gram news
Christian tweet channel avatar

Christian tweet

@christians_tweet

በዚህ ቻናል በየቀኑ ለ ➜ #Profile_picture ➜ #Instagram_story ➜ #Facebook ➜ #Telegram_story የሚሆኑ #መንፈሳዊ_ጥቅሶች በዚህ ቻናል ያገኛሉ Buy ads: https://telega.io/c/Christians_tweet ⒸSince 5-11-2015

ProjectsENReligion

12,900subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Christian tweet

    21 Sept, 18:58

    forwarded from @grow_to_god

    📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹየምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
    537731Open in Telegram
  • Christian tweet

    8 Sept, 18:33

    forwarded from @mercy_ena_berua

    🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቹበዓሉን ድምቅ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀን እንገኛለንየፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉን በዓሉ አብረን ድምቅ ብለን እናሳልፋለን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
    897533Open in Telegram
  • Christian tweet

    6 Sept, 18:40

    forwarded from @superchristiantube7

    🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቹ በዓሉን ድምቅ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀን እንገኛለን የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉን በዓሉ አብረን ድምቅ ብለን እናሳልፋለን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
    556432Open in Telegram
  • Christian tweet

    31 Jul, 14:30

    ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ዮሐንስ 1:12-13የምንኖረው የግለ ሰብ መብቶችን ሰዎች አክርረው በሚይዙበት ዘመን እና ባህል ውስጥ ነው "____ መብቴ ነው።" ባዶውን ቦታ ሙሉት። ነገር ግን ማናችንም ብንሆን በራሳችን ብቃት ወይንም ደረጃ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን መብት የለንም። ይህንን መብት የሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ይህ መብት ደግሞ ወደ እኛ የመጣው እግዚአብሔርን ትልቅ ዋጋ አስከፍሎ ነው። ኢየሱስ ወደ ምድር መጣ፣ ኖረ፣ ሞተ ከሙታንም ተነሣ። ይህንን ጸጋ ደግሞ በእምነት በኩል ተቀበልን(ኤፌሶን 2፥8-10)። ኢየሱስን እንደ ጌታችን አድርገን ስንቀበለውና ስናምነው እግዚአብሔር ዳግም ውልደትን ይሰጠናል (ሮሜ 10፥9-10)። በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ዳግም ተወልደናል(ዮሐንስ 3፥3-7፤ ገላትያ 3፥26-29፤ ቲቶ 3፥3-7)። ከእግዚአብሔር መወለድ፣ ከላይ መወለድ፣ "ዳግም" መወለድ (ዮሐንስ 3፥3-7) ማለት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አብረን ወራሾች ሆነን ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብ ተቀላቅለናል ማለት ነው (ሮሜ 8፥14-17፤ ገላትያ 4፥1-7)።@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    1,66015643Open in Telegram
  • Christian tweet

    30 Jul, 19:54

    አላምናቸው ወዳጆቼን ጓደኛዎች ዘመዶቼን ያጋልጡኛል ጠብቀው አይችሉትም ጉዴን ተሸክመው....ወረት አያውቀው ጌታዬ ዘላለም ሚስጥረኛዬ የልቤን አጫውተዋለው ገመናዬን አሳየዋለሁ😊
    1,26013762Open in Telegram
  • Christian tweet

    25 Jul, 11:26

    ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሳቅ እንዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። መክብብ 7:6@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    1,34095422Open in Telegram
  • Christian tweet

    13 Jul, 21:15

    አረጋዊውን ሰው እንደ አባትህ ቈጥረህ ምከረው እንጂ በኀይለ ቃል አትናገረው። ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች ተቀበላቸው 1 ጢሞቴዎስ 5:1ከወጣትነት ጋር ጉጉት፣ ለነገሮች ጠንካራ ፍላጎትና ግልጽ የሆነ ዐላማ አብረው ይሄዳሉ። ወጣትነትን አንዳንድ ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ጠንካራ እና ለነገሮች ምላሽ ለመስጠት ችኩል የሚኮንበት ጊዜ እንደ ሆነ ይናገራሉ። እነዚህ ደግሞ በጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ። ወጣቶች ደግሞ በእድሜ የገፉትን ሰዎች ጊዜው ያለፈባቸው፣ ተገማች የሆነ ሕይወት ያላቸውና የማይንቀሳቀሱ እንደ ሆኑ ይገልጻሉ። ይህ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ውጥረትና ግጭትን ቢፈጥርም አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት ነገር አለ። በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖች ምንም ያኽል ቢሳሳቱ በእምነት የተፈተነ ሕይወት ስላላቸው በአክብሮት ልንቀርባቸው ይገባል። ነገር ግን በእድሜ የገፉ ክርስቲያኖች ከወጣቶች በተለይም ለታላላቆቹ ፍቅር እና አክብሮት ካለው ወጣት በጸሎትና በትሕትና የመጣን እርማትን ለመቀበል ፈቃደኞች መሆን አለባቸው። ከሁሉም በላይ በምንም የዕድሜ ክልል ውስጥ ብንሆን ለኢየሱስ ለመኖር እርስ በርስ ልንረዳዳ ይገባል።@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    1,61076522Open in Telegram
  • Christian tweet

    4 Jul, 12:46

    ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። ገላትያ 5:1ነፃ ወጥተናል! ኢየሱስ ክርስቶስ በጸጋና በእርሱ ላይ ባለን እምነት በኩል ከሕግ፣ ከኀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶናል(ሮሜ 8፥1-4)። ሕጉን በመጠበቅ ለመጽደቅ ከመሞከር ነፃ ወጥተናል። አሁን እግዚአብሔርን የምናገለግለው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ድነትን በላያችን ላይ ስላፈሰሰልንና ለእርሱ ጸጋ ካለን ምሥጋና የተነሣ ነው(ቲቶ 3፥3-7)። ስለዚህ ይህንን ነፃነት እንዴት መጠቀም እንችላለን? ለኀጢአት ወይም ሕግን ለመጠበቅ "ዳግመኛ በባርነት ቀንበር" ለመጠመድ መፍቀድ የለብንም! ይልቁንም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተለውጠን ይበልጥ ክርስቶስን እንምሰል(2 ቆሮንቶስ 3፥18፣ ገላቲያ 5፥22-25)። "በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ስንመላለስ" "ሕጉ የሚጠይቀውን ጽድቅ" እናሟላለን (ሮሜ 8፥4)።@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    1,4907332Open in Telegram
  • Christian tweet

    18 Jun, 21:28

    እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ። ኤርምያስ 10:23ምንም እንኳ ልናሳካቸው የምንፈልጋቸው ግቦች እና ተልዕኮዎች ቢኖሩንም የወደፊት ሕይወታችንን ግን መወሰን ለእኛ አልተሰጠም። ማቀድ እንችላለን። ነገር ግን ይህንን የምናደርገው ጌታን ለማክበርና በእኛ ያለውን ዐላማ ለመፈጸም እንደ ሆነ መገንዘብ አለብን። እናቅዳለን፣ ነገር ግን የምንኖረው በእግዚአብሔር ፈቃድ ሥር ነው።@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    Kedus BibleThe Kedus Bible is a mobile app that offers the Bible in various languages.
    1,83011653Open in Telegram
  • Christian tweet

    29 May, 14:30

    አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም ዘፀአት 28:29ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ፣ ሊቀ ካህናቱ ወደ መቅደሱ ሲገባ ሁሉንም እስራኤላውያን "በልቡ ላይ" ተሸክሞ ነበር። ታላቁ ካህን ኢየሱስ ወደ መስቀል የሄደው፣ ኀጢአታችንን በጀርባው ተሸክሞና ይቅርታችንን ደግሞ በልቡ ይዞ ነበር! ኢየሱስ እግዚአብሔር ለዓለም ያዘጋጀው አዳኝ ነው። እኛንም ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕትን ያቀረበ ካህናችን ነው(ዕብራዊያን 7፥23-27፣ 9፥24-28፣ 10፥8-10)። .@Christians_Tweet @Christians_Tweet
    2,57012511Open in Telegram
  • Christian tweet

    24 May, 18:53

    ፍትሕን በታማኝነት(የእግዚአብሔር አገልጋይ) ያመጣል። ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።” ኢሳይያስ 42:3-4እግዚአብሔር አይወድቅም! በፍቅር ላይ የተመሠረተ ፍትሕ በምድር ላይ ኢምንት በሆነ መልኩ ቢኖርም ሰማያዊ ፍትሕ ግን በመጨረሻ እንደሚነግሥ እግዚአብሔር ብቸኛና ፍጹም ማረጋገጫችን ነው። ይህ የምድር እና የሕዝብ ሁሉ ተስፋ ደግሞ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። ዳግም ሊመለስና የእግዚአብሔርን እውነትና ፍቅርን መሠረት ያደርገ ፍትሕን ይዞልን ሊመጣ ተስፋ ሰጥቶናል፣ ማራናታ(1ቆሮንቶስ 16፥22) ጌታ ሆይ ና!@christians_Tweet @christians_Tweet
    2,0007543Open in Telegram
  • Christian tweet

    5 May, 14:09

    በእኔ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ወደ ኋላ ጣሉት፤ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ... ወደ እኔ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ! ሕዝቅኤል 18:31-32እግዚአብሔር ከራሳችን መንገድ በንሰሓ እንድንመለስ ያዘናል። ወደ እርሱ እንድንመለስና ፈቃዱን ለመከተል እንድንሻ ይለምናል። ይህንን ካልተቀበልን ግን እየሄድንበት ያለው መንገድ መዳረሻው ሞት እንደ ሆነ እንወቅ። እግዚአብሔር ዳግም ሊወልደንና ሊያድሰን ይፈልጋል። ነገር ግን ከጥፋት መንገዳችን ተመልሰን በመንፈስ ቅዱስ አዲስ እንሆን ዘንድ ልባችንን አሳልፈን እንድንሰጠው ይፈልጋል። ንሰሓ ማለት ወደ ጥፋት የሚመራውን መንገድ መተውና ሕይወት፣ ደስታና ድነት ወዳለበት ወደ አብ ቤት የሚመራውን መንገድ መምረጥ ነው።@christians_Tweet @christians_Tweet
    2,31010642Open in Telegram
  • Christian tweet

    30 Apr, 14:41

    አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4:19ጳውሎስ ይህንን ተስፋ ለፊልጵስዩስ የሰጣቸው በጥሩና መጥፎ፣ በማግኘትና በማጣት ጊዜያት ውስጥ የጌታን ጸጋ እንዳገኘ አጽንኦት ሰጥቶ ከነገራቸው በኋላ ነው። ለዚህ ተስፋ ቁልፉ ነገር የእግዚአብሔር መግቦትና በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚያስፈልገንን እንደሚሞላን በእርሱ መታመን ነው። በጌታ ለመሞላት፣ እርሱን ለማስደሰት፣ በመገኘቱ ለመባረክና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት መተማመኛን ከእርሱ ለመቀበል ልባችን አጥብቆ ሲፈልግ ያኔ ለሚያስፈልገን ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር አቅርቦት ላይ መደገፍ እንችላለን።@christians_Tweet @christians_Tweet
    1,9309763Open in Telegram
  • Christian tweet

    27 Apr, 18:31

    አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ። መዝሙር 10:14እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በግብፅ እያሉ መከራቸውን አይቶና ጩኸታቸውን ሰምቶ ሊረዳቸው እንደ ወረደ፣ ዛሬም ጩኸታችንን ያያል ይሰማል። አሁን ደግሞ እግዚአብሔር የሚሰማን ሁሉን ቻይ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን ልጁ ኢየሱስ በቀኙ ተቀምጦ ስለሚማልድልን ነው። እኛ የነበርንበት ቦታ ኢየሱስ ነበር። የሞትን ሽታ፣ ስቃይን እንግልትንና መዋረድን ያውቃል። በአብ ፊት የኢየሱስ መገኘት እግዚአብሔር ጩኸታችንን ይሰማል ማለት ብቻ ሳይሆን ህመማችንን እንደሚረዳ ያሳያል። ኢየሱስ የመጣውም ለዚህ ነበር። እግዚአብሔር እንደሚረዳን፣ እንደሚጠነቀቅልንና በመጨረሻም እንደሚያድነን ኢየሱስ ማረጋገጫችን ነው። አምላካችን በችግርና በሐዘን ውስጥ ስንሆን ያያል፣ አቅመ ደካሞችን እርሱ ይረዳል።@christians_Tweet @christians_Tweet
    1,99012664Open in Telegram
  • Christian tweet

    19 Apr, 14:59

    የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተውም የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ፣ “ሞት በድል ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። 1 ቆሮንቶስ 15:54እንደ ክርስቲያኖች ሰውነታችን ቢሞትም እኛ ግን አንሞትም! ሥጋዊ ሞት ማለት የማይበሰብሰውን ሰውነት መልበስ ማለት ነው። ኢየሱስ ከሞት አስነሥቶ የማይበሰብሰውን ያለብሰናል። የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ሞት በእኛ ላይ ሥልጣን የለውም። ድል የእኛ ነው። የመጨረሻው ሥልጣናዊ ቃል ያለው ሞት ሳይሆን ኢየሱስ ነው፤ "ተነሣ!" ይለዋል።@christians_Tweet @christians_Tweet
    1,87013521Open in Telegram
  • Christian tweet

    13 Apr, 14:48

    ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው። መዝሙር 144:4ጊዜ እጅግ ውድ ነው። ከቤተ ሰብ ጋር፣ ከልጆች ጋር፣ ከጓደኞች ጋር፣ በክርስቶስ ካገኘናቸው ወንድሞች እና እኅቶች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ እጅግ ውድ ነው። ጊዜያችሁን እንዴት እየተጠቀማችሁ ነው? የምታጠፉትስ በምንድን ነው? ጊዜያችን ከምናጠፋው ገንዘብ ይልቅ ውድ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ? የአሁኑ ጊዜ እና ይዞ የሚመጣቸው ዕድሎች ካለፉ በኋላ እንደ ገና ማግኘት አይቻልም። ስለዚህ እያንዳንዱን ቀን ስትጀምሩ "ጊዜን መረዳት" እንድትችሉና ለበለጠው መልካም ነገር ማዋል ትችሉ ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ። ጊዜ ፈጥኖ ያልፋል፣ እንደ ምሽት ጥላ ነው፤ ብዙም ሳይቆይ በሌሊቱ ጨለማ ይዋጣል።@christians_Tweet @christians_Tweet
    2,1608644Open in Telegram
  • Christian tweet

    11 Apr, 19:10

    ብወድህ ታድያ ምን ይገርማል?
    Image from a post by Christian tweetImage from a post by Christian tweet
    1,820211365Open in Telegram
  • Christian tweet

    28 Mar, 20:25edited

    ‎ያለ ምስክር ያለ ማስረጃ እንዳመነህ እንደ አብርሃም ‎የኔም ልብ ባንተ ላይ እንደዚያው ፀንቷል ‎ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም፤ ሮሜ 4፥20@christians_Tweet @christians_Tweet
    2,110138531Open in Telegram
  • Christian tweet

    28 Mar, 14:47

    አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 1 ጢሞቴዎስ 2:5-6ምንም ያኽል ኀያል፣ የተለየ ሰው ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ የሚማልድ ሌላ ሰው አያስፈልገንም። እንደ ልጆቹ በነጻነት ወደ እርሱ መቅረብ እንችላለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱ በእኛ እና በእርሱ መሐል ፍጹም አስታራቂን አኑሯል። ይህ አስታራቂ ብቻውን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ሊቀ ካህናት ሆኖ የሚቀርብና የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ጌታችን፣ አዳኛችን እና ወንድማችን ነው።@christians_Tweet @christians_Tweet
    2,060103322Open in Telegram
  • Christian tweet

    28 Mar, 03:35

    ኦሪት ዘዳግም 33:26-29 (AMH) •••••••••• ²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ። አጥፋው ይላል። ²⁸ እስራኤልም ተማምኖ፥ የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥ እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤ ሰማያቱም ጠልን ያንጠባጥባሉ። ²⁹ እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።@christians_Tweet @christians_Tweet
    1,54015332Open in Telegram