gram news
Amhara Media Corporation channel avatar

Amhara Media Corporation

@amharamassmedia

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ProjectsENNews

48,443subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 15:29

    ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ አስደናቂ ብቃት ላለው ወጣት ተጫዋች ከወዲሁ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የጣሊያኑ ኮሞ ክለብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያልተጠበቀ ድንቅ አቋም እያሳየ ይገኛል።በቀድሞው የአርሰናል አማካይ ሴስክ ፋብሪጋዝ የሚሰለጥነው ክለብ በሴሪያ ኤም ኾነ በቻምፒየንስ ሊጉ ለታላላቅ ክለቦች በቀላሉ እጅ ባለመስጠት በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ ነው።ለዚህ የቡድኑ ጥንካሬ ምሰሶ ከኾኑ ተጫዋቾች መካከል…https://www.ameco.et/sport/6894/
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 13:59

    ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጥበቃን ከብሔራዊ ልማት ጋር አቀናጅታ እየተገበረች ነው።የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር)፣ በአንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን በተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ የውይይት መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል።ሚኒስትሯ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለተሳታፊዎች ያካፈሉ ሲሆን፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ርምጃዎችን ከብሔራዊ የልማት አጀንዳ፣ ከኢንቨስትመንት እና ከኢኮኖሚያዊ የመቋቋም አቅም ጋር በተቀናጀ መንገድ የማስፈጸምን አስፈላጊነት
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 13:43

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በመልዕእካቸው ለወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የወጣቶችኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ላስተላልፍ እወዳለሁ ብለዋል።5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በ1ኛነት መምራታቸው፣የኢትዮጵያን ጥልቅ የስፖርት
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 13:22

    ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ3 ሺህ 789 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኀይል አመንጭቷል።ኢትዮጵያ በታዳሽ ኀይል ልማት እያከናወነች ያለው ሰፊ ሥራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ትልም እያፋጠነ እና ለቀጣናው ያላትን የኢነርጂ ማዕከልነት ሚና ከፍ እያደረገ ነው።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሦሥት ወራት ብቻ ከ7 ሺህ 567 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኀይል ማመንጨት መቻሉን አስታውቋል። ይህም የሩብ ዓመት ዕቅድ 95 ነጥብ 1 በመቶ
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 13:04

    ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ውይይቶች ላይ የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ ቀጥላለችየገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) በCOP31 ከባኩ እስከ ቤለም የተዘረጋውን ፍኖተ ካርታ ለመተግበር እና ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ግቦችን ወደ ተጨባጭ ስራ ለመቀየር በተካሄደ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።ውይይቱም ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቃል-ኪዳኖችን ከታዳጊ አገራት ተጨባጭ ሁኔታና የፋይናንስ ፍላጎቶች ጋር ማጣጣም ያለውን አስፈላጊነት አጉልቶ
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 12:50

    ለጀሱስ ዲ ሚጉኤል ሞት ምክንያት የሆነው በረኛ የ12 ጨዋታዎች ቅጣት ተጣለበት፤ግብ ጠባቂው ግን ዳግም ወደ እግርኳስ መመለሱ አጠራጣሪ ኾኗል።ከሳምንት በፊት በስፔን 2ኛ ዲቪዚዮን ቴነሪፌና አንዶራ ክለቦች ባደረጉት ጨዋታ አሳዛኝ ነገር መከሰቱ ይታወሳል።በጨዋታው ማብቂያ አካባቢ የቴነሪፌው አጥቂ ጀሱስ ዲ ሚጉኤል ኳስ ለማግኘት በሚጥርበት ወቅት የአንዶራው ግብ ጠባቂ ጀሱስ አዎኖ የግብ ክልሉን ለቆ በመውጣት በፈጠሩት ግጭት ዲ ሚጉኤል…https://www.ameco.et/sport/6891/
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 12:38

    በሰማይ ፣ በባሕር እና በምድር የተዘረጋው የኢትዮጵያ ክንድ!ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን እና ብሔራዊ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚቻለው በወታደሮች እና በመሣሪያዎች ብቻ ሳይኾን እነሱን ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ጠንካራ ተቋማት፣ ቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ አቅም እና ቴክኖሎጂን የሚላመድ የሰው ኀይል ሲኖር ነው።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊ፣ ቴክኖሎጂን የተገነዘበ፣ በሀገር ውስጥ ምርት ራሱን የሚችል እና ሠራዊቱ ሙያዊ ብቃቱን የጠበቀ እንዲኾን እየተሠራ ይገኛል።የሀገር መከላከያ ሠራዊት
  • Amhara Media Corporation

    14 Nov, 12:33

    “ለክሪስቲያኖ ሮናልዶ ልዩ የሽኝትና የምሥጋና መርሐግብር ሊካሄድ ነው።በቅርቡ ከ23 ዓመታት በኋላ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ራሱን ያገለለው ፖርቹጋላዊው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት ልዩ የምስጋና እና የሽኝት ዝግጅት እንደተዘጋጀለት ታውቋል።ፖርቹጋል ዛሬ በኔሽንስ ሊግ ዴንማርክን በምትገጥምበት ጨዋታ ሁሉም የቡድኑ አባላት ለርሱ መታሰቢያነት 7 ቁጥር መለያ ለብሰው…https://www.ameco.et/sport/6888/
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 13:12

    የኮሪደር ልማት፣ ተኪ ምርት እና “መሶብ” የሐረሪ ክልልን ገጽታ የቀየሩ ስኬቶችየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ልዑካን በሐረሪ ክልል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን እና የሞዴል መንደሮች ግንባታን ጎብኝተዋል።በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ አስተባባሪ፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል እንደገለጹት ክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን
    1,60011Open in Telegram
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 13:10

    ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር የተሻሻለ የረጅም ጊዜ የውል ማራዘሚያ ስምምነት ላይ ደርሷል። ይህ ስምምነት ክለቡን ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ክብር ካበቃ በኋላ ነው። ምንም እንኳን አዲሱ ውል ለስንት ዓመታት እንደሚያቆየው በይፋ ባይረጋገጥም፣ አርቴታ በኤምሬትስ ስታዲየም ቢያንስ እስከ 10 ዓመት የሚያቆየው እንደሆነ ተገልጿል። በአዲሱ ስምምነት መሰረት ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪ ተዘጋጅቶለታል። አርቴታ በዓመት 15 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚያገኝ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም ከቀድሞው የ10 ሚሊዮን ቋሚ
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 13:05

    🕊️ የመንግሥት የሰላም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) በተለያዩ አጋጣሚዎች “ከጦርነት አሸናፊነት ይልቅ የሰላም አሸናፊነት ይበልጣል፤ ፍላጎታችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግሮ ማሸነፍ ነው” በማለት መንግሥት ለሰላም ያለውን የጸና አቋም ገልጸዋል።ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያጋጠሟትን ውሥብሥብ ፖለቲካዊ እና የጸጥታ ቀውሶች ለመፍታት ከኅይል ይልቅ ሰላማዊ የውይይት አማራጮችን አስቀድማለች።መንግሥት የትጥቅ ትግልን ከመረጡ ኀይሎች ጋር
    1,29011Open in Telegram
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 11:59

    ‎#አንኳር ‎"ኢትዮጵያ በነፋስ አቅጣጫ የምትወዛወዝ ሳትኾን ሥሯን ጥልቅ አድርጋ እንደተተከለች ዋርካ ናት!" ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ‎ ‎#አሚኮ #ኢትዮጵያ #አፍሪካ
    1,49011Open in Telegram
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 11:34

    “ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን በድጋሚ ወደ ሥራ የሚያስገባው ታሪካዊው ጨዋታ” የኢትዮጵያ ወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል አቻው ጋር መስከረም 19/2019 ዓ.ም በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል። ጨዋታውን በስኬት ለማስሄድ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 11:22

    ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታው ልዩ ማሊያ ሊለብስ ነው። የአርጀንቲናው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ለብሔራዊ ቡድኑ በመጨረሻው ጨዋታ ላይ የሚለብሰውን ልዩ ማሊያ በቪዲዮ አስተዋውቋል። ሜሲ የፊታችን መስከረም 20 አርጀንቲና ከቤኒን ጋር በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ 208ኛውን እና የመጨረሻ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደርጋል። የ39 ዓመቱ የአርጀንቲናውያን ኩራት ሜሲ ይህን ልዩ ማሊያ ሲያስተዋውቅ «አንድ የመጨረሻ ጨዋታ፤ ለዘላለም የምትቀር ማሊያ» የሚል መልዕክት አጅቦታል። ሊዮኔል ሜሲ እስካሁን
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 11:20

    ኢትዮጵያ አትወድቅም፤ የወደቁትን ታነሳለች እንጂ።ጠላቶቿ ለዘመናት ሉዓላዊነቷን ሊዳፈሩ፤ ነጻነቷን ሊነፍጉ፤ የታሪክ የበላይነቷን ሊገረስሱ በኅቡህ ተንቀሳቅሰዋል። መንቀሳቀስ ብቻም ሳይኾን ኀያልነቷን ሊነጥቁ ተደጋጋሚ ጥቃት ፈጽመዋል። ኢትዮጵያ ግን ከዓለት በጠነከረ ክንዷ፤ ከነበልባል በሚልቅ ኀይሏ ጠላትን ድባቅ እየመታች ኀያልነቷን አጽንታለች።👉በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የውጭ ጥቃቶችኢትዮጵያውያን ዘመኑን የሚመጥን ቴክኖሎጂ ሳይታጠቁ፤ የሥልጣኔ መሠረቶችን ሳይጎናጸፉ፤ ባሕላዊ የጦር መሥሪያ በያዙበት ወቅት
    1,27021Open in Telegram
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 11:13

    “የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመረዳዳት እና የመተጋገዝ ባሕል እንዲጎለብት አድርጓል” አቶ ይርጋ ሲሳይየአማራ ክልል እና የፌደራል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዐቢይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን አፈጻጸምን ገምግሟል።መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የዜጎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ የመረዳዳት፣ የመተጋገዝ እና የወንድማማችነት
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 09:54

    የማድሪድ ደርቢ ዳኛ ከጨዋታዎች ሊታገዱ ነው። የስፔኑ የሬዲዮ ጣቢያ ኮፔ ባወጣው ዘገባ በሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል የተደረገውን የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የመሩት ዳኛ አልቫሮ ኦርቲዝ አሪያስ ቢያንስ ለቀጣዮቹ ሁለት የላሊጋ ጨዋታዎች ከዳኝነት እንዲገለሉ ሊደረግ መኾኑን አስነብቧል። ሪያል ማድሪድ በደርቢው ጨዋታ ከተሰጡ የዳኝነት ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ በዳኛ ኦርቲዝ አሪያስ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቧል። አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 09:21

    “የኢትዮጵያ የባሕር ኀይል ዳግም ትንሣኤ”ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ የነበራትን ታሪካዊ የባሕር ገዥነት እና የባሕር ኀይል ክብር ዳግም ለማንሳት የጀመረችው ጉዞ ተራ የወታደራዊ ዝግጅት ጉዳይ አይደለም፤ የሕልውና፣ የብሔራዊ ኩራት እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን የማስጠበቅ ዘመናዊ ራዕይ እንጂ! 🇪🇹✨📌 የነጭ መለዮ ለባሾቹ ታሪካዊ ትውስታየቀደሞው የኢትዮጵያ የባሕር ኀይል በቀይ ባሕር እና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 09:04

    የማንቼስተር ሲቲ ድንቅ ጅማሮ ይዘልቅ ይኾን? ማንቼስተር ሲቲ በ2026/27 የውድድር ዘመን ድንቅ ጅምር አድርጓል። ማንቼስተር ሲቲ በ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ 5 ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ 15 ነጥብ በመሠብሠብ የሊጉ ሰንጠረዥ መሪ መኾን ችሏል። ይህ ስኬት ከተመሳሳይ የ2025/26 የውድድር ዘመን ጅምር ጋር ሲነጻጸር የ8 ነጥብ ብልጫ ያለው ሲኾን፣ ቡድኑ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ የመጀመሪያ 5 ጨዋታዎች መሠብሠብ የቻለው 7
  • Amhara Media Corporation

    22 Sept, 08:52

    የመስቀል በዓልን በስኬት ለማክበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል።የመስቀል ደመራ በዓል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ያለምንም የጸጥታ እንከን በድምቀት እንዲከበር የተጠናከረ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል።መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ
Download the series as CSV
A feedback bot for your channel — free

Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.

How it works →
Create the bot