀት ላለው ምክርና ለገለጻችሁልኝ የጋለ መልካም ምኞት ከልብ የሆነ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በሰላም ይግጠመን ብዬ እሰናበታችኋለሁ፡፡ይህንን የተናገሩት ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳ ሃገራቸውን ከእንግሊዝ ሞግዚትነት ለማላቀቅ ይቻል ዘንድ ወደ አሜሪካ መልዕክት ይዘው እንዲሄዱ ኃላፊነት የተሰጣቸው በሽኝት መርሃ ግብር ቀን ላይ ነበር።ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳ [ በአሜሪካን --- ዋሸንግተን ዲሲ ]⬇️⬇️
Addis Admass
22 Sept, 18:50
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን እስር ኮነኑበትግራይ ክልል የሚገኙ የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች 6 የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ሰኞ ዕለት ማሰራቸው ተሰምቷል። መምህራኑ በታጠቁ ኃይሎች ተይዘው የተወሰዱት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ከሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ እንደሆነ ከምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ድርጊቱን አጥብቀው የኮነኑ ሲሆን፣ በትግራይ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያደፈርሱ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እስር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን ህልውናና የተማሪዎችን የወደፊት እድል አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 18:42
በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል፡ ተመድየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ ሊባባስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለው ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቲፋኒ ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በአገሪቱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መፍጠራቸው፣ የድሮን ጥቃቶች መደጋገማቸውና የጸጥታ ችግሮች መቀጠላቸው ለስጋቱ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አክለውም ወታደራዊ ርምጃ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንም ሆነ ነባር ቅሬታዎችን ሊፈታ እንደማይችል በመግለጽ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ አጥብቀው ጠይቀዋል።በተያያዘ ዜና፣ በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኦዞኒያ ኦጄሎ በአገሪቱ ሰላም፣ መተማመና አብሮነት እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል። ሃላፊው የሁኔታውን አሳሳቢነት በማንሳት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሉትን ልዩነቶች በሰላማዊ ንግግር ብቻ እንዲፈቱ እና ከምንም በላይ ለዜጎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስበዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 17:38
የኢራን መሪ ሞጅታባ ካሜኒ በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ይፋ ሆነየኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ማክሰኞ ዕለት የሀገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት ሞጅታባ ካሜኒ በእጅ የተጻፈ ነው ያሉት አንድ ደብዳቤ ይፋ አደረጉ።ይህ ደብዳቤ፣ በየካቲት ወር በአባታቸው ቢሮ ላይ ከደረሰ ጥቃት መሪው በሕይወት መትረፋቸውን ሊያሳይ የሚችል የመጀመሪያው ምልክት ሊሆን ይችላል ተብሏል። አባታቸው አሊ ካሜኒ በዚያው ጥቃት ሕይወታቸው አልፏል።ከጥቃቱ ወዲህ ሞጅታባ ካሜኒ በሕዝብ ፊት ታይተውም ሆነ ድምፃቸው ተሰምቶ አያውቅም። ምንም እንኳ በስማቸው የተለያዩ መግለጫዎች ቢወጡም፣ እውነተኛ ፎቶግራፋቸው፣ ቪዲዮአቸው ወይም የድምፅ ቅጂያቸው ፈጽሞ አልወጣም።አዲስ የወጣው ደብዳቤ ነሐሴ 1 ቀን የተጻፈ ሲሆን፤ የተላከውም ለኢራን አብዮታዊ ዘብ የኤሮስፔስ ኃይል አዛዥ ለሆኑት ማጂድ ሙሳቪ ነው። ደብዳቤው አዛዡ ያቀረቡትን ሪፖርት አድንቆ፣ የቁሳቁስ አቅርቦት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል።በተጨማሪም መሪው ለአዛዡ ሲጽፉ «የእርስዎን እና የሠራተኞችን ውድ ሕይወት መጠበቅ ጥብቅ አደራዬ ነው» በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።Iran International -የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 17:35
የብርቱካን ሚደቅሳ ገንቢ መልዕክት በርካታ የዘመኑ ወጣቶች ሙያን፣ሥራ እና ክህሎትን የሚይዙበት መንገድ እጅግ ይገርመኛል። ለዓመታት ተምረው ከተመረቁበት ሙያ ፍጹም በተለይ መስክ/ክህሎት (አንድም ለገቢ ሲልም ለደስታ) ራሳቸውን አሠልጥነው ብዙ ዓይነት ስራ ያለምንም መጎረባበጥ ጎን ለጎን ያስኬዳሉ። ሀኪሟ ትዘፍናለች፤ ኢንጂነሩ ይስላል ...ወዘተ። ይህን እውን ለማድረግ ሲሉ እኛ ከለመድነው በተለየ
Addis Admass
22 Sept, 17:11
የብርቱካን ሚደቅሳ ገንቢ መልዕክትበርካታ የዘመኑ ወጣቶች ሙያን፣ሥራ እና ክህሎትን የሚይዙበት መንገድ እጅግ ይገርመኛል። ለዓመታት ተምረው ከተመረቁበት ሙያ ፍጹም በተለይ መስክ/ክህሎት (አንድም ለገቢ ሲልም ለደስታ) ራሳቸውን አሠልጥነው ብዙ ዓይነት ስራ ያለምንም መጎረባበጥ ጎን ለጎን ያስኬዳሉ።ሀኪሟ ትዘፍናለች፤ ኢንጂነሩ ይስላል ...ወዘተ። ይህን እውን ለማድረግ ሲሉ እኛ ከለመድነው በተለየ የፍሪላንስ ስራ ምቾት ይሰጣቸዋል -ከአንዱ ወደሌላው ሳይቸገሩ ለመሯሯጥ።በዚህ አይነት ትጋት እና ስኬት በተምሳሌትነታቸው ካስደነቁኝ ወጣቶች አንዱ የሆነው የሀዋሳው ብርቱ ሰው Base Berhanu (የህክምና ዶክተር በዛብህ ብርሀኑ) 'አንሙት Clinic' የሚል ርዕስ ያለው ሲትኮም ጽፎ እና ዳይሬክት አድርጎ በሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለእይታ አቅርቧል።ወዳጆች፣እንይለታ!?ያለንን አስተያየትም እንለግሠው።እንኳን ደስ ያለህ ቤዝ😍የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 17:06
"በኔ ወጪ ልትሞሸሪ!?"(የግል ምልከታ)አንድ እብድ ነበር በሰፈራችን። ገና በወጣትነቱ ነው የተቃወሰው። ሁሌም መንገድ ላይ ሲሄድ አንድ ቃል ይደጋግማል። "በኔ ወጪ ልትሞሸሪ? አይሆንም! በጭራሽ!" ይላል። የሰፈሩ ሰው ለሰውዬው በጭራሽ የሚል የቅፅል ስም ሰጠው። ለምን እንደዚያ እንደሚል ብዙ ሰው አልገባውም።ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ ቅምቀማ ቤት ጋሽ ዘሌ ሲያስረዱ ሰማሁ። ልጁ ቀለሜ ተማሪ ነበር። ዩኒቨርስቲ ሳለ አንዲት ሁለተኛ ደረጃ የምትማር ጉብል ይወዳል። በሂደት ተቀራረቡ። ከዚያ እሱ ተመርቆ ስራ ያዘ። ያለውን በሙሉ በሷ ላይ invest ማድረግ ጀመረ።እሷም በለስ ቀንቷት ዩኒቨርስቲ ገባች። ይሄኔ ጀለስ ብር ይልካል። የፈለገችውን ነገር ያሟላል። እያለ ሄደና የምርቃቷ ቀን ሳትጠራው ቀረች። ሚስኪኑ ጀለሴም እተንቦገቦገ ዩኒቨርስቲ ድረስ ሄደ። ልጅት ከሌላ ጎረምሳ ጋር ሽር ብትን እያለች መሆኑን ተረዳ።ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነቀለ። "በኔ ወጪ ልትሞሸሪ? አይሆንም...!" እያለ ከዚያ ግቢ ወጣ። ወደ ቤቱም አልተመለሰም። The rest is history።ይሄ ምን አስታወሰኝ መሰላችሁ:- ህወሃት ጥምረቱን ጋልባ ወደ ሸገር ትገሰግሳለች። ከዚያስ አትሉም? ከዚያማ በኛው ወጪ ትሞሸራለች፣ ካስፈለጋትም በኛው ወጪ ጓጆ ትወጣለች (ሀገር ታዋልዳለች)።በኛው ወጪ ልትሞሸሪ!?Moges Zewdu Teshome -የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 17:00
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ እና ወታደራዊ ጀግንነት የሚያሳይ «ድል ቁርሱ» የተሰኘው መጽሐፍ ተመረቀ።መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ መሆኑን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል፡፡በዚሁ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አስፋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ዛዲግ አብራሃ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ደቦጭ በመጽሐፉ ላይ ምሁራዊ ሂስና ዳሰሳ አቅርበዋል፡፡በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 16:20
ኢትዮጵያ በ81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነውበፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ (የፕላንና ልማት ሚኒስትሯን ዶ/ር ፍጹም አሰፋን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ) 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።“መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን መፍጠር” በሚል ልዩ መሪ ሐሳብ በኒውዮርክ እየተካሄደ ያለው ይህ ጉባኤ፣ ዓለም አቀፍ መተማመንን ለማደስ እና የተቋማት ማሻሻያዎችን በጋራ ለመምራት ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።ኢትዮጵያ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በሚደረጉ በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ስብሰባዎች ላይ በንቃት እንደምትሳተፍ የተገለጸ ሲሆን፣ በጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሟን እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች እንደምትሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 16:07
“ማርገዝ“ የምትወደው የ14 ልጆች እናትአፍሪካ አሜሪካዊት የሆነችው ካረን ዴሪኮ የ14 ልጆች እናት ስትሆን፣ ማርገዝ እጅግ እንደምትወድና ጤናዋ እስከፈቀደ ድረስ ተጨማሪ ልጆችን መውለድ እንደምትፈልግ በተደጋጋሚ ተናግራለች። ከ14 ልጆች በኋላም ቤተሰቧ ሙሉ እንዳልሆነ እንደሚሰማት ነው የምትናገረው፡፡ይህ ከልክ ያለፈ የልጆች ፍላጎቷ ታዲያ ከባሏ ከዲዮን ዴሪኮ ጋር የነበራቸውን የ20 ዓመታት ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል። ጥንዶቹ እ.ኤ.አ በሰኔ 2024 በይፋ ተፋተዋል።ይሁን እንጂ ከፍቺው በኋላም ሁለቱ የቀድሞ ጥንዶች ልጆቻቸውን በጋራ ለማሳደግ መስማማታቸውን ገልጸዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 16:05
የጓደኛውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥር በመውሰድ 20ሺህ ብር ያወጣው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበትግለሰቡ ወንጀሉን የፈጸመው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ ውስጥ ነው፡፡ጉታ ገመዳ የተባለው ግለሰብ ከግል ተበዳይ ጋር በጓደኝነት አንድ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ የግል ተበዳይ ቤት ውስጥ ያስቀመጠውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥሩን በመውሰድ ከግል ተበዳይ የሂሳብ ደብተር ፊርማ ጋር በማመሳሰል በክ/ከተማው ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ 20ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡ግለሰቡ ገንዘቡን ካወጣ በኋላ የግል ተበዳይ በደረሰው መልዕክት አማካኝነት ባንኩን በመሄድ ይጠይቃል። ገንዘቡ ወጪ መደረጉን ምላሽ የተሰጠው የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለአቅራቢያው ሙገር ፖሊስ መምሪያ አመልክቷል፡፡አቤቱታው የደረሰው ፖሊስም ምርመራውን በማጣራትና ባንኩ ውስጥ የነበረን ካሜራ በመጠቀም ወንጀል ፈጻሚውን በመለየት ከነ ኤግዚቢቱ ማስመለሱን የመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኢ/ር ዮሴፍ ገረመው ተናግረዋል። ወንጀል ፈጻሚው ክስ እንደተመሰረተበትም ኃላፊው ገልፀዋል።ግለሰቦች የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥራቸውን ከራሳቸው ውጪ ለየትኛውም አካል አሳልፈው መስጠት ወይም በግዴለሽነት ለወንጀል ተጋላጭ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እንደሌለባቸው የገለጹት ኃላፊው፤ ደንበኞች ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄዱም የባንክ ባለሙያዎች የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ትክክለኛ ማንነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።ዘገባ:- ዋና ሳጅን አባብል ከበደየቴሌግራም ቻናልችን
Addis Admass
22 Sept, 15:33
በጦርነት ወቅት ዓለማቀፍ የሰብአዊነት ህግን የማክበር ሥልጠናየዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የጦር መሣሪያ ታጣቂዎችና የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግን የማክበር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። በ2026 የመጀመሪያ ወራት ብቻ ከ1,600 በላይ ታጣቂዎችን በማግኘት ስልጠናዎችን ሰጥቷል።በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች፣ መከላከያ ሰራዊት እና ታጣቂዎች ላይ ትኩረት ያደረገው ይህ ሥራ፤ በግጭት ጊዜ ንጹሐን ዜጎችን፣ የጤና ሠራተኞችን እና የቆሰሉ ሰዎችን ከጉዳት ለመጠበቅ ያለመ ነው።ኮሚቴው ከማንኛውም ወገን ጋር ወገንተኝነት ሳይኖረው በሚያደርገው ግንኙነት፣ የታጠቁ አካላት ሕጉን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል። ይህ የሰብአዊ ሕግ መከበር ሰብአዊ ስቃይን ለመቀነስ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
Addis Admass
22 Sept, 15:17
የዘንድሮ የደመራና የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ጥሪ ቀረበ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እና ከፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመሆን መጪው የመስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ በዓሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር እና የከተማው ነዋሪዎች ለሰላም
Addis Admass
22 Sept, 15:01
የትኩስ ሻይ ቡና አፍቃሪዎች ማወቅ ያለባቸው እውነታበጣም ትኩስ ሻይ ወይም ቡና መጠጣት ለጉሮሮ ካንሰር ሊያጋልጥ እንደሚችል በቅርቡ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ። ተመራማሪዎች እንዳሉት ከ10 ዓመታት በላይ ባደረጉት ክትትል፣ ትኩስ መጠጥ አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች ከቀዝቃዛ መጠጥ ተጠቃሚዎች ጋር ሲወዳደሩ እስከ ሦስት እጥፍ የሚደርስ የስጋት ደረጃ አላቸው። ከዚህም በላይ በቀን ከስድስት ሲኒ በላይ መጠጣት አደጋውን ይጨምረዋል።ችግሩ ያለው ከሻይ ወይም ከቡና ዓይነት ሳይሆን ከመጠጡ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ነው። መፍትሔው ቀላል ነው፤ ሙቅ መጠጦችን ትንሽ እስኪቀዘቅዙ መጠበቅ ከዚህ ስጋት ይጠብቃል።ተመራማሪዎቹ 1 ሚሊዮን ገደማ በሚደርሱ አዋቂዎች ላይ ጥናቱን ማድረጋቸውን ዲስካቨር ማጋዚን ጠቁሟል፡፡
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
