Latest posts

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
14 Nov, 04:54
ወለጋ ጎንደር ወሎ ሸዋ ጎጃም የሳምንቱ ጀብዶችየአፋብን ወታደራዊ ቃልአቀባይ አርበኛ አበበ ሙላቱ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://youtu.be/df5gafcCyxE?si=jaMyppHS4vzWYQkTYouTubeወለጋ ጎንደር ወሎ ሸዋ ጎጃም የሳምንቱ ጀብዶች/የአፋብን ወታደራዊ ቃልአቀባይ አርበኛ አበበ ሙላቱJournalistic & Legal Disclaimer EDITORIAL CONTEXT: This video is a professional news report produced for Educational and Documentary (EDSA) purposes. Our objective is to provide factual, on-the-ground reporting and independent analysis of current events…
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 17:58edited
በመተማ ደለሎ በተካሄደ ውጊያ የሻለቃ መሪን ጨምሮ 23 የጠላት ወታደሮች ተደመሰሱ! በሸዋ የአገዛዙ ሠራዊት በገፍ ከዳ! በታሪካዊቷ ዲማ ጊዮርጊስና ደባይ ጥላት ግን ግፍ ተፈጸመ! የመተማው ድል፣ የሸዋው ክህደትና የዲማ ጊዮርጊስ ውድመት 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/waS2pyoaB4U?si=gh3fvchYr4dY2qUW
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 17:58edited
በመተማ ደለሎ በተካሄደ ውጊያ የሻለቃ መሪን ጨምሮ 23 የጠላት ወታደሮች ተደመሰሱ! በሸዋ የአገዛዙ ሠራዊት በገፍ ከዳ! በታሪካዊቷ ዲማ ጊዮርጊስና ደባይ ጥላት ግን ግፍ ተፈጸመ! የመተማው ድል፣ የሸዋው ክህደትና የዲማ ጊዮርጊስ ውድመት 👇👇👇👇 https://youtu.be/waS2pyoaB4U?si=gh3fvchYr4dY2qUW
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 13:41
ዝክረ ሰማዕታት ሻለቃ ሞኜ ስንሻው በ24ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ ተካሔደ=================================================== ህደር 04/2019 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል በአፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በብርቅዬና ቁርጠኛ ልጆቹ የአምባገነኑን አረመኔ የብልፅግና ስርዓት ፍርስርሱን በማውጣት ዛሬ ላይ ለደረስነበት አንድ አገራዊ ድርጅት ውድና አንድያ ነፍሳቸውን በመስጠት የራሳቸውን ታሪካዊ አሻራ አስቀምጠው ያለፉ ዕንቁ ሰማዕታት ጀግኖችን በዛሬው ዕለት ጧፍና ሻማ በማብራተ ታስቦ ውሏል:: አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ ግራዝማች ሞኜ ስንሻው ሻምበል የፋኖ ትግል ችቦ ለኳሽና የምንጊዜም ጀግናዋን ግራዝማች ሞኜ ስንሻው ጨምሮ ህዳር 4/2016 ዓ.ም አንድ ክፍለ ጦር የመከላከያ ሰራዊትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ታሪክ የሰራውን ሰማዕቱ ሻለቃ ሞኜ ሰንሻውንና በዕለቱ መስዋዕትነት የከፈሉ ሌሎች ሰማዕታትን የ3ኛ አመት መታሰቢያ ዝክረ ሰማዕታት አስባ ውላለች። በዕለቱን የ206ኛ ኮር እና የ24ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ አመራሮች በቦታው የተገኙ ሲሆን የ24ኛክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አርበኛ ፲አለቃ ምህረት ተመስገን ዕለቱን አስመልክተው የግራዝማች ሞኜ ስንሻውን ታሪክ የማይሽረው ጀግንነት አውሰተው ሁሉም የሻለቃው አካላት የሻለቃ ሞኜ ስንሻውን የጀግንነት ወኔና መንፈስ በመላበስ ጀግኖቹ የተሰውለትን የትግል ዓላማ በተግባር ከግብ ለማድረስ እና ሻለቃዋም የራሷን ታሪክ ለማስቀመጥ በቀጣይ ድርጅቱ ለሚያወርደው ተጋድሎ ሁሌም በተጠንቀቅ እንድትቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ የሆኑት ፋኖ ሐብታሙ ጌትነት ሻለቃ ምኜ ስንሻው ሻለቃ ጀግኖች ዝክረ ሰማዕታትን በዚህ መልኩ አስባ መዋሏን አመስግነው ለዚህ ታላቅ ድል እና አንድነት ያበቁን ጀግኖቻችንን ዛሬ ላይ እንዲህ በቀላሉ በሻማና በጧፍ ብናወሳቸውም ለቀጣይ ታሪክ የማይረሳው ሀውልት በሰማቸው ይቆማል የፈፀሙት ገድላቸው በመፅሐፍ ታትሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል ሲሉ ሐሳባቸውን ገልፀዋልሰማዕቱ ግራዝማች ሞኜ ስንሻው ሐምሌ 27/2015ዓ.ም በደባይ ጥላት ግን ወረዳ የብልፅግናን ስርዓት በማፈራረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ፋኖን በማደራጀት በወረዳችን ፈር ቀዳጅ አርበኛ የነበረ ሲሆን ህዳር 04/2016 ዓ.ም በናዝሬት ደብረ ኢየሱስ ቀበሌ ልዩ ቦታው ጎቻ በተባለ ቦታ ከጓዶቹ ጋር በመሆን አንድ ክ/ጦር የመከላከያ ሰራዊትን ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ በዚሁ ቀን ታሪኩን በደማቁ ፅፎ ያለፈ ጀግና ነው። በዚህም የጀግንነት ስራው በወቅቱ የአፋጎ ዘመቻ መሪ የነበረው መቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን የሻለቃ ማዕረግ መስጠታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነውክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!!!!!!አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 11:28
አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ አሳምነው ኮር ከ137ኛ ውባንተ አባተ ክፍለጦር እና ከ138ኛ ራስ አንቺም ክፍለጦር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሔደ!ውይይቱም የክፍለጦሮቹ ከሻምበል መሪ በላይ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የልምድ ልውውጥ በማድረግ ወንድማማችነታቸውን አጠናክረዋል።ውይይቱን የኮሩ ከፍተኛ አመራር፣ የክፍለጦሮቹ አዛዦችና የመቄት ወረዳ ሲቪል መዋቅር አሰተዳደር የመሩት ሲሆን በትግሉ መሰረታዊ መነሻዎች እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ፣ የወታደራዊ ክንፉ እና የህዝብ አስተዳደሩ ግንኙነት፣ የሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ስራችን በተመለከተ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲል የ13ኛ ኮር ቃል አቀባይ መረጃዉን አድርሷል።መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!ህዳር 04/ 2019 ዓ/ም
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 11:12
#የአገዛዙ_ ሰራዊት_ አባላት_ የሃይማኖት_ አባቶችን_ በግፍ አሰሮ_ እየደበደበ_ ና እያሰቃየ_ ይገኛል ። ህዳር 4//3/2019ዓ/ም ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በደባይ ጥላት ግን ወረዳ በናብራ ንዑስ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ/ የብልፅግና ቅጥረኛ ሰራዊት አባላት የሃይማኖት አባቶቸን በግፍ አስሮ በመደብደብ እያሰቃየ ይገኛል። የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ሆድ አደር ለሆዳቸው አዳሪ ካድሪዎች አሰተዳድረዎለው የሚለውን ህዝቡን በብልፅግና ቅጥረኛ የወንበዴ ሰብሰቦች በግፍ እያዘረፉትና በዱላ እያሰቀጠቀጡት ይገኛሉ። የብልፅግና ጆኖሳይዳዊ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥቃት እየፈፀመ ነው የምንለው በምክንያት ነው። በግፍ ከተሰቃዩ የሃይማኖት አባቶች መካከል #ቄስ ታመነ አለሜ በደረሰበት ከባድ ድብደባ ናብራ የባላት ጤና ጣቢያ አልችል በማለት ሪፈር ባህርዳር ሆሰፒታል በህክምና ላይ ይገኛል። አሁንም የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት አባላት #ቄስ ሰጌ አባትነህ#መርጌታ ባዩ ሞላ# አንድ የቄስ ሚስት አሰረው እያገላቱ ይገኛሉ። የብልፅግና አገዛዝ ገዳይና ጨፍጫፊ የሆነ ለሰው ልጂ ህይወት ምንም ደንታ የሌለው ሰባዊነት የማይሰማው ለአንድ ግለሰብ (ለአብይ አህመድ ስልጣን) የቆመ ሰርዓት ነው።የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዲያ ክፍል
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 11:09
ከአፋብን ሴቶች ጉዳይ መምሪያ የቀረበ ጥሪ፦በአማራ ህዝብ ላይ በንጹሃን ሰዎች ፣በሴቶችና በሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ዘር ማጥፋት እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግና እና ዲያስፖራ ማህበረሰባችን ለህዝባችን ድጋፍ እንዲያደርግ የቀረበ ጥሪ፦የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ በንጹሃን ዜጎች ላይ እጅግ አስከፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈፀመ ይገኛል። በዚህ ጭፍጨፋም ምንም ዓይነት የውጊያ ተሳትፎ በሌላቸው ንጹሃን ዜጎች ላይ በተለይም ሴቶችና ሕፃናት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየተፈፀሙና በከፍተኛ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መጠዋል። በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀሙ ካሉ ጭፍጨፋዎች በተጨማሪ በመላ የሃገሪቱ ህዝቦች ላይ በርካታ በአሰቃቂ የጦር ወንጀሎች ግፍና በደሎች እየተፈፀሙ ይገኛሉ። ይህ ጥሪም የወቅቱን አስከፊ እውነታዎች መነሻ በማድረግ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል በከባድ መሳሪያ፣በድሮን ቤተሰቦቻቸውን ያጡ እና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ህፃናትን በማሰብ የሚመለከተው ሁሉ የበኩሉን እንዲወጣ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች እና ጥሪዎች እናቀርባለን 1. ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግጋት መጣስ (International Humanitarian Law Violations) በአማራ ክልል በንጹሃን መኖሪያ መንደሮች፣ በትምህርት ቤቶችና በሕክምና ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ የከባድ መሣሪያዎችና የድሮን ጥቃቶች ፣እንዲሁም ከክልሉ ውጭ በሚኖሩ አማራዎች ላይ እየተደረገ ያለው ዘር የማጥፋት ወንጀል የጄኔቫ ኮንቬንሽንን (Geneva Conventions) በቀጥታ የጣሱ የጦር ወንጀል (War Crimes) ድርጊቶች ናቸው። ለንጹሃን ከለላ ከማድረግ ይልቅ ለከፍተኛ አደጋ መዳረግ በጥብቅ ሊኮነን ይገባል።በመሆኑም ይህንን በተለያዩ የሀገራችን ክፍል በገዛ ህዝቡ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ የሚገኘውን የብልፅግና አገዛዝ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በቃህ ሊለውና ሁሉም ሊያወግዘው የሚገባ አስነዋሪ ድርጊት ነው። 2. በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ስልታዊ ፆታዊ ጥቃቶች (Gender-Based Violence) የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት ምክንያት ህይወታቸውን ካጡ ሴቶችና ልጃገረዶች በተጨማሪ ለተለያዩ ስልታዊ ፆታዊና ወሲባዊ ጥቃቶች ተጋላጭ ሆነዋል። በተለያዩ ገለልተኛ ሪፖርቶች ላይ የተመዘገቡት አስገዳዶ መድፈርና ወሲባዊ ጥቃቶች በሴቶች ላይ ዘላቂ የአካልና የሥነ-ልቦና ጠባሳ እየጣሉ ይገኛሉ። በዚህም ፆታዊ ጥቃት ምክንያት ሴቶች ለተለያዩ ጉዳቶች ተዳርገዋል ከእነዚህም ውስጥ፦ • አካላዊ መጎሳቆልና የአካል ጉዳት፦ ጥቃቶቹ በአብዛኛው በቡድን መደፈር፣ በወታደራዊ የጦር መሣሪያዎች በማስፈራራት እና በከባድ ድብደባ የታጀቡ በመሆናቸው በሴቶቹ ላይ ከፍተኛ የአካል ስብራት፣ የውስጥ ደም መፍሰስ እና ዘላቂ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። • የአእምሮ ጤና መቃወስ (Psychological Trauma)፦ ጥቃቱን ያስተናገዱ ሴቶች ለከፍተኛ ጭንቀት (Anxiety)፣ ለድብርት (Depression) እና ከድንገተኛ አደጋ በኋላ ለሚከሰት የአእምሮ መረበሽ (PTSD) ተጋልጠዋል። ማኅበረሰባዊ መገለልን በመፍራት ጉዳታቸውን ደብቀው የሚኖሩ በርካታ ሴቶች ለአእምሮ ሕመም ተዳርገዋል። • ለአደገኛ በሽታዎች መጋለጥ፦ ሴቶቹ ያለ ምንም ጥበቃ የመደፈር ጥቃት በመጋለጣቸው ምክንያት ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) እና ለተለያዩ በአካል ንክኪ ለሚተላለፉ የአባለዘር በሽታዎች ተዳርገዋል። • የቤተሰብ መፍረስ እና መገለል፦ በማኅበረሰቡ ውስጥ ባለው የተሳሳተ አመለካከት እና ወቀሳ ምክንያት፣ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በባሎቻቸውና በቤተሰቦቻቸው የመገለል እንዲሁም የመፈታት አደጋ ይደርስባቸዋል። ይህ ሁኔታ ተጎጂዎች ድጋፍ ከማግኘት ይልቅ ብቻቸውን እንዲሰቃዩ አድርጓል። • ያልተፈለገ እርግዝና እና ማኅበራዊ ጫና፦ በጥቃቶቹ ሳቢያ የተከሰቱ ያልተፈለጉ እርግዝናዎች እና ከግጭት-ነክ ጥቃቶች የሚወለዱ ሕፃናት በሴቶቹና በማኅበረሰቡ ላይ ተጨማሪ የረጅም ጊዜ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ጫና ፈጥረዋል። • የኢኮኖሚ ውድቀት የመተዳደሪያ ማጣት፦ ጥቃቶቹ የሚፈጸሙት በቤት ለቤት ፣ በእርሻ ቦታዎች ወይም ወደ ገበያ በሚጓዙበት ወቅት በመሆኑ፣ ሴቶች በነፃነት ወጥተው እንዳይሠሩና ቤተሰቦቻቸውን እንዳይደግፉ አድርጓቸዋል። • የሕክምና ወጪዎች ጫና፦ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ለአካላዊና ለአእምሮ ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ከፍተኛ ወጪ መሸፈን ባለመቻላቸው፣ ካላቸው ጥቂት ንብረት ላይ እንዲያጡ ወይም ያለ ሕክምና እንዲቀሩ ሆኗል። • የመሠረተ-ልማት መውደም፦ አገዛዙ በከፈተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ሆስፒታሎች፣ የጤና ጣቢያዎች እና የሴቶች መርጃ ማዕከላት ወድመዋል ።በዚህም ምክንያት ብዙዎች እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እያጡ ነው። • የዕርዳታ ተደራሽነት ማጣት፦ የጸጥታ ችግሮች እና በአገዛዙ የሚጣሉ የጉዞ ገደቦች ዓለም አቀፍ የሕክምና ቡድኖች (እንደ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ያሉ) ድንገተኛ የወሊድ፣ የፕሪፕ (PEP) እና የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶችን በወቅቱ ለተጎጂዎች እንዳያደርሱ አግዷቸዋል። ይህ የሕክምና መዘግየት የጉዳቱን መጠን ይበልጥ አባብሶታል። 3. የሕፃናት መብቶች መርገጥና የትውልድ ቀውስ በጦርነቱ ሳቢያ ሕፃናት ህይወታቸው ከማጣታቸው በተጨማሪ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በመሠረታዊ ምግብና መድኃኒት አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለከፋ የሥነ-ምግብ እጥረትና ለሞት ተጋልጠዋል። ሕፃናት በሕግ ሊያገኟቸው የሚገቡ የደኅንነትና የሕይወት መብቶች መጣሳቸው የወደፊቱን ትውልድ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል። አጠቃላይ አገዛዙ እየፈፀመ ያለው ድርጊት በዓለም አቀፍ ሕግ ፍፁም ተቀባይነት የሌለውና በአስቸኳይ ሊቆም የሚገባው ስለሆነ ሁሉም እንዲያወግዘው ጥሪ እናስተላልፋለን፤ . ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፦ የብልፅግናው አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ፣ ሴቶችንና ሕፃናትን ጨምሮ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጭፍጨፋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ፣ ገለልተኛና ታማኝ የሆኑ መርማሪ ቡድኖች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ግፊት እንዲደረግ እና ተጠያቂነት (Accountability) እንዲሰፍን የዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ እንዲፈጠር እናሳስባለን። . ለሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች (Humanitarian Agencies)፦ ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ዜጎች ያለ ምንም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና ገደብ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ (የሕክምናና የምግብ አቅርቦት) የሚደርስበት በአስቸኳይ መፍትሔ እንድትሰጡ እንጠይቃለን። ለመላው በውጭና በሀገርውስጥ ለምትኖሩ ወገኖቻችን፦ የብልፅግናው አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት ንጹሃን ህዝባችንን በድሮንና በከባድ መሳሪያ እየጨፈጨፈና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ሴቶችና ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ እየገደለ ይገኛል። ከመገደል የተረፉትም ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል ይሔንን ዘግናኝ ድርጊት ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ ሊያወግዘውና በጋራ ሊታገለው ይገባል። ስለሆነም ይህንን ዘር አጥፊ የብልፅግና አገዛዝ የፈፀመውን በደልና ግፍ በመታገል አስፈላጊውን የሰበዓዊ ድጋፍ እንድታደርጉ የአፋብን ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ጥሪ እናስተላልፋለን። ህዳር 3 2019 ዓ.ም
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
13 Nov, 11:09
የብልፅግና አገዛዝ በዲማ ጊዮርጊስ ኗሪዎች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ፣ ውድመት እና ከፍተኛ እንግልት እየፈፀመ ይገኛል!! ህዳር 04/2019 ዓ.ምበአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል፣ ጭቆና እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ የሚገኘው የብልፅግና አገዛዝ በምስ/ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ የሚገኙ ኗሪዎችን ሀብት ንብርት፣ በእምነት ተቋማት፣ የት/ት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ እና ውድመት ሲፈፅም ንፁሃን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። አቁስሏል።በታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ገዳም ሰፍሮ የሚገኘው የብልፅግና አገዛዝ ገዳይ ቡድን በዲማ የመጀመርያ ደረጃ ት/ት ተቋም ትውልዱ የዕውቀት ባለቤት እንዳይሆን ት/ት ቤቱ አገልግሎት እንዳይሰጥ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይሄዱ አድርጓል። በት/ቤት የሚገኙ መገልገያ ንብረቶችን አቃጥሏል። አውድሟል። በከተማዋ የሚገኙ ተማሪዎችን የእውቀት ባለቤት ለማድርግ በትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ መምህራን መገልገያ ቁሳቁስ፣ የተማሪዎች ምግብ፣ በከተማዋ የሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጥ ሹቆች፣ ቁርስ ቤቶች፣ የንጹሀን የመኗሪያ ቤቶች እና የእምነት ተቋማት በከፍተኛ ሁኔታ አውድሟል። ከእነዚህም መካከል:- 1ኛ. አቶ ሞሳ ውዱ ዲማ ከተማ ድብደባ የተፈጸመበት እና 30,000 ብር የተዘረፈ 2ኛ. አብርሃም ሃብቴ ዲማ ከተማ ኗሪ የጫማ ሱቅ ሙሉ ለሙሉ የተቃጠለ አንድ ሳይክል የተወሰደበት 3ኛ.ሰናይት ቢምረው ዲማ ከተማ ኗሪ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ በሙሉ የተዘረፈች 4ኛ.ሃይሌ ደሬ ሙሉ የቤት እቃ ሙሉ ለሙሉ የተዘረፈ 5ኛ.አቶ ጋሻነህ ማዜ ቅድስጌ ቀበሌ በአገዛዙ ጥይት የቆሰሉ የ75 አመት አዛውንት 6ኛ.አቶ መሌ ምትኩ ቀድስቅ ቀበሌ የ55 አመት አዛውንት በአገዛዙ ጥይት በከፍተኛ ሁኔታ የቆሰሉ 7ኛ. የቀለሜ መንግሰት ልጂ ዲማ ከተማ ኗሪ ልጁን በማስፈራራት አንድ Samsung Galaxy ስልክ በአፉሙዝ በማስፈራራት አገዛዙ ዝርፊያ መፈፀሙን የእነማይ ወረዳ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አሳውቋል።በዲማ ከተማ በአገዛዙ እየተፈፀሙ ያሉ ግፎች እና በደሎችን ለአለማቀፍ ማህበርሰብ እንዲሁም ለህዝባችን መረጃዎችን ሸር ሸር በማድርግ ተደራሽ እናድርግ👇ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ህዳር 04/2019 ዓ.ም
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 19:59
የጋዜጣ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሃይሎች ትብብር ለህልውና (ትብብር ለህልውና) ይፋ መደረጉን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ሎንዶን፣ ዩኬ — የአማራ ማህበራት ግብረ-ኃይል በዩኬ (AATF-UK) የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሕልውና ትግል ስብስብ (የሕልውና ስብስብ) መመስረቱን በዲፕሎማሲያዊ አክብሮት ሙሉ ድጋፉን ይገልጻል። የሕዝባችንን ሕልውና፣ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በየግንባሩ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የጀግኖች ታጋዮቻችን፣ የሕዝብ ኃይሎችና መሪዎቻችን የላቀ አክብሮታችንን እና ያልተቆጠበ ድጋፋችንን እናቀርባለን። የዚህ ስትራቴጂካዊ ስብስብ መመስረት በተበታተኑ የትግል አቅሞች መካከል የተዋሃደ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መድረክ በመፍጠር በትግላችን ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ያመላክታል። ይህ ስብስብ በአገራችን ያለውን አለመረጋጋት ለማስቆም፣ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች ለማስከበር እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት አስተማማኝ መሰረት ለመጣል ትልቅ ተስፋ ነው። የሽግግር ወቅት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዓላማዎች በስብስቡ መስራች ሰነድ ላይ እንደተቀመጠው፣ የሽግግር ወቅት የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓላማዎች በጽናት ያካሂዳል፦ 1. የሕዝብ ሕልውናን፣ ሰላምን እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ማረጋገጥ፦ ሁሉንም ግጭቶች በአስቸኳይ ማቆም፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማስከበር፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውድቀቶችን ማረጋጋት እንዲሁም ከጎረቤት አገሮችና ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ማደስ። 2. እውነተኛ ሕዝባዊና ሕገ-መንግስታዊ ውይይት፦ የአገሪቱ ዘላቂ አስተዳደርና ሕገ-መንግስታዊ መዋቅር በሕዝቡ ቀጥተኛ
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 19:57

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 19:52
ሰበር ዜና! በአፋር ቶንሳ አካባቢ የአገዛዙ ድሮን በትብብር ለሕልውና ኃይሎች ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ!በቅርቡ በተመሠረተው «የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና» የተባበሩት ኃይሎች በአፋር ክልል ቶንሳ በተባለ ስፍራ ጥቃት ለማድረስ የተሰማራ የመንግሥት ድሮን ተመትቶ መውደቁ ታውቋል።የወጡ የመረጃ ምንጮች እንደሚያመላክቱት፣ ድሮኑ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የተባበሩት ኃይሎችና በሕዝቡ ላይ የስለላና የጥቃት ተልዕኮ ለማስፈጸም በወታደራዊ ቀጠናው ሰማይ ላይ ሲያንዣብብ በነበረበት ወቅት በተሰነዘረበት ተመጣጣኝ ተኩስ ተመትቶ መሬት ላይ እንዲከሰከስ ተደርጓል።ይህ ክስተት በቅርቡ የተመሠረተው «ትብብር ለሕልውና» በየግንባሩ የተቀናጀ ወታደራዊ ምላሽ መስጠት መጀመሩን የሚያሳይ ሲሆን፣ በአካባቢው በሚገኙ የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች ዘንድም ከፍተኛ ድንጋጤን መፍጠሩ ተጠቁሟል። ኢትዮ 251 ሚዲያ
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 18:15edited
ሰበር ዜና!በጀኔራል ዘውዱ ሠጣርጌ ትዕዛዝ የኢንተርኔት አገልግሎት ሲቋረጥ መረጃ ቲቪም ማየት ተከለከለ!በአዳድ፣ ምዕራብ ወሎ ቦረና እና መካነሠላም አካባቢዎች የኢንተርኔት እና ቴሌኮም መረብ መቋረጡና የመረጃ ቲቪ የዲሽ እንዲወርድ እየተደረገ ነው !በአዳድ፣ ምዕራብ ወሎ፣ ቦረና፣ መካነሠላም አካባቢዎች የአገዛዙ ኃይሎች የኢንተርኔት አገልግሎት በማጥፋትና የመረጃ ቲቪ የዲሽ የሰቀሉ ቤቶችን ቤት ለቤት እየዞሩ እያስወረዱ መዋላቸው ታወቀ።ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ በጄነራል ዘውዱ ሰጣርጌ በሚመራው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ላይ የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጦ የሚገኝ ሲሆን፣ የአገዛዙ ኃይሎች እየተዘዋወሩ የመረጃ ቲቪ ዲሽ አውርዱ ሲሉ መዋላቸው ተረጋግጧል።ይህ ርምጃ የአካባቢውን ማህበረሰብ የመረጃ ማግኘት መብት ለመገደብ እና ማሕበረሰቡ በራሳቸው ፕሮፖጋንዳ አጥረው ለመያዝ የታለመ መሆኑን የገለጹት አካባቢያዊ ምንጮች፣ በድርጊቱ ምክንያት ማሕበረሰቡ ትክክለኛውን የትግል መረጃ ማግኘት አዳጋች እንደሆነበት ገልጸዋል።ኢትዮ 251 ሚዲያ
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 16:48
ሰበር ዜና!በዋግኽምራ ዞን የሚገኘው ድሀና ወረዳ ሙሉ በሙሉ በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በቁጥጥር ስር ዉሏል።ድሃና፣ ፣አዚላ ፣ጪላ ፣ቀዉዝባ እና በወረዳው ሰፍሮ የነበረው የአገዛዙ ሰራዊት የፋኖን አቅም መቋቋም እንደማይችል፣ ፍፁም የሃይል የበላይነት ያለው መሆኑን ያሳወቀው በአካባቢው ሰፍሮ የነበረው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ሃይል እጅ ከምትሰጥ በፍጥነት ውጣ የሚል ትዕዛዝ ከተቀበለ በኋላ ቦታውን ለቆ የወጣ ሲሆን፣ ይህንን ተከተሎ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በቁጥጥር ስር ውሏል።የወረዳውን መያዝ ተከተሎ በአካባቢው የሚገኙ የ13ኛ ኮር የፋኖ አሃዶች በወረዳው ከተማና ቀበሌዎች በመግባት ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራ መጀመራቸው የታወቀ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሁኔታውን በጥንቃቄ እየተከታተሉ ለፋኖ እያደረሱ ይገኛሉ።የወረዳው ሙሉ በሙሉ በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር አኃዶች በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በዋግኽምራ ዞንና በዙሪያው በሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ የበላይነት የሚያጎናጽፍ ነዉ።መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!መስከረም፦ 12/ 2019ዓ/ም
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 13:49
ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) መመስረቱን አስመልክቶ ከአማራ ማኅበራት ትብብር በአሜሪካ የተሰጠ የድጋፍ መግለጫአፋብንን ጨምሮ ሰባት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ማለትም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፣ የኦጋዴን ሕዝብ ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤኔሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጉምዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ንቅናቄ ጊዜ ወስደው በመምከር በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረ-ፈጅ ጦረኛ አገዝዝ ከስር ፈንቅሎ በመገርሰስ ሁሉንም የሚያሳትፍ የሽግግር ስርዓት ለማምጣት የሚያስችላቸውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) በመመስርተቻው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እና ሙሉ ድጋፍ ለመግለፅ ይህንን መግለጫ አውጥተናል። ይህ የኢትዮጵያ ትንሣዔ ተብሎ ሊገለፅ የሚችል ትብብር እንዲመጣ የአብዛኛው ህዝብ ምኞት እና ጥያቄ ከመሆኑ አልፎ የትብብር ንግግሩ ጭምጭምታ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮኖች በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ በዕብሪት ለማጥፋት የከፈተው ወረራ ሦስት አመታት ያስቆጠረ ሲሆን የሕልውና አደጋ ያላደረሰበት ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ለማለት አይቻልም። በዚህም ረገድ እነዚህ የሕልውና አደጋ የተደቀነባቸው ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች ትብብር ፈጥረው የጋራ ጠላታቸውን ተቀናጅተው በአስቸኳይ እና በአነስተኛ መስዋዕትነት ለማስወገድ መተባበራቸው ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው። ይህን ትብብር ተስፋ ሰጭ የሚያደርገው ዋነኛ አላማው በኢትዮጵያ ያለውን
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 13:49
8,640Open in Telegram
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 12:13
መዋቅራዊ ውድቀት፣ የፖለቲካ ሆድ-አደሮች እና የፋኖ ስትራቴጂካዊ ድል! አዲስ አበባ — በብልፅግና አገዛዝ ዘመን በየብሔሩ ስም የተደራጁ፣ ሕሊናቸውን ለሆዳቸው ያከራዩና መብላት-ማደርን ብቻ ዓላማቸው ያደረጉ የፖለቲካ ሆድ-አደሮች ሀገርንና ሕዝብን ለከፍተኛ መከራ ዳርገዋል። ትግራዋይ ሁኖ ትግራይን፣ አማራ ሁኖ አማራን፣ ኦሮሞ ሁኖ ኦሮሞን የካደው ይህ ርካሽና ፀረ-ሕዝብ ኃይል፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የጋራ ውይይትና ሰላማዊ የመፍትሔ በሮች እንዳይከፈቱ በማድረግ ሀገሪቱን ወደ አሰቃቂ ደም መፋሰስ መርቷታል። የዚሁ ቅጥረኛ ስብስብ ሴራ ውጤት የሆነው ጦርነት የወጣቱን ሕይወት እንደ ቅጠል አርግፎታል። ዛሬም ቢሆን እነዚህ የስርዓቱ አሽከሮች የሕዝብን ደም እያፈሰሱ የአገዛዙን የስልጣን ዘመን ለማራዘም ይፋገታሉ። በሌላ በኩል፣ የስርዓቱ ዙፋን ጠባቂ የሆነውና በደሞዝ የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት ለድሃ ልጅ ደንታ በሌለው አገዛዝ እየተገፋፋ በየገደሉና በየጫካው ሲረግፍ፣ ይፋዊ የሕዝብ ወገንተኝነት ያለውና ያለ ደሞዝ ለነፃነት የሚታገለው የፋኖ ኃይል ግን የአገዛዙን ሰራዊት በማማረክና መዋቅሩን በመበታተን ላይ ይገኛል። የስርዓቱ አባላትም ቢሆኑ የሥልጣኑን መጨረሻና የሕዝቡን ምሬት ተረድተው እጃቸውን በሰላም በመስጠት ላይ ናቸው። የዚህ ፋሺስታዊ አገዛዝ አካሄድና ውድቀት ከቀደመው የደርግ አገዛዝ የተለየ አይደለም። ደርግ በጥቁር ሳምንትና በቀይ ሽብር አደባባይ ላይ የሀገሪቱን 60 ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ምሁራን በመረሸን ሀገሪቱን አእምሮ-አልባ አድርጎ፣ የወጣቶችን በሬሳ ላይ የጥይት ዋጋ ሲያስከፍል ነበር። ከ17
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 12:13

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 11:59
“የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና” ምስረታን አስመልክቶ የቀረበ የድጋፍ መግለጫ፣በአብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ጀኖሳይዳዊ አገዛዝ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረበት ወቅት ጀምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በቆሰቆሳቸው ግጭቶና፣ ህዝቦች በመራራ ትግልና መስዋእትነት ያገኙትን የራስን ዕድል በራስ የመወሰንንና የማስተዳድርን ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለደፍጠጥ ባደረጋቸው ሙከራዎች ሳቢያ፣ ኢትዮጵያ በሚልዮን የሚቆጠር የሰው ህይወት ባጠፉና በቢሊዮን ብሮች የሚገመቱ ንብረቶች ውድመት ባስከተሉ ግጭቶችና ጦርነቶች ውስጥ ተዘፍቃ እንደምትገኝ ይታወቃል።ይህንን ብልፅግና መር የሆነውን ጨካኝ የዘር ማጥፋት በደልና ግፍ ለመመከት፣ ህዝቦቻቸውን ከመጥፋት ለመከላከልና ተፈጥሮአዊ የመኖር መብታቸውን ለማስከበር ሲሉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች መሳርያ ኣንስተው በተናጠል በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የህልውና ትግላቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል።የብልፅግናው ጀኖሳይዳዊ አገዛዝ ይህንኑን ፍትሐዊ የህልውና ትግል በአጭር ለመቅጨትና ለማክሰም፣ ሰሜን-ደቡብ የሚል ከፋፋይ ትርክት ከመፍጠር ጀምሮ ሁሉንም ዓይነት ሴራ በመጎንጎን፣ ባሰማራቸው ጀሌዎች አማካኝነት እኩይ ተግባሩን ለማሳካት በመጋጋጥ ላይ ይገኛል።ሆኖም ግን የዚህን የዘረ-ፈጅ የብልፅግና ስርዓት ጨካኝነትና ስግብግብነት በሚገባ የተረዱ የህልውናና የነፃነት ታጋዮች፣ ኢትዮጵያ ካለችበት የእልቂት ኣዙሪት ለመውጣትና ህዝቦችዋም መብታቸው ተከብሮ በሰላም የሚኖሩበትን አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ብቸኛው አማራጭ ፣ ይህንን ጭራቅ ስርዓት በተባበረ ክንድ ከስልጣኑ
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 11:59

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
22 Sept, 10:25edited
አዲስ አበባ ዙሪያ የተካሄደው ከባድ ውጊያ እና የፋኖ አስደማሚ ወታደራዊ ድሎች! ከአገዛዙ ሠራዊት የተከደነው ከባድ እርምጃ፡ የኮማንዶና አየር ወለድ አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ! አፋብን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረበው አስቸኳይ ጥሪ እና በበለሳ የተካሄደው ሕዝባዊ ውይይት! 👇👇👇👇👇👇👇https://youtu.be/Fr2i5jaRJnw?si=9oTu-KHpKzUGnD9nYouTubeአዲስ አበባ ዙሪያ የተካሄደው ከባድ ውጊያ እና የፋኖ አስደማሚ ወታደራዊ ድሎች!ከአገዛዙ ሠራዊት የተከደነው ከባድ እርምጃ፡Journalistic & Legal Disclaimer EDITORIAL CONTEXT: This video is a professional news report produced for Educational and Documentary (EDSA) purposes. Our objective is to provide factual, on-the-ground reporting and independent analysis of current events…
Links
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
