gram news
✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠ channel avatar

✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

@betgubae

በዚህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ተከታታይ ትምህርት በጉባኤ ተገኝተው መማር ላልቻሉ በሃገር ውስጥም ከሃገራችንም ውጪ ለሚኖሩ ምዕመናን መማማሪያ የተከፈተ ነው። t.me/betgubae የፌስቡክ ኣድራሻዬንም ይጎብኙ https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

ProjectsENReligion

8,060subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    16 Sept, 07:53

    የወንድማችን የአመኑ ይልማ የሕመም ሁኔታን እና እርዳታ እንድናደርግለት አካውንቱን አጋርቻችሁ ነበር የባንክ አካውንቱ እንዳስቸገራችሁ በነገራችሁኝ መሠረት እርሱን ጠይቄው መርዳት የምትችሉበትን ሌላ ትክክለኛውን አካውንት አሳውቆኛል በምስሉ ላይ የትብብር ደብዳቤ በሚለው ላይ ታገኙታላችሁ (ከሥርም ያስቀመጥኩላችሁ ላይም ማግኘት ትችላላችሁ) እባካችሁ ረዳት ሰው ስለሌለው እና ሕመሙም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ስለ ደረሰ በተቻለን መጠን ፈጣን ትብብር እናድርግለት እርሱን በስልክ ለማውራት ከፈለጋችሁ 0910115204 በዚህ ደውሉለትበቴሌ ብር ለመርዳት 0910115204 / 0960192121በንግድ ባንክ 1000277663167 በአቢሲንያ 247151842 በአሀዱ ባንክ 0018050810101 በንብ ባንክ 9260 (7000003735608 )
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    13 Sept, 16:33

    «ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ወደ እርሱ ጠርቶ፦ የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠበቅ? ብሎ ወደ ጌታ ላካቸው።» (ሉቃ 7፥19)📌 ጥያቄ፦ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የጌታችን አምላክነቱን ፥ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት በሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረው እራሱ መሆኑን አስቀድሞ የሚያውቅ ሆኖ ሳለ እንደ አዲስ መጠየቁ ስለምንድን ነው?-> መልስ፦ አይሁድ ክርስቶስ መሆኑን ክደው ገና ይመጣል እያሉ ይጠብቁ ነበርና ከቃሉ (ከራሱ አንደበት) ሰምተው ይመኑ ብሎ ነው እንጂ እርሱማ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት በሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረው እራሱ መሆኑን ዐውቆ በማኅፀን ሳለ ሰግዶለታል ፣ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ ብሎ መስክሮለታል። ( ሉቃ 1፥44 ፤ ዮሐ 1፥24 )✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ📌 የtiktok ቤቴን ይወዳጁ https://www.tiktok.com/@amha1627?_r=1&_t=ZN-99fmhmlZZW
    1,4801251Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    12 Sept, 14:10edited

    🍀መስከረም🍀-> ይህ ወር የቀኑ ሰዓት ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ አሥራ ሁለት ሰዓት ነው :: ከዚህ በኋላ ቀኑ እያነሰ ይሄዳል ።# መስከረም ማለት ምን ማለት ነው ?1- በቁሙ ስመ ወርኅ ቀዳማይ የወርና ያመት መጀመሪያ በግብጽና በኢትዮጵያ ቍጥር " ዝ ውእቱ ርእሰ ዓመት ዘግብጽ ወኢትዮጵያ፡፡ አመ ዐሡረ ለመስከረም " እንዲል (ስንክ መስ 1) . ጥንትም ከሥጋዌ በፊት ለዓለም ኹሉ መጀመሪያ ወር ነው ይኸውም በአይሁድ ዐውደ ዐመት በበዓለ መጥቅ ይታወቃል ፡፡2- መስ ከመስየ መጥቶ በከረም ላይ ወድቋል ስለዚህ መስየ ክረምት ፣ ምሴተ ክረምት ተብሎ ይፈታል ፤ ምስጢሩ ፀአትና መሰስ ማለት ነው የክረምት ጫፍ መካተቻ የመፀው መባቻ መኾኑን ያሳያል፡፡ በዓመት ዘይቤ ሲፈቱት ግን መቅድመ አውራኅ ርእሰ ክራማት ያሰኛል፤ ይኸውም መንና ስን ለየብቻቸው ተነጣጥሎ መቅድምና ርእስ ብሎ ነው፡፡ መስ ዐለፈ ከረም ክረምት በተገናኘ መስከረም ክረምት ዐለፈ ማለት ነው። ክረምት ዐልቆ በጋ ሲጀ(ዠ)መር የዐመት መጀመሪያ ዐውደ ዐመት መስከረም ከረመ ክረምት መስከረም ነጋ (ጠባ) እንላለን። መዝ 64፥113- መስከረም ማለት ከግእዝ የመጣ ቃል ሲሆን (ከሪም- ወይም- ከሪሞት) (መዝከረ - ወይም -ከረም)ከሚሉ የግእዝ ቋንቋዋች የተገኘ የውሀድ አረፍተ ነገሮች ውጤት ነው ። - # ከሪም ወይም # ከሪሞት ማለት ምን ማለት ነው ? ከሪም ወይም ከሪሞት ማለት-በግእዝ የከረመ፣የቆየ ፣ የሰነበተ ማለት ሲሆን ይህም የክረምት ቆይታ የሚገልፅ እና የክረምት መገባደጃ እንደሆነ የሚያመለክት ነው በሌላ ፍቺ የከረመው ክረምት ማለቂያ
    1,84083Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    12 Sept, 11:29edited

    አዲስ የተከፈተው የtiktok አካውንቴን ይወዳጅ👇https://www.tiktok.com/@amha1627?_r=1&_t=ZN-99fafpxKAfG
    1,21021Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    12 Sept, 08:52

    ✝️ ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 7 ድረስ ያለው ሳምንቱ (ወቅት) ዮሐንስ ይባላል፡፡ -> እነዚህ ሰባቱ ዕለታት ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የተሰጡ የጸጋው (ሀብቱ ) ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህም፦ - ጻድቅነት - ስብከት - ክህነት - ብህትውና - ድንግልና - ሰማዕትነት - ትንቢት ናቸው።-> የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላት ፦መስከረም 26፡ በዓለ ጽንሰቱ ሰኔ 30፡ በዓለ ልደቱ መስከረም 2፡ ራሱ የተቆረጠበት ሚያዝያ 15፡ ነፍሱ ከራሱ የወጣችበት የካቲት 30፡ ራሱ የተገኘችበት ሰኔ 2፡ ራሱ በኤልሳዕ መቃብር የተቀበረበት መስከረም 1፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ
    1,720119Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    11 Sept, 04:58edited

    “በዚህች ዓመት ደግሞ ተዋት” ሉቃ ፲፫÷፮-፱ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ያሸጋገረን ቸሩ አምላካችን ይክበር ይመስገን ! የንስሓን ፍሬ የምናፈራበት ይሆንልን ዘንድ ዘመናችንን ይባርክልን
    1,6601675Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    25 Aug, 05:28

    ✥✥✥ ቅዱሳን መላእክት ✥✥✥➛ መላእክት የሚለው ብዙ ቁጥርን አመላካች ሲሆን በነጠላ መልኣክ ይሆናል እንደ የአገባቡም የተለያዩ ሁለት ትርጉሞችን ሊሰጥ ይችላል፡፡ መልአክ :- 1. ተመልአከ ከሚለው የግእዝ ግስ ሲወጣ አለቃ ሆነ በሚለው መሪ፣ አስተዳዳሪ፣ አዛዥ፣ አለቃ የሚለውን ይገልፃል፡፡ (ዮሐ.፫÷ ፩) ኒቆዲሞስን « መልኣኮሙ ለአይሁድ» ይለዋል የአይሁዳውያን አለቃ ሲል፡፡ የጌታ ወዳጅ ባለራዕይ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊም በተደጋጋሚ ራዕዩን ለሰባቱ የቤተ ክርስቲያን መልአክ እያለ ሲገልጽ በዚህ ትርጉም የገባ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ (ራዕ ፩፥፳)2. ለአከ ከሚለው ግስ ሲነሳ ላከ የሚለውን ስለሚያስገኝ መልእክተኛ ጠባቂ ተብሎ ይፈታል፡፡➛ መላእክት ከሰባቱ ሰማያት በኋላ ነው የተፈጠሩት ይህም ለምን እንደኾነ አክሲማሮስ ሲገልጥ፡- “በፊት ፈጥሯቸው ቢኾን እኛም አብረነው ፈጠርን፤ ያዝንለት፤ ተራዳነው ባሉ ነበር፡፡ አንድም ርሱ ቢመሠርት እኛ ገነባን፤ ርሱ ቢገነባ እኛ መሠረትን ባሉ ነበር፡፡ ይህም ሳጥናኤል በኋላ እኔ ፈጠርኳችኁ እንዳለው ማለት ነው” ይላል፡፡➛ "ቅዱሳን" መላእክትመላእክት "ቅዱሳን" መባል እንደሚገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናገኛለን ማር. 8 ፥38 “በዚህ አመንዝራና ኃጢአተኛ ትውልድ በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ ያፍርበታልና። "ይህ አባባል “ቅዱሳን መላእክት” የሚለውን ቃል ይጠቀማል። መላእክት በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቦታዎች ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ ለምሳሌ በማቴዎስ 25፥31 እና በራዕይ 14፥10
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    21 Aug, 13:48

    ✥ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ ✥ ✥ ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ ✥. ነሐሴ 16 የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ ሃገር ወደ ሃገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ዕረፍተ ሞቴን በዕረፍተ ዕለትሽ አድርጊልኝ ይህም ባይሆን በዚህ አሕዛብ ሃገር ተቀብሬ አልቅር ከሚያምኑት ሃገር እቀበር ዘንድ ፍልሰተ ሥጋዬን ከፍልሰተ ሥጋሽ ዕለት አገናኝልኝ ብሎ ተማጽኗት ነበር።. ይህም የዕለቱ አርኬ « ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል ዘተቶስሓ ፍልስተ ዐፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ ኀቤሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ። » ተብሎ ተገልጿል ልመናውንም ተሰምቶለት የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።ከፍልሰተ ሥጋዋ ሰማዕቱን ያሳተፈች እመሰማዕታት እኛንም ከበረከቷ ለመሳተፍ የበቃን ታድርገን። (ስንክሳር ነሓሴ ፲፮)✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬhttps://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
    2,980221Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    21 Aug, 07:07

    ✥✥✥ ሰማይ ተገረመች ✥✥✥➛ አስቀድሞ አባቷ ዳዊት « አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ 131፥8) ብሎ እንደዘመረው ድንግል እንደልጇ ባለትንሣኤ ከሙታን ተለይታ በልጅዋ ሥልጣን ተነስታ "ሰማይ ዳግሚት" ወደ ሰማይ ጉዞ አደረገች። ሰማይም ተገረመች አማናዊቷን ሰማይ ማርያምን ስላየች። አስቀድሞ ሰማይ በምስራቅ መስኮቷ ወጥታ በምዕራብ መስኮቷ በመግባት በምትመላለሰው በብርሃኗ ፀሓይ ትመካ ነበረ፤ ከፀሓይ ይልቅ ሰባት እጅ የምታበራን እመኣምላክን ወደርሷ ስትመጣ ዓይታ ግን ግርማዋን አድንቃ « ይህች ሰማይ እንደዚህ ካበራች ከርሷም የተገኘው ፀሓየ ጽድቅማ እንደምን መንክር ነው ብላም ተደመመች »።ጌታን መሸከም የማይችለው አቅሟንም አስባ፣ ሰማያውያን ኪሩቤል ሱራፌል ሊያዩት የማይደፍሩት አቅፋ ያሳደገች የዚች ታላቅ እናት ክብሯንም ተረድታ እንደ ቅድስት ኤልሳቤጥም አንደበቷም በምስጋና ተመልታ የእንግዳዬ ክብር ከማንም ይለያል የጌታዬ እናቱ ወደኔ ልትመጣ እንደምን ይሆንልኛ እያለች በትህትና ሆና በደስታ ዝማሬ አቀረበች። ፍጡራን በሙሉ የኔን ፀሓይ ሳይሆን ያንቺን ፀሓይ ይሙቅ ዳግሚት ሰማይ ሆይ « የጽድቅ ፀሓይ ይወጣላችኋል » የተባለለትን ወልደሽላቸዋልናም ኣለች። (ት ሚል 4፥2)የንጉሥ እናት በቤተመንግሥት በክብር እንደሚያኖራት፤ ንጉሥ ክርስቶስም የከበረች እናቱን በመላእክት ዝማሬ በክብር አጊጣ በመንግሥተ ሰማያት ይኸው አንግሷት።✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬhttps://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)https://m.facebook.com/mekur
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
    2,290101Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    19 Aug, 14:23

    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    19 Aug, 14:23

    "እመብርሃንን ክጄ እንጀራ ከምበላ እስከ ልጆቼ በሃይማኖቴ ጸንቼ በረሃብ ብሞት ይሻለኛል"በሀገሩና በኃይማኖቱ ድርድር የማያዉቀዉ የጎንደር ሕዝብ እያለማ በረሀብ አይሞቱም!አቶ ቻሌ ኃብቴ እና ወይዘሮ በቃቢል አባተ የሚባሉ ሁለቱም እጅግ የሚዋደዱና በጉልበታቸው ሠርተው የሚተዳደሩ ኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ነበሩ። በ2015 ዓ.ም የካቲት 16 ምሽት ላይ ቀን ዘንብሎባቸው የቤቱ ምሰሶ የሆነው ባልየው ባልታሰበ አደጋ ስድስት ሰዎች ተሰብስበው ጭንቅላቱን ደበደቡትና በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት ሄዱ በዚህም ክፉኛ ተጎድቶ ፓራላይዝድ ሆኖ እጅ እግሩ ተሳስሮ አንደበቱ ተዘግቶ እየተኮላተፈ ለዓመታት በሕክምና ቆየ።ከብዙ ድካም በኋላ ቀስ ብሎ መራመድ ሲጀምር ለዕለት ጉርስ የጉልበት ሥራ ሲሠራ ቤት ተደርምሶበት እግሩ ተሰበረ እንደ ድሮው ፈጽሞ መራመድ አቃተው።አቶ ቻሌ በዚህ ዓይነት ሁኔታ እያለ ሚስቱ በቃቢል በጎን እሱን እያሳከመች በጎን ጥጥ ፈትላ ለቤታቸውና ለሕፃናት ልጆቿ የዕለት ጉርስ እያመጣች ባለችበት ሁኔታ በጸና ታመመች በሽታዋም የቆዳ ካንሰርና የደም ግፊት እንደ ሆነ ተነገራት። ለባልና ሚስቱ ለሕክምና የሚሆን ገንዘብ ባለመገኘቱ ሁለታቸውም አልጋ ላይ ዋሉ።ወጥቶ መግባት ሠርቶ መብላት ቀረ። የሚበሉት ሲቸግራቸው የቤት እቃቸውን ሁሉ ሽጠው በሉ።በእኒህ ባልና ሚስት የተወለዱት ሁለቱ ሕፃናትም ገና ቦርቀው ሳይጨርሱ እናትና አባታቸውን በጽኑ ደዌ ታመው ማየቱ ሳቃቸውን ወደ ለቅሶ ቀየረው። የ10 ዓመት ልጃቸውም ትምህርቷን ልታቋርጥ ተገደደች።ይባስ ብሎ በቤታቸው ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩ
    2,240104Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    18 Aug, 08:15edited

    👉 ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል፡፡👉 ቡሔ ይባላል ፡- ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡ • አንድም፡- ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡ ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡ • አንድም፡- ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንደሚባል ወቅቱ በሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት ፤ በዶፉና በጎርፉ ተሸፍና የነበረች መሬት የምትገለጥበት በመሆኑ ነው፡፡ • አንድም፡- ቡሔ (ቡሔእየ) ተብሎ ይተረጎማል ይኸውም የደብረታቦር እለት እርሾ ሳይገባበት ተቦክቶ የሚጋገረውን ኅብስት ያሳያል፡፡✔ 4. ችቦ የመብራቱ ፣ የሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት፡-👉 መብራት የሚበራው 12 ለ13 ዋዜማ ሌሊት በ3 ሰዓት ነው ። • የጌታችን ክብሩ በተገለጠበት ጊዜ ብርሃኑ የሌሊቱን ጨለማ ገፍቶት እስከ አርሞንዔም ደርሶ ነበርና በዚያ አካባቢ የነበሩ እረኞች በሁኔታው ተገርመው ቀንም መስሎአቸው ሌሊቱም ተዘንግቷቸው በዚያው ቆይተው ነበርና ቤተሰዎቻቸው ምን አግኝቷቸው ይሆን በማለት መብራት አብርተው (ችቦ ይዘው)፣ የሚመገቡትን ይዘው ወገኖቻቸውን ፍለጋ ወጥተዋል እረኞችም ያሉበትን ቦታ ለቤተሰዎቻቸው ጅራፍን በማጮኸ አመልክተዋቸዋልና
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    18 Aug, 08:15

    ✥✥✥ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌስሑ✥✥✥ (መዝ.88÷12)👉 በዚህ ርዕስ ሥር1. በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት/ ከሐዋርያት ሦስቱ ሐዋርያት ብቻ መመረጣቸው ፤ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስ መገለጣቸው ስለምን ነው? 2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ 3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?) 4. ችቦ የመብራቱ ፣ ሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት እንመለከታለን፡፡✔ 1. ይህ በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን የሚከበረው ጌታችን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነቱን ያስመሰከረበት፣ ጌትነቱን እና ክብሩን የገለጠበት በመሆኑ ነው፡፡ (ማቴ.17÷1 ማር.9÷2 ሉቃ.9÷28 2ጴጥ.1÷16-18)፡፡👉 ጌታችን ሐዋርያትን ‹‹ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ብለው ይሉታል? ›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ቅድስናህን ዓይተው ሙሴ ነህ ይሉሃል፤ የኃይል ሥራህን ድንግልናውንም ዓይተው ኤልያስ ነህ የሚሉህ አሉ ……… ብለውት ነበረና እግዚኣ ሙሴ ወኤልያስ (የነቢያት ጌታ) መሆንኑን ለመግለጥ፤ አንድም ጌታችንም መልሶ ‹‹ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ? ›› አላቸው ቅዱስ ጴጥሮስም እስከ ክርቶስ ተብሎ የተነገረልህ ‹‹ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ›› አለው (ማቴ.16÷13-20/ ትን.ዳን.9÷25) ይህን በፍጡር አንደበት የተመሰከረውን ጌትነቱን በአብ ምስክርነት ለማጽናት እና በተግባር ለመግለጥ የሐዋርያትንም እምነታቸውን ለማጽናት አዕማደ ሐዋርያት የሆኑትን ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ያዕቆብ፣ ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ ወደ ቅዱሱ ተራራ አወጣቸው፡፡
    2,02944Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    12 Aug, 17:41

    ✥✥✥ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ✥✥✥👉 ነሐሴ 7 እመቤታችን የተፀነሰችበት ነው። ቤተክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከልም ነው።👉 አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን የመፀነስዋን ነገር ሲናገር ድንግል ሆይ በልተው ጠጥተው ጾር ሲጸናባቸው በሚያደርጉት ግንኙነት የተፀነሽ ኣይደለሽም ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው ብዙ ተባዙ ባለው ፈቃድ በሩካቤ ዘበሕግ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ በማለት ያደንቃል!👉 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም " የእግዚኣብሔር ልጆች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ማኅበር እንግዲህ ይህችን ንጽሕት ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናድንቃቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግል የተባረከችይቱም ፍሬ የተፈራችባት የሩካቢያቸው ንጽሕት ቀን እንደምን ያለች ናት፡፡ ከይሁዳ ወገን የምትሆነውን ንጽሕት ርግብ ለመፀነስሽ ለእግዚኣብሔር ፈቃድ የሆነው የመገናኘታቸው ቀን እንደምን ቅድስት ናት፡፡ የንጉሥ አዳራሽ የምትሆን የርሷ መሠረት የተመሠረተባት ዕለት እንደምን ደስ ያለች ናት፡፡➛ ነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ አለ " ከዕሤይ ሥር በትር ትወጣለች፡፡ ከግንዱም አበባ ይወጣል በላዩም የእግዚኣብሔር መንፈስ ያርፍበታል፡፡ " (ኢሳ ፲፩፣ ፩፣ ፪)- ይኸውም ትንቢት በጽዮን የተነገረው በኢየሩሳሌም የተሰበከው በነቢያት አንደበት የተሰማው በሌዋውያን እጅ በዕብራይስጥ ልሳን የተጻፈው ሊፈጸም የክህነት በትር በቀለችልን፡፡ የመንግሥትና የኃይል የሕይወትና የመድኃኒት የሃይማኖት የንጽሕና የቅድስና በትር የኃይል የመዊዕ በትር በቀለችልን፡፡➛ "ከዕሴይ ዘር በትር ትወጣለች፤ ከግንዱም አበባ ይወጣል
    3,1001863Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    8 Aug, 08:10

    #፯ቱ_ዕለታት_ለእመቤታችን_ምሳሌዋ_ናቸው➕ በዕለተ እሁድ ትመሰላለች- በዕለተ እሁድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከሷም ዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲለው አሥራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና ።➕ በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች- በዕለተ ሠኑይ ከዚህ ምድር እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሀ ከሶስት ከፍሎታል፣አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው አንዱን እጅ በዙሪያው ወስኖታል አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሃን ማኅደር አርጎታል። ዕለቲቱ የሱዋ ጠፈር ከሱዋ የነሣው ሥጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ።➕ በዕለተ ሠሉስ ትመስላለች- በዕለተ ሠሉስ ለታብቀል ምድር ሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ በበአርአያሁ ወበአምሳሊሁ ባለ ጊዜ በእጅ የሚለቀሙ አትክልት በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት በምሳር የሚቆረጡ ዕፀዋት ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ተገኝተዋል። የመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታም ከሱዋ ተገኝቷልና ።➕ በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች- በዕለተ ረቡዕ በይቁሙ ብርሃናት በገጸ ማይ ካለ ጊዜ ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ፀሓይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል ። ለመንፈሳውያን ምግብ የሚሆን ጌታ ከሱዋ ተገኝቷልና ።➕ በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች
    3,560143Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    6 Aug, 15:15edited

    ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ - 1ኛቆሮ. 5፥11፦ ወይእዜኒ ጸሐፍኩ ለክሙ ከመ ኢትደመሩ፡፡ - 1ኛዮሐ. 2፥14፦ ጸሐፍኩ ለክሙ አበው እስመ አእመርክዎ - ሓዋ.ሥራ 12፥18 ፦ ወጸቢሖ ተሀውኩ ሠገራት፡፡- ምስባክ መዝ 44፥16-17፦ ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፡፡ ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፡፡ ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ- ወንጌል ሉቃስ.6፥20፦ ወውእቱሰ አንሥአ አዕይንቲሁ፡፡- በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ )➕ ነሐሴ 12- በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ቅዱስ ሚካኤል አስተርአዮ ለቈስጠንጢኖስ ወነግሠ ቈስጠንጢኖስ በሮሜ ወ፳፻ ሰማዕታት ማኀበራነ ፋሲለደስ፡፡- ምስባክ ዘነግህ መዝ 137፥1-2፦ በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ፡፡ ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ፡፡ ወእገኒ ለስምከ፡፡- ወንጌል ማቴዎስ 25፥31 ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው፡፡☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ
    3,190871Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    6 Aug, 15:15

    ✥✥✥ የጾመ ፍልሰታ ምንባባት ✥✥✥➕ ነሐሴ 1- አመ ዓሚሩ ለነሐሴ አቦሊ ሰማዕት ፣ ወተዝካረ ሐና እመ እግዝእትነ፣ ወዮሴፍ ወኒቆዲሞስ እለ ገነዝዎ ለእግዚእነ፡፡☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ- 1ኛጢሞ. 5፥1፦ ሊቃናተ ኢታመጉዕ፡፡ - 1ዮሐ. 5፥1፦ ኵሉ ዘየአምን ከመ ኢየሱስ ውእቱ መሢሕ ሐዋ.ሥራ 5 ፥ 26:- ወእምዝ ሖረ መጋቤ ምኵራብ፡፡ - ምስባክ መዝ 118፥47-48 ፦ ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር ወኣነብብ ትእዛዘከ ዘኣፍቀርኩ ጥቀ፡፡ ወኣነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘኣፍቀርኩ- ወንጌል ዮሐንስ.19፥38፦ ወእምድኀረዝንቱ ሰአሎ ለጲላጦስ ዮሴፍ- በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ አው (ወይም) ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፡፡➕ ነሐሴ 2- በዚህ ዕለት የሚተሰቡ ፦ ኣትናስያ ቅድስት ወደሚና ሰማዕት ወአኃዊሁ ወኢዮጰራቅስያ ብዕፅት፡፡
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    5 Aug, 17:34

    የገጠሪቱ ቤተክርስቲያን የጾመ ፍልሰታ ቅዳሴ እንዳይታጎል እርዳታ እናድርግላቸው ! አድራሻው በወረቀቱ ላይ አለ
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    26 Jul, 15:58

    -> በመላእክቱ ዘንድ ጽኑ ብለህ ያጸናኻቸው እኛንም በሃያማኖት በምግባር አጽናን-> ነቢዩ ዳንኤልን ከተራቡ አናብስት ያዳንከው እኛንም ሊውጠን ሽቶ ዘወትር በዙሪያችን ከሚያጋሳ ሰይጣን አድነን-> ሠለስቱ ደቂቅን ከሚነድድ እሳት ፣ ቅድስት ኢየሉጣን እና ቅዱስ ቂርቆስን ከሚፈላ ውኃ የታደካቸው እኛንም ከፍትወት እሳት ታደገንከጥንት ጀምሮ በጎ ምሥራችን ማብሰር ልማድህ የሆነ መልአክ ሆይ ለእኛም ልቡናችንን የሚያረጋጋ የምሥራችን አሰማን
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
    3,250285Open in Telegram
  • ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

    25 Jul, 16:10

    ➕ የ3 ዓመት ሕፃን የእናቱ የእምነት ጉድለት በጸሎት አራቀላት በእጁም ይዟት ወደ ሕይወት መራት እናቱም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው።➕ ከፍላቱ የተነሣ እንደነጎድጎድ የሚያስፈራ የነበረው እንደ ማለዳ ውርጭ ቀዘቀዘላቸው ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።➕ በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል ( አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም )➕ እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን።✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬhttps://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71http://bit.ly/42nkRDS(የዩቱብ አድራሻ)
    Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠Image from a post by ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
    3,530217Open in Telegram