Latest posts

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
1 Sept, 18:29edited
ፍኖት መንፈሳዊትመጽሐፍ ዳሰሳ በዲ/ን መስፍን ተከሥተ#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
1 Sept, 16:44edited
#ፍኖት_መንፈሳዊት እና #የትዳር_ወግ#አሳታሚና_አከፋፋይ #አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0925421700_ይውሰዱ!https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
1 Sept, 14:45edited
በእግዚአብሔር ቸርነት ክርስቲያን ነኝ፤ በምግባሬ ግን ታላቅ ኀጢአተኛ፤ አጠራሬም ቤት አልባና የትሕትናን ምንጭ በመፈለግ ላይ ያለ ከርታታ፤ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር የሚል ነው። ንብረቶቼ በጀርባዬ ያዘልሁት ደረቅ ዳቦ ያለው የከረጢት ቦርሳና በእቅፌ የያዝሁት መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው፤ ይኸው ነው ያለኝ።ከበዓለ ኀምሳ በኋላ በኻያ አራተኛው እሑድ ወደ ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ላይ ለመሳተፍ ኼድሁና ልክ [የቅዱስ ጳውሎስ] መልእክት እየተነበበ ሳለ ገባሁ። ንባቡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ከላከው የመጀመሪያ መልእክት የተወሰደ ሲሆን፥ ይህም “ሳታቋርጡ ጸልዩ” ይላል።እነዚህም ቃላት በእኔ ላይ ጥልቅ ስሜት ፈጠሩብኝና እንዲህ ስል ዐሰብሁ፤ “አንድ ሰው ለሕይወት የሚያስፈልጉትን ነገሮች በመፈለግ ብዙውን ትኩረቱን በሚይዝበት በዚህ ዓለም ሳያቋርጥ እንዴት መጸለይ ይቻለዋል?” መጽሐፍ ቅዱሴን ከፍቼ ያለማቋረጥ መጸለይ እንዳለብን [፩ተሰ.፭፥፲፯] በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በመንፈስ መጸለይ አስፈላጊ እንደሆነ [ኤፌ.፮፥፲፰]፤ በሁሉም ቦታ በጸሎት እጅን በክብር ማንሣት እንደሚገባ [፩ጢሞ.፪፥፰] የሰማሁትን በገዛ ዐይኖቼ በትክክል ዐየሁ። ስለነዚህ ቃላት ደጋግሜ ተማርሁ፤ዐስብም ነበር፤ ነገር ግን ምንም መረዳት አልቻልሁም።#ፍኖት_መንፈሳዊት የሽፋን ዋጋ 550 ብር #አሳታሚና_አከፋፋይ #አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
1 Sept, 08:57edited
እንግዲህ ቡሩክ ጢሞቴዎስ ሆይ “አርእስተ ትምህርተ መለኮትን” ከፈጸምኩ በኋላ፥ አሁን አቅሜ በፈቀደ መጠን ወደ አስማተ መለኮት ትርጓሜ እሻገራለሁ። ኾኖም ግን፥ ልንጸናበት የሚገባን የቅዱሳት መጻሕፍት መርኅ አለ፤ ይኸውም ስለ እግዚአብሔር የኾነውን እውነት የምናጸናው በሰው ጥበብ ማባበያ ቃላት አይደለም፣ ይልቁንም በመንፈስ በተቃኘው በነገረ መለኮት መምህራን ኃይል ምስክርነት ነው። በዚህ ኃይል ከማይገለጹ እና ከመታወቅ በላይ ከኾኑ እውነታዎችህ ጋር የማይገለጽ እና ከመታወቅ በላይ የኾነ ኅብረትን እናደርጋለን። ይኸውም ኅብረት የሚኾነው በውስጣችን ባሉ የአእምሮ እና የኅሊና ሕዋሳት በግብራቸው አንድ በኾኑበት መጠን ነው። ስለኾነም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር ከገለጠልን ሐሳብ በቀር ከፍጥረት ኹሉ በላይ ስለኾነውና ኅቡዕ ስለኾነው አምላክ ምንም ነገር መናገርም ኾነ ማሰብ በፍጹም አይፈቀድልንም። ስለዚህ ይህን “ልዕለ ባሕርያዊ ዕውቀት” ልንሰጠው የሚገባው ‘አግኖስያ’(አለማወቅ) ተብሎ ለሚጠራው ነው።ሐዋርያውያን አበው ቅጽ 1 ገጽ 227 ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስ በእንተ አስማተ መለኮት#አሳታሚና_አከፋፋይ #አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ! https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
31 Aug, 12:50edited
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ፍቅረማርያም ባዘዘው #ለደብረ_ታቦር_4ቱ_ጉባኤ_ቤት ራሳቸው ያዘጋጁት #ሃይማኖተ_አበው 4ኮፒ ሰጥተውናል።እቅዳችን 100ኮፒ ነው 60ኮፒ ይቀረናል። 60ሰዎች ካጣን ግን አንድሰው እንዲሸፍነው እናስገድዳለን። @orthokiha እዘዙ ከቤታችሁ ያሉትን አምጥታችሁ ስጡ።#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!https://t.me/BetMetsahfte

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE pinned «የዓመቱ ታላቅ ቅናሽ አድርገን መጻሕፍት ለእናንተ ልናቅርብ ነው።ለመች ይሁንላችሁ? የቀኑ ምርጫ በእናንተ ይወሰናል።»
28 Aug, 17:40

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
28 Aug, 14:11
ለደብረ ታቦር ጉባኤ ቤት መጻሕፍት ማሰባሰቡ እንደቀጠለ ነው። ወለተ ሐና 26 መጻሕፍት ሁለት ወንድሞቻችን 4መጻሕፍት አዘውናል ወንድማችን 1 አንድ ወንድማችንም 7 መጻሕፍት ሰጥተውናል። 34 መጻሕፍት ደርሰናል።እቅዳችን መቶ ነው 66 መጻሕፍት ይቀራል አሁንም አምጡልን። ወይም @orthokiha እዘዙን።#update ዲ/ን ዘሚካኤል ሓጎስ 2ት ሐዋርያውያን አበው አንድ ወንድማችን ደግሞ ፈላስፋው ቅዱስ ዩስጢኖስ አሁን ሰጥተውናል።



አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
28 Aug, 13:48edited
#የትዳር_ወግ #በትእዛዙ_ካሣ“ከሦስት ዓመት በፊት ዕድሜያቸው በሠላሳዎቹ ያሉ ባለጠጋ የሚባሉ ጥንዶች ለምክር ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ ከተጋቡ ገና ሁለት ዓመት አልሞላቸውም፡፡ ከጋብቻ በፊትም ብዙም አይተዋወቁም፡፡ ፍቅር ጠናብን ብለው በችኮላ ነው ሰርጉንም ያጣደፉት፡፡ ትዳር ጣፋጩንም መራራውንም አጣምራ የያዘች እንቆቅልሽ መሆኗንም አልተረዱትም ነበር፡፡ ጫጉላ ሽርሽሩ ሁሌም የሚቀጥል ሳይመስላቸው አልቀረም፡፡“ሚስትም በተደጋጋሚ የምታነሣው ‘አያዳምጠኝም’ የሚል ነበር፡፡ ባል በቅሬታዋ ግራ ሳይጋባ አልቀረም፡፡ ‘ስትናገር እንኳን አቋርጫት አላውቅም፡፡ እርሷ ራሷ ምስክር ናት’ ይላል ደጋግሞ፡፡ ለካስ ነገሩ ሌላ ነው፡፡ ‘ስሜቴን አይረዳልኝም፤ ሲከፋኝ እንኳ ልብ አይለውም፡፡ ፍላጎቴን ለመረዳት ትዕግሥት የለውም፡፡ እያዋራሁት ዓይኑ ሌላ ቦታ ነው የሚያዬው፤ ጆሮው ቢሰማም ወደ ልቡ አይዘልቅም’ እያለች ሚስት ናዳውን አወረደችው፡፡“‘እንዲያውም በሚገርም ሁኔታ ሲከፋኝ ከባለቤቴ ይልቅ ውሻችን መከፋቴን ዐውቃ ከጎኔ ተኮራምታ ትቀመጣለች፡፡ ሳለቅስ ቆይቼ ፊቴ ተለዋውጦ እርሱ ወደ ቤት ሲገባ እንኳ ምን እንደ ሆንኩ ስለማያስተውለው አይጠይቀኝም’ አለች….“ያንጊዜ ነው ባል የባነነው፡፡ በእርግጥ አስተዋይ ሰው ነበረ፡፡ በሴትና በወንድ መካከል ያለውን የስሜትና የአረዳድ ልዩነት ለማስረዳት ስሞክር ነው ነገሩ የገባው፡፡ መፍትሔ ባይኖርህ እንኳ ሚስት ችግሯን ስትረዳላት መፍትሔ ያገኘች ያክል ይሰማታል፡፡ ሴት አዛኝ የመሆኗን ያህል ቶሎ መደሰትም ቶሎ መከፋም ያጋጥማታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ጠባያቸው እንደ ማዕበል ይወጣልም
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
28 Aug, 07:17edited
ስለ ደራሲው ትእዛዙ ይሁኔ ካሣ በዓለም አቀፍና በተቋማዊ የአመራር፣ የፋይናንስና የፕላኒንግ መስኮች ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ ያካበቱት ሰፊ ልምድ ያላቸው ደራሲና አሰልጣኝ ናቸው። የሙያ ጉዟቸው በአሜሪካ መቀመጫውን ካደረገ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ተቋም እንዲሁም ፣ በኢትዮጵያ ቀደምት በሆኑ የግል ዘርፍ ውስጥ የነበራቸውን ከፍተኛ የአመራር ሚና፣ እንዲሁም በአገሪቱ ትልቁ ባንክ ተግባራዊ የሥራ ልምዶች ያቀናጀ ነው። በጠንካራ የትምህርት መሠረትና በብዙ ዘርፎች ባላቸው ጥልቅ ተሞክሮ የታነፁት ደራሲው፣ እነዚህ ሦስት መጽሐፍትን ለ አንባቢያን አቅርበውልናል። አዲሶቹ በእንግሊዘኛ የቀረቡ መጽሐፍቶቻቸው «Why Strategy Fails: Eleven Gaps Between Ambition and Results» እና «The Silent Soul»፣ ቀደም ሲል ካተሟቸውና ከፍተኛ አድናቆትን ካተረፉት «ቅን መሪ» እና «ባለ ራዕይ መሪ» ከተሰኙት ድንቅ መጻሕፍቶቻቸው ፣እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ ከሚገኙት «የትዳር ወግ» ከተሰኘው በጣም ተወዳጅ ከሆነው የአማርኛ ሥራቸው ጋር በአንድነት ለአንባቢዎች የቀረበ የላቀ የዕውቀት ገጸ-በረከት ነው።#የትዳር_ወግ የፊታችን ሰኞ ይወጣል።የሽፋን ዋጋው 650 ብር ነው።ቀድመው ለሚከፍሉ ደንበኞቻችን ታላቅ ቅናሽ አድርገናል። የትዳር ወግ የተሰኘ መጽሐፍ ለመውሰድ 500 ብር ብቻ ቀድማችሁ ክፈሉ።2ቱ እንግሊጣ መጻሕፍትም ከኅትመት ሊወጡ ሲሉ ቅናሹ እናሳውቃለን።CBE 1000499547629 KIFLOM H AND/OR YILEMA TSEGAYEScreenshot @orthokiha ላይ ላኩልን።


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
27 Aug, 09:29
ስሜን አትጥቀስ ያሉኝ አንድ አባት አንገብጋቢ ችግር ላይ ላለው ገዳም ጤፍ ገዝተህ አስፈጭተህ ስጥልኝ ብለው 256ሺ ብር አስገብተውልኝ ነበር።በዛሬ ቀን ለደብረ በንኩል አቡነ መድኅኒነ እግዚእ ገዳም አበምኔቱ በተገኙበት 19 ኩንታል ጤፍ በ13,500 ብር ሒሳብ 256,500 ብር ከፍለን 19 ኩንታል ጤፍ ገዝተን አስረክበናል።ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።



አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
26 Aug, 13:24edited
#የልዳው_ኮከብ የልጆች መጽሐፍ 2ኛ ዕትም በስርጭት ላይ ነን! አዘጋጅ ፡- ዶክተር ብሩክታዊት ተስፋይ የሽፋን ዋጋ፡- 300 ብር#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
25 Aug, 08:00

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
22 Aug, 19:03edited
#የመጽሐፍ_ጥቆማ!ደራሲ አቶ ትዛዙ ካሳ አዳዲስ እና ድንቅ ህሊናን የሚያነቁ፣ ህይወትን የሚያንፁ 3 ግዙፍ መጻሕፍትን በአንድ ላይ ይዞላችሁ ብቅ ብሏል።እነዚህን ሦስት ድንቅ ሥራዎች ለንባብ ብቁ የሚያደርግበት ታላቅ የመጽሐፍ ምረቃ ከሰልጣኞች ምረቃ ጉን ለጉን ቅን መሪ አካዳሚ ማቋቋሚያ የመጽሐፍ ምረቃ መርሐ-ግብር ተዘጋጅቷል!በምረቃው ላይ የሚመረቁት መጻሕፍት፦፩. የትዳር ውግ (በአማርኛ)በትዳር ህይወት ውስጥ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን፣ የፍቅርና የተስማሞት ምስጢሮችን፣ እንዲሁም የጠበቀ አብሮነትን የሚገነቡ ጥበቦችን በድንቅ አቀራረብ የሚያስጎበኝ ድንቅ መጽሐፍ!፪. WHY STRATEGY FAILS (በእንግሊዘኛ)The Eleven Hidden Gaps Between Ambition and Results – And How to Turn Strategy into Successለተቋማት መሪዎች፣ ለቢዝነስ ባለቤቶችና ለስራ አመራር ባለሙያዎች የተዘጋጀ ፍጹም ተግባራዊ መመሪያ! በእቅድና በውጤት መካከል ያሉ 11 ስውር ክፍተቶችን በመፈተሽ እቅድዎን ወደ ታላቅ ስኬት እንዴት መቀየር እንደሚችሉ የሚጠቁም ድንቅ ስራ።፫. THE SILENT SOUL (በእንግሊዘኛ)


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
22 Aug, 07:04edited
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለትንሣኤ ማርያም! የእሷ መነሳት የትንሣኤ ጉባኤ ተስፋችን ነውና።ጽሑፉ የላከልኝ የአብአለ ነው።ለደብረ ታቦር ጉባኤ ቤት አንድ ሰው ማጣቴ ግን እጅግ ገርሞኛል ከኪሳችሁ ብር ባታወጡም እቤታችሁ ያለ መጽሐፍ መስጠት እንዴት አቃታችሁ? አንብባችሁ ቁጭ ያደረጋችሁት ለጉባኤ ቤት ተማሪዎች ለንባብ ይጠቅማል ግድየላችሁም አንድ አንድ መጽሐፍ እንስጥ በረከት እንፈስ። @orthokiha እዘዙ ወይም ከቤታችሁ ያለው መጽሐፍ አርጋኖን መጥታችሁ ስጡ። መልካም አሸንዳ፤ሸደይ፤ሶሎልያ፤ማርያ!

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE pinned a photo
21 Aug, 09:54

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
21 Aug, 09:54edited
የደብረ ታቦር መድኃኒዓለም የ4ቱ ጉባኤ ምስክር ቤት መጻሕፍት እንድናሰባስብ መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ ባለፈው በአካል መደብራችን መጥተው ደብዳቤ ሰጥተውናል።ያለፉ ሳምንታት ለአርዕስተ አበው ጉባኤ ቤት እየተሰበሰበ ስለነበር ትንሽ ጠብቁን ብለን እስካሁን አቆይተነዋል።የሱባኤው መዝግያ በበረከት በመቀበል እንዝጋው።በረከቱ እያስጀመርን ነው። አንድ መጽሐፍ ለጉባኤ ቤት ስትሰጡ እኛም አንድ ተጨማሪ እንሰጣለን።የምንፈልገው የሰው ብዛት 100 ሰዎች ነው።በድምሩ 200 መጻሕፍት ይሆናሉ።ኑ ለታላቁ የቤተ-ክርስትያን ዩኒቨርስቲ መጻሕፍት እንስጥ። @orthokiha ለደብረ ታቦር ጉባኤ ቤት አለሁኝ በሉኝ።#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ! https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
20 Aug, 12:08edited
መልካም ዜና!ከእነዚህ ዓለም ዐቀፍ መንፈሳዊ መጻሕፍት መኻከል ኹለቱን በ #አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር በዐማርኛ ተተርጕመው በቅርቡ ለንባብ ይበቃሉ።#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንጻ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
20 Aug, 10:05edited
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የተሰናዳው #የብርሃን_እናት የተሰኘው መጽሐፍ 14ኛ ዕትም በማከፋፈል ላይ ነን!#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውንዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
17 Aug, 11:22edited
ፖሊካርፐስም ወደ ሜዳው ሲገባ "ፖሊካርፐስ ሆይ በርታ ፤ ጽኑ ኹን! " የሚል ቃል ከሰማይ መጣ ተናጋሪውን ያየው ማንም የለም ፤ ነገር ግን በዚያ የነበሩት ወንድሞች ድምፁን ሰሙ ።በመጨረሻም ወደ ፊት ሲያቀርቡት ሀገር ገዢው ፖሊካርፐስ እርሱ መኾኑን ጠየቀው ፤ እርሱም መኾኑን ሲያምን ሃይማኖቱን እንዲክድ ሊያግባባው እየሞከረ እንዲህ አለው "ለሽምግልናህ እዘን ደግሞም እነርሱ እንደሚያደርጉት ኹሉ በቄሳር መልካም እድል ማል ፤ ሐሳብህንም ለውጥና 'አምላክ የሌላቸው ይጥፉ' በል " አለው ። ያንጊዜም ፖሊካርፐስ በመሰብሰቢያው የነበሩትን ዓመፀኞች አረማውያን ኹሉ በእርጋታ ተመለከተ ፤ በእጁም እነርሱን አመለከተ ቃተተም ወደ ሰማይም ቀና ብሎ "አምላክ የሌላቸው ይጥፉ ! " አለ ።ከዚያም ሀገረ ገዢው እየገፋፋው "ማል ፤ እኔም ነጻ አወጣሃለሁ ፤ ክርስቶስን ስደብ " አለው ። ፖሊካርፐስም "ሰማንያ ስድስት ዓመት አገልግዬዋለሁ ፤ እርሱም ከቶ ምንም አልበደለኝም ። ታዲያ ንጉሤንና መድኃኒቴን እንዴት ልሰድብ እችላለሁ ? " ብሎ መለሰለት ።ዜና ስምዑ ለቅዱስ ፖሊካርፐስ ፤ ሐዋርያውያን አበው ገጽ 127@orthokiha ይዘዙ!#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0925421700_ይደውሉ!https://t.me/BetMetsahfte


አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
14 Aug, 06:48edited
ዲያቆን መስፍን ተከሥተ ሐዋርያውያን አበው መጽሐፍ እንዲህ ዳሰሳ አቅርቦልናል መልካም ንባብ!#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ!
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
