Latest posts

Development Bank of Ethiopia (DBE)
24 Sept, 06:27
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, Applicable Thursday, September 24,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
24 Sept, 06:12
የመድኃኒት መድኃኒቱ «የመድኃኒት ፋብሪካዎች ለጠኔ ፈውስ ሆኑ፤ የመድኃኒቱ መድኃኒት ግን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነው!» አቶ አባይነህ ጥላየ ትረስት ፋርማሲዩቲካልስ ፋብሪካ ባለቤት ሥራ ሕይወታቸው በሙሉ ከሕክምና መድኃኒት ምርት ጋር የተያያዘ ነው።ከ1980ዎቹ ወዲህ ያለው የኢትዮጵያ የመድኃኒት ፋብሪካዎችን ታሪክ በቅጡ መናገር ይችላሉ።የምናወጋው ስለ መድኃኒት ቅመማ ባለሙያው አባይነህ ጥላየ ነው።በሕክምና መድኃኒት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከባለሙያ እስከ አመራር ባገለገሉበት ጊዜ ትልቁን የፋይናንስ አጋር ማንሳት ይወዳሉ፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን።የመድኃኒት ፋብሪካዎች በከፍተኛ ደረጃ የበቃ የሰው ኃይል እና የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ:: ይህንን ለማቋቋም ደግሞ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ግድ ይላል።ይህንን ከፍተኛ ፋይናንስ በረጅም ጊዜ ብድር ማቅረብ የቻለው ደግሞ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስለመሆኑ ተቋም እየጠቀሱ አቶ አባይነህ ይተዝታሉ ።በ1988 ዓ.ም. ግዙፍ አዲስ መድኃኒት ፋብሪካ ሲቋቋም ባልደረባ የነበሩት ፋርማሲስቱ፣ ትልቁ የፋይናንስ ምንጭ ልማት ባንክ ነበር።ባለዘጠኝ መስመሩ ግዙፍ ፋብሪካ ኢንቨስት በተደረገበት ልክ ለሀገር የብዙ ጠኔ ፈውስ መድኃኒቶች ማምረት የቻለ ነው።በተለይም በዘመነ ኮቪድ መድኃኒት ከውጭ በማይገባበት ጊዜ፣ ፋብሪካው ወገንን በምርቶቹ ታድጓል።ካዲላ ፋርማሲዩቲካልስ ሌላኛው የፋርማሲስቱ የሥራ መዳረሻ ነበር።በላቀ የመድኃኒት ምርት ጥራት የሚታወቀው ይህ ፋብሪካ፣ በሀገር ልጆች እና በውጭ ተቋማት በጥምረት የተመሰረተ ነበር።ፋብሪካው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ ሲደረግ ዝርዝር ሂደቱን የሚያስታውሱት ባለሙያው፣ ፋብሪካው- ባንኩ ለጤናው ዘርፍ የሰጠው የጸጋበረከት እንደሆነ ያምናሉ።ልማት ባንክ ፋይናንስ ያደረጋቸውን መድኃኒት አምራቾች በብዙ የሚያወሱት አቶ አባይነህ፣ አሁን ደግሞ የራሳቸውን መድኃኒት ፋብሪካ በባንኩ ድጋፍ መትከላቸውን በኩራት ይናገራሉ።በኢትዮጵያ የቆዳ ሕክምና መድኃኒቶችን ብቻ በማምረት ቀዳሚ የሚሆነው ፋብሪካ፣ትረስት ፋርማሲዩቲካልስ ይሰኛል።በዓመት 158 ሚሊዮን ቲዩብ የቆዳ ሕክምና ቅባት፣ ክሬም፣ ሻምፖ እና ሎሽኖችን የማምረት አቅም አለው። የሕፃናት ሕመም ማስታገሻ ሳፖዚተሪም ሌላኛው ምርቱ ነው።የዘመኑ ቴክኖሎጂ እና ማሽኖች የተከለው ፋብሪካ፣ በአንድ ሽፍት ብቻ ለ170 ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።የፋብሪካው የሀገር ውስጥ የገበያ ፍላጎት ከማርካት አልፎ፣ ለጎረቤት ሀገራት እና ለመላው አፍሪካ ምርት የመላክ አቅም እና ዕቅድ አለው።የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመድኃኒት አምራቾች የሚያቀርበው ግዙፍ ፋይናንስ ሀገር 85 በመቶ ከውጭ የምታገባውን መድኃኒት በሀገር ውስጥ ለመተካት አቅም መፈጠር ያስቻለ መሆኑን አቶ አባይነህ ይናገራሉ።ባንኩ በመድኃኒት ማምረቻ መስክ፣ በተኪ ምርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ ብሎም በውጭ ምንዛሬ ግኝት የሚዘከር ታሪክ ስለመጻፉም አክለዋል።በመጨረሻም ፋርማሲስቱ ይህን ይላሉ፦ «የመድኃኒት ፋብሪካዎች ለጠኔ ፈውስ ሆኑ፤ የመድኃኒቱ መድኃኒት ግን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነው!»
Development Bank of Ethiopia (DBE)
23 Sept, 12:01
The Development Bank of Ethiopia (DBE) today hosted a World Bank mission for constructive discussions on the restructuring of the Financial Sector Strengthening Project (FSSP) and other areas of mutual priority.The engagement provided an important opportunity to review ongoing initiatives, align on key priorities, and explore ways to further strengthen collaboration in support of DBE’s institutional transformation and Ethiopia’s broader financial sector development agenda.DBE values its continued partnership with the World Bank and looks forward to deepening cooperation toward building a stronger, more inclusive, and sustainable financial system.#DBE #WorldBank #FSSP #FinancialSectorDevelopment #DevelopmentFinance #Ethiopia #Partnership #InstitutionalTransformation




Development Bank of Ethiopia (DBE)
23 Sept, 06:28edited
ሀምሳ እንደ አንድ - አንድ እንደ ሀምሳወጣቶች ናቸው፤ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን። የዓመታት ጥረታቸው ወደ ሥራ ዓለም ያመራ ይዟል።ሆኖም ሥራ በዋዛ የሚገኝ አልነበረም። ይህም ከ10 ዩኒቨርሲቲዎች በ11 የትምህርት መስኮች ለተመረቁት ወጣቶች ግራ የሚያጋባ ነበር።የሆነ ጊዜ ወጣቶቹ ቢሾፍቱ በሚገኝ አንድ የሕክምና መድኃኒት ፋብሪካ ውስጥ ራሳቸውን አገኙ። የሥራ ፍለጋው ጊዜ አከተመ፤ ደስታም ሆነ።ፈንጠዝያው ግን ዕድሜው ድንክ ነበር፤ ወር ሙሉ ተሠርቶ የሚገኘው 2,800 ብር ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ ለመባል እንኳን አቅም ያጣ ሆነ። ከፍተኛ የሥራ ጫና፣ ተቀጣሪ ሆኖ መሥራት የሚያስከትለው የመንፈስና የኢኮኖሚ ነፃነት እጦት ለወጣቶቹ የማይታረቁ ጥያቄዎች እንደሆኑ ቀጠሉ።"ችግር ብልሃትን ታስተምራለች" እንዲሉ፣ በሥራ ምክንያት የተዋወቁት 50 ወጣቶች በዚህ ጉዳይ ላይ መምከር ጀመሩ።መተዋወቅ ያዳበረው ወዳጅነት "እንዴት?"፣ "ለምን?" እና "እስከ መቼ?" የሚሉ ወሳኝ ነጥቦችን ለማንሳት ደፈረ።ወጣትና ጀማሪ ሠራተኞች እንደ መሆናቸው መጠን ቅርብ አዳሪ መሳይ መላ መቱ… "ዕቁብ ብንጥል?" አይነት ፤ "እድር ይሻለናል" ብለውም ነበር።ውይይቱ ሲዳብርና ሃሳብ ሃሳብን ሲወልድ፣ የአስኳላ ቤት ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ተስማሙ።የኢኮኖሚ ነፃነታቸውን የሚያውጅና ለሀገራቸውም አስተዋጽኦ የሚያደርግ የልማት ማህበር ብንመሠርት የሚለው ነጥብ በሃሳብ ባሕር ላይ መልሕቁን ጣለ።ሁለት ኮሚቴዎችን አደራጁ፤ አንደኛው የልማት ማህበሩ እንዴት ይመሠረት የሚለውን ሲያጠና፣ ቀሪው ደግሞ በምን መስክ እንሰማራ የሚለውን ያዘ።"ብልጥ ልጅ የያዘውን ይዞ ነውና " ወጣቶቹ ይህን ሁሉ የሚያደርጉት መደበኛ ሥራቸውን ሳይበድሉ በብልሃት ነበር።የኋላ ኋላ የልማት ማህበሩ 50 አባላትን ይዞ "ቶኩማዋ ኦዳ ነቤ" የሚል መጠሪያ በመያዝ በ2010 ዓ.ም. ተመሠረተ።ከስምንት ዓመት በፊት እንደ ሀገር 95 በመቶ የሚሆነው የምግብ ዘይት ከውጭ ይገባ ነበር። ይህም ሀገሪቱን ለከፍተኛ ወጪ ፣ ለጥራትና ለጤና እክሎች ዳርጓት ነበር። የጥናት ቡድኑ ይህንን የገበያ ክፍተት አስልቶ አቀረበ። የቢዝነስ ሃሳቡ ለወጣቶቹ የሚበጅ፣ ለሀገርም የሚያኮራ ሆኖ ጸደቀ።ወጣቶቹ በአማካሪዎቻቸው አማካኝነት ይህንን ግዙፍ ሃሳብ ፋይናንስ የሚያደርግላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደሆነ ተነገራቸው፤ ወደ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍም አመሩ። ተገቢው የቢዝነስ ሰነድ ተመርምሮ በሊዝ ፋይናንሲንግ ተጠቃሚ ሆኑ።የሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ዝግጅት እያለ ነገር ግን ማሽነሪ የመግዛት አቅም ሳይኖር ሲቀር፣ ባንኩ ማሽነሪውን በራሱ ወጪ ገዝቶና ተክሎ ለአልሚዎች የሚያስረክብበት አሠራር ነው። አልሚዎች ማሽነሪውን ሥራ ላይ በማዋል ከሚያገኙት ገቢ ላይ የሊዝ ክፍያውን (ኪራዩን) በየጊዜው ለባንኩ ይከፍላሉ። በዚህ መሰረት የኢትጵያ ልማት ባንክ የ36.6 ሚሊየን ብር የዘይት መጨምቂያ ማሽነሪዎች ገዝቶ፣ ተክሎ እና ተገቢውን ፍተሻ አድርጎ ለወጣቶቹ አስረከ፡፡አሁን ላይ "ቶን" የሚል መጠሪያ ያለው የምግብ ዘይት በቢሾፍቱና አካባቢው ገበያ ተለምዷል።የሀገራችንን አኩሪ አተር በዋና ግብዓትነት የሚጠቀመው ይህ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በቀን 15 ሺህ ሊትር ዘይት ያመርታል። ከአካባቢ ብክለት የፀዳው የፋጉሎ ተረፈ ምርት ለእንስሳት መኖ ይውላል፡፡ ፍብሪካው በቀጥታ ለ36፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ ለ200 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ አሁን ላይ የማህበሩ አጠቃላይ ሀብት 300 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
Development Bank of Ethiopia (DBE)
23 Sept, 05:49
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, Applicable Wednesday, September 23,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
22 Sept, 14:15
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ብራዚል በማሊ ግብርናንና የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡ ስምምነቱ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በግል ዘርፍ ልማት እና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ ያተኮረ ነው። የብራዚልን የቴክኒክ ልምድ እና የአፍሪካ ልማት ባንክን የልማት አቅም በማቀናጀት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ማጠናከር የስምምነቱ ዋና ግብ ነው። በትብብሩ መሠረት በግብርና፣ በምግብ ሥርዓት፣ በኃይል ሽግግር፣ በሙያና ክህሎት ማሳደግ እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በስፋት ይሰራል። እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ፣ ስምምነቱ የማሊን «ቪዥን 2063» እና የዘላቂ ልማት ስትራቴጂ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ ነው። ባንኩ በማሊ በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ በኃይል መሠረተ ልማት እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።


Development Bank of Ethiopia (DBE)
22 Sept, 10:51
#DBE
Development Bank of Ethiopia (DBE)
22 Sept, 10:14
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, Applicable Tuesday, September 22,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
21 Sept, 12:46
#DBE #production
Development Bank of Ethiopia (DBE)
21 Sept, 06:08
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, Applicable Monday, September 21,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
21 Sept, 05:04
መልካም የሥራ ሳምንት! ....... የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! የኢትዮጵያ ልማት ባንክትክክለኛ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et (http://www.dbe.com.et/? ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡


Development Bank of Ethiopia (DBE)
18 Sept, 14:13
https://youtu.be/Z4uVoAC7km0?si=DX5Vune6f7OrnhmvYouTubeStrict New Directive Issued by the National Bankl DBE🏦 Strict New Directive Issued by the National Bank 🏗️ Asian Infrastructure Investment Bank Backs Ethiopia's Infrastructure Agenda 🤝 New Strategic Partnership Formed for Inclusive African Development 🚀 African Development Bank & South Korea Partnership Entering…
Development Bank of Ethiopia (DBE)
18 Sept, 12:24

2,940Open in Telegram
Development Bank of Ethiopia (DBE)
18 Sept, 12:23edited
የካፒታል ዕቃዎች ተከላና ኮሚሽኒንግ አጋሮች የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያየኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) በሊዝ ፋይናንስ የተገዙ የካፒታል ዕቃዎችን ለመትከል (Installation) እና ሥራ ለማስጀመር (Commissioning) ብቁ የኤሌክትሮ መካኒካል ኩባንያዎችን በግልጽ የፍላጎት መግለጫ (EOI) እንዲያመለከቱ ይጋብዛል፡፡ ለበለጠ መረጃ ሐሙስ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ/ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሙሉ መረጃውን ማግኘት ይችላሉ። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ#DBE #commission #installation
Development Bank of Ethiopia (DBE)
18 Sept, 08:01
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል። ለበለጠ መረጃ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሙሉ መረጃውን ማግኜት ይችላሉ። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
3,120Open in Telegram
Development Bank of Ethiopia (DBE)
18 Sept, 06:20
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, Applicable Friday, September 18,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
17 Sept, 12:17
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የደቡብ ኮሪያ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው።አጋርነቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በግል ሴክተር ኢንቨስትመንት ዙሪያ በስፋት ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሷል።ልዩ የተባለው ይህ ስምምነት የደቡብ ኮሪያን ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስ እና የኢንዱስትሪ ልማት በስፋት ለመጠቀም ዕድል የሚሰጥ ነው።የደቡብ ኮሪያ ፈንድ (KOAFEC Trust Fund) የአፍሪካ ልማት ባንክ የረዥም ጊዜ አጋር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ 132.82 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ አድርጓል።8ኛው የኮሪያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባኤ በደቡብ ኮሪያ ሰሞኑን መካሄዱ ይታወሳል።#DBE #KOAFEC #ADB


Development Bank of Ethiopia (DBE)
17 Sept, 07:48
#DBE
Development Bank of Ethiopia (DBE)
17 Sept, 05:55
Development Bank of Ethiopia Exchange rate, ApplicableThursday, September 17,2026 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን:: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ! #DBE #ExchangeRate


Development Bank of Ethiopia (DBE)
16 Sept, 13:49
https://youtu.be/KhK66opzSqs?si=sZ4Mu_nzU8XH-1pAYouTubeThe Engineer Bakerlመሀንዲሱ ዳቦ ጋጋሪDerje’s Journey: From Civil Engineer to Baker Derje was once a dedicated civil engineer working on Addis Ababa creditor development projects. Throughout his engineering career, he successfully designed and managed many road construction projects across Ethiopia.…
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
