Latest posts

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
22 Sept, 15:17edited
"ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነውና በጊዜህ ሁሉ ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት አይምሰልህ። ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።"(ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
22 Sept, 11:18edited
“ምስጋና ማለት ታላላቅ በረከቶችን ለመቀበል የምትዘረጋ እጅ ናት። ስላለህ ጥቂት ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን ስትጀምር፣ የሰማይን መስኮቶች ለተጨማሪ በረከት ትከፍታለህ። የሚያጉረመርም ልብ በጨለማ ውስጥ ይኖራል፤የሚያመሰግን ነፍስ ግን ሁልጊዜ በብርሃን ውስጥ ነው።’’(ማር ይስሐቅ ሶርያዊ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
22 Sept, 06:26
"ማንንም አትወንጅል ማንንም አትዳኝ ስህተታቸውን አትዘርዝር ድካማቸውን አታጉላ ራስህን ብቻ ውቀስ ለራስህም 'እኔ ነኝ መጥፎ ኃጢአተኛ' በለው ይህ ነው የመንፈሳዊ ሕይወት ጅማሮ አንዱ መንገ።" (አባ ሴራፊም)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
21 Sept, 17:11edited
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።(ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ -የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
21 Sept, 10:29edited
"በመንፈሳዊው መንገድ ላይ የምትጓዙ ከሆነ እንዳትወድቁ በራሳችሁ አትደሰቱ። ትዕቢትን የምንፈራው እድገታችንን እንዳያቆመው ብቻ ሳይሆን እንዳይጥለንም ነው። መጽሐፍ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል፦"ትዕቢት ጥፋትን ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።" ምሳ 16፥18..."(መንፈሳዊው መንገድ - በአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
20 Sept, 18:06
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል። በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
20 Sept, 10:24
ሰላም እንደምን አላችሁ! ከዚህ ቀደም ለ2019 የትምህርት ዘመን ለ10 ችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ለማሟላት ባቀረብነው ጥሪ መሠረት፣ አንድ ደግ ወንድማችን የሁሉንም ተማሪዎች ወጪ ሙሉ በሙሉ ችሎልን ዛሬ መስከረም 10/2019 ዓም አስረክበናል። በዚህም፦ ለ8 ተማሪዎች፦ ሙሉ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም፣ እያንዳንዳቸው 1 ደርዘን ራዲካል ደብተር፣ 6 እስክርቢቶ እና 3 እርሳስ ተሟልቶላቸዋል።ለ2 እናትና አባት ለሌላቸው ሙስሊም እህትማማቾች፦ የደብተር እና የዩኒፎርም መግዣ የሚሆን በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው 4,450 ብር (በጠቅላላው 8,900 ብር) ማስረከብ ችለናል። ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግ ወንድማችንን ልዑል እግዚአብሔር ያክብርልን፣ ያሰበውን መልካም ሥራ ሁሉ ይባርክለት። በሥራው፣ በጤናውና በቤቱ ሰላሙን፣ ጤናውንና በረከቱን ያብዛለት፤ ቅድስት ድንግል ማርያም በእናትነት ፍቅሯ ትጠብቀው፤ የህፃናቱ ደስታና የወላጆቻቸው ጸሎት ዘወትር ከእሱና ከቤተሰቡ ጋር ይሁን!ለዚህ መልካም ስራ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁና በጸሎት ለደገፋችሁን በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልን!
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
20 Sept, 09:52edited
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
20 Sept, 09:05edited
የቤተክርስቲያን ጌጥ የሆንክ መምህራችን ዶክተር ሮዳስ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ በፍቅር ያኑራችሁ!
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
19 Sept, 05:43
ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ስታነቡ ዝም ብላችሁ ቃላትን ለመቁጠር ብቻ አይሁን። ነገር ግን በቃሉ ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ጣዕም ለማግኘት ጸልዩ። የምታነቡትን በተግባር ለመተርጎም ትጉ። 'ቃሉን የሚሰሙ ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉት ይጸድቃሉ' ተብሏልና። አንድ ምዕራፍ እንኳ ብታነቡ ያቺ ለአንድ ቀን ስንቅ ትሆናችኋለች። ንስሐ የገባ ሰው ልቡ በቃለ እግዚአብሔር ካልታጠበ ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ጭቃ መመለሱ አይቀርም። ቃሉ ግን ልባችሁን ይጠብቃል፤ አእምሮአችሁንም ያበራል።ሰዎች ሆይ! መጻሕፍትን አትናቁ። እነርሱ ከሰማይ ወደ እኛ የተላኩ ደብዳቤዎች ናቸው። የሰማዩ ንጉሥ የላከልህን ደብዳቤ ችላ ብለህ እንዴት ሰላምን ታገኛለህ? በመጻሕፍት ውስጥ የታመሙት ፈውስን፣ ያዘኑት መጽናናትን፣ የወደቁት መነሳትን፣ ንስሐ የገቡት ደግሞ የተስፋን ብርሃን ያገኛሉ። በቃለ እግዚአብሔር የምትታጠብ ነፍስ ዘወትር ለምለም ትሆናለች።ስለዚህ በቤታችሁ መጻሕፍትን ለማንበብ ጊዜ መድቡ። ልጆቻችሁንም በቃለ እግዚአብሔር ኮትኩቱ። ዓለማዊ እውቀት ለሥጋዊ ሕይወት ይጠቅም ይሆናል፤ መንፈሳዊ እውቀት ግን ለዘላለም ሕይወት ያበቃል። ንስሐችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ፣ ሕሊናችሁም ከክፉ ሐሳብ ይነጻ ዘንድ ዘወትር በመለኮታዊ መጻሕፍት ንባብ ተጉ። እግዚአብሔር ቃሉን በልባችን ይጻፍልን።"(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
18 Sept, 18:03edited
“በአውሎ ነፋስ መካከል ብትሆን እንኳ አትፍራ፤ መርከቧን የሚመራት ክርስቶስ እስካለ ድረስ ማዕበሉ አያሰምጥህም፤ እግዚአብሔር ፈተናውን ባያርቀው እንኳ ፈተናውን የምትችልበትን ኃይል ይሰጥሃል።’’ሊቁ አውግስጢኖስ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
18 Sept, 17:15
#የሐዲስ_ኪዳን_መምህሩን_ሕይወት_እንታደግ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በርካታ ደቀ መዛሙርትን እያነፁ የሚገኙት መምህር ቀለመወርቅ አመሃ ዛሬ የእኛን የደግነት እጅ መዘርጋት የሚሻ ከባድ የልብ ሕመም ገጥሟቸዋል። በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ጉባላፍቶ ወረዳ በድጎ ደብረ ኢየሱስ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ5 ዓመታት ተምረው ከተመረቁ በኋላ፣ በጉባላፍቶ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
18 Sept, 04:29
ንስሐና ምጽዋት የነፍስ ሁለት ዓይኖች ናቸው። አንዱ ቢጠፋ ሌላኛው ብቻውን ሙሉ እይታ አይሰጠውም።ኃጢአትህ እንዲፋቅልህ ትፈልጋለህን? እንኪያስ የምሕረት በርን በምጽዋት አንኳኳ። 'የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና' ተብሏል። አንተ ለባልንጀራህ ካልራራህ እግዚአብሔር እንዲራራልህ እንዴት ትጠይቃለህ? ምጽዋት ሰጪውን ከኃጢአት እስራት ትፈታዋለች፤ ተቀባዩንም ከችግር ታሳርፈዋለች።ወንድሞቼ ሆይ! አትሳሳቱ፤ ገንዘባችሁ እዚህ ምድር ላይ ይቀራል። ይዛችሁት የምትሄዱት ምጽዋታችሁን ብቻ ነው። በሕይወት እያላችሁ ለነፍሳችሁ ስንቅ አዘጋጁ። ድሆች የእግዚአብሔር መሠዊያዎች ናቸው። በቤተክርስቲያን ያለውን መሠዊያ እንደምታከብሩ ሁሉ፣ እነዚህን ሕያው መሠዊያዎች (ድሆችን) አክብሩ። በድሃው እጅ ላይ የምታስቀምጠው ስጦታ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር እጅ ይደርሳል። ስለዚህ ንስሐችሁ ፍሬ እንዲያፈራ፣ ጸሎታችሁም እንዲሰማ ዘወትር በምጽዋት ትጉ።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
17 Sept, 17:49
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድምህ ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
17 Sept, 00:53
#የሐዲስ_ኪዳን_መምህሩን_ሕይወት_እንታደግበሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በርካታ ደቀ መዛሙርትን እያነፁ የሚገኙት መምህር ቀለመወርቅ አመሃ ዛሬ የእኛን የደግነት እጅ መዘርጋት የሚሻ ከባድ የልብ ሕመም ገጥሟቸዋል።በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ጉባላፍቶ ወረዳ በድጎ ደብረ ኢየሱስ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ5 ዓመታት ተምረው ከተመረቁ በኋላ፣ በጉባላፍቶ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜን ወንበር ዘርግተው በማስተማር ላይ ይገኛሉ።አሁን ላይ መምህሩ በገጠማቸው የልብ ሕመም ምክንያት በወልድያ ሆስፒታል ቢታከሙም ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ አዲስ አበባ ለከፍተኛ የልብ ሕክምና ተልከዋል። ሕይወታቸውንም ለማዳን ለሚደረገውን አስቸኳይ የልብ ቀዶ ጥገና ከ300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ያስፈልጋቸዋል።ሰውን ለማዳን ሰው መሆን በቂ ነውና መምህሩ እንደገና ወደ ወንበራቸው ተመልሰው ደቀመዛሙርትን ማፍራት እንዲችሉ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንና ደግ አሳቢዎች በሙሉ የቻላችሁትን በሚከተለው አካውንት ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እንጠይቃለን።#በኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ለመምህር ቀለመወርቅ አመሃ በላይ 1000513559821#ለበለጠ_መረጃ፦ ➛ መምህር ቀለመወርቅ - +251920120104ሼር በማድርግ ይተባበሩ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
16 Sept, 18:21
ከእራት በኋላ ያለው ጊዜ የምስጋና ጊዜ ነው፡፡ ምስጋናን የሚያቀርብ ደግሞ ንቁና የተረጋጋ ይሆናል፡፡ ከእራት በኋላ ወደ ጸሎት እንጂ ወደ መኝታ አንሂድ፡፡ ያለበለዚያ ግን በደመ ነፍስ ከሚመሩት አውሬዎች የበለጠ በደመ ነፍስ የምንመራ እንሆናለን፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
16 Sept, 13:21edited
ሰይጣን ኃጢአት እንድትሠራ ሲገፋፋህ 'ድፍረትን' ይሰጥሃል። 'እግዚአብሔር መሐሪ ነው፣ አንድ ጊዜ ብትሠራው ምን ይልሃል? ቆይተህ ንስሐ ትገባለህ' እያለ በኃጢአት ላይ እንድትደፋፈር ያደርግሃል። አንተ ተሸንፈህ ኃጢአቱን ከፈጸምክ በኋላ ግን ሰይጣን ስልቱን ይቀይራል። ያን ጊዜ ደግሞ 'እፍረትንና ተስፋ መቁረጥን' ያመጣብሃል። 'እንዲህ ያለ ኃጢአት ሠርተህ እንዴት እግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ? አንተ ረክሰሃል፣ ንስሐህ ተቀባይነት የለውም፣ ሞትህም ለገሃነም ነው' እያለ በልብህ ይጮኻል።አንተ ግን የሰይጣንን ተንኮል አሸንፈው። ኃጢአት ልትሠራ ስትል 'እፈር'፤ ንስሐ ልትገባ ስትል ግን 'ደፋር ሁን'። ሰይጣን ግን ኃጢአት ስትሠራ እንድትደፍር፣ ንስሐ ስትገባ ደግሞ እንድታፍር ያደርግሃል። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ኃጢአት ቍስል ነው፣ ንስሐ ግን መድኃኒት ነው። ቍስል ያለው ሰው ቍስሉን ለሐኪም ለማሳየት አያፍርም፤ ካሳየው ይፈወሳል፣ ከሸሸገው ግን ይበሰብሳል። አንተም ኃጢአትህን ለእግዚአብሔር ንገረው፤ እርሱም ይፈውስሃል።(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
16 Sept, 02:50edited
"የቤተ ክርስቲያን ካህን ለአንተ እንደ መንፈሳዊ አባት ይኹንልህ፡፡ አንድ ሕመምተኛ ስውር በሽታዎቹን በግልፅ ለሐኪም እንደሚያሳይና ከዚያም እንደሚድን ኹሉ፥ አንተም ምሥጢሮችህን ለካህን በግልፅ ንገር፤ ትድንማለህ፡፡”(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
15 Sept, 10:05
"የአባቶቻችን የሐዋርያት ትዕዛዝ ነው፡፡ ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ፡፡"(ሥርዓተ ቅዳሴ)
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
15 Sept, 00:18
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! በዓይንህ ውስጥ ጉድፍ እንዲገባ የማትፈቅድ ኾነህ ሳለ በነፍስህ ላይ እልፍ ወትእልፊት የጉድፍ ክምሮች እንዲገቡ ቸለል ትላለህን? ታዲያ ዕለት ዕለት በነፍሳችን ብሌን ላይ እያከማቸነው ያለነውን ቆሻሻ የምናጸዳው መቼ ይኾን? እሾኾቹን የምንቆርጣቸው መቼ ይኾን? አረሞችን የምንነቅላቸው መቼ ይኾን? እንግዲህ ወዲህ መከሩ እንደ ቀረበ አታውቅምን? እኛ ግን እርሻችንን እንኳን ገና አላረስንም፣ አላለሰለስንም፡፡ እንግዲህ ገበሬው (የወይኑ ባለቤት) በመጣ ጊዜ ስሕተት ቢያገኝ ምንድን ነው የምንለው? እኮ የምንመልሰው ምን ይኾን? ዘር የሚሰጠንን ሰው አጥተን ነው ብለን ነው የምንለው? በፍጹም! ዘሩ'ማ ዕለት ዕለት እየተዘራ ነው፡፡ እሾኾቹን የሚቆርጥ ሰው አጥተን ነው የምንለው? ኧረ በጭራሽ! ዕለት ዕለት ማጭዱን እንደ ሳልን ነው፡፡ የዚህ ዓለም ሕይወት ውጣ ውረድ ይዞህ ነውን? ለምን ታዲያ ይህ ዓለም በአንተ ዘንድ ስቁል አልኾነም? የተበደረውን ዕጥፍ ሳያደርግ ያንኑ ብቻ መልሶ የሚከፍል እርሱ ክፉ አገልጋይ ከኾነ ይህቺውን ብትኾን የሚያጠፋስ ምን ብለን ነው ልንጠራው የምንችለው? ያ ሰው እጁና እግሩ ታስሮ ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ከተጣለ፥ ሠናያትን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ የሚያነሣሡን እልፍ ምክንያቶች እያሉ ወደ ኋላ የምንልና የማንፈቅድ እኛ ታዲያ እንደ ምን ያለ መከራ ይገባን ይኾን?እንዲህ እንዳታደርግ አንተን ለማሳመን የማይበቃው እስኪ የትኛው ነው? የዓለሙን ርኵሰት አላየህምን? የዚህን ዓለም ሕይወት ርግጠኛ ያለመኾን አልተመለከትክምን? የዚህን ዓለም ድካም፣ በዚህ ዓለም ለሚቀር ደመወዝ
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
