Latest posts
Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ pinned «የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ማስተማር ይጀምራል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ከKG እስከ 4ኛ ክፍል የማተማር ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ። የማስተማር ሥራውን ለማስጀመርም በ14/01/2019 ዓ/ም ለትምህርት ቤቱ መምህራን የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ…»
25 Sept, 15:54

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
25 Sept, 15:47edited
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ማስተማር ይጀምራልየደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ከKG እስከ 4ኛ ክፍል የማተማር ሥራ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ። የማስተማር ሥራውን ለማስጀመርም በ14/01/2019 ዓ/ም ለትምህርት ቤቱ መምህራን የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።በስልጠናው መክፈቻ ላይ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ይሄይስ አረጉ (ዶ.ር) ለመምህራኑ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን መምህራን በመማር ማስተማር ሂደት ሊኖራቸው ስለሚገባው ስነምግባር፣ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ዉጤታማ እንዲሆኑ ሊከተሏቸዉ ስለሚገቡ የማስተማር ዘዴዎች እና ለልጆች ተስማሚ የትምህርት አካባቢ ስለመፍጠር ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ዶ/ር ይሄይስ አክለዉም ት/ቤቱን የመክፈት ሀሳብ ካመነጩ አካላት ጀምሮ በግንባታውና በአፈጻጸሙ ላይ ለተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው አመራርና ሠራተኞች፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያስጀምረው የቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ት የማስተማር ሥራ ላይ ለሚሳተፉ መምህራን ምስጋና አቅርበዋል።በሌላ በኩል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ ሽግግር ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ በዛብህ (ዶ.ር) በስልጠናው ወቅት ባደረጉት ንግግር መምህራን ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ተማሪዎችን በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ-ምግባር ማነጽ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።በተጨማሪም መምህራን ተግባራዊ ትምህርትን በማጠናከርና ለተማሪዎች ምቹና ተስማሚ የመማሪያ አካባቢ በመፍጠር ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት ማብቃት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዉ ተናግረዉ ት/ት ቤቱ ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ስራዉን እንደሚጀምር አክለዉ ገልጸዋል፡፡የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠናው የስነትምህርት እና ስነባህሪ ተቋም ዲን በሆኑት መብራቴ በላቸው (ዶ.ር) እና የስነ ትምህርት መምህር እና ተመራማሪ በሆኑት አስቻለ ታደገ (ዶ.ር) የተሰጠ ሲሆን፣ መምህራኑም በስልጠናው ወቅት ሀሳባቸውን፣ አስተያየታቸውን፣ ልምድና ተሞክሯቸውን በማካፈል በንቃት ተሳትፈዋል።የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ከKG እስከ 4ኛ ክፍል የሚጀምረው የትምህርት ሥራ ለዩኒቨርሲቲው እና አካባቢዉ ማህበረሰብ ልጆች ጥራት ያለውና ተማሪ-ተኮር ትምህርት ለማቅረብ ያለመ ሲሆን፣ የመምህራን የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠናውም ለዚህ ተልዕኮ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ ነው።
Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
25 Sept, 06:09edited
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለማስጀመር የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሄደደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመን ሃንቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በፎክሎር 3ኛ ዲግሪ ለመጀመር የሚያስችል የስርዓተ ትምህርት ግመገማ አካሂዷል።በግምገማ መርሃግብሩ ላይ ከኣዲስ አበባ እና ጅማ ዩኒቨርስቲዉች የተጋበዙ ምሁርን በገምጋሚነት የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርስቲዉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና መምህንም በመርሃ ግብሩ ታድመዋል፡፡መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ይሄይስ አረጉ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞችን ከዓለም አቀፍና ሀገራዊ ፍላጎቶች ጋር ማጣጣም ዩኒቨርስቲዉ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ተግባር መሆኑን ጠቁመዉ በፎክሎር የሶስተኛ ዲግሪ ፕግራም ለመጀመር የተጀመረዉ ስራ ወቅታዊ እና አገራዊ ፋይዳዉም ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ጎጃም በርካታ ባህል፣ ጥበብ፣ ትውፊትና ወጎችን አቅፎ የያዘ ቢሆንም ታሪኮቹ በቅጡ ተሰንደው ያልተያዙ በመሆናቸው፣ በዘርፉ ጥናትና ምርምር በማድረግ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ እና ባህሉን ማበልጸግ አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት ም/ፕሬዝደንቱ የዚህ ፕሮግራም መከፈት ፋይዳዉ ከአካዳሚያዊ ጉዳዮች የላቀ ነዉ ብለዋል፡፡በመድረኩ የፕግራሙ ስርዓተ ትምህርት ይዘት በአማርኛ ት/ክፍል የፎክሎር መምህር እና ተመራማሪ በሆኑት ተባባሪ ፕፌሰር መስፍን ፍቃዴ የቀረበ ሲሆን እንዲሁም በዉጭ እና በዉስጥ ገምጋሚዎች የማሻሻያ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሥርዓተ ትምህርቱ ይዘትና አፈጻጸም ዙሪያ ሀሳቦችንና ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡ፕሮግራሙ ከጀርመን ሀንቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በታቀደ ትብብር የሚካሄድ መሆኑ የትምህርቱን ጥራትና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
25 Sept, 06:00
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ማይክሮ ባዮሎጅ እና ህብረተሰብ ጤና የ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች ለማስጀመር የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሄደደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ማይክሮ ባዮሎጅ እና በህብረተሰብ ጤና የትምህርት ዘርፎች የ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞችን ለመጀመር የሚያስችል የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሄደ።በዚህ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ መርሃ ግብር ላይ ከጎንደር፣ አዲስ አበባ፣ ወሎ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ የውጭ ገምጋሚዎች፣ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ እና ከአማራ ህብረተሰብ ጤና ተቋም የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች እና መምህራን ተሳትፈዋል። ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይሄይስ አረጉ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ፣ ዩኒቨርሲቲው ከጤናው ዘርፍ አንፃር የሚገኙ ክፍተቶችን ለመሙላት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም፣ እነዚህ ስርዓተ ትምህርቶች መቀረፃቸው በዕውቀትና ክህሎት የዳበሩ ባለሙያዎችን በማፍራት የሰውን ልጅ ጤና ለመጠበቅ፣ በሽታዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከል፣ አዳዲስ ወረርሽኞችን ለመግታት እና ለጤና ፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው አጽንኦት ሰጥተዉ አብራርተዋል፡፡በካምፓሱ የህክምና ማይክሮ ባዮሎጅ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር ተበላይ ድልነሳ በበኩላቸው፣ በሀገራችን በባክቴሪያ፣ ቫይረስና ፈንገስ የሚመጡ አደገኛ በሽታዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው እና በ3ኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎች እጥረት ስላለ ፕሮግራሙን መጀመር የግድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።ፕሮግራሙ የተሻለ እና የተለየ ምርመራ የሚያስፈልጋቸውን በሽታዎች ለመከላከልና ህክምና ለመስጠት እንዲሁም ብቁ ተመራማሪዎችን ለማፍራት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል። የህክምናና ጤና ሳይንስ ካምፓስ የድህረ ምረቃ ትምህርት አስተባባሪ እና በህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር እስከዚያው አግደው፣ አዲሶቹ ስርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ባገናዘበ መልኩ ጤና ነክ ችግሮችን ለመፍታት እንደተነደፉ አስረድተዉ ፣ የጤና ጥራትን ለማሻሻል፣ የድንገተኛ አደጋ ዝግጅትና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የጤናውን የአሰራር ስርዓት፣ የአገልግሎት ጥራት እና ስነምግባር ሊያስተካክሉ የሚችሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።በግገማ መርሃ ግብሩ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጋበዙ ገማጋሚያን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እነዚህን ፕግራሞች ለመክፈት ያሳየዉን ቁርጠኝነት አደንቀዉ ፕግራሞቹን ያበለጽጋሉ የሚሏቸዉን ምሁራዊ ሃሳቦች አበርክተዋል፡፡የመድረኩ ተሳታፊዎችም በርካታ ጥያቄዎች እና አስተየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን ከስርዓተ ትምህርት አዘጋጆችም መልስ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
23 Sept, 18:16
ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የሰነበተዉ ስልጠና ተጠናቀቀደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ''Public Interpreneurship and Innovation Ecosystem Building''በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ለከፍተኛ አመራሮች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና የስትራቴጂክ ዕቅድ ቡድን አባላት ከመስከረም 11-13 /2019 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡በስልጠና መርሀ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳይህ ካሳው (ዶ/ር) እንደገለጹት ስልጠናው አመራሩ የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት አቅምን የሚያጎለብት፣ እይታን የሚያሰፋ፣ ፈጠራን የሚያበረታታ፣ በየደረጃው ያሉ መሪዎችን የሚያነቃቃ፣ የአሰራር መንገዶችን እና ክህሎቶችን የሚያስታጥቅ፣ አፈጻጸምን የሚያሻሽልና ውጤታማ የሚያደርግ ነው ብለዋል። ስልጠናዉ ከኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲቲዩት (Enterpreneurship Development Institute) ጋር በትብብር የተሰጠ መሆኑን ተናግረዉ የመሪነት ባህልን እንደገና ለመተርጎምና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ክህሎቶች ለመታጠቅ እድል ይሰጣል በማለት ተናግረዋል።የስልጠናውን አስፈላጊነት በተመለከተ ሀሳባቸውን የገለፁልን የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲቲዩት አሰልጣኝ አቶ ሀይማኖት በዛብህ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ችግር ፈች አመራርን ለመገንባትና ተቋማዊ የፈጠራ አሰራርን ለማስፍፍት የሚያስችሉ ሰፋፊ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ዩኒቨርሲቲዎች አሰራራቸውን ወደ ስራ ፈጣሪነት ደረጃ በማሸጋገር ችግር ፈቺ፣ ውጤታማና ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ እንዲሆኑ ማስቻል፣ የኢኮኖሚና የፈጠራ እድገትን በመምራት ተቋማቱ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት ለተማሪዎችና ለሰራተኞች ምቹ የፈጠራ ምህዳር መፍጠር እንዳለባቸውም አንስተዋል።የስልጠናው ተሳተፊ የሆኑት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክት ኮሌጅ ዲን በዛ ሙጨ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ስልጠናው እንደተግባር ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠን ተልዕኮ ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ በአመራሩ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶችን ለማሳለጥ ከተለመደው አሰራር በመውጣትና አዳዲስ አስተሳሰቦችን በማፍለቅ ምርምሮችን መስራት፣ ችግር ፈች የማማህበረሰብ አገልግሎትን በማምጣት ተማሪዎችን ስራ ፈጣሪ የሚያደርግ እይታ እንዲኖረን ያደረገ ስልጠና ነው ብለዋል።የዩኒቨርሲቲዉ ቅጥርና ስራ ፈጠራ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይበልጣል ታረቀኝ እንዳሉት የዚህ ስልጠና መዘጋጀት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈችና ለተቋሙም ሆነ ለአካባቢው ማማህበረሰብ በዘላቂነት እሴት ፈጠራ ላይ እንዲሰራ፣ የተለወጠና የተቀየረ Enterpreneurial /የአዕምሮ ውቅር ያለው አመራር መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ይሄይስ አረጉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎችን ማቅረብ ጥበብ ይጠይቃል በመሆኑም ከስልጠናዉ የተገኘዉ ዕውቀት የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታና ከአሉብን ችግሮች የሚያወጣ እንዲሁም ተጠቃሚ የሚያድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ከእዚህ አንፃር ይህን ስልጠና ላቀረቡ አካላት ምስጋና ይገባችኋል በማለት በስልጠናው ለተሳተፉ አካላት የእውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት አጠቃለዋል።ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መስከረም 13/2019 ዓ.ም
Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
23 Sept, 07:33
PhD Curriculum Validation Workshop!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ pinned a photo
21 Sept, 17:46

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
21 Sept, 08:16
ለደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች Public Entrepreneurship and Innovative Ecosystem building በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከመስከረም 11 - 13/2019 ዓ.ም ድረስ ቆይታ የሚያደርግ ስልጠና ተጀመረ።ስልጠናውን የሚሰጡት ከኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲቲውት በመጡ ባለሙያች ሲሆን ችግሮችን የሚፈቱና ፈጠራ የታከለበት አመራር መስጠት የሚችሉ አመራሮች ለማፍራት የሚያስችል ስልጠና እንደሚሆን ይጠበቃል።




Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
19 Sept, 13:15
ለማታ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!


Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
18 Sept, 13:19
የተስተካከለ የቅጥር ማስታወቂያ!




Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
16 Sept, 13:32



Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
16 Sept, 07:05
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቡሬ ካምፓስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!



Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
15 Sept, 16:25edited
የጥሪ ማስታወቂያ!ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን 1ኛ አመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ ነባር የዋናው ግቢና የቡሬ ካምፓስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2019 የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 18 – 19/2019 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡#ማሳሰቢያ!በ2019 የትምህር ዘመን አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ለሚመደቡ ተማሪዎች፣ በ2018 በዩንቨርስቲው ሪሚዲያል ሲከታተሉ የነበሩና ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች እና በ2019 አዲስ በሪሚዲያል የሚመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ማስታወቂያ ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል።ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 05/2019 ዓ.ም


Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
13 Sept, 14:15
የቅጥር ማስታወቂያ (Reminder)




Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
11 Sept, 10:14edited
የጥሪ ማስታወቂያ!ለነባር የህክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች በመሉ፡-በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ካምፓስ ነባር የህክምና እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን።ስለሆነም ነባር የህክምና እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ ካምፓሱ በአክብሮት ያሳስባል።ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 01/2019 ዓ.ም


Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
10 Sept, 13:04
የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በምስራቅ ጎጃም ዞን አስትዳደር እና ደብረ ማርቆስ ከተማ ለሚገኙ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች 300 ደርዘን ደብተርና የእስክርቢቶ ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም ለአቅመ ደካሞች የዘመን መለወጫ በዓል መዋያ 1500 እንቁላል እና ሶስት በጎች እገዛ አድርጓል። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት እንመኛለን!ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም




Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
10 Sept, 09:38
አዲስ ዓመት፣ አዲስ እቅድ፣ አዲስ ስኬት!!ውድ ቤተሰቦቻችን፤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልጻል። የጤና እና የስኬት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን!!


Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
8 Sept, 16:34
#ማስታወቂያ!በ2018 ዓ.ም ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ ፈተና የሚሰጠው ነገ ማለትም ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5 ሰዓት ድረስ ስለሆነ በሰዓቱ በተመደባችሁበት ኮምፒውተር ቤተሙከራ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን።



Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
8 Sept, 13:10
Updated Postgraduate Programs for the coming academic year (2019 E.C.) of Debre Markos University. For those who are unable to apply in person due to distance or any other reason, you can apply using the link below: http://pgms.dmu.edu.et




Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
7 Sept, 18:57
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!!



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
